ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

የአብይ አህምድ አሊ በመተግበር ላይ የሚገኙ ዘር የማጥፋት ስልቶች

 የአብይ አህምድ አሊ  በመተግበር ላይ የሚገኙ ዘር የማጥፋት ስልቶች 


የአብይ አህመድ አሊ የአእምሮ ወላጆችና ተልዕኮው

አብይ አህምድ አሊ ከጣሊያን ፋሽት፥ ከግራኝ አህመድ ላኪዎች ጽንፈኞች እና  ዓለምን በባርነት ለመግዛት ከሚሠሩ ኃያላን አገራት አስተምህሮ እና ከቅድመ ክርስትና አሕዛባዊ የአረሜነነት ጠባይ ተቀይጦ  በተፈጠረ አስተምህሮ የተወለዱ  ደርግ፥ ማርክሲስት ንቅናቄዎች፥ የጎሣ ነጻ አውጭዎች፥ በተለይ ሕወሃትና ኦነነግ  ተዳቅሎ የተወለደውን የአነግ-ኦርኦሙማ የብልጽግና ፓርቲ ሠሪና መሪ ነው።

ይህ ሰው የአእምሮ ወላጆቹን ዕሳቤዎች አዳቅሎ የቆየ ዓለማቸውን ከግብ ለማድረስ ሥልጣን ላይ እንዲቀመጥ የተደረገ ሰው መሆኑን በቆይታው በተግባር አረጋግጧል።  በፖለቲካ አስተዳደጉ ከሤራ፥ ቁማርና ዘረኝነት፥ ሌብነትና ሐሰተኝነት ውጭ ምንም አይነት ከሰብአዊነት፥ ከፍቅር፥ ከእውነት፥ ከአገራዊነትና የማኅበረሰብ ሰላምና ተዋህዶ ጋር የሚያስተዋውቅ  ፖለቲካ፥ ትምህርት፥ አስተዳደርና አሠራር ለማየት እድል አላገኘም። 

  • ያደገው በሕወሃትና በኦነግ የጥላቸና የሐሰት ትርክት የመርዝ ጡጦ ነው። ጥመቱን፥ ክህደቱን፥ አላዋቂነቱንና ለማንኛዉም አነይት የባዕዳን አጀንዳ ተሸካሚነት የተዘጋጀ መሆኑን የተረዱ የውጭ አካላት ተሯሩጠው ሕወሃትን ተክቶ የተጀመረውን፦
  • በአፍ መፍቻ ቋንቋው አማራ የሆነ (ሕወሃትና ኦነግ በጻፉት የብሔርና ብሔረሰብእ ተርጓሜ መሠረት አማራ የተባለ ሁሉ)  ማንኛውንም ሰው እና 
  • ሁለተኛ   በሃይማኖት ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የሆነ ማንኛውንም ማኅበረሰብእ   
ከኢትዮጵያ ምድር አስተሳሰቡንና ታሪኩን፥ ከተቻለ በአካል የማጥፋት ፕሮጄክት አስፈጻሚ አድርገው ሾሙት፤ በገንዘብ ደገፉት፥ ወንጀሉ በመላው ዋና ዋና ሚዲያ እንዳይነገር ተከላከሉለት፥ መግደያ መሣሪያ በእርዳታና በግዥ አቀረቡለት፥ የሚጨፈጨፈውን ወገን የጤናና ሌሎች በእርዳታ የሚሸፈኑ በጀቶችን ነፈጉት (ለምሳሌ የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት ሕወሃትና ብልጽግና የአማራን ሕዝብ በጦርነት ባስከበቡት ወቅት የአማራ ክልል የጤና በጀት እንዳይለቀቅ የወቅቱ አምባሳደር አግዶ ነበር)።

