ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ተገፊዎች ግፍን ይቅርታ ጠየቋት

ተገፊዎች ግፍን ይቅርታ ጠየቋት በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። አሜን። 17/11/2015 የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ክርስቶስን ዘንግተው በፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ በተፈጠረ ቡድንና የቋንቋ ዘውግ ዘረኝነት ተከፋፍለው የየሰፈራቸው ጣዖት ፈጥረዋል። ይህን የሸክላ፥ የብረት፥ የመዳብ፥ የወርቅና የብር ጣዒት አይደለም። ዘመናዊው   ጣዖት የተፈጠረው ከተረፈ ማርክሲዝም፥ ከተረፈ ናዚ የተወለደው ዘረኝነት እምነቶችና በኦነግና በሕወሐት ፈጻሚነት፥ በኢትዮጵያዊነትና ኦርቶዶክሳዊነት ላይ ለ700 ዓመታት የተሰለፉ ታሪካዊ ጠላቶች አስፈጻሚነት የተመሠረተው የጎሣ ሕገ መንግሥት ነው።   ይህ ሕገ መንግሥት መግቢያው  ብሔር ብሔረሰብና ሕዝብ የሚል ርዕስ አለው፤ ዝርዝሩ አማራና ኦርቶዶክስን መስበር ነው። ግቡና  የመጨረሻው የብሔርተኞች መንግሥተ ሰማይ በምድር ማስገኘት ነው፥ እርሱም ከኦርቶዶክስና ከአማራ ነፃ የሆነ ፓጋን ትግራይ፥ ፓጋን ኦሮሚያ ወይንም ፓጋን ኢትዮጵያን መፍጠር ነው፤  በዚህ አዲስ የዘረኞች “ሃይማኖት”  ዶግማው ትግራዋይነት (ሕወሐትነት) እና ኦሮሙማ ከነባር እምነቶችና ባህሎች ሁሉ በላይ ነው፥ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት፥ ኦርቶዶክሳዊነት እና ኦርቶዶክስ የሁለቱ አዳዲስ እምነቶች ጠላቶች ናቸው።  የአዳዲሶቹ “ሃይማኖቶች” የአምልኮ አፈጻጸም የሐሰት ትርክት፥ ስም ማጥፋት፥ ማፈናቀል፥ መግደል፥ ማደኸየት፥ ማምከን፥ ማሰደድ፥ ጦርነቶችን ጭሮ መፍጀት፥ ከእምነት ማስወጣት፥ በቁጥር ማሳነስ (ዲሞግራፊ መቀነስ)፥ ከውጭ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር መሰለፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ኦርቶዶክሳዊነትን፥ ኢትዮጵያዊነትንና አማራን መክሰስ ናቸው።   የሕወሓትና የኦነግ/ኦሮሙማ/ ብልጽግና ማንነት የሚገለፀው በታሪ...

ኢትዮጵያኖችን ከእብደት ጠርቶ የማስታረቅ ኃላፊነታችሁን ተወጡ፡--

ኢትዮጵያኖችን ከእብደት ጠርቶ የማስታረቅ ኃላፊነታችሁን ተወጡ፡-- ለጳጳሳት፣ ለካህናት፤ ለሸኾች፣ ዑስታዞች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የጎሣ መሪዎች፣ የዘረኝነት ደዊ ያልለከፋችሁ የዩኒቭረሲቲ ፕሮፌሰሮች ሁሉ፡- ተቆንጥጦ ያላደገ ልጅ ጉልበት ሲያወጣ ወልደው ያሳደጉትን ወላጆቹን አንደሚዳፈር በሐገራዊ እውቀት፣ ጥበብ፣ አስተዳደርና ፍልስፍና ሳይበለጽጉ ላለፉት 100 ዓመታት ከውጭ በተቀዳ ባዕድ ትምህርተት የደነቆረው ትውልድ ወደ ፍጹም እብደት ደርሶ እናት ሀገሩን እየተዳፈረ ይገኛል፡፡ ይህ ትውልድ እውነተኛ ሀገራዊ ሰው የመሆንና የመኖር ትርጉምን፣ እውነተኛ ታሪክን የሚማርበት እድል ተነፍጎታል፤ በተቃራኒው የታሪክ ትምህርትና ትርጓሜ   የሚሰጠው ግልብ በሆነ የባዕድ ትምህርት ማያቸው በተባለሹ ከእውነት ይልቅ ለፖለቲካ ርዕዮተዓለም ታማኝ በሆኑ ካድሬዎችና የፖለቲካ ሰባኪዎች(አክቲቪስቶ)   ነው፡፡ የሰው ልጅ ምንነትና ማንነት የሚበየነው በኢኮኖሚያዊ ጥቅምና በሆድ ደረጃ ብቻ ነወው፤ የሰው መንፈሳዊና ባህላዊ ክብሩ ተዘንግቶአል፤   ኢትዮጵያዊያን እንደ ምርት ግብአት፣ እንደ ኢኮኖሚ ማሽን፣ አንደ ጦር መሣሪያ በሚቆጥሩት የጎሣ ፖለቲከኞች   እጅ ተይዟል፤ ወደ ራሱ ተመልሶ ከወገኒ አንዳይ ታረቅ ገዥዎችና የሚዲያ ጀግኖች አጨልመውበታል፡፡ የፍትህና የእስተዳደር ሥርዓት ትርጉም የሚያገኘው በብልጥና ጉልበተኛ   ልጆች አመራር   ሥር ከሆነ ሰነባብቷል፡፡   ሰው በጎሣና በታሪካዊ ልዩነቶች እየተፈረጀ እኛና እነርሱ በመባባል አንዱ በሌላው ላይ የጠላትነት እንቅስቃሴ በማድረግ ሰውን እንደ በግ ሲያሳርድና ሲያሳድድ፣ ሕፃናትን በቡድን ሲያስደፍር፣ ጎረቤትን በቆንጭራ ሲያስቆርጥ (ቡራዩን፣ በሻሻ፣ አወዳይን፣ ጅጅጋ፣ ቀይና ...

ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ የሚለው የሀገሬ ብሂል የወ/ሮ መዓዛን የኤል ቲቪ ቃለመጠየቅ ተከትሎ ተመላለሰብኝ

ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ የሚለው የሀገሬ ብሂል   የወ/ሮ መዓዛን የኤል ቲቪ ቃለመጠየቅ ተከትሎ ተመላለሰብኝ፡፡ እንዲሁም የቤተክርስቲያን እና ኢትጵያዊ ምነነትን   በሁሉመ ዘርፍ የመድፈር ሂደት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ታየኝ፡፡ አንዴ በማርክሲዝም፣ ሌላ ጊዜ በፌሚኒዝም፣ ሌላ ጊዜ በካፒታሊዝም፣ ሌላ ጊዜ በተሐድሶ፣ አንዴ …. በስንቱ እንደፈራለን!!!   ይህ ሁለንተናዊ ድፍረት አሳሰበኝ -- እናንተስ? ----የሚያሳስባችሁ ሁሉ የ ዚህ መፍትሔው የክርስቲያኖች ከጥልቅ እንቅልፍ መንቃት ነውና !!!!   ነቅተን በትምህረትና በእውቀት ልዕልና፣ በህግ፣ በጸሎት፣ወዘተ መከላከል መጀመር ነው፡፡ ጊዜ የለንም፡፡ ይህ ካልሆነ ባዕድ አምልኮ፣ ሰዶማዊነት፣ የሰው ልጅ አካል እየበለቱ ለመለዋወጫ መጠቀም፣ አሁን በኢትዮጵየ የተፈቀደው ውረጃ ሰውን መብት ነው እያሉ ራሱን አንዲገድል መፍቀድ፣ ወዘተ ተማርን፣ ሠለለጠንን በሚሉ የሀገራችን ልጆች ጀርባ ተጭኖ   ከምዕራባዊያን   የሚፈሰው የርኩሰት ጎርፍ   ነገ አስገዳጅ ሐገራዊ ሕግ ሆኖ ይቀርብልናል፡፡   ቅድስት ቤተክርስቲያናችን የተደፈረችባቸው ዘርፎች፡ እና የሁላችንንም ጥረትና ተሳትፎ የሚጠይቁ ጉዳዮችን ከማንሳቴ አስቀድሞ በዚህ መልዕክቴ ቤተክርስቲያን ብዬ የምጠራው፡ ----   ክርስቲያን ግለሰብ ሰው፣ ---- የክርስቲያኖች ስብስብ፣ ---ክርስቲያናዊ እምነት ያመነጫቸውና ክርስትና የሚገለጥባቸው   የግልና የማኅበራዊ ኑሮ ዘይቤዎች ማጠበቂያ ማኅበራ ዊ አደረጃጀት ፤ --- ክርስቲያኖች አምልኮ የሚፈጽሙባቸው ቦታዎችና ለአገልግሎት ተለይተው የሚሠሩ ቁሳቁሶች፤ ---የክርስቲያኖች መልዕክት የሚለዋወጡባቸውና አምልኮአቸው...

