ተገፊዎች ግፍን ይቅርታ ጠየቋት
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። አሜን።
17/11/2015
የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ክርስቶስን ዘንግተው በፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ በተፈጠረ ቡድንና የቋንቋ ዘውግ ዘረኝነት ተከፋፍለው የየሰፈራቸው ጣዖት ፈጥረዋል። ይህን የሸክላ፥ የብረት፥ የመዳብ፥ የወርቅና የብር ጣዒት አይደለም። ዘመናዊው ጣዖት የተፈጠረው ከተረፈ ማርክሲዝም፥ ከተረፈ ናዚ የተወለደው ዘረኝነት እምነቶችና በኦነግና በሕወሐት ፈጻሚነት፥ በኢትዮጵያዊነትና ኦርቶዶክሳዊነት ላይ ለ700 ዓመታት የተሰለፉ ታሪካዊ ጠላቶች አስፈጻሚነት የተመሠረተው የጎሣ ሕገ መንግሥት ነው።
ይህ ሕገ መንግሥት መግቢያው ብሔር ብሔረሰብና ሕዝብ የሚል ርዕስ አለው፤ ዝርዝሩ አማራና ኦርቶዶክስን መስበር ነው። ግቡና የመጨረሻው የብሔርተኞች መንግሥተ ሰማይ በምድር ማስገኘት ነው፥ እርሱም ከኦርቶዶክስና ከአማራ ነፃ የሆነ ፓጋን ትግራይ፥ ፓጋን ኦሮሚያ ወይንም ፓጋን ኢትዮጵያን መፍጠር ነው፤
በዚህ አዲስ የዘረኞች “ሃይማኖት” ዶግማው ትግራዋይነት (ሕወሐትነት) እና ኦሮሙማ ከነባር እምነቶችና ባህሎች ሁሉ በላይ ነው፥ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት፥ ኦርቶዶክሳዊነት እና ኦርቶዶክስ የሁለቱ አዳዲስ እምነቶች ጠላቶች ናቸው። የአዳዲሶቹ “ሃይማኖቶች” የአምልኮ አፈጻጸም የሐሰት ትርክት፥ ስም ማጥፋት፥ ማፈናቀል፥ መግደል፥ ማደኸየት፥ ማምከን፥ ማሰደድ፥ ጦርነቶችን ጭሮ መፍጀት፥ ከእምነት ማስወጣት፥ በቁጥር ማሳነስ (ዲሞግራፊ መቀነስ)፥ ከውጭ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር መሰለፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ኦርቶዶክሳዊነትን፥ ኢትዮጵያዊነትንና አማራን መክሰስ ናቸው።
የሕወሓትና የኦነግ/ኦሮሙማ/ ብልጽግና ማንነት የሚገለፀው በታሪክ ውስጥ በሚታወቁት ዘር አጥፊዎች በናዚዝም፥ በኦቶማን ቱርክ የአርመን ፍጅት፥ በቱትሲዎች የዘር ፍጅት፥ በአውሮፓዎች የአውስታራሊያና የአሜሮላ የነባር ሕዝቦች ፍጅት ነው።
ይህን ሁኔታ ወደ ጤናማ ለመመለስ፥ በሐሰት የተፈጠረውን ጥላቻና መለያየት ለማከም፥ ዜጎችን ወደ ሰብአዊ አእምሮአቸው መልሶ አንድ ቤተሰብነታቸውን ለማስታወስ ምክክር ይፈልጋል፤ እውነትን መናገር የጠይቃል፥ ተናጋሪው ጀግና በፍቅር የሚኖር መሆን ይገባዋል፥ ብልጣብልጦቸ ለሰላም ግንባታ አይሆኑም፤ ልበ-ንጹሐን ይፈለጋሉ፥ ራስወዳዶች ፍትሕ አይሰጡም፥ ራሳቸውን የናቁና ለሌለች የሚያስቡ ያስፈልገፉናል፤ የተደራጁ ሐተኞችና ቁማርተኞች አያዳምጡም፥ በኃይል የሚበልጣቸውና ለማዳመጥ እንዲቀመጡ የሚያስገድዳቸው አሸናፊ ያስፈልጋል።
አሁን ባለንበት ሁኔታ በድሎ የሚያኮርፍ፥ ዋሽቶ ዋሽታችኋል የሚል፥ ገድሎ ሞትኩኝ በማለት ይቅርታ ጠይቁኝ የሚል፤ በተቃራኒው አገር የበለጠ ይጎዳል ብሎ ይሉኝታ ቢሱን፥ ኅሊና ቢሱን፥ ፈሪሐ እግዚአብሔር የተለየውን እየተከተለ የሚለማመጥ፥ ይቅርታ የሚጠይቅ አለ።
