ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ኢትዮጵያኖችን ከእብደት ጠርቶ የማስታረቅ ኃላፊነታችሁን ተወጡ፡--


ኢትዮጵያኖችን ከእብደት ጠርቶ የማስታረቅ ኃላፊነታችሁን ተወጡ፡--
ለጳጳሳት፣ ለካህናት፤ ለሸኾች፣ ዑስታዞች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የጎሣ መሪዎች፣ የዘረኝነት ደዊ ያልለከፋችሁ የዩኒቭረሲቲ ፕሮፌሰሮች ሁሉ፡-
ተቆንጥጦ ያላደገ ልጅ ጉልበት ሲያወጣ ወልደው ያሳደጉትን ወላጆቹን አንደሚዳፈር በሐገራዊ እውቀት፣ ጥበብ፣ አስተዳደርና ፍልስፍና ሳይበለጽጉ ላለፉት 100 ዓመታት ከውጭ በተቀዳ ባዕድ ትምህርተት የደነቆረው ትውልድ ወደ ፍጹም እብደት ደርሶ እናት ሀገሩን እየተዳፈረ ይገኛል፡፡
ይህ ትውልድ እውነተኛ ሀገራዊ ሰው የመሆንና የመኖር ትርጉምን፣ እውነተኛ ታሪክን የሚማርበት እድል ተነፍጎታል፤ በተቃራኒው የታሪክ ትምህርትና ትርጓሜ  የሚሰጠው ግልብ በሆነ የባዕድ ትምህርት ማያቸው በተባለሹ ከእውነት ይልቅ ለፖለቲካ ርዕዮተዓለም ታማኝ በሆኑ ካድሬዎችና የፖለቲካ ሰባኪዎች(አክቲቪስቶ)  ነው፡፡ የሰው ልጅ ምንነትና ማንነት የሚበየነው በኢኮኖሚያዊ ጥቅምና በሆድ ደረጃ ብቻ ነወው፤ የሰው መንፈሳዊና ባህላዊ ክብሩ ተዘንግቶአል፤  ኢትዮጵያዊያን እንደ ምርት ግብአት፣ እንደ ኢኮኖሚ ማሽን፣ አንደ ጦር መሣሪያ በሚቆጥሩት የጎሣ ፖለቲከኞች  እጅ ተይዟል፤ ወደ ራሱ ተመልሶ ከወገኒ አንዳይ ታረቅ ገዥዎችና የሚዲያ ጀግኖች አጨልመውበታል፡፡
የፍትህና የእስተዳደር ሥርዓት ትርጉም የሚያገኘው በብልጥና ጉልበተኛ  ልጆች አመራር  ሥር ከሆነ ሰነባብቷል፡፡  ሰው በጎሣና በታሪካዊ ልዩነቶች እየተፈረጀ እኛና እነርሱ በመባባል አንዱ በሌላው ላይ የጠላትነት እንቅስቃሴ በማድረግ ሰውን እንደ በግ ሲያሳርድና ሲያሳድድ፣ ሕፃናትን በቡድን ሲያስደፍር፣ ጎረቤትን በቆንጭራ ሲያስቆርጥ (ቡራዩን፣ በሻሻ፣ አወዳይን፣ ጅጅጋ፣ ቀይና ነጭ ሽብር፣ በእር ቤት ጥፍር ነቀላና ሶዶም መፈጸም ወዘተ እንደ ምሳሌ  እንመልከት) ብዙ አሥርት ዓመታት እያሳለፍን ነው፡፡  በየቤተ እመነቱን ሰርገው የገቡ የፖለቲካ ሠራተኞች ሃይማኖት ከፈጣሪ  ጋር የሚገናኙበት፣ ራስን ከሀሰትና ከክፋት የሚጠብቁበት፣ ሆድና ፍተወትና  ድል የሚነሱበት፣ ለሌላ ሰው የሚኖርበት መሆኑ ቀርቶ ቡድን የሚደራጅበት፣ አንዱ ሌላውን ከምጣኔ ሀብትና ከሀገራዊ ተሳትፎ ለማግለል የሚደራጅበት  መሰባሰቢያ ሆኗል፤  የሀገር ልጆች አጠገባቸው ከቆመው ወንድማቸው በበለጠ በእምነትና በሀሳብ ይቀርበኛል፣ ርእዮተ ዓለሜን ይደግፍልኛል ከሚለው የባሕር ማዶ ባዕድ ጋር ተባብሩ ጎረቤቶን የሚያጠቃበት የሀሰት አውድ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡  