ይድረስ ለተከበሩ ወ/ሮ መዐዛ አሸናፊ፣ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት

ይድረስ ለተከበሩ ወ/ሮ መዐዛ አሸናፊ፣   ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አዲስ አባባ በኤል ቲቪ ከጋዜጠኛ ቤተልሔም ታፈሰ   « የሴቶችን የእርስ በእርስ ጋብቻ ትደግፊያለሽ ?» ተብሎ ለቀረበልዎት ጥያቄ አርስዎ « የሰብአዊ መብት ተከራካሪ እንደመሆኔ ይህን በተመለከተ የራሴ የሆነ አመለካከት አለኝ፤ አሁን ባልመልስልሽ ደስ ይለኛል » ማለትዎን ሰምቼ ትልቅ ሥጋት ውስጥ ወድቅሁ፡፡ መሪዎቻችን ስለምን በእሴቶቻችን መተማመን አልቻሉም? ለምን ያፍሩብናል? ለምንስ የተውሶ ፍልስፍና ተሸክመው ሀገራዊ ማንነታችንን እየተቃወሙ ይመሩናል(ሊነዱን የሚሞክሩት)?   ካፈሩብን የፖለቲካ ሥልጣን የሚየይዙት በድብቅ የሚያምኑበትን ማንነታቸውን ሊያላብሱን ነውን? በሀገራቸው እውቀት፣ በሕዝባቸው እሴትና የሞራል ለከት፣ የእምነትና የባህል ሕግ መመራትን ስለምን ይጸየፉታል? የሚሉ ተከታታይ       ጥያቄዎች አእምሮዬን ወጠሩት፡፡   በእርግጥ የዚህ አይነት ጥያቄዎች ዛሬ በእርስዎ ቃለመጠይቅ ላይ ብቻ የማሰላስላቸውው አይደሉም፣ በአብዛኛው ፖለቲከኞቻችን ችግሮቻችንን ለመፍታት፣ ግቦቻችንን ለማሳካት፣ ርዕዮቻችንን አዉን ለማድረግ የሚመርጡልን መንገዶችን ባሰብሁ ጊዜ ሁሉ ነው፡፡ ግጭት ስለመፍታት፣ ምርት ስለማሳደግ፣ እርሻ ስለማዘመን፣ ትምህርት ስለማሻሻል፣ ፍትህና አስተዳደርን ስለማዘመን፣ ሕግ ስለመደንገግ፣ ስለ እስረኛ አያያዝ፣ ስለ ወታደራዊ ዶክትን፣ ሌብነትን ስለመዋጋት፣ የተፈጥሮ ሀብታችንን ስለመንከባከብ፣ አፈርን ስለማዳበር፣ የሰብልና የእንስሳት ዝርያን ስለመምረጥ፣ ስለመስኖ፣ ስለ ጎሣና ታሪክ፣ ስለ ስነልቡናና ማኅበራዊ ደኅንነት   ወዘተ ባነሱ ቁጥር የሚጠቅሱት የውጭ ሀገራትን...

