ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ የሚለው የሀገሬ ብሂል
የወ/ሮ መዓዛን የኤል ቲቪ ቃለመጠየቅ ተከትሎ ተመላለሰብኝ፡፡ እንዲሁም የቤተክርስቲያን እና ኢትጵያዊ ምነነትን በሁሉመ ዘርፍ የመድፈር ሂደት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ታየኝ፡፡ አንዴ በማርክሲዝም፣
ሌላ ጊዜ በፌሚኒዝም፣ ሌላ ጊዜ በካፒታሊዝም፣ ሌላ ጊዜ በተሐድሶ፣ አንዴ …. በስንቱ እንደፈራለን!!! ይህ ሁለንተናዊ ድፍረት አሳሰበኝ -- እናንተስ?
----የሚያሳስባችሁ ሁሉ የዚህ መፍትሔው የክርስቲያኖች ከጥልቅ
እንቅልፍ መንቃት ነውና !!!! ነቅተን በትምህረትና በእውቀት ልዕልና፣
በህግ፣ በጸሎት፣ወዘተ መከላከል መጀመር ነው፡፡ ጊዜ የለንም፡፡
ይህ ካልሆነ ባዕድ አምልኮ፣ ሰዶማዊነት፣ የሰው ልጅ አካል እየበለቱ ለመለዋወጫ መጠቀም፣ አሁን በኢትዮጵየ የተፈቀደው
ውረጃ ሰውን መብት ነው እያሉ ራሱን አንዲገድል መፍቀድ፣ ወዘተ ተማርን፣ ሠለለጠንን በሚሉ የሀገራችን ልጆች ጀርባ ተጭኖ ከምዕራባዊያን የሚፈሰው የርኩሰት ጎርፍ ነገ አስገዳጅ ሐገራዊ ሕግ ሆኖ ይቀርብልናል፡፡
ቅድስት ቤተክርስቲያናችን የተደፈረችባቸው
ዘርፎች፡ እና የሁላችንንም ጥረትና ተሳትፎ የሚጠይቁ ጉዳዮችን ከማንሳቴ አስቀድሞ በዚህ መልዕክቴ ቤተክርስቲያን ብዬ
የምጠራው፡
---- ክርስቲያን ግለሰብ ሰው፣
---- የክርስቲያኖች ስብስብ፣
---ክርስቲያናዊ እምነት ያመነጫቸውና ክርስትና የሚገለጥባቸው የግልና የማኅበራዊ ኑሮ ዘይቤዎች ማጠበቂያ ማኅበራዊ አደረጃጀት፤
--- ክርስቲያኖች አምልኮ የሚፈጽሙባቸው ቦታዎችና ለአገልግሎት ተለይተው የሚሠሩ ቁሳቁሶች፤
---የክርስቲያኖች መልዕክት የሚለዋወጡባቸውና አምልኮአቸውን ለመግለጽ የሚገለገሉባ ምልክቶች (symbols)፣ መንፈሳዊ
ይዘትና ትርጉም ተሰጥቷቸው የኪነጥበብ ውጤቶች፣
----የክርስትና የተቀደሰ ተውፊትና ታሪክ ትርክት፣ የክርስቲያኖች አስተዳደራዊና አመራር ፍልስፍናዎች፣ የክርስትና ዶግማዊ
አስተምህሮዎች፣
---የክርስቲያኖች የክህነት ተዋረዳዊ ደረጃዎችና ቅብብሎሽ፣ ሲኖዶስ፣ የክርሰቲያን ትዳርና ልጅ አስተዳደግ ሥርአትና
አስተምህሮ ወይንም ዳኝነት ሁሉ በሙሉ በአንድነት ተጠቃሎና ተተርጉሞ ሲታይ ነው፡፡
በዚህ ትርጉም መሠረት ቤተክርስቲያናችን የተደፈርባቸው (በስንፍናችን ያስደፈረናቸው) ዘርፎች፡-
(1)-- ክርስቲያን ግለሰብ ሰው ተለይቶ በስለት የመንግሥጥ ሠልጣን በያዙ መዋቅራት ንብረቱን ይነጠቃል፣ ሕይወቱንም
ያጣል (ጅጅጋ፣ በሻሻን ያስታውሷል)
(2)--- የከርስቲያኖች ስብስብ ወይንም ማኅበር ሥልጣን ባላቸው ወይንም የራሳቸው ሌላ ስብስብ ባበጁ አካላት ያለ ፍርድ
ቤት ብያኔ፣ ያለአንዳች ማስረጃ በአክራሪነት፣ በአትፊነት ይፈረጃል (በሀገሪቱ አንዳንድ ባለሥልጣናትና መሥሪያቤቶች የተሞከረውን የማኅበረቅዱሳን ፍረጃ ያስታውሷል)
(3)--- ክርስቲያናዊ እምነት ያመነጫቸውና
ክርስትና የሚገለጥባቸው የግልና የማኅበራዊ ኑሮ ዘይቤዎች ማጠበቂያ
ማኅበራዊ አደረጃጀቶ በፈቀዱት መንገድ
