ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

የነጻነታችን ጊዜ እንዲቀርብ ሁሉም ድርሻውን የወጣ!!


የነጻነታችን ጊዜ እንዲቀርብ ሁሉም ድርሻውን የወጣ!!
ኦነግና ሕወሃት በሜንጫና በመጥረቢያ፣ በማምከንና በማደኸየት፣ በማፈናቀልና በማሳደድ፣ ፍትሕ በመንፈግና በለከት የለሽ የሐሰት ትርክታቸው በማጠልሸት የጀመሩትን ጠፋት #የብልጽግና መንግሥት ወደ መደበኛ፣ ግልጽና በአዋጅ የተደገፈ የዘር ማጥፋት መንግሥታዊ መደበኛ ተግባርነት አሳደገው።
በዚህ ሰይጣናዊ ፕሮጄክት ዒላማ የተደርገው #የአማራ ሕዝብ ራሱን ለማዳን ተጋድሎውን ጀምሮታል። አማራ መነሳት ተፈጥራዊ ህልውናን የማስጠብቅ ተፈጥሮአዊ ንቅናቄ ነው!! ትግሉ ለሰብአዊ ክብር፣ ለፍትሕ፣ ለእውነት የሚደርግ ተጋድሎ በመሆኑ ያሸንፋል። አለማሸነፍ ከምድር መጥፋት ነውና አለማሸነፍ አይቻልም!!
ግን ግን ---- በዚህ ወቅት አራት አይነት ዜጎች ይታዩኛል፦
(1) እንደ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በድንዛዜ ፈዝዞ የሚጨፈጨፍና ከብዙነት ወደ አናሳነት እየወረደ የሚገኝ፤ እየሞተና እየተሰደደ ነጭ ልብስ ለብሶ ሜዳ ላይ እየዘመር ለዓለም ሚዲያ ሁሉ "እዩኝ በሰላም እየኖርኩ ነው" እንዲልና እልቂቱን እንዲደብቅ በሚያደርጉት ግብዝና አስመሳይ አገልጋዮች የሚታለል፤ የገዛ እረኞቹ አደንዝዘው ለእርድ የሚያቀርቡት፣ እንዳይተባበር የሥላሴ ልጅነቱን አስክደው በጎሣ የሚካፈሉት ጳጳስት ያለው--- በዙ ሆኖ እያለ እንደ አናሳ፣ ታሪካዊ ሆኖ እያለ እንደ እንግዳ፣ በዓለ ሀገር ሆኖ እያለ ስደተኛ፣ እውነት እያለው እንደ ዋሾ የሚሰቃይና ሰቃዩን ለማስቆም ለህልውናው ተጋድሎ ያልጀመር፣ ግራ የተጋባ ።
(2) እንደ ኦሮሞና ትግራይ ወጣት የጎሣ ነጻ አውጭዎች የ50 ዓመታት የስሁት ርእዮትና ሐሰተኛ ትርክት ፕሮፓጋንዳ እውነቱን ሐሰት-ሐሰቱን እውነት አድርጎ እንዲመልክት አእምሮውን አጥቦ ሃይማኖቱን ክዶ፣ ዘሩን በጣዖትነት የሚያመልክ፤ ትልቋን ሀገሩን ክዶ ሕወሃትና ኦነግ በጻፉት የድንቁርናና የክፋት ሕገ-መንግሥት የከለለትን ቦታ ወደ ሀገር ለመለወጥ የሚገድልና የሚሞት፤ ለዚህ ዓላማዊ ሌሎች ጎርቤት ማኅበረስቦችን ወደ ጠላትነት የፈረጀና የነጻ አውጭዎቹ የአእምሮ ባሪያ፣ የጦርነት ማካሄጃ መሣሪያ የሆነ፤ ለእልቂትና መከራ መቀጠል መሣሪ መሆኑን ያላቆመ ወገን፣
(3) አማራ ነጻ ሲወጣ እኛም አብረን ከዚህ ከሕውሃትና ኦነግ የዘረኝነት ዲቃላ ከብልጽግና መንግሥት፣ ከእልቂትና ስደት ነጻ እንሆናለን ብሎ በዝምታ መከራ እየተቀበል፣ አንዳንዴም እንደ ሲዳማ የ2011 ነሐሴ አይነት በኦሮምያ ማፍያዎች እየተመራ ወንጀል እየፈጸመ፣ ኦርቶዶከሳውያንና አማሮችን እያጠቃ፣ እንደ አብዲ ኢሌ ዩጎና በሕወሃት ሤራ ክርስቲያን እያረደና በእሣት እየጠበሰ፣ አቢያተ ክርስቲያናትን እያጋየ የሚያደፍጥ፤ ለእውነት፣ ለፍትሕና ለሰባዊነት፣ ለሀገር ሰላም መከፈል የሚገባውን ዋጋ ሳይከፍል እይተሽሎከሎከ ቁሳዊ ሀብት ለማካበት የሚኖር አድርባይ ዜጋ አለ።
(4) የሀገር ሥልጣንን ይዞ በኦነግ-ኦሮሙማ፣ በኦሮ-ውሃቢዝም እና በናዚ-ፕሮቴስታንቲዝም ጥምረት፣ በኦሮምያ መንግሥትና አብይ አህመድ መዋቀራዊ ቅንጅት የሚካሄደውን የጥፋት ስፋትና ጥልቀት የተገንዘቡ፣ ነገር ግን መውጫ መንገዱ ርቋቸው በሀዘን፣ በጸሎት፣ ታጋዮችን በህቡዕ በማበረታት ወይንም ደንዝዘው ገዕዛን እንደሌለው ያበደ ሰው እየቆዘሙ የሚኖሩ ናቸው።
