ብሔርተኞች ከፈጠሩት ግጭት፥ ከዘሩት ጥላቻ፥ ከከፉት የመጠፋፋት በር የተወሰነ ጊዜ ለማረፍና ራሳቸውን ማደላደል ሲፈልጉ የሚቀርቧቸው ደካማ የማስታረቂያ ንንግግሮች አሉአቸው፦
ተዋልደናል
የመከራ ጊዜን አብረን አሳልፈናል
እጣ ፈንታችን አንድ ነው
በመቻቻል እንደ ሌሎቹ አገራት መበልጸግ እንችላለን
ያለፈ ቁስልና የታሪክ ቁርሾን መልሶ መቀስቀስ አያስፈልግም
አጥፍተናል ብለው የታሪክ በደልን የሻሩ አገራት አሉ
እንድ ቤተ እምነት ውስጥ እናመልካለን
ወዘተ
ይላሉ። እንዚህ አነጋገሮች ሁሉ ውስጥ የመለያየት፥ የበቀል፥ የልዩነት፥ እነርሱና እኛ የሚል ድምጸት፥ የታሪክ ካሣን ባልነበሩበት ዘመን አሁን ካለው ትውልድ የመፈለግ፥ ጥላቻ፥ አለመተማመን በግልጽ ይታያል። በሌላ አነጋገር ብንዋለድም እኔ የተለየሁ ፍጡር ነኝ ብቻ ሳይሆን እኔና አንተ ጠላቶች ነን የሚል መልእክት ያዘለከሚል ነው። በዚህ ንግግር ውስጥ ክብረ-ሰብእ፥ እውነት፥ ፍትሕ፥ የትውልድ የመዋሐድ ተስፋ የለም። ሁሉም ተጠባብቀን በጥንቃቄ መኖር ወይንም መጠፋፋት ከደጃችን አለ የሚል በትክክል የሰው ልጅን ክብር፥ የአገርን ምሥጢር፥ የእውነተኝነትና የሕይወት መሠረት፥ የፍትሕና የርትዕና የሰብአዊነት መገለጫ ፈጽሞ የዘነጋ መሠረተ-ፍልስፍናው ጸረ-ሰላም፥ ጸረ-ሰብእ እና ጸረ-ሀገራዊ አንድነት የሆን አስተምህሮ ነው።
ለምሳሌ እነ አቶ ወልደአብ ወልደማርያም ውልደታቸው ትግራይ ቢሆንም በጣልያን ቅኝ ግዛት ግዜ ጣልያንንም ሆነ አንግሊዝን ሲቃወሙ አልታዩም። እነ አክሊሉ ሀብተወልድ ከጣልያንና ከጣልያን ደጋፊዎች የካቶሊል ሀገሮች ጋር ተናንቀው የኤርትራን ከቅኝ ግዛት ካላቀቁ ቦሀላ እነ በስዊዲን ሚስዮን የተማሩትና የሉተራን ፕሮቴስታንት ሰባኪ የተደረጉት አቶ ወልደአብ ወልደማርያም ጸረ ኢትዮጵያ ሆነው ብቅ አሉ። በአጭችሩ ሀማሴንና አክሱም፤ አከካለ ጉዛይና አድዋ የሚያገናኛቸው ገመድ የለም በሚል ትርክከት ነበር።
የአንድነትና የመዋሐድ ጥላቻን የሚፈጥረው የትርክት ምንጭና መነሻ ጠላት መሆኑን ማሰብ የማይችል ምሁር ማንኛውንም ዕሳቤና ፖለቲካዊ ግብ ከማስቀመጡ አስቀድሞ መጠየቅ ያለባቸውን ጠቃሚ ጥያቄዎች ነበሩ። እነዚህም፦
ከረዥሙ የሺ ዘመናት ታሪካችን የቅኝ ገዥ ግማሽ ምዕተ ዓመት የፈጠረውን አስተሳሰብ ለምን መረጥሁ?
ነጻነት ምን ማለት ነው? ከመለያየት በምን ይለያል?
