በትውልዱ ሥነ ምግባር ላይ የቤተክርስቲያን በዓላት
ሰመኑን ተደጋግሞ ከጋዜጠኞችና ከፖለቲከኞች የሚነሳ ሁለት ጥያቄዎች አሉ፡፡ ምናልባትም ታላቁን የቤተክርስቲያን በአል የፈጣሪያችን፣የጌታችን፣ የመደድኀኒታችንን ልደት (ገና)ን ምክኒያት በማድረግ ጥያቄው የጎላና የተደጋገመ ይመስላል፡፡ በሌላ በኩል በሀገራችን ያለውን የግጭትና የሰላም መታጣት የሚያስብ ሰው ቤተክርስቲያን ጎልታና በንቃት ለምን አልተሳተፈጭም ከሚልም ይመስላል፡፡ መጠየቁ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ያለ ዳራውና ተጨባጭ ሁኔታውን ያላገናዘብ ምላሽ በመስጠት በቤተክርስቲያን ላይ አሉታዊ ጣት መቀሰር ጤናማ አካሄድ አይደለም፡፡ ስለዚህ የሚከተሉት ጥያቄዎች የሚጠየቁበትና የሚመለሱበትን ተጨባጭ ሁኔታ ማስገንዘብ አስፈላጊ ስለመሰለኝ የግል ምልከታዬን መስጠት ፈለግሁ፡-
(1) የቤተክርስቲያን በዓላት አከባበርና አስተምህሮው ለትውልድ ሥነ ምግባር መታነጽ፣ ለሰላምና ለፍቅር መጎልበት ምን አስተዋጽኦ ያድርጋል?
(2) የቤተክርስቲያን አባቶች ትውልዱ በሥነ-ምግባር እንዲህ ሲወድቅ ለምን ዘምታን መረጡ?

ሥነ ምግባር ከሃይማት አንጻር ሲታይና እምነት የለሽ በሆነ መነጽር ሲታይ ምላሹም ሆነ ዓላማው ይለያያል፡፡ ሃይማኖት ያለው ሰው መልካም ሥራና ጠባይ እንዲኖው የሚፈልገውና የሚረው በዚህ ዓለም በምድር በሚገኝ ጠቀሜታን ብቻ አስልቶ አይደለም፡፡ በተለይ በክርስትና ሥነምግባር የእመነቱ ተግባራዊ መገለጫና ለሰማያዊ ዋጋ ፈለማ ወይንም ቀብድ ነው፡፡
የሥነ ምግባር ምንጩ እሴት ነው፡፡ የእሴት መሠረትና ማህቀፉ ደግሞ እምነት ነው፡፡ እምነት በአስተምህሮና ዶግማ ተቀንብቦ በቀኖና አትርነት የሚኖር፣ ዛሬን ተስፋ በሚያደርጉት ግብ ምክኒያት መወሰን ማለት ነው፡፡ የእምነት ትርጉም በፈጣሪና በፍጡር መካከል ያለውን አንድነት ማስጠበቂያና ውጤቱን ተስፋ በማድረግ በነፃ ፈቃድ ሰዎች የሚመሩበትና የሚገዙበት ሁለንተናዊ የመሆንና የማድረግ ሥርዓተ-ሕይወት ነው፡፡ ሀሳብም፣ ምኞትም፣ ድርጊትም፣ መስዋዕትነትም፣ መስጠም፣ መማርም፣ ሁሉና ሁሉ በእምነት ተመርተው ሲከወኑ ሥነምግባር ይሆናሉ፡፡
ሥነምግባርን ልዩ ልዩ የሚያደርገው የእምነት አይነት ልዩነትና ጥልቀት ደረጃ ነው፡፡ እምነት የሌለው አእምሮ ያለው የሰው ልጅ የለም፡፡ ከሀዲ የምንላቸው እንካ ለመካድ ምክኒያት የሚያድርጉት ሰብአዊ ፍለልስፍናቸው እምነትን ተክቶ የሚዳኛቸው ቅጽረ አእምሮ ነው፡፡ እኔ ክርስቲያን ስለሆንኩኝ የሥነ ምግባርን አዎንታዊነትና አሉታዊነት የምለካበት መሥፈሪያ የሚገኘው የሚከተሉትን ዘላለማዊና ማንም አእምሮ ሳይጠይቀው ያማያላፍቸውን ጥያቄዎች ስመልስ በቤተከክርስቲያን አስተምህሮ በመመራት ነው፡---
(1) ከየት መጣው፣ ማን አስገኝን፣
(2) ለምን አስገኘኝ፣
(3) ከሞት በኃላ ምን ይጠብቀኛል፣
(4) አስገኚዬ ከእርሱጋር እና እርሱ ከፈጠራቸው ሌሎች ፍጡራን ጋር በምን መልኩ መስተጋብር እንዲኖረኝ ይፈቅዳል
