ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ትንሳዔን የምናከብረው እኛ ራሳችን ልንነሳ ነው! አዘቅት ውስጥ ሆነው ክንፍ ስላበቀሉት መዘመርና በዓል ማክበር በእግርም አያራምድም! በንስሐ ለመብረር መነሳት ይቀድማል!

ትንሳዔን የምናከብረው እኛ ራሳችን ልንነሳ ነው! አዘቅት ውስጥ ሆነው ክንፍ ስላበቀሉት መዘመርና በዓል ማክበር በእግርም አያራምድም! በንስሐ ለመብረር መነሳት ይቀድማል!

በ2014 ተጽፎ የተሰራጨ

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀዳማዊ ቃል ነው፥ ያቃል እግዚአብሔር ነው፥ ያቃል በአግዚአብሐየር አብና በአግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ዘንድ ነበረ። ያ ቃል ሰው ሆነ። ለምን?
      
እኛ በገዛ ፈቃዳችን ከሕይወት አልባውና በሐሰቱ ራሱን ካጠፋው ከሰይጣን ጋር ተወዳጅተን፥ የሕይወት ምንጭና መሠረት ከሆነው ከእግዚአብሔር በአመጻችን ተለይተን  ሙታን ሆንን። ከዚህ አይነት ከሕይወት ምኝጭና መሠረት ከእግዚአብሔር በመለየት  ሚሞቱት ሞት  በፍጡር ኃይልና ጥበብ፥ ተጋድሎና ምልጃ መዳን አይቻልም። 

ከዚህ አይነት ሞት መዳን  የሚቻለው በማይሞት፥ በጥበቡ በሞት ላይ ሥልጣን ባለው፥ በደልን መሰረዝ በሚችል፥ ሙቶ ሞትን ድል በሚነሳ፥ በሁሉ ላይ ሥልጣን ባለው አካል ብቻ ነው። ይህ ደግሞ እግዚአብሔር ብቻ ነው። እርሱ ከሶስቱ አካል አንዱ ቃል ከባርሕይ አባቱ ከአግዚአብሔር አብ እና ከባሕርይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፍስ ቅዱስ በመለኮት ሳይለይና ሳይንስ በተለየ አካሉ ቃል ከእመቤታችን ከቅድሰት ድንግል ማርያም ሞት የሚስማማውን የእኛን ሥጋና ነፍስ ነስቶ በመዋሀድ ስለ እኛ ለመሞት ፈቀደ። 

ከአዳም በደልና ጉስቁልና ነጻ አድርጎ ከጠበቃት ከእናታችን ሰው ሆነ፥ አርሱን የሚመለከት አንዳች ኃጢአትና በደል ሳይኖርበት እኛ በነፃ ፈቃዳችን መርጠን ስለሞትንበት አመጽ አርሱ እኛን ተገብቶ መከራ ተቀበለ፥ ታመመ፥ ሞተ፥ መለኮት በተዋሐደው ሥጋው ወደ መቃብር፥ መለኮት በተዋሐዳት ነፍሱ ወደ ሲዖል ወርዶ  ከሞት እሥራት ሁሉ ፈታን። 

ከሙታንም ተለይቶ ተነስቶ ለምናምንበት ለሁላችን የትንሳዔአችን በኩር ሆነን።  ዛሬ የምናከብረው በዓላችን ፋሲካ እያንዳንዳችን ሞት ከምታመጣዋ የኃጢአት ሕይወት ተለይተን በንስሐ የምንነሳባት  ልዩ የሕይወት ቀን ናት። 

የአርሱ የጌታችን ትንሳዔ አንዴ የተደረገ  ነው ፤ ውጤቱ ግን   በግዜ በቦታ ተፈጽሞ ውጤቱም አብሮ ታሪክ ሆኖ አንደሚቀረው  ሐላፊ የፍጡር ሥራ አይደለም። እስከ ዓለም ፍጻሜ በትውልዶች  ለሚያምኑበት፥ በጥምቀት ከሥላሴ ተወልደው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ለሆኑ፥ ፈቃደ ዓለምን፥ ሥጋና ሰያጣንን ስል ተስፋ ምንግሥተ ሰማያት ተዋግተው ለማሸነፍ እርሱ  እንዳፈቀረን በፍቅሩ ለመኖር  እርሱ ራሱ በመለኮታዊ አንደበቱ “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።“ (ዮሐ 14፥15)  እንዳለው ለሚጋደሉ የትንሳዔው በዓል ለምናከብረው ሁሉ እስከ ዓለም ፍጻሜ የማያቋርጥ የእያንዳንዳችን የትንሳዔ የጸጋ ዥረት ነው። ፈቅደን እንደ ሞትን ሁሉ አሁን ፈቅድን እንድንነሳ እነሆ በጌታችን ትንሳዔ ኃይልን ተቀብለናል። መጠቀም የእያንዳንዳችን ሐላፊነት ነው።

ዘሬ ትንሳዔን ስናከብር  የታወቀውን የጌታችንን ትንሳዔ በመታሰቢያነትና በታሪክነት ብቻ አይደለም። በእምነት የተደረገልንን ታላቅ የዘላለም ሕይወት ስጦታ ለማጽናት ልናመሰግን፥ ያንን የተሰቀለውን ጌታ ሥጋና ደም ተቀብለን ልንታተምና ዓለምን ድል ልናደርጋት ኃይል የምንቀበልበት፥ የተዘናጋን የምንነቃበት፥ የሰነፍን የምንበረታበት፥ የወደቅን በንስሐ ትንስዔ ልቡና የምናደርግበት ዕለት ነው። 

ልማድና ባህል ማድመቂያ አለመሆኑን የሚያስብ ይህጭን ቀን የነፍሱ ዘላለማዊነት ዋስትናውን የሚያድስባት ናትና በዋዛ ፈዛዛ አያሳልፋትም። 