በትልቅ አገር ውስጥ የሚስማማንን ስነ መንግሥት ከሌሎች ጋር መገንባት ነው ወይስ ቅኝ ገዥዎችና አፍሪካን ባርያ ለማድረግ፥ ኢትዮጵያን ከውሃ አካላትና ከልዩ ልዩ አካላቷ መቆራረጥ ከሚሹት ጋር እንድተባበር የሚያሳስበኝ ፍልስፍና ምንድነው?
ነጻነት ከሰብአዊነት፥ ከፍትህ፥ ከእኩልነትና ሰላም፥ ከትውልድ ብሩህ ተስፋ የተለየ ትርጉም አለው? ከሌሎች እነዚህ ጸጋዎች በመለያየትን ጥግ ላይ ክፍለ አገርን ሀገር ማድረግ፥ በተባበሩት ምንግሥታት መምዝገብ ለነጻነት ዋስትና ነው?
የኢትዮጵያ አካል ብቻ ሳንሆን ማእከልና ታሪክ የነበረን የሰሜን ክፍል ቅኝ ገዥ ጠላት ከእናቱ ከኢትዮጵያ ቆርሶ ከ4ኛ ክፍል በላይ የማይማሩ ለባርነት የተዘጋጁ አእምሮዎችን ሲፈጥር 60 ዓመታት ስለበደለን በባርነት ዘመናችን ኮርትን ሺ ዘመናት በማእከልነት ያኖርናት አገራችንን ጥለን መሄድ ጥቅሙ ምንድነው?
—- ወዘተ የሚሉ ይያቄዎችን ጠይቆ ለመመለስ የአእምሮ ነጻነት ያስፈልጋል። ከክፉ የጠላት አስተምህሮ የበላይነትና የበታችንት ስነልቦና ውቅር መላለቀቅ ይጠይቃል — ወለደአብ ወልደማርያምና እንርሱን ተከትለው የተነሱት የኤርትራ ነጻ አውጭ መሪዎች ይህን ለመጠየቅ አቅም አልነበራቸውም። ለእነርሱ ቁም ነገሩ ከአረቦችና ከምእራባውያን በሚለገስላቸው የጠላት ምክርና ገንዝብ፥ መሣሪያና ሙደሳ ወጣቶችን በታጠበው አእምሮአው መልሰው እያጠቡ ጦርነቱን ለ30 ዓመታት ለሃይማኖት እንደሚሰዋ ሰማዕት በጭካኔ መዋጋት ነበር።
ለመለየትና አገር ለመፍጠር ትግል የሚጀምሪ ብሔርተኞች ወሳኝ ለትውልድና ለአገር የሚተርፉ፥ ከስህተት የሚጠይቁ ጥያቄዎችን የማንሳት ሙሉ አቅማቸው የተሰለበ ነው። ሙሉ አእምሮአቸውን እንደ ማኅደር ክፍት አድርገው ለባዕዳን ትምህርትና አስተሳሰብ ክፍት አድርገው ከመጋትና ወደ ተግባር ለመለወጥ ከመጋደል የተለየ አቅም ኤእኖራቸውም። ሕሃትናና ኦነግን የመሠረቱና በዘመናት የጸጠሯቸው መንጋ ተከታዮቻቸው በዚህ ያለማሰብና በጭፍን የመከተል ደዌ ተጠቂ ናቸው። አቅማቸውና ኃይላቸውን የሚያባክኑት የሐሰት ትርክት በመፍጠርና ቀድሞ የነበረውን በማጠልሸት፥ አሻራ በማጥፋት ላይ ነው። ለምሳሌ ከሸዕብያ፥ ሕወሃትና ኦነግ ጀምሮ የጎሣ ነጻ አውጭዎችና ልሂቃን ሁሉ በሚከተሉት የኢትዮጵያ ታሪክ ምንጮችና ትርክቶች ላይ በአሉታዊነት የዘመቱ ናቸው፦
፩) ክብረ ነገሥት
፪) የኢትዮጵያ የ3000 ዘመን ታሪክ እና የሕገ ልቡና የ2000 አመን ትውፊታዊ ትርክት
፫) በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጉልህ የታሪክ አሻራ ያላቸው ክርስቲያን ነግሥታት ዙና መዋዕልና ታሪክ
