ኢትዮጵያን እየመራችሁ ላላችሁና ወደፊት ለመምራት የምትፎካከሩ ሁሉ
በፖሊሲና በሀሳባችሁ ሁሉ ውስጥ የሚከተለውን ሀሳቤን ብታጤኑ ሀገራችንን ለዘለቁታዊነት የሚጠቅም ይመስለኛል፡-
አፍሪካን በተፈጥሮ
ሀብትና በርካሽ የሰው ኃይል ምንጭነት የሚፈልጉ ሀገራት ሁሉ የኢትዮጵያን መነሳት እጅግ ይፈራሉ፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያና እትዮጵያዊነት የሚል አስተሳሰብና ለእኛ ለእትዮጵያን ቢሰወርብንም ታሪካችንን ሲያጠኑ፣ ብራና መጽሐፎቻችንን ሲበረብሩ፣ በእምነት ፍልስፍናችንን
የነበረንን ልዕልናና መንፈሳዊ ኩራት ያወቁ፣ መድኃኒት፣ አስትሮኖሚ፣ አስተዳደር፣ ኪነ ጥበብ እንደነበረን የደረሱበት ሁሉ ይሰጋሉ፡፡
ሥጋታቸው አሁን ያለው ትውልድ ወደራሱ ማንነት ማየት ከጀመረ፣ የተሰወረበትን የአባቶቹን ጓዳ ለመመርመር
ፊቱን ከጭፍን ግልበጣ ወደ ተረጋጋ ተመራማሪነት ከመለሰ እስካሁን
የሚዘርፉትን ያስቆማል፤ በስደት እየፈሰሰ ጠላቶቹን ከማገልገል ይቆጠባል፤ ከጊዜአዊ ስሜታዊ እርካታ ይልቅ ለትውልድ ማብ ይጀምራ፤
የምዕራባዊያን ጭራና ተከታይነቱን ለውጦ በእኩልን የመኖ አቀም ያዳብራ፤ ሌሎች አፍሪካን በልጠውና ተከታይ አድርገው የመቀጠል እድላቸው
ይፈተናል፤ የኢትዮጵያኖ መንፈስ ወደ ሁሉም አፍሪካ ተጋብቶ ራን ለመቻልና ለመተባበር ሀገራትን ያነቃቃል፤ በመሆኑም ---- ፈጂና ጨፋሪ፣ ገልባጭና አቋራጭ ብልጽግና ፈላጊ ትውልድ ስለሚያጡ
ምዕራባዊያን ራዕይህን ለማምከን ሁሉንም ወጥመድ ይዘረጉብሃል፡፡ ሥለዚህ ትልቅ አደጋ ላይ ትወድቃለህ፤ የአንተን
ሀሳብ የሚደግፉ ሰዎች፣ ፍልስፍናዎችና እምነቶ ሁሉ አደጋ ላይ ናቸው፡፡ በመሆኑ ጥበብ የተሞላበት አካሄድ ያሻል፡፡ የሰፈራችንን
ራ ወዳድ የሆድ ሌሎ ፖለቲከኞችን ለማሸነፍ ብለህ ከባድ፣ ሩቅ ዓላሚና ሌሎችን የሚስነሳብህ ስልታዊ ንግግሮች ከማድረግ አንድተቆጠብ
እመክርሀለሁ፡፡
ለስንኩሎቹና ለአኩራፊዎች መድኀኒት መስጠት ከፈለጋችሁ በአደባባይ በሕዝብና በሽማግሌ ፊት ለፊት ማወያየትና የሚመለሱት እንዲመለሱ፣
ተንኮለኞች ከሕዘብ እንዲነጠሉና ማንንም እዳያሳስቱ መድረኮችን መዘርጋ ያስፈልጋል፡፡
ፈጣንና ስልታዊ እርምጃዎች፡-
1. አርኪዮሎጂ ቁፋሮና ምርምር ከባዕዳን ጣል ገብነት
ነፃ ሆኖ ሁሉም በኢትዮጵያዊያን ብቻ እንዲካሄዱ ማድረግ
2. የኬሚካል ማዳበሪያን በመተካት የኤትዮጵያን አፈር በሌሎች ፈቃድና ድጋፍ የሚያበቅልና የሚነሳ አንደይሆን
ነጻ የማውጣት አስቸኳይ
ስተራትጂ መዘርጋት
3. መድኃኒቶች ከኢትዮጵያ ጥበብ ተመርተው አንዲተኩ
በማድረግ ሀገሪቷን ከውጭ-ገብ መድኀኒት ቢያንስ ከ80 በመቶ በላይ መተካት፡፡ መተካት ባይቻል በስጠትና በመቀበል ደረጃ ከሌሎች