ኢትዮጵያን እየመራችሁ ላላችሁና ወደፊት ለመምራት የምትፎካከሩ ሁሉ

ኢትዮጵያን እየመራችሁ ላላችሁና ወደፊት ለመምራት የምትፎካከሩ ሁሉ በፖሊሲና በሀሳባችሁ ሁሉ ውስጥ የሚከተለውን ሀሳቤን ብታጤኑ ሀገራችንን ለዘለቁታዊነት የሚጠቅም ይመስለኛል፡ -     አፍሪካን በተፈጥሮ ሀብትና በርካሽ የሰው ኃይል ምንጭነት የሚፈልጉ ሀገራት ሁሉ የኢትዮጵያን መነሳት እጅግ ይፈራሉ፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያና እትዮጵያዊነት   የሚል አስተሳሰብና ለእኛ ለእትዮጵያን ቢሰወርብንም   ታሪካችንን ሲያጠኑ፣ ብራና መጽሐፎቻችንን ሲበረብሩ፣ በእምነት ፍልስፍናችንን የነበረንን ልዕልናና መንፈሳዊ ኩራት ያወቁ፣ መድኃኒት፣ አስትሮኖሚ፣ አስተዳደር፣ ኪነ ጥበብ እንደነበረን የደረሱበት ሁሉ ይሰጋሉ፡፡ ሥጋታቸው አሁን ያለው ትውልድ ወደራሱ ማንነት ማየት ከጀመረ፣ የተሰወረበትን የአባቶቹን ጓዳ ለመመርመር ፊቱን ከጭፍን ግልበጣ ወደ ተረጋጋ ተመራማሪነት ከመለሰ   እስካሁን የሚዘርፉትን ያስቆማል፤ በስደት እየፈሰሰ ጠላቶቹን ከማገልገል ይቆጠባል፤ ከጊዜአዊ ስሜታዊ እርካታ ይልቅ ለትውልድ ማብ ይጀምራ፤ የምዕራባዊያን ጭራና ተከታይነቱን ለውጦ በእኩልን የመኖ አቀም ያዳብራ፤ ሌሎች አፍሪካን በልጠውና ተከታይ አድርገው የመቀጠል እድላቸው ይፈተናል፤ የኢትዮጵያኖ መንፈስ ወደ ሁሉም አፍሪካ ተጋብቶ ራን ለመቻልና ለመተባበር ሀገራትን ያነቃቃል፤ በመሆኑም   ---- ፈጂና ጨፋሪ፣ ገልባጭና አቋራጭ ብልጽግና ፈላጊ ትውልድ ስለሚያጡ ምዕራባዊያን ራዕይህን ለማምከን ሁሉንም ወጥመድ ይዘረጉብሃል፡፡   ሥለዚህ ትልቅ አደጋ ላይ ትወድቃለህ፤ የአንተን ሀሳብ የሚደግፉ ሰዎች፣ ፍልስፍናዎችና እምነቶ ሁሉ አደጋ ላይ ናቸው፡፡ በመሆኑ ጥበብ የተሞላበት አካሄድ ያሻል፡፡ የሰፈራችንን ራ ወዳድ የሆድ ሌ...

በትውልዱ ሥነ ምግባር ላይ የቤተክርስቲያን በዓላት

በትውልዱ ሥነ ምግባር ላይ የቤተክርስቲያን በዓላት ሰመኑን ተደጋግሞ ከጋዜጠኞችና ከፖለቲከኞች የሚነሳ ሁለት ጥያቄዎች አሉ፡፡ ምናልባትም ታላቁን የቤተክርስቲያን በአል የፈጣሪያችን፣የጌታችን፣ የመደድኀኒታችንን ልደት (ገና)ን ምክኒያት በማድረግ ጥያቄው የጎላና የተደጋገመ ይመስላል፡፡ በሌላ በኩል በሀገራችን ያለውን የግጭትና የሰላም መታጣት የሚያስብ ሰው ቤተክርስቲያን ጎልታና በንቃት ለምን አልተሳተፈጭም ከሚልም ይመስላል፡፡ መጠየቁ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ያለ ዳራውና ተጨባጭ ሁኔታውን ያላገናዘብ ምላሽ በመስጠት በቤተክርስቲያን ላይ አሉታዊ ጣት መቀሰር ጤናማ አካሄድ አይደለም፡፡ ስለዚህ የሚከተሉት ጥያቄዎች የሚጠየቁበትና የሚመለሱበትን ተጨባጭ ሁኔታ ማስገንዘብ አስፈላጊ ስለመሰለኝ የግል ምልከታዬን መስጠት ፈለግሁ፡- (1) የቤተክርስቲያን በዓላት አከባበርና አስተምህሮው ለትውልድ ሥነ ምግባር መታነጽ፣ ለሰላምና ለፍቅር መጎልበት ምን አስተዋጽኦ ያድርጋል? (2) የቤተክርስቲያን አባቶች ትውልዱ በሥነ-ምግባር እንዲህ ሲወድቅ ለምን ዘምታን መረጡ? ሥነ ምግባር ከሃይማት አንጻር ሲታይና እምነት የለሽ በሆነ መነጽር ሲታይ ምላሹም ሆነ ዓላማው ይለያያል፡፡ ሃይማኖት ያለው ሰው መልካም ሥራና ጠባይ እንዲኖው የሚፈልገውና የሚረው በዚህ ዓለም በምድር በሚገኝ ጠቀሜታን ብቻ አስልቶ አይደለም፡፡ በተለይ በክርስትና ሥነምግባር የእመነቱ ተግባራዊ መገለጫና ለሰማያዊ ዋጋ ፈለማ ወይንም ቀብድ ነው፡፡ የሥነ ምግባር ምንጩ እሴት ነው፡፡ የእሴት መሠረትና ማህቀፉ ደግሞ እምነት ነው፡፡ እምነት በአስተምህሮና ዶግማ ተቀንብቦ በቀኖና አትርነት የሚኖር፣ ዛሬን ተስፋ በሚያደርጉት ግብ ምክኒያት መወሰን ማለት ነው፡፡ የእምነት ትርጉም በፈጣሪና በፍጡር መካከል ያለውን አንድነት ማስጠበቂያ...