ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

በኦርቶዶክስ ዘፈን ይፈቀዳልን?

ይህን ሰሞን ስለ ዓለማወ ዘፈንና ሙዚቃ የሚወዛገ መምህራኖችን ተመልክቻለሁ።


እኔ የቀኖና ሊቅ አይደለሁም። ነገር ግን በሃይማኖት የማስብ ስለሚመስለኝ አስተያየት መስጠት አስፈላጊ መስሎ ታየኝ።


ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖትን ሕይወቱ ስላደረገ ሰውና ማኅበረሰብ ስንነጋገር የሰሞኑን ፖለቲካና ከመንፈሳዊ ዓላማ ውጭ የሆኑ ድብቅ ፍላጎታችን በተቻለ መጠን ያልተቀላቀለበት  ትምህርት መስጠት ምእመናንን በማሳሳት ምክንያት ከበጎቹ ጌታ ከእየሱስ ክርስቶስ ቅጣት ያድናል።

ቤተ ክርስቲያን ከሁሉ በላይ የቅዳሴ የጸሎት ዜማን እስከነ ዓላማውና መንፈሳዊ ግቡ፥ ከእነ ጥልቅ ምሥጢሩ ተረድተን እንድናዜም ትፈልጋለች። ታስተምራለች፥ በተግባርና በህይወት ታሳያለች። በሂደቱ ሁሉ ህሊናችን፥ ዓይነ ልቦናችን እና መላው ተስፋችን ሁሉ ሰመያዊ ማንነታችንን አንጾ በመገኘት ላይ ታተኩራለች።  ልጆቿም እንዲሁ በግልና በጋራ ድምፍ አውጥተው ወይንም በአርምሞ ሲያዜሙና ሲናገሩ ቅዳሱው ባመለከታቸው መሠረት ነፍሳቸውን ወደ ሰማዩ አባታቸው እንድታተኩር አድርገው ፈጣሪያቸውንና መድኀኒታቸውንን ክፍ ክፍ ማድረግና ማመስገን እንዲሆን እንደምታስተምር የቅዱሳን ሕይወት ሁሉ ይጠቁማል።

ቤተ ክርስቲያን በግልጽና በአትቃላይ ዓለማዊ/ሥዝም ዘፈንን ኣታወግዝም። በመጽሐፍ ቅዱስ  የሚሰጠን ምልክት በጥንቃቄ  መመልከት ያስፈልጋል፦

ሮሜ 13፡13-14 “በቀን እንደምንመላለስ በአግባብ እንመላለስ። በጭፈራና በስካር አይሁን፤ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፤ በክርክርና በቅናትም አይሁን።  ይልቁንም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም ይፈጽም ዘንድ ለሥጋ በዐሳባችሁ አትመቻቹለት። “

1 ጴጥሮስ 4:3 “አሕዛብ ፈቅደው እንደሚያደርጉት በመዳራት፣ በሥጋዊ ምኞት፣ በስካር፣ በጭፈራ፣ ያለ ልክ በመጠጣት፣ በአስጸያፊ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል። “

ገላትያ 5:16-25፤ ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። 17፤ ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም። 18፤ በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም። 19፤ የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ 20፤ መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ 21፤ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። 22፤ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፣ 23፤ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። 24፤ የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። 25፤ በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ።

 የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክትና የቤተ ክርስቲያናችን የምንመለከተው ተግባራዊ ሕይወት የሚናበቡና የሚተረጓጞሙ መስለው ይታያሉ።  የጠቀስናቸው ጥቅሶች በአንድ መሥመር ቢጠቃለሉ ገላ 5፥25 ይሆናሉ። እርሱም “በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ፨“ የሚለው ይሆናል። 

 እንግዲ ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ በመንፈስ የመኖር አቅም እንዲያዳብሩ፥ ጎጂውንና ጠቃሚውን በራሳቸው እየለዩ አምላካቸውን እንዲያስደስቱ፥ የመንፈስ ቅዱስ ማኅደርበነታቸውን በሕይወት እንዲቀምሱ ታበረታታለች። 

እንደ ኣይሁንና እንደ እስላም ወይንም እንደ ሌሎች ሰው ሠራሽ እምነቶችና ድርጅቶች ንካ-ኣትንካ፥ ቁም-ተቀመጥ እያለች በትምቀት በክርስቶስ ሞትና ትንሳዔ በጥምቀት ተካፍለው ዓለምን ሊዋጁ በውትድርና የተሠማሩ ልጆቿን በመንፈሳዊ ተጋድሎ ውስት አልፈው እንዲኣድጉላት “በመንፈስ ኑሩ!” ብላ የገዳማውያንን ሕይወት እንደ ምሳሌ በተግባር እያሳየች በጎቿን ትመግባለች።


እንግዲህ ዘፈን ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም የሚለውን እሰታ ገባ ለሊቃውንት ጉባኤ ብያኔ ትቼ እኔ የበለጠ እስክማርና እስክረዳ አሁን እንደምረዳው ከሆነ  ዘፈንን በሚመለከት የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ እንድንል ትፈልጋለች፦

