ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ይድረስ ለተከበሩ ወ/ሮ መዐዛ አሸናፊ፣ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት


ይድረስ ለተከበሩ ወ/ሮ መዐዛ አሸናፊ፣  ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት
አዲስ አባባ
በኤል ቲቪ ከጋዜጠኛ ቤተልሔም ታፈሰ  «የሴቶችን የእርስ በእርስ ጋብቻ ትደግፊያለሽ?» ተብሎ ለቀረበልዎት ጥያቄ አርስዎ «የሰብአዊ መብት ተከራካሪ እንደመሆኔ ይህን በተመለከተ የራሴ የሆነ አመለካከት አለኝ፤ አሁን ባልመልስልሽ ደስ ይለኛል» ማለትዎን ሰምቼ ትልቅ ሥጋት ውስጥ ወድቅሁ፡፡ መሪዎቻችን ስለምን በእሴቶቻችን መተማመን አልቻሉም? ለምን ያፍሩብናል? ለምንስ የተውሶ ፍልስፍና ተሸክመው ሀገራዊ ማንነታችንን እየተቃወሙ ይመሩናል(ሊነዱን የሚሞክሩት)?  ካፈሩብን የፖለቲካ ሥልጣን የሚየይዙት በድብቅ የሚያምኑበትን ማንነታቸውን ሊያላብሱን ነውን? በሀገራቸው እውቀት፣ በሕዝባቸው እሴትና የሞራል ለከት፣ የእምነትና የባህል ሕግ መመራትን ስለምን ይጸየፉታል? የሚሉ ተከታታይ    ጥያቄዎች አእምሮዬን ወጠሩት፡፡  
በእርግጥ የዚህ አይነት ጥያቄዎች ዛሬ በእርስዎ ቃለመጠይቅ ላይ ብቻ የማሰላስላቸውው አይደሉም፣ በአብዛኛው ፖለቲከኞቻችን ችግሮቻችንን ለመፍታት፣ ግቦቻችንን ለማሳካት፣ ርዕዮቻችንን አዉን ለማድረግ የሚመርጡልን መንገዶችን ባሰብሁ ጊዜ ሁሉ ነው፡፡ ግጭት ስለመፍታት፣ ምርት ስለማሳደግ፣ እርሻ ስለማዘመን፣ ትምህርት ስለማሻሻል፣ ፍትህና አስተዳደርን ስለማዘመን፣ ሕግ ስለመደንገግ፣ ስለ እስረኛ አያያዝ፣ ስለ ወታደራዊ ዶክትን፣ ሌብነትን ስለመዋጋት፣ የተፈጥሮ ሀብታችንን ስለመንከባከብ፣ አፈርን ስለማዳበር፣ የሰብልና የእንስሳት ዝርያን ስለመምረጥ፣ ስለመስኖ፣ ስለ ጎሣና ታሪክ፣ ስለ ስነልቡናና ማኅበራዊ ደኅንነት  ወዘተ ባነሱ ቁጥር የሚጠቅሱት የውጭ ሀገራትን ልምድና  ሊቃውንት መጠበብ ብቻ ነው፡፡  በእርስዎ አገላለጽ ዛሬ የሰማሁት ነገር ግን እንደ ምዕራባዊያኑ በመሪዎቻችን ወዴት እንደምንመራ ፍንጭ የሚሰጥ መስለ ታየኝ፡፡ ስለዚህም ለእርስዎ ለተከበሩት የዚች ታላቅ ሀገር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘደንት አነጋገር በዝምታ ማለፍ በሀገር ላይ ለሚመጣው የወደፊት የስነ ምግባር መላሸቅ ተባባሪ እንደመሆን ተሰማኝና ይህጭን አስተያየትና ጥያቄ በግልጽ ደብዳቤ መልዕክቱን ባገኘውበት በዚሁ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሀን በሚከተለው መልክ ለመጻፍ ጀመርኩ (ወደ ፊት በዚሁ መልክ በሀገራችን ሥነ ምግባራዊ ጉዳዮች ላይ እቀጠጥላለሁ)፡- 