በአገራችን በገዳይነታቸው የሚታወቁ፥ ማኅበራዊ፥ ፖለቲካዊ፥ ባህላዊ እየሆኑ የመጡ በአመጻችንና ከመንፈሳዊ ጣዕም ፈጽሞ በመራቃችን መብቴ ነው ብለን በመርከስ፥ ነጻነቴን አላስነካም በሚል ሕይወት ከሚሰጥ ቀኖና ቤተክርስቲያን አኗኗር፥ “ይመቸኛል” ብለን ፍጹም አሕዛባዊ የሥጋ ድሎት ፍለጋ የሚደረግ ዉካታ፥ “እግዚአብሔር ፍቅር ነው”  ስለሆነም ምንም አይነት ሕይወት ቢኖረኝ እስካልካድኩት ድረስ እድናለሁ በሚል እና በባዕዳን የክህደት ትምህርቶች በሕግ ደረጃ የለመድናቸው ከክርስቶስ ሰው መሆን፥ መሞትና መነሳት ዓላማ ጋር የሚቃረን ሕይወት በኢትዮጵያ ተለምዷል፦

፩) በጥምቀት የአንድ የአግዚአብሔር ልጆች የመሆን ሥልጣናቸውንና በክርስቶስ ሁሉም አንድ መሆናቸውን (ዮሐ 1፥12፤  17፥20-21) የዘነጉና በጎሣ “ነጻ አውጭዎች” ሥር ተሰልፈው በዘረኝነትም በክርስትናም መኖር የሚመስላቸው፥ ወገናቸውን በመግደል፥ በማሳደድና በጥላቻ ትርክት ክፋታቸውን ለትውልድ የሚወርሱ “የጌታን ትንሳዔ እናከብራለን” የሚሉ ብዝተዋል፤ በአንዚህ ፊት እንቀድሳለን ፥ አንባርካለን የሚሉ የሐሰት ካህናትና ጳጳሳትም ተፈጥረዋል፤ እነዚህ በዛሬዋ የትንሳዔ በዓላችን ንስሐ አንደገቡና የሚያከብሩትን በዓል ትርጉም በሕይወት እንዲቀምሱት የበታችሁ ሁሉ በጸሉት አስቡን።

፪) አታመንዝር እና አትግደል የሚለውን የእግዚአብሔር ሕግ በመተላለፍ በኢትዮጵያ በቀን 5000 ውርጃ የሚፈጽሙ ሰዎች ይህን ኃጢአታቸውን በኢአማንያን ድንጋጌ መሠረት “ሕጉ” ይፈቅድልናል በሚል ጌታ የሞተለትን አካላቸውን በዝሙት ሲያረክሱ፥ በውርጃ ነፍስ ሲገድሉ ይኖራሉ፤ በዛረዋ የትንሳዔ በዓለም ከክርስቲያኖች ጋር እናከብራለን ሲሉ ይመደጣሉ፤ በዓሉን ሳይሆን ራሳቸውን ሰው የሆነው አምላክ ባከበራቸው ልክ በንስሓ አንዲያከብሩ የበረታችሁ ሁሉ በጸሎት፥ መምህራን በትምህርት እርዱን።

፫) አምላክ የለሹ ምእራባዊ ዓለም በሰይጣን መሪነት ሰዶማዊነትን መብትና ሕግ አድርጎ ከመደንገግ አልፎ አስገድዶ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እንዲያገኝ በሚጥርበት በዚህ ዘመን በአገራችን ከምዕራብና ከምሥራቅ የመጣውን ባህል፥ እምነት፥ ፖለቲካና አስተሳሰብ ሁሉ በጭፍን የሚጋተው ትውልድ ወርሶ ሰዶማዊነት በትምህርት ቤቶቻችን ሁሉ ተስፋፍተዋል፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ትንሳዔ ክርስቶስን እናከብራለን ብለን ስንሰለፍ ለእነዚህ ነፍሳት መዳንና የትንዔን ዋጋ ተረድቶ መጠቀም የበረታችሁ ሁሉ በምትችሉት አግዙን።

፬) ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን መልዕክቱ ስለ ወንድና ሴት ትዳር ባብራበት አንቀጹ እግዚአብሔር የሠራው፥ እጅግ የከበረ፥ ማነጻጸሪያው  ክርስቶስ በደሙ በዋጃት ቤተክርስቲያንና በራሱ መካከል ያለውን ምሥጢራዊና ረቂቅ ምሥጢር ጋር የተካከለ ሆኖ እንደ ገለጸው፦  “ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ። (5፥31-32)” የትንሳዔ ልጆች የሚኖሩት የትዳር  እጅግ ረክሶና ተዋርዶ     የመንግሥታዊ አስተዳደር እና  የግለሰቦቹ ሥጋዊ ፍላጎትና አስተሳሰብ ላይ የተመሠረተ ብቻ ሆኗል፤ የዛሬን ትንሳዔ በዓል የምታከብሩ ባለትዳር ክርስቲያኖች የትንሳዔ ትዳር መልሶ ለመመሥረት ካህናትን ጎብኙ፥ አሕዛባዊ መንግሥትና የክህደት ፍልስፍና፥ የሥጋ ፈቃድና ክፉ ምኞት እየጋለበን ትንሳዔ ክርስቶስን ማክበር እጅግ ያሳቅቀን። 

በዚህ ዕለት ዝንጋኤ እንዳይዘን መጽሐፍት እንዲህ እያሉ ያነቃቁናል፥ ይመሩናል፦

✔️ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።(ሮሜ 5፥ 8)

✔️በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። (ዮሐ 3፥16) 

✔️ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው።(ሮሜ  4፥24-25)

✔️ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...