1. የዘፈኑ ዓላማ ይዘት፦ ክርስቲያኖች ዘፈን ሲሰሙ (ሲዘፍኑ አላልኩም) የዘፈኑን ዓላማና ይዘትን በሚመለከት በክርስቲያናዊ መንፈሳዊ ሚዛን ሊለኩ ይገባል። ይዘቱ ከመንፈሳዊ ዓላማ የሚያዘናጋ፥ ሥጋዊ ስሜት የሚቀሰቅስ፥ አሉታዊ ጠባይ እንድንለማመድ ምክንያት የሚሆን እና መንፈሳዊ ተመስጦን በሚያዳክም መንገድ በአእምሮ ምስለ-ዘማን  (ፖርኖገራፊክ ምስሎች) የሚያትም  እንዳይሆን አትብቃ እንደምታስጠነቅቅ ከአባቶቻችን ትንቃቄ እንማራለን።  

 

2. በነፍስ ላይ የሚኣሳድረው ተጽእኖ፦  ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ተግባራዊ ሕይወት እንደምንረዳው ቅዳሴውና ማኅሌቱ ከይዘቱና አካል እንቅስቃሴ፥ ዝውውርና ሂደት ሁሉ የክርስቲያኖችን ነፍስ (ካህን በዓብይ ዜማ “ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር ከፍ አድርጉ” ሲል ምእመናን ደግሞ “ብግዚአብሔር ዘንድ አለን/ነን” ማለታቸው የማዜማችንን ዓላማ ያመለክታል።  ዜማ/ሙዚቃ በነፍስ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንደሚኣሳድር ከቤተ ክርስቲያን የበለጠ የሚረዳ ያለ አይመስለኝም። የቅዱስ ያሬድ ክግዚአብሔር የአገልግሎት፥ የውዳሴና የቅዳሴ ዜማ መቸሩ ይህንነኑ ተጽእኖ ያመለክታል።  ከዚህ ተነስታ ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ ዓለማዊ ዜማና ዘፈንን ከእግዚአብሔር ጋር ከሚኖረን የቀና ግኑኝነትና ከመንፈሳዊ እድገታችን አንጻር እንድንመረምር ታስተምረናለች። 


3. አቅመ-ማንጸር፦  ምእመናን ሙዚቃ ወይንም ዘፈን ለማዳመጥ  የትኛው ለነፍስ የሚጠቅም ወይንም እንደሚጎዳ የማንጸር አቅም እንዲያዳብሩ ታበረታታለች እንጂ እንደዚህ እንደ ኣሁኑ ትውልድ በጭፍን መንጋነት ብዙኃን የወደዱትን መከተል፥ ዘመኑ ያገለለውን መጥላት፥ ማስታወቂያ ያገነነውን በጭፍን መጋትን እንድንጸየፍ ታሳየናለች።  ማንጸሪያችን ዘፈኑ ከክርስትና እሤት፥ ዓላማና የመኖር ትርጉም ጋር ያለውን ግኑኝነት በመመዝን መሆን አለበት። ጥያቄውም ዘፈኑ ወደ እግዚአብሔር ፍቅርና ምስጋና የሚመራ ነው ወይስ ለመንሳዊነት እንቅፋት ነው? በሚል ማንጸር ያሻል።   


4. ከመምህረ ንስሐ መመሪያ መቀበል፦  የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ በተለያዩ  መንፈሳዊ አቅም፥ በተለያዩ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ስለሚኖሩ አንድ አስገዳጅ ሕግና መመሪያ የሰጠቸን ኤእመስለኝም። በዚህ ምትክ ክርስቲያኖች በሚኣደርጉት ብቻ ሳይሆን በሚኣስቡትና ባቀዱት ጉዳይ ከንስሐ አባቶቻቸው ከካህን ጋር በመምከር ለነፍሳቸው የሚበጀውን መመሪያ መቀበል አንደሚገባቸው እንደምታስተምር ቤሌሎች የትዳርና የግል ሁኔታዎች ውስጥ ሁላችንም እናውቀዋለን።  ለክርስቲያን “መዝናኛ” በሚል ዓለማዊ ስሜት ቀስቃሽ፥ ርኩሰትና ኃጢአትን የሚኣበረታታ የዘመኑን ዘፈን ከክርስትና መንፈሳዊ ሕይወት ጋር ፈጽሞ የማይስማማ በመሆኑ ከንስሐ አባት ጋር  መምከርን ታዛለች።   


ሲጠቃለል ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያን ዘፈንን ሁሉ ስታወግዝ አልመለከትም። ግልጽ ሆኖ የሚታየኝ ምእመናን ሙዚቃን/ዘፈንን በሚመለከት  የመጀመሪያ ጥያቄያቸው “የምሰማው ወይንም የምዘፍነው ዘፈን ለመንፈሳዊ ሕይወቴ እድገትና  ከእግዚአብሔር  ጋር ያለኝን ግኑኝነት ያሳድግልኛል ወይስ መንፈሳዊ ሕይወቴን ይጎዳል?” ብሎ በመጠየቅ፥ እንዲሁም ከመምህረ ንስሐ ጋር በመምከር መበየን ይኖርባቸዋል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...