፬) የኢትዮጵያ ጥንታዊ ካርታና የሕዝቦች አሠፋፈር ታሪክ
፭) የአህመድ ግራኝ ወራሪነት፥ አውዳሚነትና የኦቶማን ቱርክ ጂሃድ መልዕከተኛነት
፮) የተለያዩ ብሔረሰቦች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ባደረጉት ያደረሱት አሉታዊ ተጽእኖ ታሪክ
፯) የእምነቶች መስፋፋትና መልሶ መዳከም ታሪክ ከውጭ ጣልቃ-ገብነት ጋር ያለው ቁርኝት
፰) በውጭ ጠላት ወረራ አጋጣሚዎች ከጠላት ጋር በማበር አገራቸውን የወጉ ወገኖች ታሪክ እና የልጅልጀጆቻቸው የባንዳነት ስነልቦና ለዛረዋ የኢትዮጵያ ያለው አስተዋጽኦ
፱) አንዳንድ ውጭ-ገብ እምነቶች ቅኝ ገዥዎች መንገድ ጠራጊነትና አንድነትን በማዳከም፥ ትውልድን በመከፋፈል፥ ነባር ባህልን በማዳከም ላይ የነበራቸውን ተጽእኖ ማንሳትና መግለጥ —ወዘተ
በተቃራኒው እነዚህ ልሂቃን የሚከተሉት ጊዳዮችና ትርክቶች በማራመድና በማግነን ነባሩን ለመተካት እጅግ የተጋሉ፦
፩) የምዕራባውያን ወይንም የአረብ ስነ-አስተዳደር፥ የዘመን አቆጣጠር፥ ፊደል፥ ቋንቋ አስፈላጊነትና ልህቀት
፪) የምእራባውያን ወይንም የሌሎች ፖለቲካዊ ርእዮትና የአኗኗር ዘይቤ ከአገራዊው ነባር እንዴት ብልጫ እንዳለው
፫) የአገር ነባር እምነታዊና ባህላዊ የረዥም ዘመናት ሕየወት አገር ያዳበረቻቸው የሕግ፥ የፖሊሲ፥ የማኅበራዊ ሥርዓትና መዋቅራት ኋላቀርነት፥ ቆሞ ቀርነትና የእድገትና የሥልጣኔ እንቅፋትነት
፬) የአርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአጼዎቹ የጭቆና መሣሪያነት እና የአዲስ እምነቶች መስፋፋት አስፈላጊነት — ወዘተ።
እነዚህ የዘመኑ የብሔር የነጻነት፥ የሥልጣኔና የእድገት፥ የዲሞክራሲና የእኩልነት ዘማሪዎች በተግባር ተፈትነው ወድቀዋል። የሚናገሩትና በተግባር የሚያደርጉት ሁሉ ተቃራኒ ሆኖ ተገኝቷል። እንደ አምላክ የሚመለከቷቸው የውጭ አማካሪዎቻቸውና መሪዎቻቸው የአድዋ ቁስ ባሳከካቸው ቁጥር ኢትዮጵያን ለመበተን አዳዲስ ስልት የሚቀይሱና የሚተገብሩ ናቸው።
እነዚህ አካላት ለዘመናት አሰላስለውና ጠይቀው የመለሱት ጥያቄዎች አሏቸው፦
የአድዋን ድል ያስገኘውን ኢትዮጵያዊ ስነ-ልቦና ያነጸው ማነው? እነዚያን የድል ጦርነቶች የመሩ ወገኖኝ በአብዝኃኛው ከየትኛው የእመነት ወገንና ባህል ነው?
ኢትዮጵያውያን እኛ ከሌሎች አገራት ሰዎች በፍጥረታችን እኩል ነን! አንበልጥም አናንስም! ስለዚህ በርነት አይገባንም፥ ባሮች ከምንሆን መሞትን እንመርጣለን የሚለውን አስተሳሰብ ከወዴት አገኙት?