ጋር የምንገዳደርበት ደረጃ ላይ አንድንገኝ የሚየስችሉ ምርምችን መጀመር፡፡ በኢትዮጵያ የኦርቶክስ ክፍርስትና፣ በሙስሌም፤ በጠረፋማ
አካባቢ የሚኖሩ ማኅበረሰቦች ሰፊ የመድኀኒት አውቀቶች ምርምር አንዲጀምርባችቸው ማድረግ
4. የእህልና የእንስሳት ዝርያ ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵየዊያን
ተመራማሪዎችና የገበሬ ባህል የዘር አቀማመጥና ማስተላለፍ ሥረዓት መመለስ፤ የጂን ባንክ ከውጭ አካላት ነጻ በማድረግ የትበቃና ማባዛት
ቴክኖሎጂን ማሻሻል፡፡ በዚህ ዘርፍ ዓለም አቀፍ የሰው ልጆች ምግብን ቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚሠሩ ሀገራትና ካምፓኒዎች ድለላ የማያሸንፋቸው
ምሁራንን መልምሎ የቴክኖሎጂ ቀሰማ ስኮላርሺፕ መላክ፡፡
5. ሀበትን ማከማቸት ሳይሆን ሀብት እንዲዋለድና አንዲባዛ
ወደ ምርትና ኢዱስቲሪ፣ ትምህርትና ምርምር ትውልዱን የመምራት ስልት የሚዘረጉ ምሁራን ስብስብ ያለበት ተቋም መመሥረት
6. ቱሪዝም ቁጥጥር የሚደረግበትና ለገቢ እንጂ ለባህልና
እሴት ብክለት እንዳይሆን መሥራት አግባብነት ያለው ፖሊሲና አመራር
መስጠት
7. ሁሉን ቅርስና እሳቤ ሴኩላራይዝ ለማድረግ ከሚሠራው
ከዩኔስኮ ትምህርትንና የቱሪሰዝም መስህቦችን ነጻ ማውጣት
8. ስኮላር ወደ ውጭ ለትምህርት የሚሄዱ ተማሪዎች ሁሉ
ኢትዮጵያዊ ፍልስፍናና ራስን ከጥገኝነት ለማላቀቅና በማንነታችን ለመቆም የሚያስችለን ሚሥጥራችንን የሚገነዘቡ፣ ጠቃሚውን ትምህርት
እንጂ አእመሮ አጣቢውን መቋቋም እንዲችሉ ማሠልጠን
9. በማንም ሀገር የማይታወቅ፣ በእርዳታ የማይደገፍ
ዝግ የኢትዮጵያዊያን የምርምርና የትምህረት ዩኒቭሲቶ መመስረት፤ ከሚለሙ ልዩ እውቀቶች በመነሳት ከውጭ ከምናገባው ጋር በማዋሀድና
በማዋደድ፡፡
10. የአፍሪካ አህጉር-ፈለቅ እውቀት ስብሰባ፣ ምርምርና
ልማት ተቋም በአፍሪካ አንድነት ሥር በኢትዮጵያዊያን መሪነት መመሥረትና አፍሪካዊ ሳይንስ ማዳበር፤ከምዕራባዊን እርዳታ ነጻ በሆነ
መንገድ የሚካሔድ
11. ወደ አፍሪካ የሚገቡ ሸቀቶችን በበይነ መንግሥታት
ደረጃ ተነጋግሮ ጥራታቸውን መወሰን፣ የሚተኩበትን የጋራ ፕሮዤዎች መመሥረት
12. ከቻይና ጋር ጠንካራ የእኩልነት ጥቅም ላይ የተመሠረተ፣
ከምዕራባዊያን የብልጣብልጥነት ግኑኝነትና ጣልቃገብነት የፀዳ የንግድ፣ የትምህርት፣ የዲፕሎማሲና የምርምር
ፍኖተ ካርታ ለ20 ዓመት (በየ 2 ዓመቱ የሚመዘን ራስን ወደመቻልና ጥገኝነትን ወደመቀነስ በሚያመሩ መሥፍቶች ላይ መመሥረት)
ፋንታሁን ዋቄ
አስተያየቶች