አስተያየቴ፣ መልዕክቴና ጥያቄዬ እነሆ፡-
የኢትዮጵያ ሕዝብ እስላም፣ ክርስቲያንና የባህል እምነት ተከታዩ ሁሉ በአንድ ድምጽ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን ይቃወማል፣ ይጸየፋል፡፡ አንድም ባህሉንና አምነቱን ወክሎ የሚደግፍ አየይገኝም፡፡ ስለዚህ ማንም ቢሆን በሁሉም የመሪነትና የማገልገል ኃላፊነት  ደረጃ ሲቀመጥ   የሚመራውና የሚያጋላግለው ይህን ሕዝብ እስከሆነ ድረስ የሕዝቡን እመነትና ፍልስፍና፣ የሞራል ለከትና መሥፈርት ማክበር ይጠበቅበታል፡፡  መሪና አገልጋይ ኃላፊነቱ የመራውን ሕዝብ እምነት፣ እሴትና ማንነት እየተቃወመ፣ በስህተት ልማት ተሰኝቶ የሚጠራውን ቁሳዊ ልማት ብቻ ትኩረት አድርጎ ሊሠራ አየይችልም፡፡ ከሞከረም ውጤቱ ዘለቁታዊነት የለውም፡፡ ከባህር ማዶ እየተቀዳ በመደበኛ ትምህርት በኩል የተቀዳብንን ባዕድ ፍልስፍና በመያዝ ሀገራራዊውን አውቀትና እምነት መዋጋት ከመሪዎች አይጠበቅም፡፡  ሕዝብ ግዑዝ እና በጠጥቂት መሪዎች አእምሮ ልክ እንደ ሮቦት የሚዘወር አይደለም፤በተለይ ኢትዮጵያዊ፤ በዝምታው ብቻ የእሴቱ ተፃራሪ የሆኑትን ሁሉ እያስወገደ አሳየይቷል፡፡  በአእርግጥ በዚህ ዘመን በኳስ፣ በርካሽ የሚዲያ ወሬና ፕሮፓጋንዳ የተወሰነውን የኅብረተ ሰብ ክፍል በመንጋ ተከታይነት ማከተል የቻሉ አክቲቪሰቶችና መሪዎች አሉ፤ ግን አየይዘለቅም፡፡   
ለመሆኑ  ሰብአዊ መብት ማለት ምን ማለት ነው ሲባሉ  ምላሽዎ ²የግል አመለካከት ነው² ሊሉን ይገባል? አይሆንም፡፡ መልስዎ መሆን የሚገባው የሰብአዊ መብት ትርጉም ከማገለግለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማዕከላዊ ጋርዮሻዊ  የኢትዮጵያዊያን እሴት (widely shared, time and condition endured value system that transcends cultural differences of all Ethiopians)   ላይ የተመሠረተ እርግጠኛ ምላሽ መስጠት ይጠበቅብዎታል፡፡፡  የመብት ተከራካሪ ከሆኑ መብት እንዲያገኝ የሚከራከሩለት ሕዝብ ስለመብት ያለውን ትርጉምና የእሴት መሠረት ተከትለው ብቻና ብቻ ነው፡፡ በችግራችንና በመሪዎቻችን የአመራር ብልሽት  በገባንበት ሁለገብ የጥገኝነት ቅርቃር ተጠቅመው አበዳሪዎችና እርዳታ ሰጭዎች ያመጡትን ውጭ-ገብ የመብትና የነፃነት ትርጉም የይዘው ሊገልፁንና ሊመሩን መሞከር የውክልና ቀኝ ገዥነት እንጂ በዜግነት የሚሠሩት ኃላፊነት አየይደለም፡፡
ኢትዮጵያዊ ማንነት ሳይኖራቸው ሥልጣን ላይ የሚወጡ ሰዎች ከሕዝቡ እሴት ጋር የሚጋጭ ፍልስፍና በመጠቀም የተወሰነውን ሲያስከትሉ፣ ሌላውን ሲያሳዝኑና ሲገፉ በሀገሪቷ ውስጥ የእሴት ብዝሀነትና መፃረር እንዲፈጠር፣ ያልነበረ ሰው ሰራሽ የትግል ጎራ ያበራክታሉ፤ የተከፋፈሉ ዜጎችን በመፍጠር ከሰላም፣ከፍቅር፣ ከአንድነትና በጠቅላይ ሚኒስተራችን አነጋገር በመደመር ፈንታ ግጭትን ያለማሉ፡፡ ትውልዱን ጋራ ያጋቡታል፡፡ ዐዕርስዎም ምላሽ ያንን የይመስላል፡፡