በማለት ስህተትም ይሁን አውነት የመለሱት ምላሽ፦
ኦርቶዶክሰዊት ክርስትና፥
ረዥም የብዝኃ-ማንነቶች ተመጋጋቢ አሐዳዊነት መፈጠሩ፥
በየዘመናቱ የውጭ ወረራዎችን ጦርነት የመሩ ነገሥታትና መሳፍንትን፥ የውስጥ መለያየትን መልሰው አንድ ለማድረግ የጣሩ የእምነትና የመንግሥት ወገኖች በአብዝኃኛው ሥነ ጽሑፍ ያላቸውና ታሪክና ጥበብ የሚያስተላለፍ አቅም የነበራቸው እነ “አገሌ” ናቸው ብለው በየኑ—- እናም
ይህን የፈረጁትን ማኅበረሰብ፥ ባህሉን፥ ስነ ጽሑፉን፥ ስነ-ንግሥቱን፥ ባህሉን፥ እምነቱን፥ ሥርዓተ ማኅበሩን፥ ታሪኩንና ትርክቱን የእጠዮጵያውያን የጋራ ሀብት እንዳል ሆነ፥ ሐሰት አንደሆነ፥ የጥቂት በተለይ የዐመሓራና የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች፥ የዐመሓራ አጼዎች አንደሆነ ጠንክሮ በማስተማር ሕዝቡን የጋራ እሤት ማሳጣትና ባርያ እንዳናደርጋቸው እንቅፋት በሆኖብን ጸጋዎቻቸው ላእ መዝመት የሚል ስልት ተቀየሰ። በዚህ መሠረት የሮማን ኢምፓየር አፈራርሶ ወደ ትናነሽ መንደር የለወጥ፥ ሂትለርና ሚሲሎኒን የወለደውን ብሔርተኝነት ለኢትዮጵያ በማስተዋወቅ በአገር ውስጥ አገር፥ በአንድ ሕዝብ መካከል ሕዝቦች እንዲፈጠር ፕሮጄክት ተዘርግቶ ከ70 ዓመታት በላይ በመሥራት የዛሬዎቹን ህሊና ቢስ፥ አምላክ-የለሽ፥ የሐሰተኝነትና የደም አፍሳሽነት ሱሰኞች ለመንግሥታዊ ሥልጣን ማብቃት ቻሉ።
የዐመሓራ ሕዝብ የህልውና አደጋ የመነጨው ከዚህ ታሪካዊ ሂደት ነው። ስለዘህ ዐመሓራ የሚዋጋውን አውቆ የሚዋጋቸውን ፋሽት ብሔርተኞ ራሱም ፋሽትና ሐሰተኛ፥ ኢሰብአዊና ኢፍትሐዊ በመሆን አይኖርበትም። የብሔርተኝነት ቅዱስና መድኀኒትነት የለዉም። ሌሎችን በልቶ ራሱ እንደሚጠፋ ማገዲ ያለቀበት የእሳት ነዲድ ነው።
ዐመሓራ እነሲህን ከውጭ ተዘርተው አገር ውስጥ ያደጉ የፖለቲካ ዐረሞች ለማረም ራሱም መርዛማ አረም ሳይሆን ንጹሕ ስነዴተነቱን ሳያበላሽ የሰብአዊነትና የፍትሓዊነት፥ የአውነተኝነትና የሰብአዊ ፍጡር እኩልነት እሤቶቹን ከሚጋሩ ሌሎች የኢትዮጵያ ማኅበረሰቦች ጋር ሁሉ የሚያሰልፈውን ዐመሓራነቱን ከብሔርተኝነት ምረዛ መከላከል አለበት።
ዶሮን ሲያታልሏል በመጨኛ ጣሏት እንዲሉ በበታኝ፥ ከፋፋይና ዘር አጥፊ ብሔርተኝነታቸው የዐመሓራን ሕዝብ በተለይ እና አጠቃላዩን ኢትዮጵያዎ የአገራችንን ማኅበረሰቦች የህልውና አደጋ ላይ የጣሉ፥ ፍትሕና እኩልነት የነፈጉት ብሔርተኞች የላኳቸው አንዳንድ የዐመሓራ ልሂቃን ለዐመሓራ ሕዝብ ለህልውና አደጋ መጋለጥ መንስዔ፦