ራሳቸውን እንዳይመሩ ጫና ደረግባቸዋል (በኢትዮጵያ ዩኖቨርሲቲዎች የሚማሩ የኦርቶዶስ ወጣቶች እምነታቸው የሚፈቅደውን ልብስ (ነጠላ
እነዳይለብሱ)፤ የከፈሉበትን የቁርስ ምግብ በጾም ወቅት አውጥተው እንዳይመፀውቱና ለማኅበራዊ አገልግሎት ወደ ገንዘብ ለውጠው እዳያውሉ
በተቋማቱ አስተዳደር ክልክላ ደረግባቸዋል)
(4)---ክርስቲያኖች አምልኮ የሚፈጽሙባቸው
ቦታዎችና ለአገልግሎት ተለይተው የሚሠሩ ቁሳቁሶች የእምነቱ አባላት ባልሆኑ ኢአማኒያን፣ ዘፋኞች፣ መናፍቃን መጫወቻ ሲሆኑ ምንም
አይነት የሕግ ጠበቃ አያገኙም፤ ለዚህ አይነት ጥፋት እርምት የሚደረግበት መድረክ በሀገሪቷ አልተዘጋጀም
(5) ---የክርስቲያኖች መልዕክት የሚለዋወጡባቸውና አምልኮአቸውን ለመግለጽ የሚገለገሉባ ምልክቶች (symbols)፣
መንፈሳዊ ይዘትና ትርጉም ተሰጥቷቸው የኪነጥበብ ውጤቶችን ከዓላማቸው ውጭ በሌሎች አገልግሎት ላይ ሲውል ለማረም የሚዪስችል ምንም
አይነት የመንግሥት፣ የማኅበረሰብና የቤተክህነት መዋቅር ተዘጋጅቶ አይሠራም፡፡
(6)---የክርስትና የተቀደሰ ተውፊትና ታሪክ ትርክትን በፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም በመመራት፣ በአካባቢየዊ የፖለቲካ ትግል
አሸናፊ ለመሆን ያለ ጥናትና ማረጃ በሀሰት ሲበላሽ፣ አፈራሽ በሆነ መንገድ ሲተረክ ማስረጃ እያመጣ የሚሞግት አካል ኤታይም፤ ወደ
ሕግ የሚቀርበውን አጥንቶ የሚቂርብ የለም፡፡
(7)--- የክርስቲያኖች አስተዳደራዊና አመራር ፍልስፍናዎች፣ የክርስትና ዶግማዊ አስተምህሮዎችን በመቃረን ሀገራዊና
ማኅበረሰባዊ ደንቦች ልዩ ፍስፍናና ፍላጎት ባላቸው አካላት መሪነት ሲሸረሸርና ሕግ ሆኖ በክርስቲያኖች ላይ ሲጫን እየተከታተል እያጠና
በአውቀትና በህግ የሚሞግት አካል የለም፡፡
(8)---የክርስቲያኖች የክህነት ተዋረዳዊ ደረጃዎችና ቅብብሎሽ፣ ሲኖዶስ ልዩ ዓማ ባለቸውና እምነቱን ከውስጥ ለመሸርሸር
በተሰለፉ ግለሰቦችና ቡድኖች ክብሩ ሲደፈር፣ አርያነቱ ሲጎድፍ የመከላከልና የማረም ሂደቱ እጅግ ደካማና ዘገምተኛ ነው፡፡
(9)--- የማኅበረሰብና የእምነት መሠረት የሆነው የክርሰቲያን ትዳርና ልጅ አስተዳደግ ሥርአትና አስተምህሮ ወይንም
ዳኝነት በመደበኛ ትምህርት ይዘትና በመገናኛ ብዙሀን ሲወቀስ፣ ሲዋረድና በምትኩ ኢአመናያን የሚከተሉት ዘይቤ በሕግ በክርስቲያኖች
ላይ ሲጫን፤ የልጅ አስተዳደግና የትዳር አመራር ሙሉ በሙሉ ወጭ-ገብ ባዕድ ሲሆን የዚህን ሂደት ጥቅምና ጉዳት ተንትኖ ለመሞገት
የሚያስች መድረክ በሀገሪቱ የለም፡፡
ስለዚህ ቤተክርስቲያን በሁሉም ዘርፎች ተደፍለች፡፡ ልጆቿ ሙቸውን፣ አውቀታቸውንና መላ አቅማቸውን ተጠቅመው ይህን መደፈር
የሚየሰቆሙበት አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡ አንዲያው የኖረ
ውበቷን በሴኩላር ቱሪሰት ዓይን እያዩ ማድነቅ፣ መዐዛ እጠኗን በበዓላት ብቅ ብሎ ማሽተት፣ ሰማያዊ ዜማዋን ምሢር ዘንግቶ በመዝናኛና
ሙዚቃ ደረጃ ማጣጣም፣ ያከማቸቻቸዋን የታረክና የጥብብ ብራና እየገላበጡ በመቆንጠተር አርቲክል ጽፎ ድግሪ መውሰድ፣ ወዘተ ብቻ ኤበቃም አያዋጣምም፡፡ ተግባር!!! ተግባር!!! ተሳትፎ!!! ተሳትፎ!!!
አስተያየቶች