የተከበሩ መዐዛ ለመሆኑ በምዕራባዊያን ሰው የሚባለው ፍጡር ትርሁም የሚያጋኛው ከዳርዊን መላምታዊ የሥነ ፈፍጥረት አስተምህሮ መሆኑን ጠኝቅቀው ያውቃሉ፡፡ በዚህ አስተምህሮ መሠረት  ሰው ከዝንጀሮ የተገኘ እድገቱ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የሚያሰብ ዝንጀሮ ነው፡፡ በዚህ አስተምህሮ ለሚመሩ ሀገራት መንግሥታትና ሊቃውንት መብት፣ ነጻነትና ሕግም የሚሰኙ ፅንሰ ዐሰሳቦች ከዚሁ ሰውን ዝንጀሮ አድርጎ ከሚበይነው  ዳራ  በመነሳት ይቃኛል፡፡ ማንኛውም አእምሮው የሚሠራ ጤናማ ሰው በሐሕይወት ዘመኑ የሚኖርለት፣ የሚሞትለትና እንደ ሕይወት ኮምፓስ የሚጠቀምበት እሴት አለው፡፡  እሴቱ የሞራል፣ የሥነ-ምግባርና የመልካም ስብዕና ልኬቶች ምንጭ በመሆን ለመኖሩ ምክኒያት ይሆኑታል፡፡
ለኢትዮጵያያኖች ሁሉ ሃይማኖትና ባህል ሳይለይ ሰው ዝንጀሮ አይደለም፤ ስለ መብትና ስለ ነጻነት  ያለው ፍልስፍናውም ዘንጀሮ ነን ከሚሉት ይለያል፡፡ ይህ አውነት መሆኑን ለማስረገጥ ኢትዮጵያኖች ዘርና ጎሣ፣ ቦታና ፆታ ሳይለዩ ዝነጀሮ ናችሁና ልንዳችሁ ብሎ ከሮም እስከ አፍንጫው በዘመኑ ዘመናዊ የመግደያ መሣሪያ ታጥቆ ሊያሳጋብረን የመጣውን የታሊያን ወራሪ ጦር በአንድነት ሽንፈት በማከናነብ ሰው ሁሉ እኩል  ክቡርና ሰው መሆኑ በቃል ሳየይሆን በሕይት ዋጋ ከፍሎ አሳይቷል፡፡ በዘግምተ ለውጥ የሚያያምን ሕዘብ ቢሆን ኖሮ ነጭ ዘግመቱ ያለቀለት ሥልጡን፣ ጥቁር ገና መመሠራት ላይ የሚገኝ ያላለቀ ዝንጀሮ ብሎ ነወው በማለት መገዛት የይቀበልነበበር፡፡ ግን አልተቀበለም፡፡
በኢጥዮጵያዊያን ፍልሰርና፣ እሴትና እምነት፣ ባህልና የየሥነ ምከባር ለከት መሠረት ጋብቻ ትርጉም የሚያገኘው በሁለት ተቃራኒ ፆታ ባለቸው ሰዎች መካከል ለዚያውም ማኅበረ ሰቡ ፈቅዶና መርቆ ሲፈጸም ብቻ ነው፡፡ ይህንን እሴት በመጠራጠርር ወይንም በመናቅ አዲስ እሴት ለማተዋወቅ የሕዝቡን ሥልጣን ይዞ መናገር ከፍተኛ ድፍረረት ነው፡፡ በእርስዎ አነጋገር መሠረት  ኢትዮጵያውያንን  ²በነበርክበት የ5 እና 3 ሺዘመመን ታሪክህ ሁሉ ስለ መጋባትና ሰው ስለመሆን ያለህ ፍልስፍና ትክክል ስላልሆነ ዛሬ በዚህ ዘመን ከአንራክህ ተገኝቼ፣ ተምሬና ሠልጣን ይዤ፣ እኔ ልጅህ አዲስ አድርጌህ ልሠራህ ነው² ብሎ እንደመሳለቅ የቆጠራል፡፡   
የተከበርሽ ወ/ሮ መዐዛ አሸናፊ፡- ከቤተልሔም ጥያቄ የሚቀድም መሠረታዊ  ጥያቄ ልጠይቅዎት፣ በእርስዎ ፍልስፍና፡-
(1) ሰው ምንድ ነው?
(2) የሰው ክብሩና መብቱ በምን የይመዘናል?
