ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

የነጻነታችን ጊዜ እንዲቀርብ ሁሉም ድርሻውን የወጣ!!

የነጻነታችን ጊዜ እንዲቀርብ ሁሉም ድርሻውን የወጣ!! ኦነግና ሕወሃት በሜንጫና በመጥረቢያ፣ በማምከንና በማደኸየት፣ በማፈናቀልና በማሳደድ፣ ፍትሕ በመንፈግና በለከት የለሽ የሐሰት ትርክታቸው በማጠልሸት የጀመሩትን ጠፋት #የብልጽግና መንግሥት ወደ መደበኛ፣ ግልጽና በአዋጅ የተደገፈ የዘር ማጥፋት መንግሥታዊ መደበኛ ተግባርነት አሳደገው። በዚህ ሰይጣናዊ ፕሮጄክት ዒላማ የተደርገው #የአማራ ሕዝብ ራሱን ለማዳን ተጋድሎውን ጀምሮታል። አማራ መነሳት ተፈጥራዊ ህልውናን የማስጠብቅ ተፈጥሮአዊ ንቅናቄ ነው!! ትግሉ ለሰብአዊ ክብር፣ ለፍትሕ፣ ለእውነት የሚደርግ ተጋድሎ በመሆኑ ያሸንፋል። አለማሸነፍ ከምድር መጥፋት ነውና አለማሸነፍ አይቻልም!! ግን ግን ---- በዚህ ወቅት አራት አይነት ዜጎች ይታዩኛል፦ (1) እንደ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በድንዛዜ ፈዝዞ የሚጨፈጨፍና ከብዙነት ወደ አናሳነት እየወረደ የሚገኝ፤ እየሞተና እየተሰደደ ነጭ ልብስ ለብሶ ሜዳ ላይ እየዘመር ለዓለም ሚዲያ ሁሉ "እዩኝ በሰላም እየኖርኩ ነው" እንዲልና እልቂቱን እንዲደብቅ በሚያደርጉት ግብዝና አስመሳይ አገልጋዮች የሚታለል፤ የገዛ እረኞቹ አደንዝዘው ለእርድ የሚያቀርቡት፣ እንዳይተባበር የሥላሴ ልጅነቱን አስክደው በጎሣ የሚካፈሉት ጳጳስት ያለው--- በዙ ሆኖ እያለ እንደ አናሳ፣ ታሪካዊ ሆኖ እያለ እንደ እንግዳ፣ በዓለ ሀገር ሆኖ እያለ ስደተኛ፣ እውነት እያለው እንደ ዋሾ የሚሰቃይና ሰቃዩን ለማስቆም ለህልውናው ተጋድሎ ያልጀመር፣ ግራ የተጋባ ። (2) እንደ ኦሮሞና ትግራይ ወጣት የጎሣ ነጻ አውጭዎች የ50 ዓመታት የስሁት ርእዮትና ሐሰተኛ ትርክት ፕሮፓጋንዳ እውነቱን ሐሰት-ሐሰቱን እውነት አድርጎ እንዲመልክት አእምሮውን አጥቦ ሃይማኖቱን ክዶ፣ ዘሩን በጣዖትነት የሚያመልክ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...

ከሊቢያ ውድቀት ኢትዮጵያ ምን መማር አለባት?