፩ኛ/ ዐመሓራ ኢትዮጵያዊነቱን ይዞ በመጽናቱ ሌሎች የሚጠሉት ሲደራጁ ራሱን ለመከላከል ሳያዘጋጅ መቅረቱ ነው፥
፪ኛ/ ብሔርተኝነት ያመጣውን አደጋ ለመቀልበስ ዐመሓራ ራሱ ብሔርተኛ መሆን አለበት፥
፫ኛ/ ከብሔርተኝነት ውጭ አንድ ጠንካራ ንቅናቄ መፍጠር አይቻልም፥ እና ህልውናን ለማረጋገጥ “የዐመሓራ ብሔርተኝነት ይለምልም”
በሚል ስሑት ኢመክንያዊ ተጠየቅ ላይ ተመሥርቶ ፋኖ ከዐመሓራነት እሤቶቹ አንዲያፈገፍግ እና ሁለት አደገኛ ስህተቶችን እንዲያደርግ ግፊት እያደረጉበት ይገኛል። እነዚህም
ሀ) ኢትዮጵያዊነትን ለዐመሓራነት ባዕድ በማድረግ በትርፍነት ደረጃ ማስቀመጥ
ለ) መርዛማውን አግላይ፤ ሌላ የማኅበረሰብ፥ ባህል ቋንቋ፥ ታሪክ፥ እምትና ማንነቶችን በጠላትነት ሳይፈርጅ መቆም የማይችለውን አጥፊ ብሔርተኝነት እንዲጋት እየገፋፉት ይገኛሉ።
በዚህ ጽሁፍ የፋኖን የህልውናና የፍትህ ትግል ወደ ክልላዊ ብሄረተኝነት ካወረድነው ሊመጣ የሚችለውን አደጋ ለመጠቆም እንሞክራለን።
ፋኖ ብሔርተኛ ከሆነ በሚከተሉት ወጥመዶች ውስጥ ወድቆ ራሱን ያሣሥራል፦
፩) ድንበር የተበጀለትና ብቸኛ አማራ ሊኖርበት መብት የሚያገኝበት የተወሰነ አካባቢ መወሰን፥
፪) ዐመሓራን ዐመሓራ የሚያሰኘው የአማርኛ ቋንቋ፥
፫) ዐመሓራ የሚያሰኝ ቢያንስ እስከ ፯ የቤተሰብ ሐረግ የሚቆጠር የዐመሓራ ወላጅ ቤተሰብ፥
፬) ሌሎች የማይጋሩት የዐመሓራ ብቻ የሆነ አዳዲስ ታሪክና ትርክት መፍጠር፥
፭) ዐመሓራን ከሌሎች ማኅበረሰቦች የላቀ፥ ታላቅ፥ የተሻለ መብት የሚገባው፥ ከአገሩ ልጠዩ ጥቅም የሚፈልግና ለዚህ ሌሎችን እስከማጥፋት የሚጨክን መሆን፤
፮) አገር ውስጥ ጠላት የተባለውን ወገን ለማሸነፍና የብሔሩን “መብት” ለማስከበር ወይንም “ነጻ ለማውጣት” ከሚረዳ ማንኛውም የውጭ አካል “የታወቀ የኢትዮጵያ ጠላም ቢሆን” ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆን፤
፰) ብሔሩ በእምነት፥ በቋንቋ፥ በትርክት፥ በአሠፋፈር፥ በጸሎት ቤት፥ በባህል፥ በዕሤት ከሌሎች ምንም እንዳይጋራ ሁሉንም በአዲስ መልክ ማደረጃት፤
፱) መጽሐፍ ቅዱስ፥ ቁራንና ማንኛውም ነባር ታሪክ ተፍቆ ዐመሓራን ከፍ አንዲያደርግ ተደርጎ እንደገና መጻፍ፤ መጅሊስና ሲኖዶስን ለዐመሓራ ትርክት እንዲያገልግሉ አድርጎ ማዋቀር፥