(5) መልካም ምንድ ነው፣ እንዴት ይመዘናል
በሚሉ ሲሆኑ--- ምላሾቹ የሚንተራሱት ዋና መርህ ---
(1) የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤
(2) ሰው በዚህ ምድር በዓለም ላይ የተገኘው በእግዚአብሔር ነወው፤
(3) አፈጣጠሩም እግዚአብሔር አምሳል ነው፤ አኗኗሩም የእግዚአብሔን አርአያ ለመንሳት መጋደል ወይንም መድከም ነው
(4) ከሌሎ ሰዎችና ፍጥረታት ጋር ያለው መስተጋብር ሁሉ ሰው የሆነው የኢግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በትምህርትና በአርአያነት ያሳየውን፤ ሌሎች እርሱን ተከትለው በመኖር እርሱን የመሰሉትን ምሳሌ አድርጎ መኖር፤
(5) አእምሮዬ የክርስቶስ፣ ማያዬ የቤተክርስቲያን እስከነ ትምህርቷ፣ ትውፊቷና ታሪኳ ሁሉ ተጠቃሎ ነው በሚል ይወሰናል
በዚህ ምክኒያት ስበላ፣ ስለብስ፣ ስሠራ፣ ስፈላሰፍ፣ የፖለቲካ ሥራ ስሠራ፣ ሚሰት/ባል ሳገባ፣ በሀገርና በቤተሰብ ደረጃ ሳስተዳደር፣ ስነግድና ሳርስ፣ ወዘተ ዓላማዬና ግቤ አርአያ አምላክን ለመንሳት ያለኝን ምኞትና እምነታዊ ቁርጠኘኝነት ወይንም የምመኘውን የቅድስና ሕይወት ለማግኘት አስተዋኦ ያደርጋል፣ ወደፍጽምና በሚደረገው የጉዞ ጎዳና ላይ መሆን አለመሆንን እየመዘንኩ-- ይህ መልካም ሥነ ምግባር ነው፤ ይኼኛው አሉታዊነት ያለው ነው እያልኩ እመዝናለሁ፤ እታረማለሁ፣ ንስሐ ገባለሁ፡፡ ሌሎች ኢ-ስነምግባረዊ ሥራ ይሠራሉ ብዬ የምበይንባቸውና የምኮንናቸው ሰዎች ካሉ የምመዝናቸው ከእምነቴ ተነስቼ ነው፡፡ በሃይማኖት ብንለያይም በሚገለጠው ምግባር እንተዋወቃለን፤ መልካም የምናደርግበት ምክኒያት ቢለያይም በዚህ ምድር በዓም፣ በአንድ ሀገርና ቤተሰብነት ስንኖር በግባችን ሳይሆን በደርጊታችን ደረጃ እንግባባለን ወይንም እንለያያለን፡፡
በክርስቲያኖች ዘንድ ለሥነ ምግባር መታጣት፣ ለክፋትና ለመለያየት ዋና ምክኒያት አንድ ክርስቲያን ሰው ራሱን በሁለት ከፍሎ ማየቱ ነው፡፡ ራሱን መንፈሳዊና ሥጋዊ ብሎ የሚሠነጠጥቅ ሰው ውሎውን በቦታና በጊዜ ደረጃ መንፈሳዊ የሆነና ያልሆነ ቦታና ጎዜ ብሎ በመክፈል በሁለትነት ይገለጣል፡፡ መንፈሳዊነትና ዓለማዊነት የይጋጩበታል፡፡
ክርስትናን እንደሚገባ ለተረዱ፣ በቤተክርስቲያን እንድነት ለሚኖሩ ሰዎች ዓለማዊና መንፈሳዊ የሚባል ሁለት ሕይወት የለም፡፡ በተዋህዶ አካልና ነፍስ የፍላጎት ልዩነት ያላቸው የአንድ ሰው ጠባዮች ሲሆኑ ሥጋዊ ሕይወት የምንለው ሥጋን በደመነፍሳዊ ፍላጎቱ ስናገለግለው፣ አምላካዊ ጠባይ ያላት ነፍሱን በሚጠቅም መንገድ ብቻና ብቻ መሆን ስለሚገባው የዕለት ተዕለት ሥራችን፣ ውሳኔያችን፣ የኑሮ ምርጫችን ሁሉ የሁለቱን በተዋህዶ በመስማማት የጸጋ አምላክ ቢያዳርጋቸው ሰው ሆኖ ፍለጋውን (አርአያነቱን) በሰጠን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ የፍጹምነት መጨረሻት አንጻር መመላለስ ነው፡፡