(3) የሰው ቅድስና እና ርኩሰት መሥፍቱ ምንድ ነው? መብትና ቅድስና ወይንም መብትና ሥነ-ምግባር ምን ግኑኝነት አላቸው?
(4) ሰውና እግዚአብሔር ምን ያገናኛቸዋል? የሰው መብትና የሰው ሃይማኖቱ ወይንም ባህሉ ግኑኝነት አላቸው?
(5) ዜግነት፣ መሪነት እና ሀገራዊ እሴት የሚናበቡት አንዴት ነው? የመሪዎች ሚና ስለሚመራቸው ማኅበረሰቦች እሴትና እምነት መጠበቅ ያለው ኃላፊነት እስከምንድነው?
(6) መብት፣ ነጻነት፣ እኩልነት  የተሰኙ ፅንሰ ዐሳቦች ትርጉም የሚያገኙት ከላይ በሚልሱት የአምሰቴ ጥያቄዎች  ምላሾች ይዘት በመሆኑ አርስዎ መብት ብለው የሚጠሩትና የሚከራከሩለት የመብት ፅንሰ ዐሳብ የቱ ነው?
አምስቱን መልሶችዎን በማገጣጠም  ሰለ ተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ  የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትን የሚመራ ባልሥልጣን ምን አይነት እሴት እንዳለው መመዘን ይቻላል እና ባክዎን ለእነዚህ ጥያቄዎች «የሰብአዊ መብት ተከራካሪ እንደመሆኔ ይህን በተመለከተ የራሴ የሆነ አመለካከት አለኝ፤ አሁን ባልመልስልህ ደስ ይለኛል» ብለው ሳያልፉ ይመልሱልኝ፡፡ መልሱን የሚያቆዩት ከሆነ ሥልጣን መያዙንም ከኢትጵያ ሕዘብ እሴት ጋር ታርቀው ከገል አመለካከት እስኪወጡና የሕዘብ አመለካከት እሰኪላበሱ  ደረስ ያቆዩት፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ከፍርድ ሰጭዎቻችን እሴት በመነሳት ማን ምን እያሰብ እንደሚያስተዳድረን መመዘን እንችላለን፡፡  ሁላችንም ባህል፣ እምነት ፍልስፍና አለን፡፡  ሌሎች የፈለጉት እንዲጨመምሩብን ተዘጋጅተን ባዶ ሆነን የተቀመጥን እርጥብ ሮቦቶች አየይደለንም፡፡ ለእኛ ጋብቻን ለመተርጎም ሰው ምንድነው ብለን በምንመልሰው መልስ ይወሰናል?  የግል አስተሳሰብ ያለው ሰው የዩነቭረሲቲ መመህር ሆኖ አዳዲስ ፍልስፍናዎችን  በነጻነት እየተከራከር ማስተማር፣ መጽሐፍ መጻፍና ዐሳቡን ማራመድ ይችላል፤ ነገር ግን በግል አስተሳሰብ የሀገርን የኖረ የሞራል፣ የፍልስፍናና የእምነት መሠረት መሸርሸር ተቀባይነት የለውም፡፡  ሥልጣን ላይ የመቀመጥ ዓላማው የሚመሩትን ሕዝብ እሴት፣ እምነትና ፍልስፍና ያለማወላወል  ከልብ በመቀበል  ዪመሩትን ሕዘብ ከፍ ካለልዕልና ላይ የማድረስ ኃላፊነት እንጂ ማንነቱ የመሸርሸር ሠርጎገብነት አይደለም፡፡ 
ስለሆንም የተመሳሳይ ፆታን ጋብቻ ተደግፊያለሽ ወይስ ትቃወሚያለሽ? የሚለውን ጥያቄ ያለማድበስበስ መልሰዎን ይስጡንና  ቁርጣችንን እንወቀው!! እሴታችንን የሚያከብሩ መሪዎች እንዲመሩን እንፈልጋለንና፡፡