  ከሊቢያ ውድቀት ኢትዮጵያ ምን መማር አለባት? አገር የሚጠፋው በብዙ መንገድ ቢሆንም የሊቢያን አወዳደቅና የምዕረባዊያንን ሤራ በአጭሩ በመመልከት አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚካሄደው ማመሳከሩ መፍትሔውን ቶሎ እንድንፈልግ ይረዳናል ብዬ አምናለሁ። (አቶ ቱምሳ ዹጋ) መምህር ፋንታሁን ዋቄ “ኦርቶዶክሳዊነትና የሰይጣን መንግሥት በሚል ርዕስ ካሳተመው የትርጉም መጽሐፍ ምዕራፍ አንድ  በባለቤቱ ፈቃድ ተቀንጭቦ የተወሰደ። በትዕግስትና በማሰውተዋል ያንብቡ፣ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚካሄደው ሁለገብ ብጥብጥ ጋ ያገናዝቡ፣ ከዚያም ለአገራችን የሚበጀውን ሀሳብ እያመነጩ ለሕዝቡና ለሚመለከታቸው ባገኙት መንግድ ሁሉ ያጋሩ። ለአገርዎ ውለታ በመሥራት የደገሰውን ጥፋት ይቀንሱ። መልካም ንባብ የአገራት መንግሥታትን መውደቅና የሚጀመርው መሪዎች ከገዛ አገራቸው ሕዝብ ጋር በማይጣጣም አስተሳሰብ ሲመሩ ብቻ ሳይሆነ የአገራቸውን ፈቃድ ለመፈጸም በሚያደርጉት አርቆ አስተዋይነት ምክኒያት ኃያላን አገራት ሥጋት ከገባቸው በሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት ነው። በኢትዮጵያ ያለው ሁለት መልክ አለው። የአገራችን ጠላት ራሳቸው የአገሪቱ ልሂቃን ሲሆኑ ሁለተኛው የውጭ ጣልቃ ገብነትን ባለመዋቅ ወይንም በጊዜዊ ጥቅም ተገዝተው የሚያገለግሉ የፖለቲካ ልሒቃን መንሰራፋት ነው።  የሊቢያ ግን በግልጽ መንግሥትን ከራሲ አገር ሕዝብ ጋር በማጋጨት የጣሉት ምዕረባዊያን ነቸው።   ለዚህ የሊብያን  ቀውስ  መመርመር ማስረጃ ነው፡-  ጋዳፊ ሥልጣን ከዯዘ በኋል፡-  1. ሕዝቡን ከበረሃ ችጋር አውጥቶ ዜጎችን ለከፍተኛ ሰላምና የኑሮ ደረጃው እንዲያድግ ያደረገውን መሪውን ሙሀመድ ጋዳፊን አስገደሉት 2. ይህን ተከትሎ ኢስላማዊ መንግሥትን (Islamic S...

በኦርቶዶክስ ዘፈን ይፈቀዳልን?

ይህን ሰሞን ስለ ዓለማወ ዘፈንና ሙዚቃ የሚወዛገ ቡ መምህራኖችን ተመልክቻለሁ። እኔ የቀኖና ሊቅ አይደለሁም። ነገር ግን በሃይማኖት የማስብ ስለሚመስለኝ አስተያየት መስጠት አስፈላጊ መስሎ ታየኝ። ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖትን ሕይወቱ ስላደረገ ሰውና ማኅበረሰብ ስንነጋገር የሰሞኑን ፖለቲካና ከመንፈሳዊ ዓላማ ውጭ የሆኑ ድብቅ ፍላጎታችን በተቻለ መጠን ያልተቀላቀለበት   ትምህርት መስጠት ምእመናንን በማሳሳት ምክንያት ከበጎቹ ጌታ ከእየሱስ ክርስቶስ ቅጣት ያድናል። ቤተ ክርስቲያን ከሁሉ በላይ የቅዳሴ የጸሎት ዜማን እስከነ ዓላማውና መንፈሳዊ ግቡ፥ ከእነ ጥልቅ ምሥጢሩ ተረድተን እንድናዜም ትፈልጋለች። ታስተምራለች፥ በተግባርና በህይወት ታሳያለች። በሂደቱ ሁሉ ህሊናችን፥ ዓይነ ልቦናችን እና መላው ተስፋችን ሁሉ ሰመያዊ ማንነታችንን አንጾ በመገኘት ላይ ታተኩራለች።   ልጆቿም እንዲሁ በግልና በጋራ ድምፍ አውጥተው ወይንም በአርምሞ ሲያዜሙና ሲናገሩ ቅዳሱው ባመለከታቸው መሠረት ነፍሳቸውን ወደ ሰማዩ አባታቸው እንድታተኩር አድርገው ፈጣሪያቸውንና መድኀኒታቸውንን ክፍ ክፍ ማድረግና ማመስገን እንዲሆን እንደምታስተምር የቅዱሳን ሕይወት ሁሉ ይጠቁማል። ቤተ ክርስቲያን በግልጽና በአትቃላይ ዓለማዊ/ሥዝም ዘፈንን ኣታወግዝም። በመጽሐፍ ቅዱስ   የሚሰጠን ምልክት በጥንቃቄ   መመልከት ያስፈልጋል፦ ሮሜ 13፡13-14 “በቀን እንደምንመላለስ በአግባብ እንመላለስ። በጭፈራና በስካር አይሁን፤ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፤ በክርክርና በቅናትም አይሁን።   ይልቁንም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም ይፈጽም ዘንድ ለሥጋ በዐሳባችሁ አትመቻቹለት። “ 1 ጴጥሮስ 4:3 “አሕዛብ ፈቅደው እንደሚያደርጉት በመዳራት፣ በሥጋዊ ምኞት፣ በስካር፣ በጭፈራ...