ኢአማኒያን ሕግ አውጨዕዎች፣ ነጋዴዎች፣ መምህራን በሚዘረጉት ሥርዓተ መንግሥትና ሥርዓተ አስተዳደር ውስጥ መንፈሳዊ ሕይወትን በማኅበር አምልኮ የምንፈጽምበት የቤተክርስቲያን የአገልግሎት ሰዓት ጋር ብቻ በማቆራኘት ለመወሰን ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ስለዚህ በመደበኛ ትምህርት ቤት፣ በገበያ፣ በሥራ ቦታ፣ በምርምርና የህግ ድንጋጌ ጎባኤ ውስጥ ሁሉ የሰውን የመንፈሳዊት ነፍስና የሥጋ ተዋህዶ በመነጣጠል አሁን ዓለማዊ ሥራ የሚራበት ቦታና ሰዓት ነው፤ ከእምነት የሚገኝ ማንነትህን፣ እሴትህንና የዓላም ማያ መነጽርሕን ጣለው፤ በሰንበት ቀን ወይንም በቅጽረ ቤተክርቲያን ብቻ ተጠቀመው ወደ ሚል በአዋጅ ያልተነገረና በተግባር ግን አስገዳጅ የሆነ ከፍተኛ የሴኩላሪዝም ረቂቅ ጭቆና ነው፡፡
ዓለማዊና መንፈሳዊ ሕይወት ይጋጫል ለማለት የሚቻለው ከፋፍለው ለማየት ለሚሞክሩት ሰዎች ነው፡፡ ለእኔ አይጋጭብኝም፤ ክርስቲያን በመሆኔ ባለን መንፈሳዊ ማንነት ወይንም ወደ አምላኬ ለማደግ በማደርገው ተጋድሎ ውስጥ በሁሉም ቦታና ጊዜ ማንነቴን የሚጻረር አለባበስ፣ አነጋገር፣ አመጋገብ፣ ማኅበራዊ መስተጋብር፣ ንግድ፣ ዳኝነት፣ ውሳኔና ድርጊት ሁሉ ጋር የሚኖረኝ ግጭት ክርስቲያን በመሆኔ ለተጋድሎ የተሰጠኝ የእድገት መንገድ ብዬ አምናለሁ፡፡ እንዲህ ካመንኩኝ ለእኔ ሁለትነት የለኝም፡፡
አሁን ቤተክርስቲያን አባቶች፣ በአላትና አገልግሎቶች ስለምን የኢትዮጵየዊውን ሥነ-ምግባር አንደሚገባ ማነጽ አልቻሉም ለሚለው ጥያቄ መልሱ ቀላል ነው፡፡
(1) ከሃይማኖት አስተምህሮ፣ ከባህልና ከቤተሰባዊ ተዋረዳዊ መከባበር የተከኘውን ማኅበራዊ እውቀትና እምነት ሴኩላር በተሰኘ ውጭ-ገብ የተውሶ ፖለቲካና የአስተዳደር ዘይቤ በመተካት በቦታና በጊዜ መገደብ ከተጀመረ ከመቶ ዓመት በላይ ስላስቆጠረ ነው፣
(2) የክርስቶስ ልደት የአግዚአበሕር ቃል ሰው መሆን እና ቅድስት፣ ልዩ በሆነች በድንግል ሴት እጅ ታቅፎ መታየት የሚታወስበት ብቻ ሳይሆን ምስጋናና አምልኮ የሚፈጸምበት ዕለት ነው፡፡ ከሶስቱ አካል አንዱ ወልድ ሰው የመሆኑ አስፈላጊነት በፍጡር አቅም የማይፋቅ በደል፤ የማየይፈርስ የጥል ግድግዳ በመኖሩ ነው፡፡ ስለዚህ ዕለቱ የእርቅ ነው መባሉ አግባብነት አለው፡፡ ይሁን እንጂ
ይህ በዓል ሲከበር ዓላማውን የሚያደናቅፉ ክዋኔዎች ይካሄዳሉ፡-
• እንደ ምዕራባዊያን እምነት የለሽ ከተሞች የንግድ እግዚብሽን ይዘረጋል
• ሚዲያዎች ሁሉ ስለ ቱሪዝምና ስለመዝናናት ያላዝናሉ
• ሃይማኖታዊ የበአል ክዋኔዎች ትርጉሙ በማይታወቅ የአርት/ኪነ-ትበብ ስም የምንዝር ጌጥ ሆኖ ይቀርባል
በዚህ ምክኒየት አባቶችን በመስማት፣ ትምህርት በመማር ራሱን ማረቅ የሚጠበቅበት ተውልድ ሁሉ ጆሮውን ወደእነዚህ ክዋኔዎች ይመልሳል፡፡
ሃይማኖታዊ በዓልና ትምህርት አሁን ካለው ሃገራዊ የዘውጌ ፖለቲጃ፣ የጎሣ ገግጨት፣ በሃይማኖት መለያየት ላይ ያለው ሚና ምንድነው?
