ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ከሚያዝያ 20 ጀምሮ በኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክርስቲያን ከሚካሂደው ከዝክረ ኒቂያ ጉባኤ ምን እንጠብቅ?

ከዝክረ ኒቂያ ምን እንጠብቅ?   

በትንሹ  ከዚህ በታች ያለውን ጉዳይ የመፍትሔ አቅጣጫና ቀኖና ነው፦

(1)  በጎሣ ፖለቲካ እየተመራ የተሾሙ ኤጲስቆጶሳትና ጳጳሳት  እንዲሁመ መለካዊነት፣ ሲሞናዊነት፣ ዘረኝነት በደዌ ደረጃ የተጣባቸው፣ በቁሳዊ ሃብት ማጋበስ ምንኩስናን ያዋረዱ ወገኖቻችን ሕይወት የሚመዘንበትና የሚታረምበት  ውሳኔና ቀኖና ማወጅ፤

(2) ምእመናንን በጎጥና በቋንቋ፣ በትርክት፣ በውጭ-ገብ የፖለቲካ ርእዮተ ዓለም ክርስቲያኖችን  መከፋፈሉን፣ እያጭራርሰ እንደሚገኝ፣ የጎሣ ሲኖዶሳት እየትፈለፈሉ በመሆኑ የተከተለውን የምእመናን መለያየት፣ መጠላላት፣ መዋጋት፣ ተበትኖ ለክርስትና ጠላት ለሆኑት አካላት የተመቻቹ  መሆናቸውን ያገናዘበ ኦርቶዶከሳዊ መመሪያና ለመእመንና ለካህናት ማስተላለፍ፤

(3) አርአያ ምንኩስናን በማራከስ በከተማ የከተሙ መነኮሳት፣ ሀብት በማፍራት ላይ በማተኮር ምእመናንን፣ ካህናትን አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን  ተልእኮን የዘነጋ አኗኗርን የሚመለከት ግልጽ  የእርምት መመሪያና ቀኖና፤

(4) ሲኖዶስ የጳጳሳት ብቻ እንጂ የካህናትና ምእመናን  ተሳትፎ የሌለበት ሆኖ መቀጠሉ ያስከተላቸውን ጥቅሞችና ጉዳቶች በመገምገም ለወደፊቱ ግልጽ የሆነ የተሳታስፊዎች፣ የአጀንዳ አቀራርጽ፣ የውሳኔ አሰጣጥና አፈጻጸም ቀኖና ፤

(5) በምእመናን ላይ በመንግሥት የተፈጸመውን ጭፍጨፋ፣ ማፈናቀል፣ ሲኖዶስ ውስጥ የሚገባውን ጣልቃ ገብነት፣ የገዳማትና አድባራት፣ መናኒያን መደፈርን፣ የነገረ መለኮት ት/ቤቶችና ማሠልጠኛዎች ከመናፍቃን መምህራን፣ ከመናፍቃን መጽሐፍትና ኮርስ የመጠበቅነ አሠራርና የሊቃውንት መዋቅራዊ ተሳትፎ መበየን፤

(6) የሚሊዮኖች መመናን ፍለሰት የውስጥና የውጭ መንሴዎችና መፍትሔዎችን በግልጽ ማሳየትና ለመፍትሔው ቀኖናዊ ግዴታ ያለባቸውን የቤተ ክርስቲያን መዋቅራትን ቀጣይ ድርሻ፣ የአፈጻጸም ክትትል ሥራዓት ማመላከት፤

(7) ኦርቶዶከሳዊነትን የሚጻረሩ ሐገራዊና ክልላዊ ሕጎችን በሚመለከት ምእመናን ምን አይነት ክርስቲያናዊ ምላሽ መስጥት  እንድሚግባቸው ግልጽ ቀኖናዊ መመሪያ፤

