ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

እየገደሉ የምሥራች

 የድንቁርናና ሕሊና-ቢነስት ያነገሣቸው  የጎሣ ልሂቃን "የምሥራች" ትርጉም

አምባገነን፥ ቁማርተኛና የወሮበሎች መንግሥት የሚመራውን ሕዝብ መከራ "የምሥራች" እያለ ያለማምደዋል።  የሕወሃት/ኢሕአዴግና ብልጽግና በዚህ ሞትና መከራን ድልና እድገት አድርገው በማቅረደብ አንድ አይነት ናቸው።

ስዩም መስፍንና አሊ አብዶ  የሕወሃትና የሻዕብያ የዘረፋ ሀበት ክፍፍል ግጭት በባድሜ እንደ ምክንያት ትርጉም-የለሽ   ከ120 ሺህ ሕዝብ በላይ ወገን አስፈጅተው፥ ይግባኝ በሌለው የአልጀርስ ስምምነት "የምሥራች፥ እንኳን ደስ ያላችሁ" ብለው ሕዝቡን አስጨፍረዉታል።

የፈረደበትን ዐመሓራና ኦርቶዶክስ ክርስትናን በማጠፋት አጀንዳ ላይ ቢስማሙም  ነገር ግን በተለመደው የሀብት፥ የብሔር ግዛት በሰስፋት፥ ዲሞግራፊ በመቀየር፥ አሰስ አገር የመፍጠር እና የበላይነት ለማስፈን ባደረጉት ግጭት ሕወሃትና ብልጽግና በየበኩላቸው ወደ ጦርነት የመሩትን ወገን ድል አግኝተናል፥ የባሰ አደጋ እንዳይመጣ አድርገናል ብለው "የምሥራች" ብለዋል።

ብልገግና የአባይ ግድብ ከደ ጋየወረደው የክረምት ጎርፍ ስለ ሞላ የምሥራች በሚ ልሕበቡን በተለይ አሰስ አበባ ውስጥ አስጨፈሩ ፥ ግን የኢትዮጵያን ባንዲራ ያውለበለቡ ወጣቶችን የኦሮሙማው ፖሊስ ሠራዊት ቀጠቀጠው፤

አብይ አህመድ የአዲስ አበባ፥ የደብረ ዘይት፥ የናዝሬትና ሌሎች ከተሞች ነዋሪችን የሕዝብ አሠፋፈር ለመቀየር ኦርቶዶክስ ክርስቶያቸኖችን፥ ጉራጌዎች፥ ኮንሶዎች፥ ወላይታና ጋሞዎች ወዘተ ዒላማ ያደረገ ማፈናቀል እያካሄደ "ከተሞቻችን እያማሩ ነውና የምሥራች"  ብሏል።   

የአማራን ሕዝብ በምድርና በረር ኃይል ሕዓናትን፥ ካህናትን፥ ገዳማውያንን፥ ገበሬዎችን በመጨፍጨፍ ላይ የሚገኘው የአብይ አህመድ አስተዳደር "ጽንፈኛው ፋኖ እየተመታ ለስሆነ የምሥራች" የሚሉ በበሉበት የሚጮኹ ሕሊና ቢስ  ሰዎችና የጎሣ አደረጃጀቶች እንዲጮኹ ታዘው እያደረጉት ነው። 

የአፍሪካ አንድነ ትድርጀት የግዛት አንነድትን የሚመለከት የቻርተሩን አንቀጽ የሚጥስ የእውር ድንብር ውሳኔ በመወሰን ከሶማሌ ላንድ ጋር  የቀጠናውን አጠቃላይ ሰላም ያወከ፥ ቱርክ ናግብጽን ወደ ምሥራቅ አፍሪካ በመጎተት ኢትዮጵያን ባመስከበብ አደጋ የደቀነው የአብይን እብደት "የባህር በር አገኘሁላችሁ – የምሥራች" ብሏል።

ሕዝቡ ፈዝዞና ደንዝዞ እየገደለው፥ አገሩን እያፈረሰበት፥ እያፈናቀለውና እያሳደደው "የምሥራች" እያለ ከቀሚልድበት ድንቁርናና ሕሊና-ቢስነት ካነገሣቸው የጎሣ ቁማርተኛ ልሂቃን ራሱን ነጻ ማውጣት ይኖርበታል። 

አንድ ሕዝብ በመተማመን አንድ ሆኖና ጠንክሮ ከግፈኛ ሥርዓት ነጻ እንዳይወጣ እንቅፋት የሚሆኑት ጆሮ ጠቢ፥ ዘረኛ፥ ጉበኛ፥ ሳይሠራ ለመበልጸግ የሚሰለፍ፥ ባንዳ፥ ሆድ አደርና ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌላቸው አድርባዮች በመካከሉ ሲንሰራፉ ነው። እናም እነዚህ አይነት ሰዎች   መራቅ ብቻ ሳይሆን  በመቅጣት ራሱን እያጸዳ ሕዝቡ ለክፉ ሥርዓት መወገድ የሚቻለውን በግልና በወል ማድረግ አሁን፥ ዛሬ የሚጀመር ጉዳይ ነውና   ---- ነጻ አውጭና መፍትሔ ሰጭ ከመጠበቅ ተላቅቆ ወደ ትግል ይግባ!!!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...