ጥፋትን በፍጥነት ለማስቆም ከተፈለገ፦
1) የመጀመሪያው ብቻ ሳይሆን ከህልውናና ፍትሕ የትጥቅ ትግል ጎን ለጎን የትግራይ ወጣትና ሕዝብ ከሕውሃት ስሑት ፖልቲካዊ ርእዮት፣ የሐሰት ትርክት፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በመካድ ኢትዮጵያን የማጥፋት የውጭ አጀንዳ አግልጋይነት ሆኖ 50 ዓመታት ከመዋተት መላቀቅ፤ ሌሎች ጎረቤቶቹን በጠላትነት ከመመለከት፣ ግዛት ለማስፋፋት ከምቋመጥ፣ ከቅሚያና ግድያን እንደ ዓላማ ከሚያደርግ የአእምሮ ባርነት ነጻ መውጣት፤ እውነትን፣ ክብረ-ሀገርን፣ ፍትሕን፣ ክብረ-ሰብእን፣ መዋሀድን፣ ከአንድ ስሁት የዘር ፓርቲ ባርነት ወደ ሰዋዊና ኢትዮጵያዊ ላዕልና መመለስ እንዲችሉ የተዘፈቁበት የሕውሃት ትርክትና አስተሳሰብ ባርነት እንዲላቀቁ በሁሉ መንገድ መርዳት። የሰው ወይንም የብሔር ጠላት ሳይሆን የአስተሳስብና የርእዮት ጥመት የመክራው ምንጭ እንደሆነ እንዲረዳ መርዳት።
(2) የኦነግ-ኦሮሙማ፣ የኦሮ-ዉሀብያ፣ የናዚ-ፕሮተስታንትና የአስተባባሪያቸው የብልጽግና መንግሥትን ከሐውሃትና ኦነግ የተወርሰ ስሑት ፖልቲካዊ ርእዮት፣ የሐሰት ትርክት፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን መካድ፣ ሌሎች ጎረቤቶቹን በጠላትነት ከመምለከት፣ ግዛት ለማስፋፋት ቅሚያና ግድያን እንደ ዓላማ ከሚያደርግ የአእምሮ ባርነት ነጻ መውጣት። በ50 ዓመታት የኦነግ ትርክት፣ ከጀርባው ተሳፍሮ ደም የሚያፍሰውን ዉህቢዝምና ናዚያዊ-ፕሮቴስታንታዊ ክርስትና፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሳይቀር ኤዲት የሚያደርገው ጸረ-ሴመቲኩን የኦነግ ፕሮቴስታንታዊ ክንፍ ስይጣናዊ ግብ በመረዳት ወደ እውነት፣ ክብረ-ሰብእ፣ ክብረ-ሀገር፣ ከናዚያዊ የዝረኝነት እይታና ድርጊት ወደ መዋሀድና አንድነት ማሰብ እንዲችሉ መርዳት።
(3) ሁልቱም የሕውሃትና የኦነግ መንፈስ ባሮች የሆኑ የየጎሣዎቹ ወጣቶች ከክልል አስተሳሰብ ወደ ሀገራዊ፣ ከጎሣ ትርክት ወደ ኢትዮጵያዊ ትርክት፣ ከሕወሃትና ኦርነጋዊ አስተሳሰብ አምልኮ ወድ ክርስትናና እስልምና፣ ከቅሚያና የመስፋፋት ዝንባሌ የሁላችንን አገርን ወደማጠናከር፣ ወደ በመወሐድና እኩል በጋራ ባለቤት የምንሆንባትን ሀገር ከዘርኛ ፖልቲካ ነጻ ወደ ማውጣት
ርእዮት መለወጥ።
(4) የሃይማኖት መሪዎች ነን ብለው ቦታው በምያዝ ለዘር ፖልቲካ የሚያገለግሉ ሙሰኛ አባቶችን፣ መምህራንን ከየቤተ እምነቶቻችን ማጽዳት።
(5) ግድ ሆኖበት ራሱን ከታወጀበት የ50 ዓመታት የዘር ማጥፋት ሂደት ለማዳን የተነሳውን የአማራ ሕዝብ የህልውናና የፍትሕ፣ የስባዊነትና የእውነት ተጋድሎ በሚቻል ሁሉ መደግፍ፡፡
(6) ከወዲሁ ምን አይነት ሰላማዊ፣ ከዘረኝነት የጸዳች፣ ሰብአዊ ክብር የገነነባት፤ ዜጎች በቦታና በቋንቋ፣ በእምነት የማይቧደኑባት የእኩልነት ምድር ለመሥራት የሚያስችል ሀገር-በቀል ፖልቲካዊ ርእዮት፣ አሰባሳቢ ሀገራዊ ትርክት፣ ከብረ-ሰብእና ፍትህ የሚነግሥበት የአስትዳደር ሥርዓትና መንግሥታዊ መዋቅር እንደምናበጅ መወያየት መጀመር።
ሌላ መፍትሔ ሰጭና ነጻ አውጭ መጠበቅ የባርነት ስነ-ለቦና ሰለባ ለሆኑ ሰዎች ብቻ የሚስማማ በሽታ ነው። ሁሉ ድርሻውን የወጣ!!

https://youtu.be/HrYA9rWKcGE?feature=shared

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...