አሁን በአብይ አገዛዝ  እየተገተገበሩ የሚገኙ ዘር የማጥፋት ስልቶች፦

  1. ፩) መደበኛ ሠራዊት በማዝመት በሕግ ማስከበር ሽፋን ፍጅት መፈጸም
  2. ፪) ዒላማ የተደረገውን ሕዝብ በኢኮኖሚ ማድቀቅ
  3. ፫) በአሮሚያ ክልል መንግሥት መዋቅር አስተባባሪነት ማፈናቀል፥ መግደል እና ማደኸየት
  4. ፬) ዒላማ የተደረገውን ሃይማኖትና ሕዝብ ልጆች ከትምህርት ማስተጓጎል
  5. ፭) ታጣቂዎችን ለይስሙላ በፓርላማ "አሸባሪ" አሰኝቶ በተግባር እያስታጠቀ፥ ባንክ እንዲዘርፉ እያመቻቸ ፍጅት እንዲፈጽሙ ማድረግ
  6. ፮) በነባሩ ልማድ ደሀ ተበደለ፥ ፍርድ ተጓደለ የሚሉ የሃይማኖትና የባህል መሪዎችንና መዋቅራትን በዘረኝነት በመከፋፈል፥ በሙሰኞች እንዲመሩ በማድረግ የዘር ማጥፋት ፕሮጄክቱን እንዲደግፉለት፥ ካልሆነ ማረሳሻ ተግባር ላይ ተጠምደው የካድሬነት ሥራ አንዲሠሩ፥ ካልሆነም ዝም እንዲሉ ማድረግ
  7. ፯) የኦሮሞን ሕዝብ "አጼዎቹ መጡብህ፥ ልትገዛ ነው፥ ለልጣንህ ሊወሰድ ነው፥ ኦርቶዶክስ እምነትና አማራ ጠላትህ ነው" ወዘተ በሚል 50 ዓመት ሕወሃትና ኦነግ የዘሩትን መር ዝበማደስ እያስፈራራ እውነቱን እንዳያይ፥ ፍትሕን አንዳያውቃት ማዘናጋትና የወንጀል መሣሪያ የሆኑ ሠራዊትን ማጠናከር
  8. ፰) መንግሥት በኢትዮጵያ ውስት በአማራና በኦርቶዶክስ ሰው ላይ ከመዝረፍ እስከ መግደል ሙሉ ፈቃድ መስጠቱን በሚያረጋግጥ ደረጃ ለ፮ መዓታት መቶ በመቶ ወንጀሎችና ግፎች ፍትሕ እንዳያገኙና እንዳይገቱ ማድረግ
  9. ፱) ሽመለስ አብዲሳ ካቢኔ ከተለያዩ ክልል መሪዎች ጋር እየተገናኘ በአሮሚያ የሚፈጸመው አነይት አማራንና ኦርቶዶክስ ክርስቲያቸችን የማጽዳት ተግባር እንዲጠናከር በማግባባትና በመርዳት ፍጅትና ማፈናቀሉን ማስቀጠል
  10. ፲) በትግራይ፥ በአማራና ኦርቶዶክስ የሸዋ ኦሮሞዎች መካከል መግባባት እንዳእኖር፥ ተባብረው ይህን ሥርዓት እንዳያስወግዱት በሕወሃት በመጠቀም ማጋጨትና ማባላት።

የሕዝብ ድንዛዜ


እነዚህን የአብይ መንግሥት የጥፋት ስልቶች በመረዳት ለሰስቆምና ሕዝብን ከጥፋት አገርን ከመፍረስ ለማዳን አውቆ በተግባር ወደ ትግል የገባው የአማራ ፋኖ ብቻ ነው።  ሌላው ነጻ አውጭና መፍትሔ ሰጭ እየጠበቀ እጁን አጣጥፎ መከራውን ያጋታል።
    •  በመንግሥት ሤራና የምእረባውያን ታዛዥነት ኑሮ ሲወደድ ዝም
    • ቤቱ ሲፈርስበት ዝም
    • ልጆቹ የአረብ ባርያና ገረድ ለመሆን ሲሰደዱ ዝም
    • ወገኑ ከየ ክፍለ ሀገሩ ሲፈናቀሉና ሲጨፈጨፉ ዝም
    • ታሪ ኩሲጠለሽ ዝም
    • ቤተ ሃይማኖቱ በሐሰተና ካድሬ አባቶች ሲወረር ዝም
    • ትውልዱ ሱሰኛ፥ አመንዝራ፥ ሰዶማዊና ዘረኛ እንዲሆን በእቅድ ሲፈጸምበ ትዝም --- ዝም ! ዝም!


የዘር ማፈፋት ሂደቱ መንግሥታዊ ባሀሆን ኖሮ አብ ይአህምድ እንደ አገ ርመሪ መምን ማድረግ  ይችል ነበር?

  1.  ለጥቃት የሚያጋልጡና፥ አርሱ ሥልጣን ከመያዙ አስቀድሞ የተነዙ መርዛማ የሐሰት ትርክቶችን የሚያመነጩ አካላትን በመረጃና በማስረጃ የሚያጋልጡ የምሁራን ተቋም በመፍጠር ከአየር እንዲወርዱ ያደርግ ነበር 
  2.  ለጥቃት የሚያጋልጡና፥ አርሱ ሥልጣን ከመያዙ አስቀድሞ የተነዙ መርዛማ የሐሰት ትርክቶችን ያመነጩ ልሂቃን፥ ድርጅቶችን ለሕግ ማቅረብ
  3.  እልቂትና የአገር መፍረስ ምክንያት የሆነውን የሕወሃትና የኦነግ ሕገ መንግሥ ትማገድ
  4. በተⶄመበትና ሙሉ የሕዝብ ድጋፍ ባገኘበት መቅጽበት የጎሣ ፓርቲዎች ወደ አገራዊነት እንዲለወጡ  ማድረግ  
  5. ለ27 ዓመታት የተፈጸሙ  ግቸችን የሚያጠናና ወደ ፍትሕ የሚያመጣ ተቋም በመመሥረት፥ መልሶ ማቋቋም፥ ካሣ መካስ
  6. የሐሰት ትርክትና ስሑት ርእዮትን የሚያርም ኮሚሽን መመሥረት 
  7. የጎሣ ታጣቂዎችን በሙ ሉወደ ሕብረ ብረራዊ ሠራዊት በመቀላቀል ፍትሕን፥ መከላከያን ወዘተ አገራዊ ማድረግ
  8. በጎሣና በሃይማኖት የተመሠረቱ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተቋማትን ወደ አገራዊነት መለወጥ 

መፍትሔው፦

    • የሚጠበቅ መፍተሔ ሰጭ፥ ነጻ አውጭ የለም! ይህን ክፉ አጥፊ ሥርዓትና በቤተ ሃይማኖት ውስጥ የተሰገሰጉትን ደም መጣጭ ምደኞች ጠርጌ ላስወግዳቸው ብሎ መነሳት!
    •  ያለማወላወልና መጠራጠር የአማራ ፋኖን ትግል በመደገፍ አገሪቷን ከመከራ መገላገል!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...