እየገደሉ የምሥራች

 የድንቁርናና ሕሊና-ቢነስት ያነገሣቸው  የጎሣ ልሂቃን "የምሥራች" ትርጉም አምባገነን፥ ቁማርተኛና የወሮበሎች መንግሥት የሚመራውን ሕዝብ መከራ "የምሥራች" እያለ ያለማምደዋል።  የሕወሃት/ኢሕአዴግና ብልጽግና በዚህ ሞትና መከራን ድልና እድገት አድርገው በማቅረደብ አንድ አይነት ናቸው። ስዩም መስፍንና አሊ አብዶ  የሕወሃትና የሻዕብያ የዘረፋ ሀበት ክፍፍል ግጭት በባድሜ እንደ ምክንያት ትርጉም-የለሽ   ከ120 ሺህ ሕዝብ በላይ ወገን አስፈጅተው፥ ይግባኝ በሌለው የአልጀርስ ስምምነት "የምሥራች፥ እንኳን ደስ ያላችሁ" ብለው ሕዝቡን አስጨፍረዉታል። የፈረደበትን ዐመሓራና ኦርቶዶክስ ክርስትናን በማጠፋት አጀንዳ ላይ ቢስማሙም  ነገር ግን በተለመደው የሀብት፥ የብሔር ግዛት በሰስፋት፥ ዲሞግራፊ በመቀየር፥ አሰስ አገር የመፍጠር እና የበላይነት ለማስፈን ባደረጉት ግጭት ሕወሃትና ብልጽግና በየበኩላቸው ወደ ጦርነት የመሩትን ወገን ድል አግኝተናል፥ የባሰ አደጋ እንዳይመጣ አድርገናል ብለው "የምሥራች" ብለዋል። ብልገግና የአባይ ግድብ ከደ ጋየወረደው የክረምት ጎርፍ ስለ ሞላ የምሥራች በሚ ልሕበቡን በተለይ አሰስ አበባ ውስጥ አስጨፈሩ ፥ ግን የኢትዮጵያን ባንዲራ ያውለበለቡ ወጣቶችን የኦሮሙማው ፖሊስ ሠራዊት ቀጠቀጠው፤ አብይ አህመድ የአዲስ አበባ፥ የደብረ ዘይት፥ የናዝሬትና ሌሎች ከተሞች ነዋሪችን የሕዝብ አሠፋፈር ለመቀየር ኦርቶዶክስ ክርስቶያቸኖችን፥ ጉራጌዎች፥ ኮንሶዎች፥ ወላይታና ጋሞዎች ወዘተ ዒላማ ያደረገ ማፈናቀል እያካሄደ "ከተሞቻችን እያማሩ ነውና የምሥራች"  ብሏል።    የአማራን ሕዝብ በምድርና በረር ኃይል ሕዓናትን፥ ካህናትን፥ ገዳማውያንን፥ ገበሬዎችን በመጨፍጨፍ ላይ የሚገኘው የአብ...

የአብይ አህምድ አሊ በመተግበር ላይ የሚገኙ ዘር የማጥፋት ስልቶች

 የአብይ አህምድ አሊ  በመተግበር ላይ የሚገኙ ዘር የማጥፋት ስልቶች  የአብይ አህመድ አሊ የአእምሮ ወላጆችና ተልዕኮው አብይ አህምድ አሊ ከጣሊያን ፋሽት፥ ከግራኝ አህመድ ላኪዎች ጽንፈኞች እና  ዓለምን በባርነት ለመግዛት ከሚሠሩ ኃያላን አገራት አስተምህሮ እና ከቅድመ ክርስትና አሕዛባዊ የአረሜነነት ጠባይ ተቀይጦ  በተፈጠረ አስተምህሮ የተወለዱ  ደርግ፥ ማርክሲስት ንቅናቄዎች፥ የጎሣ ነጻ አውጭዎች፥ በተለይ ሕወሃትና ኦነነግ  ተዳቅሎ የተወለደውን የአነግ-ኦርኦሙማ የብልጽግና ፓርቲ ሠሪና መሪ ነው። ይህ ሰው የአእምሮ ወላጆቹን ዕሳቤዎች አዳቅሎ የቆየ ዓለማቸውን ከግብ ለማድረስ ሥልጣን ላይ እንዲቀመጥ የተደረገ ሰው መሆኑን በቆይታው በተግባር አረጋግጧል።  በፖለቲካ አስተዳደጉ ከሤራ፥ ቁማርና ዘረኝነት፥ ሌብነትና ሐሰተኝነት ውጭ ምንም አይነት ከሰብአዊነት፥ ከፍቅር፥ ከእውነት፥ ከአገራዊነትና የማኅበረሰብ ሰላምና ተዋህዶ ጋር የሚያስተዋውቅ  ፖለቲካ፥ ትምህርት፥ አስተዳደርና አሠራር ለማየት እድል አላገኘም።  ያደገው በሕወሃትና በኦነግ የጥላቸና የሐሰት ትርክት የመርዝ ጡጦ ነው። ጥመቱን፥ ክህደቱን፥ አላዋቂነቱንና ለማንኛዉም አነይት የባዕዳን አጀንዳ ተሸካሚነት የተዘጋጀ መሆኑን የተረዱ የውጭ አካላት ተሯሩጠው ሕወሃትን ተክቶ የተጀመረውን፦ በአፍ መፍቻ ቋንቋው አማራ የሆነ (ሕወሃትና ኦነግ በጻፉት የብሔርና ብሔረሰብእ ተርጓሜ መሠረት አማራ የተባለ ሁሉ)  ማንኛውንም ሰው እና  ሁለተኛ   በሃይማኖት ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የሆነ ማንኛውንም ማኅበረሰብእ    ከኢትዮጵያ ምድር አስተሳሰቡንና ታሪኩን፥ ከተቻለ በአካል የማጥፋት ፕሮጄክት አስፈጻሚ አድርገ...

