ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

የአንድነት ሚዲያ እንመሥርት ውይንም አሁን ካሉት መካከል መርጠን እናብቃ

ረዥም ያልተቆራረጠ የሥነ መንግሥት ያላት አገራችን ኢትዮጵያ ብዙ ጠላት ያፈሩላት ጸጋዎች አሏት።  በተፈጥሮ ከምትገኝበት የመልክዐ ምድር አቀማመጥ ጀምሮ ሕዝቧ ካዳበረው የነጻነትና የጸረ ቅኝ ግዛት  ጋር ተጣምሮ  ነባር እሤቶችና የአፍሪካ መግቢያ በር፥ የአባይ ወንዝ መነሻ፥ የቀይ ባህርና የህንድ ውቂያኖስ መተላለፊያ የመቆጣጠር አቅም የሚሰጣት አቀማመጧና የገናና ታሪኳ መመለስ አስፈሪነት፥ በዓረብና በአፍሪካ ድንበሮች አካባቢ መኖሯና አፍሪካን የጓሮ አርሻቸው፥ የተለያዩ አደንዛዥ እምነቶቻቸው ማራገፊያነት እንቅፋት መሆኗ፤ እንዲሁም ልዩ የተፈጥሮና የማዕድናት ሀብት ባለቤትነት፥ የሕዝቡ ጥበብኝነትና የጀግንነት ታሪክ፥ የአክሱምና ቀዳሚ ሥልጣኔ የመመለስ እድል ሁሉ  ዓይን ውስጥ አስገብቷታል። 


ፖረቱጋል፥ ኦቶማን ቱርክ፥ ጣሊያን፥ ኢንገሊዝ፥ ጀርመን፥ ፈረንሳይ፥ አሜሪካ ዛሬ የአውሮፓ ሕብረት፥ ሩሲያ፥ ቻይና፥ ግብጽ ወዘተ ወደ አፍሪካ አህጉር፥ ወደ ህንድ ውቅያኖስ፥ ወደ ቀይ ባሕር ሲመለከቱ የኢትዮጵያን  አቅምና ሚና ከጥቅማቸው አንጻር  የመበየን ፍላጎታቸውን መግታት አይችሉም። በዚህም ኢሰብአዊና ኢፍትሐዊ ፍልስፍናን ከሤራ ጋር ቀምረው፥ አገር በቀል ባንዳን መረማመጃ አድርገው  ኢትዮጵያ ያለማቋረጥ በሁለገብ ጥቃት ሥር ማኖራቸው ይታወቃል። ይህ ሂደት በትንሹ ከ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ አገሪቷን ሲያቆስላት፥ ሲቆነጻጽላት፥ ከህንድ ውቅያኖስ ባለቤትነት ወደ ባህር በር አልባነትና አሁን ወዳለዉ የክልል አፓርታይድ ሥርዓት ያደረሳት ነው። 


ሂደቱ ከቀጥታ ወረራ ጀምሮ፥ የንግድ በር መዝጋት፥ አገርን አንድ ሉዓላዊ ሕዝብ በጎኃና በእምነት ዘውግ ከፋፍሎ ማጋጨት፥ በመጨረሻ በትምህርትና በእውቀት ስም ልጆቿን አእምሮ በማጠብና በመከፋፈል  በባዕዳንና በተውሶ ርአዮተ ዓለም ሺ ዘመናት አገር ያቆመውን ስነ መንግሥት የሚያጠፋና የሚቃረን  መንግሥታዊ ሥርዓት እና  ሥርዓተ ትምሕርት በአገር ላይ የሚያጸኑ ቡድኖችን መፍጠር ችለዋል። ዛሬ የምንገኘው ኢትዮጵያዊነትን፥ ነባር እምነቶችንና ባህሎችን፥ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት፥ ከሁሉም በላይ የአማራን ማኅበረሰብና ኦርቶዶክሳዊ ክርስትናን በዋና ጠላትነት የፈረጁ የጎሣ ነጻ አውጭዎችና ከፋፋዮች የፖለቲካውን ሥልጣንና አውድ የተረከቡበት ግዜ ነው።  በዚህ የጥፋት አውድ ውስጥ የአማራን ሕዝብ፥ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያንን፥ ነባር እስልምንና ባህሎችን የማጥፋት ግብ ያለው መንግሥት ሥልጣን በመያዝ የዘር ማጥፋት መርሐግብርን ዘርግቶ እየከወነ ነው።

ስለሆነም ይህ የቡድናዊ ጥቃትንና ሀገራዊ ጥፋትን ለመታደግ የአማራ ሕዝብ ልጆች ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር ጥምረት በመፍጠት ሀገራዊ የቁልቁልት ጉዞውን ለማስቆምና የማኅበረሰብ አንድነት ለማምጣት የአንድነት ሚዲያ በመመሥረት ውይንም አሁን ካሉት መካከል በመምርጥ በማጠናከር ዙሪያ ኢትዮጵያውያን በተለይ ለሰው ልጅ እኩልነት፣ ለሀገር ሏአላዊነትና አንድነት፣ ለፍትህ፣ አሁን ቦርቶዶክሳውያንና አማራ ላይ የተቃጣውን የህልውና አድጋ ለመቀልበስ፣ የተዘራውን የ50 ዓመት የጎሣ ፓርቲዎችና ምሁራን መርዛማ የሐሰት ትርክት ማጽዳት ላይ እንዲተኮር ምክረዐሳብ ያላችሁ በዚህ ቴሌግራም ላይ አጋሩን https://t.me/+Sl9K6hQuMjFmNzU8 ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...