ጥሪይ ከዚህ ሁሉ ዘመናዊ ድንቁርና አምለጣችሁ፣ በባህላችሁና በእምነታችሁ ጸንታችሁ ላላችሁ የባህል፣ የእምነትና የእውቀት አባቶችና ሊቃውንት ነው፡፡
ከለይ በወፍ በረር ያነሳሁትን የሀገራችንን ትውልድና መሪዎች ጠባይ ስናጤን ለጳጳሳት፣ ካህናት፣ ሸኾች፣ ዑስታዞች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የጎ መሪዎች፣ የዘረኝነት ደቄ ያልለከፋችሁ የዩኒቭረሲቲ ፕሮፌሰሮች  የባለጌ ልጆች ወላጅና አሳዳጊ የሆናቸሁት እናንተ ናችሁ ለማለት እደፍራለሁ፡፡ ልጆቻችሁ ከቤት ወጥተው ከባዕዳን ውለው ሀገራቸውንና ማንነታቸውን በወሬ ጠገብ ግልብ እውቀት ሲበክሉት እንደሚገባ አልሞገታችሁም፡፡  ይህ ስንፍና ነው፡፡ ይህ ስንፍና ልጆችንም ወላጆችንም የሚጠፋበት የእብደት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ዜጎች በቡድን በቋንቋ ተደራጅተው ሀገር ሊካፈሉ ድንበር የሰምራሉ፣ ጦር ያሠለጥናሉ፤ ወጣቶች ፈጠራና ሥራን ዘንግተው እንዴት አድርገው በአቋራጭ አንደሚከብሩ ያሰላሉ፣ የትኛው ቡድን የትኛውን ቢያጠቃ መሬት አንደሚሰፋው ያልማሉ፡፡
ነጠላ ድግሪ ከባዕድ ሀገር ተውሰው፣ ምላሳቸውን ስለው፣ ሕሊናቸውን ሸጠው ራሳቸውን መሪ ያደረጉ ዕድሜያቸው ከ50 ያልዘለሉ ካድሬዎችና አክቲቪስቶች ይህንን በሀሰት ትምህርት የተወናበደውን፣ በስሜታዊነት የነደደውን፣ በመንጋነት የታሰረውን ወጣት ወደ ጥልቅ ገደል እየነዱት ነው፡፡   ስለዚህ እኔ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋና ደካማ ልጃችሁ ከፍተኛ ሥጋትና ጭንቀት ስለአደረብኝ  የሚከተለውን ጥሪ በማኅበራዊ ሚዲያ እጮኻለሁና በምታምኑት አምላክ፣ ስለ ሕሊናችሁ፣ ስለ ልጆቻችሁ ብላችሁ በፍጥነት ይህን እብደት ከእብድ ገላጋዮች እጅ ወስዳችሁ ኢትዮጵያዊ (ሀገራዊ) መድኀኒት ስጡት፡፡  ያጣነው እውቀት፣ አደረጃጀት፣ ጥበብና ልምድ የለም፡፡ ከዚህ በታች የጠቃቀስነውን እንኳ ሀብት ወደ ተግባር ብንተረገመው ከዚህ ከቁልቁለት መንገድ ለመመለስ ያስችለናል፡-
1)     ጳጳሳትና ካህናት በትምህርታቸውን በፍትሐ ነግሥታቸው
2)    ሼኾችና ፁስታዞች በትምህርታቸውን በሸሪአቸው
3)    አባ ገዳ በገዳው
4)    ጡልጣኑ በመድዓ
5)    ኮንሶ በኾንሶ-ሤራ
6)    አማሮው በኢኼ ሥርዓት
7)    ቡርጂው በሙጭንታታ-ሤራ