፲)በመጨረሻ ፋኖ የሚችለውን ተጋድሎ ሁሉ አድርጎ ሕወሃትና ኦነግ በጻፉለት ሕገ መንግሥት መሠረት እንዲሰበሰብበት በተፈቀደለት “የአማራ ክልል” በተባለው የአፓርታይድ ሥርዓት ውጤት ውስጥ ይቀራል።
ብሔርተኛ ማምነትን ለማጠናከር በትንሹ እነዚህ ፲ ነጻሰውጭዎችን ገንጣዮች የተጠቀሙባቸውን መንገዶች መከተል የግድ ይላል። ዐመሓራ ከዐመሓራነቱ እሤቶች በተቃራኒ የቆሙ ኢሰብአዊነት፥ ኢፍትሐዊነት፥ ሐሰተኝነት፥ ጥላቻ፥ አገርን መካድ፥ አዲስ ከእውነተኛ እምነት የሚያወጣ ሃይማኖት መፍጠር የሚያስገድድ ምርጫ ካደረገ “የአማራ ብሔርተኝነት ይለምልም” ከሚሉት ሩቅ ማለም ማየት ከተሳናቸው የባእዳን ማደሪያ፥ የዐመሓራነት መልካም እሤቶች ጠላቶች ምክር መመራጥ ይጀምራል። ያን ጊዜ ጠላቱ ሌላ ማኅበረሰብ፥ ባህል፥ ታሪክና የሰው ልጅ ስለሚሆን እንደ ሕወሃትና ኦነግ ያሉ ዘር አጥፊ፥ ፋሽስት፥ ሐሰተኛ፥ ኢፍትሓዊ፥ ዘራፊ፥ አፈናቃይ ይሆናል። ይህነ ከሆነ ሌሎችም ከዐመሓራ ብሔርተኛ የሚደቀንበትን የህልውና አደጋ ለመከላከል ጫካ ይገባል። ውጤቱ ማንም የማያሸንፍበት የሲቪል ጦርነት ይሆናል። በዚህ ውስጥ የትኛውም ሕዝብ አሸናፊ ሳይሆን የህወሃትና የኦነግ መርዝ ያሳበደው የሚነካከስ ትውልድን በመላው አገሪቱ እንፈጥራለን። ይህ ደግሞ ለአድዋ ቁስለኞች፥ ለኢትዮጵያዊነት ጠላቶችና ዐመሓራንና ኦርቶዶክስ ክርስትና ለማጥፋት ከ፸ ዘመናት በላይ ለደከሙ የውጭ ኃይላት ትልቅ ድል ይሆናል።
ይህ እንዳይሆን ዐመሓራ በዐመሓራነቱ ይጽና!!! ክፋትንና ክፉዎችን ያሸኝፋል!! ካልሆነ ሰይጣን ሆኖ ሰይጣንን እዋጋው ማለት ከንቱነት ይሆናል።
=======================
እነዚህን መገናኛዎቼን ሱበሰክራይብ፥ ማጋራት፥ አባል በመሆን፥ እንደየ አመለካከታችሁ የመወያያ ጉዳዮችን በገጾቼ ላይ በመጻፍ ለአገራችንና ለቤተክርስቲያናችን ሰላምና አንደነት አስተዋጽ እናድርግ
Telegram: https://t.me/+io2m-XA1OBE2NmM0
YOUTUBE:- https://www.youtube.com/@Orthodox_Secular_FantahunWakie/videos
ትዊተር፦ @fwakie
FB:- https://www.facebook.com/fwakie
Blog:- https://ethiopiaorthodoxchristian.blogspot.com
እግዚአብሔር ያክብርልኝ፤
ታናሽ ወነድማችሁ ፋንታሁን ዋቄ
አስተያየቶች