ለእኔ የዚህ ጥያቄ ምላሹ መሠረታዊ ጉዳይን ከመገንዘብ ቢጀመር ይጠቅማል ብዬ አምናለሁ፡፡
(1) ሰሰው በብሔር፣፣ በዘር፣ በሃይማኖ የመከፋፈሉ ነገር ምንጩ የትምህርት ብልሽት ነው
(2) በተበላሸ ትምህርት የተበላሰ የዓለም ማያ የይፈጠራል
(3) በተበላሸ የዓለም ማያ የተበላሸ የፖለቲካና የመኖር ትርጉም ፍልስፍና ይበለሻል
(4) የመኖር ትርጉምና የፖለቲካ ፍልስፍና ብልሽት በአንድ አምላክ አምሳል የተፈጠሩትን፤ የመነሮር ትርጉማቸው ወደ አርአያ አምላክነት ማደግ የሚገባቸውን የሰው ልጆች በዘርና በጎሣ ከፋፍሎ ወ በዳርዊን የሥነፍጥረት አስተምሀሮ መሠረት ሁሉም በየፊናው መሠረቴ ነው ወደ ሚለው ዝንጀሮነት አንዲያድግ መገፋፋት ነወው
(5) ዘረኝነት በክርስትና ጽዩፍ፣ኃጡአትና የራስን ክቡር ፍጥረት ማዋረድ ነነው
(6) በሃይማኖት መለያየት ማለት ግን በእምነት አስተምህሮ ስለሚሆን ለእውነት የመቆም መንገድ ስለሆነ ከመጣላት ጋር አየይነፃፀርም፡፡ ሰዎች በሃየይማኖት መለያየት የለባቸውም የሚለውም አስተምሀሮ ለዘረኝነት በር ይከፍታ፤ምክኒያቱም ሁሉም ትምህርት ትክክልነው ወደሚል ድምዳሜ የይወስዳል
(7) ሁሉም እምነት ትክክል ነው ካልን ዝንጀሮ ነኝ ብለው የሚምኑትን ሰዎችና የለብ በእግዚአብሔር አምሳለል የተፈጠርን ነን የሚሉት ሁለቱን አንድ ናቸውሁ፣ ትክክል ናችሁ ማለት የተጣረሰ ርእዮተ-ዓለም ነው
(8) በዓለም ላይ ለዘላለም ስህተትና ትክክል፣ አውነትና ሀሰት፣ ጨለማና ብርሃን መኖራቸው አይቀርም፡፡ የይህ ግን የሰውን ሰው መሆን አያስቀረውም፤ የሰውን በሰላም በዚህ ምድር በዓለን አውነትን እየመሰከሩ አብሮ መኖር ኤኬሌክልም
ይልቁንም በመላምት ከሌላ ሀገራት እየተቃረም፤ ባህልን ሃይማኖትን እየረገጠ ሰዎችነን በጎራና የሚከፋፍል ፖለቲካ ነው የሰላም ጠንቅ --- እና የፍልስፍና ምንጫችንን ወደ ሀገራዊነት ለመመለስ መሥራት ነው፡፡ ቤተ እምነቶችን እንደ ታኮ በችግር ጊዜ ብቻ ማተንፈሻ መጥራት ቀልድ ነው፡፡

አስተያየቶች