ዛሬ የምንገኝነት አጠቃላይ ሀራዊ ውድቀት የመጣው ሀገራችን ኢትዮጵያ የበነራትን የ5 እና 3 ሺ ዘመን የእውቀት ድልብ መንዝረው ችግራችንን መፍታት ተስኖአቸው በቀጥታ በተውሶና በጭፍን ገልባጭነት   የማርክሲዝም አስተመህሮ ማኅደር በመሆን ላለፉት 50 ዓመታት ሀገሪቱን ያመሱት ወገነቻችን ትምህርት ይበቃናል፡፡  የዚያን ትውልድ አይነት ሌላ ውጭ-ገብና ባዕድ  አእምሮ  የተሸከሙ የድግሪ ቅሱፋን ወደ ሌላ አዲስ ግራ መጋባት አንዲያስገቡን መፍቀድ ሌላ መሪዎችንም እኛንምተከታዮቹን ለበለጠ ጥፋት ይዳርገናል፡፡ ሌላ ግራ መጋባት፣ ሌላ ማኅበበረሰባዊ ቀውስ መሸከም የምንችል አየይመስለኝም እና በትንሹ መተራረም ያስፈልገናል፡፡  
መንግሥት በአንድ በኩል  ሰላም ፍቅርና አንድነት፣ ዘለቄታዊ ልማትና እርጋታ እንዲሰፍን ይደክማል፤ በሌላ በኩል መሪዎችና ተመሪዎች በእሴት ተማምነው ተደማምጠውና ተመራርተው ከችግር እንዲወጡ የሚሾማቸውን ሰዎች እሴት ሀገራዊነት የሚያረጋግጥበት መሥፍርት የለውም፡፡  መሪዎቻችን በሀገራዊ እሴታችን እያፈራችሁና እያመነታችሁብን  በሚዲያ የምትታዩ ከሆናችሁ በምን መሥፈርት ነው በእምነትና በልበ ሙሉነት አመራራችሁን ተቀብለው ወደፊት የምንራመደው? 
ከሌላ ዓለም አስተሳሰብ ለመዋስ መጀመሪያ የራስን ሀገር የብዙ ሺህ ዘመናት የብዝሀነት መስተጋብር የወለደውን እሴትና ፍልስፍና መረዳት፤ ቀጥሎ የጎደለውን ምርም ባለቤቱ የሆነወነው ሕዝብ ሲረዳው ማሟላት ይጠይቃል፡፡  
እንዳውም ይህንን የወ/ሮ ማዐዛን ሁለት ልብ ያለው ምላሽ መነሻ በማድረግ ለወደፊቱ የሚከተሉትን መሥፍቶች የማያሟሉ ዜጎች ሀገራችንን እንዳይመሩ ትውልዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ግፊት ማድረግ፣ የሃይማት አባቶችና የባህል መሪዎችም እሴታቸውን ለማስከበር ድምጻቸውን ማሰማትና ተከታዮቻቸውን ማስተማር ስለሚገባቸው፣ 
የወደፊት መሪዎቻችን ሀገራችንን የሚመሩትና የሚያስተዳድሩት፣ የሚያለሙትና የሚያሠለጥኑት  ቁሳዊውን ብቻ ሳይሆን እሴታችንን አክብረውና አስከብረው መሆኑን ቃል ሲገቡ ብቻ መሆኑን የሚያስገድድ ሕግ መኖ ይገባዋል፡፡ የማኅበረሰቡ የእምንትና የየባህል አእሴት መቀናትና መሻሻል ሲኖርበት በፖለቲካ ሥልጣን ወይንም በተውሶ ፍልስፍና ሳይሆን የእሴቱ ባለቤቶች ሊቃውንትና ተከከታዩ በሚወስኑት መንገገድ ብቻ ይሆናል፤ እንደተለመደው ሀገራዊ ማንነተትን ለመሸርሸር በሰብአዊና ዲሞክራሳዊ መብት አራማጅነት ወይንም በጎጂ ባህላዊ ድርጊት አስጋጅነት ከለላ የባዕዳንን ፍልስፍናና እርዳታ በመቀበል በሚመሠረቱ ድርጅቶች ወይንም በተገዙ ባለሥልጣናት አፈቀላጤነት መሆኑ በሕግ መከልከል ይኖርበታል፡፡ እንደሚታወቀው በሀገራችን የጎጂ ባህልዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ የሚወጣውን ወጭ 1/100ኛ የጠቃሚ ባህላዊ እውቀቶችና ድርጊቶች አጎልባች ተብሎ የሚመደብ በጀት ቀርቶ የሬዲዮ ስርጨጭት አንኳ ታየይቶ አታወቅም፡፡