ይቅርታ ተጠየቅሁ፥ ይቀረኛል፥ ጥፋቴን ልማት ነው በሉልኝ፥ አንግሡኝ የሚል አለ።
ክርስቲያኑ ሌላው ይሰናከላል ብሎ እየተበደለ መከራን ይሸከማል፤ ያኛው ከክርስቶስ ይልቅ የቋንቋ ዘውጉንና ዘረኛ የፖለቲካ ድርጅቱን ያመልካል፤ ሌላኛው ከዘመዶቹ የሰማውን የቂም ትርክት፥ ያለፈውን ዘመን ወሬና ፕሮፓጋንዳን ከቅዱሳት መጽሐፍት አስበልጧል።
ሁሉም ለራሱ አዋቂ ሆኖ የሐዋሪያትን ትምህርትና የክርስቶስን ነገር ትቶታል። ሚሊዮኖችን ገድሎና አገዳድሎ ሲያበቃ ይቅርታ ጠይቀኝ ይልሃል። ንስሐን ፈጽሞ ዘንግቶታል፥ ይቅርታ መጠ'የቅን እንጂ መጠየቅን ነውር አድርጎታል።
በዚህ ውስብስብ የፖለቲካ፥ የእምነት ጉድለት፥ የቡድን-እሳቤ እስረኝነት ባሮች ሆነን የምንገኝ እኛ ምክር ሳይሆን እንዴት እንደምናሸንፍና ሂሳሳብ እንደምናወራረድ ነው የምናሰላው።
የትግራይና የኦሮሚያ ሕዝብ በዚህ አይነት የሐሰት ትርክትና የበቀል አዙሪት ውስጥ የ50 ዓመታት ስብከት ተጠልፎ እሥረኛ የሆነ ነው። መቆጣት እንጂ ማዳመጥም ይገበሀል፥ እውነቱን ምርምር ሲሉት የዘር ፓርቲከኛውና ሕዝቡ "እንድ ናቸው" በሚል አምልኮ ተይዟል። የእኔ አይነቱ የእውቀት ሕፃን፥ ጎዶሎ ሰው ምን መምከር ቢችል ነው ይህን ውስብስብ የሚመክረው ነገር ቢኖረኝ፦
💠ሁላችንም ይሉኝታን በመተው በሐዋሪያት ቀኖና፥ በቀደምት አበው ተግባራዊ ትውፊት፥ በመቅዱሳት መጽሐፍት ብቻ እና ብቻ መሟገት፥ "ይመስለኛል፥ ደስ ይለኛል፥ እኛ እገሌዎች እንዲ እናስባለን ወዘተ" በሚል ከንቱ ልማድ አለመጠለፍ፤
💠የሳቱ ዘመዶቻችንን ከመሳሰል እና ነፍሳችንን የመንጋ እሥረኛ ከምናደርጋት ጨክነን በመሸሽ ክርስቶስን ለመምሰል ብቻ መኖር—> በዚህ ምክኒያት የሚመጣ ፈተና (መገለል፥ ሥራ ማጣት፥ ግብርና ሌሎች ጫናዎች ውስጥ መውደቅ፥ ባንዳ እና ከሀዲ መባል፥ በሐሰት መከሰስና መታሰር፥ አልፎም መገደል፥ ወዘተ) ስለሚኖር ለዚያ መዘጋጀት፤
💠በጊዜውም ያለጊዜዉም በፍቅር ሆኖ እውነትን መናገር፥ ማድረግ እና ከእውነተኞቹ የጥምቀት ልጆች ከሠፈርና ቋንቋ ወጥቶ በመተባበር የፖለቲካ ድንበርን ማፍረስ፥ የክርስትና አንድነትን ማሳየት (ጨው፥ ብርሃን፥ ምስክር መሆን)
💠ከላይ የተባለውን በተግባር ለመሞከር ለራስ ቃል መግባት፥ ቀጥሎ ከሚመስሉን ሰዎች ጋር መመካከርና አንድ አቋም ላይ መገኘት፥ አብሮ አቅዶ ከሐሰተኞችና ስሑታን ጋር ለመጋደል ማቀድ፥ የሚችሉትን መሞከር፤
💠በንስሐ፥ በጸሎት፥ በዕንባና በፍርሐት፥ በትሕትና በመሆን ሆነ ተብሎ የሚሠራ ክፋት፥ ፀረ-ክርስትና አቋም ያለው ፖለቲካና ባለሥልጣን፥ ካህንና ጳጳስን ፈጽሞ ከማክበርና ከማበረታታት ይልቅ ወደ ንሥሐ ሚመለሱበት፥ ወይንም በጥፋታቸው ከጸኑ የሚወገዱበትን (ወደ ንስሐ የብአኝነት ገዳም የሚላኩበት) ማንኛውንም (ርኩሰትና ኃጢአት) ያልሆነ እርምጃ ሁሉ መውሰድ እና እንዲወሰድ ማስተባበር፥ ማድረግ የሚችሉት እንዲያደርጉ ግንዛቤና ጫና መፍጠር።
—— ይህ ሐሳብ በተግባር ከመሞከራችን አስቀድሞ በውይይት ቢዳብርና ሊቃውንት ቢመክሩበት መልካም ይመስለኛል።
አስተያየቶች