ለፋኖ ብሔርተኝነት የሚሰብኩ ልሂቃን የዐመሓራነት፥ የኦርቶዶክሳዊነት፥ የኢትዮጵያዊነት ጠላቶች ናቸው

 ለፋኖ ብሔርተኝነት የሚሰብኩ ልሂቃን የዐመሓራነት፥ የኦርቶዶክሳዊነት፥ የኢትዮጵያዊነት ጠላቶች ናቸው! አንዴት? እነሆ የእኔ የግሌ መከራከሪያ ብሔርተኞች ከፈጠሩት ግጭት፥ ከዘሩት ጥላቻ፥ ከከፉት የመጠፋፋት በር የተወሰነ ጊዜ ለማረፍና ራሳቸውን ማደላደል ሲፈልጉ የሚቀርቧቸው ደካማ  የማስታረቂያ  ንንግግሮች አሉአቸው፦ ተዋልደናል የመከራ ጊዜን አብረን አሳልፈናል እጣ ፈንታችን አንድ ነው  በመቻቻል እንደ ሌሎቹ አገራት መበልጸግ እንችላለን ያለፈ ቁስልና የታሪክ ቁርሾን መልሶ መቀስቀስ አያስፈልግም አጥፍተናል ብለው የታሪክ በደልን የሻሩ አገራት አሉ እንድ ቤተ እምነት ውስጥ እናመልካለን ወዘተ  ይላሉ። እንዚህ አነጋገሮች ሁሉ ውስጥ የመለያየት፥ የበቀል፥ የልዩነት፥ እነርሱና እኛ የሚል ድምጸት፥ የታሪክ ካሣን ባልነበሩበት ዘመን አሁን ካለው ትውልድ የመፈለግ፥ ጥላቻ፥ አለመተማመን በግልጽ ይታያል።  በሌላ አነጋገር  ብንዋለድም እኔ የተለየሁ ፍጡር ነኝ ብቻ ሳይሆን እኔና አንተ ጠላቶች ነን የሚል መልእክት ያዘለከሚል ነው።  በዚህ ንግግር ውስጥ ክብረ-ሰብእ፥ እውነት፥ ፍትሕ፥ የትውልድ የመዋሐድ ተስፋ የለም። ሁሉም ተጠባብቀን በጥንቃቄ መኖር ወይንም መጠፋፋት ከደጃችን አለ የሚል በትክክል የሰው ልጅን ክብር፥ የአገርን ምሥጢር፥ የእውነተኝነትና የሕይወት መሠረት፥ የፍትሕና የርትዕና የሰብአዊነት መገለጫ ፈጽሞ የዘነጋ መሠረተ-ፍልስፍናው ጸረ-ሰላም፥ ጸረ-ሰብእ እና ጸረ-ሀገራዊ አንድነት የሆን አስተምህሮ ነው። ለምሳሌ እነ አቶ ወልደአብ ወልደማርያም ውልደታቸው ትግራይ ቢሆንም በጣልያን ቅኝ ግዛት ግዜ ጣልያንንም ሆነ አንግሊዝን ሲቃወሙ አልታዩም።  እነ አክሊሉ ሀብተወልድ ከጣልያንና ከጣልያን ደጋፊዎች የካ...