 እንደእኔ ግንዛቤ ሀገራዊ ማንነታችንን አስከብረን፣ ከጥገኝነት ተላቀን ዘለቄታዊና ሁለገብ (ማኅበራዊ፣ መንፈሳዊ፣ ቁሳዊና አእምሮአዊ) እምርታ ለማምጣት የወደፊት መሪዎቻችን በሚከተሉት መሥፍረቶች እየተመዘኑ እና  በሃይማኖቶቻችንና ባህሎቻችን   ሊቃውንት እየተገመገሙ፣ ከመንግሥት ጋር በሚደረግ ምክክር የሚከተሉትን መሥፈርት ሲያሟሉ ብቻ የሚሾሙ እንዲሆኑ እመኛለሁ፡-   
ለመሪነት የሚታጩ ዜጎች፡  
1)  የሀገራችንን እምነቶችና ባህሎች የስነ-መምግባር ለከቶችና መሥፍቶች፣ እሴቶችና ፍልስፍናዎች የተረዱ፣ የሚያምኑና በሚመለከታቸው ሀገራዊያን ሊቃወንት ፊት ቀርበው በማስረዳት ቃል የሚገቡ፣ ከመሾማቸው አስቀድሞበመነበራቸው ሕይወትም ይህንን በኑሮ የገለጹ ለመሆናቸው ምስክርነት ያላቸው፤
2)  ዘረኝነት (አሉታዊ አካባቢያዊነት)፣ የሀገሪቷን ጋርዮሻዊ አዎንታዊ የማንነት እሴት የሚያከከብሩ፣ በምንም መልኩ በግል ፍላጎታቸው፣ አመለካከታቸውና በተለያየ ምክኒያተት  ባዳበሩት ከሀገራዊነት ያፈነገጠ የማንነት ዝንባሌ  የማያሳዩ፤
3)  የተከበረውንና የማኅበረሰብ የመጨረሻ ወሳኝ መሠረት የሆነውን  ትዳር  በማክበር በተግባር ያሳዩ፣ ወይንም በሚከተሉት እምነተትና ባህል ምከኒያት በምንኩስና የጸኑ፣ ራሳቸውን ነባሩ ባህልና አስተምሮ የሚያዋግዘውን ሁሉ የሚጸየፉ
4)  ሀብትን ለማፍራት ሐሕግን፣ የባህልና የእመነት መሥፈርቶችን በመጠነንቀቅ የሚተጉ ሠራቶኞች፤ ራሳቸውን ሳይሠሩ በአቋራጭ ሀብት ለማጋበስ ከሚሞክሮ ሰዎች የሚጠብቁ፤
5)  ከወንጀል  ራሳቸውን የሚጠብቁ፣ በሚኖሩበት ማኅበረሰብ በመልካም ሥነ ምግባራቸው  የተከበሩና ባህልና በእምነት  ሕግ መሠረት ያልተወገዙ፤ 
6)  ከሀገሪቷ ጠላቶች ጋር በምሥጢር እየተገናኙ ከሕዝቡ ጀርባ ሌላ አጀንዳ  እንደሚያራራምዱ ፈጽመው የማይጠረጠሩ
7)  ሀገር በመከራ ውስጥ ስትወድቅ ለግል ደኅንነታቸው ሳሱ ለሀገራቸው መስዋዕትነት በሚያያስከፍሉ የትግል ዘርፎች  በአአቅማቸው ሁሉ የተሳተፉ     

በእኔ አስተሳሰብም ይሁን በማንኛውም አመክንዮ ተረጋግቶ ለሚያስብ ሰው የሚመራውን ሕዝብ የማንነት መሠረት የሆኑ የባህልና የእምነት እሴት የሚጠራጠርር፣ የሚዳፈርና የማያምን ዜጋ በምንም መልኩ ወደሠልጣን መምጣት የለበትም፡፡ ከመጣም እርሱ የባዕዳን ሠራተኛ ጠላት አንጂ ወገን አየይሰኝም፡፡

እኛ ኢትዮጵያዊያን ቁሳዊ ሀብታችን ተዘረፈን፣ እሴታችንም ተሸረሸረ--- እኛ ማን ነን ብለን ልንጠራ ይሆን? እንጃ!!!

እኔ ምስኪን ኢትዮጵያዊ ዜጋና ታዛዥዎ
ፋንታሁን ዋቄ
ከተከበረ ሰላምታ ጋር
ጥር  !2 ቀን !)1 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...