8)    የአምሓራውና የትግራዩ የጎበዝ አለቃና የአባት ሥርዓት
9)    የዋጉ ወይት-ኸሚርነይ
10)   የራያው አቦ-ገረብ ሥርዓት
11)    የዋጅራቱ (ትግራይ) የቃንጪ ወይንም የገረብ
12)   ጉራጌው በጆካ-ሤራ -----ወዘተ    ከክርስትናና ከእስልምና፣ ከይሁዲነትና ከባህል እምነቶች፣ እንዲሁም  ባህላቱን የመሠረቱ ፍልስፍናዎች ለኀገራችን በሽታ መታከሚያ መተኪያ የሌላቸው መድኀኒቶች ናቸውና ተሰባስባችሁ ይህን እብደት አክሙት፡፡
ወገኖቹን በሰፈር በቋንቋ ከፋፍሎ፣ በክልል ድንበር አሥሮ፣ በዘረኝነት ስብከትና በሀሰተኛ ታሪክ ትርክት አሳውሮ፣ በማይጨበጥ ግላዊ ታላቅ የመሆን ተስፎ አጨጭበርብሮ ግጭትን እያለማ፣ ሀገርን እያደማ የቆየው የጎሣ መሪ ሁሉ ማንነቱ የጠፋበት የነጠላ ድግሪ መቅሰፍት የመታው ድውይ ነውና  ድረሱልን፡፡  የእናንነት እውቀት የኮርስ ውጤት አይደለም፣ ግኝቱ የአንደ ሊቅና ወይንም ፈላስፋ ሐቲት አይደለም፤ አሠራሩ ዘመን የወለደው ቀመር አይደለም፤ ይልቁኑ በብዚ ሺ ዘመናት ከባህል እና ከእምነት ብዝሀነት፣ ከስነ ምህዳር ውጥንቅጣዊ መስተጋብር በመውደቅና በመነሳት፣ በጦርነትና በሠላም፣ በጋብቻና በስደት፣ በገባርነትና አስገባሪነት፣ በጋብቻና በአምቻ፣ በጸሎትና በምክር ዘመናተርን የተሻገረ ሁለገብነት ያለው ነው፡፡  እንደ ዘመናዊው ከምን እንደተሠራ ሳናውቀው እንደምንውጠው የፈረንጅ ኪኒን አይደለም፡፡
ዛረዉኑ ተሰባሰቡ፣ የሚያምነው ገዝቱት፣ ከሀዲውን መንግሥት ያስተናግደው፡፡
ሰዎች ሲሞቱ ፍታትና ሰላት አድርጎ መቅበር ለነፍስ ይጠቅማል፤ በቁም ከእብደት መልሶ እንደ አራዊት ከመግደልና ለመገደል መመለስ ለንስሐ ያበቃል፡፡  ሁለቱም የእናነት ሥራዎች ናቸው፡፡ ፍቅር ጠፍቶና እብደት ነግሦ በዝምታ የምትመለከቱ ከሆነ ሃይማኖታችሁን የምትሰብኩት ከልባችሁ አምናችሁ ሳይሆን ምናልበት በተከታዮቻችሁ ላይ ለሚሰጣቸው መንፈሳዊ  ሥልጣን በመጠቀም ሥጋዊ ፈቃዶቻችሁን ለማገልገል የምትተጉ አሳቾች ሊያሰኛችሁ ይችላል፡፡ ለነፍስም ለሥጋም የማትጠቅሙ ተብላችሁ ትውልዱ ዘመናዊ ድግሪ ያደነቆረውን ወጠጤ ተከትሎ ይጠፋላችኋል፣ እናንተም በልጆቻችሁ ደም ሕሊና የይወቅሳችኃል፣ ፈጣሪም ይጤቃችኋል፡፡
መንግሥት ባለሥልጣናት ሀገራዊ መድኀኒቶቻችንን በመናቅ፣ በፕሮፓጋንዳና በውጭ ገብ አማካሪ፣ በጊዜአዊ አሸነፊነት ፍላጎት ታውራችሁ የሀገር አባቶችን ወደጎን ከመግፋት በመቆጠብ  እውነተኛ ድጋፍ ስጡ፡፡ ትህትና ይኑራችሁ፣ እውነተኛ ሁኑ፤  በገዛ እናታችሁ ላይ ጌም አትጫወቱ፡፡



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...