(8) በጎሣ ፓርቲዎችና ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያንን፣ እርሷ የቀባቻቸው ነግሥታትን፣ ታሪከን፣ አስተምህሮዎችን፣ ሃይማኖትን የአንድ ጎሣ ቋንቋ ተናጋሪ በማድርገ ፈርጆ ማጥቃትን፣ የጨቋኝና የተጭቋኝ ትርክት በመተርክ  ቤተ ክርስቲያንን አጥፊ ተብሎ ከሚሰየመው ወገን አድርጎ በመዋቅር ማጠቃት ላይ በሚገኘው የፖልቲካ ሥራዓት አንጻር ምእመናን፣ ካህናት፣ ኦርቶዶክሳውያን ምሁራንና ሊቃውንት ሊወጡት የሚገባቸው ድርሻን የሚያሳይ ቅኖናቂ መመሪያ መስጠት፤

(9) የቤተ ክርስቲያን ሥራ መፈጸሚያ የሆነው ከመንበረ ፓትሪያርክ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን  በተዝረጋው መዋቅር ላይ የተሰየሙ ኃላፊዎች ሁሉ ምእመናን ከማብዛት፣ ከማጽናት፣ ከመጠበቅ፣ አንድነታቸውን ከዘርም ሆነ ከዘመናዊ የአቅሌሲያው ቅዱስ ሕብረት የሚነጥል ሁኔታ በመጠበቅ አንጻር የሚገመገሙበትና የሚጠየቁበት አሠራር እንዲኖር አቅጣጫና ቀኖና ማስቀመጥ

(10) የቤተ ክርስቲያን የገንዘብና የሰው አስተዳደር ማእከላዊ አመራርና ስርጭት ኖሮት አገልግሎት ከከትማ ክምችት ወደ ጠረፍና ገጠር እንዲወጣ የማድርገ አቅጣጫ ማስቀመጥ

(11) መነኮሳት ሀብት ከማፍራት የታገዱ እንዲሆኑ ነባሩን ቀኖና ማጽናትና የአፈጻጸም መመሪያ መስጠት፤

(12) የጎሣ ሲመተ ጵጵስና እንዲሻር ቀኖናውን መመለስ፣ በየክፍለ ሀገሩ ዘርኞች የሚመሠርቱት ፖለቲካዊ ሲኖዶስ ምእመናን እንዳይከትሉ፣ ቢከተሉ በንፍሳቸው ላይ የሚምጣውን ጥፋት የሚያሳይ መግለጫና ትምህርት መስጠት፤

(13) ሥራዓተ ገዳም፣ ሥራዓተ ምንኩስና፣ መነገጃ የሆነው ጸበል፣ ስለ መሳለም ጉዞና ሥራዓቱ፣ የካህናትና መነኮሳት አለባብስ፣ የመመናን ጋብቻ፣ ውርጃ፣ ቅድመ ጋብዛ ዝሙት፣ የዘር ፖልቲካ ወዘት የትብራራ ቀኖና

(14) አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን መዋቅርና የመንግሥት መዋቅር ግኑኝነት፣ 

(15) የቤተ ክርስቲያን ሚዲያ የምእመናን (የአጥቢያ፣ ወረዳ፣ ሀገረ ስብከት ጉዳዮቸ፣ የትምህርት) ንብረትና ጉዳይ መነጋገሪያ እንዲሆን ህግ መድንገግ

(16) ኦርቶዶክሳውያን በየአጥቢያው ተመዝግበው እንዲታወቁ፣ አስተዋጾአቸው ብቻ ሳይሆን መፍናቅል፣ መገለል፣ መግደልና ልዩ ልዩ ምንግሥታዊና ማኅበራዊ ጥቃቶች መዝገብና ሥርጭት ሥራዓት እንዲዘርጋ


(17) የቀደሙ ለክርስትና መልካም ነግሥታት ክብር፣ አሁን ክፋት የሚፈጽሙትን የመውቀስ

(18) የቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ዕቅበትና የመዋቅሩን ኃላፊዎች ተጠያቂነት ግልጽ ማድረግ

(19) በስደትና በውጭ ስላለችው ቤ/ክ፣ አስተዳደር፣ መመናን፣ ካህናት አገልግሎትና አኗኗርን የሚመለከት ቀኖናና አሠራር ማመልከት
ስ/rSGreMfBtOw

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...