ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ጳጳሳት ከፈለጉ የኦርቶዶስ ክርስቲያኖች እልቂትን ማስቆም ይችላሉ

ለጳጳሳት ካልለገማችሁ በስተቀር ሥርዓታዊ የክርስቲያን ፍጅቱን ማስቆ  ትችላላችሁ‼️
=====================
እንዴት❓

ይኼው ምክረ ሀሳብ፦

ጳጳሳት ሥርዓታዊውን የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ዜጋ ዘር የማጥፋቱን ያፈጠጠ ያገጠጠ ሂደት በጉባኤቸው የሚከተሉትን በመወሰን ማስቆም ትችላላችሁ:-

(፩)👉 ከአጥቢያ ጀምሮ በክርስትናቸው በመንግሥት መዋቅ ግብር የተጨመረበት፣ ግፍ ተፈጽሞበት ፍትሕ የተነፈገ፣ የተፈናቀለ፣ የተገደለ፣ ንብረት የተቀማ ከ፩-፪ ሳምንት ውስጥ ማሰባሰብ፤ በቀጣይ ፪ ሳምንት ውስጥ ማሳተምና ለዓለምና ለምእመናን አሰራጩ፤

(፪) 👉 "የክርስቲያን ሁለገብ (ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርሥ፣ ማኅበራዊ መዋቅር፣ ኢኮኖሚ፣ በአካል መግደል፣ ማምከን፣ ማፈናቀል፣ ጅምላ ፍጅት፣ ፍትሕ መንፈግ) ዘር የማጥፋት ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ፕሮጄክት ተዘርግቶ ፍጅት እየተፈጸመብን ነው" መግለጫና የድረሱልን ጥሪ ለመላው ዓለም አግባብነት ላላቸው ተቋማትና መንግሥታት ኦፊሴላዊ ጥሪ ከማስረጃው ጋር አያይዛችሁ  ጠይቁ፤ 

(፫) 👉 በመላው ዓለም የተሰራጨው የኦርቶዶክስ ምእመንና አጥቢያ ሁሉ ቸዘር ማጥፋት መከላከል ግብረ ኃይል በመመሥረት የሁለገብ ዘር ማጥፋቱይ መረጃ በመያዝ ከሕግ ባለሙያ፣ ከወትዋቾችና ከዲፕሎማቶች፣ ከሌሎች አቢያተ ክርስቲያናት ጋር ንቅናቄና ክስ መመሥረት እንዲችሉ ትዕዛዝ ስጡ፤

(፬) 👉 መንግሥት ያወገዝነውን ከአጥቢያዎቻችንና ከገዳሞቻችን ስለማያግድ፣ በጎሳ እንደንሾም ቀኖናችን ውጭ  ከጫና አልፎ በወታደር መንበረ ጵጵስና ለመገልበጥ ደም እስከማፍሰስ ደርሶ ኦርቶዶክስን ስላገለለ፣ ኦርቶዶክሳውያን በአገራቸው የፖለቲካ ሥልጣን እንዳይሳተፉ በመደረጉ፣ ላለፉት ፰ ዓመታት ለተካሄዱት ግፎች ሁሉ ፍትህ ስለነፈገን፣ ፍጅቱን ለማስቆም ፈቃደኝነት ስለሌለው እና የእረኝነት  ኃላፊነት እንዳንወጣ እንቅፋት ስለሆነብን ሁሉንም የአገር ውስጥ መንበረ ጵጵስና ዘግተን መፍትሔ እስክናገኝ በገዳም ተወስነናል በሉ፤

(፭) 👉  ለእስልምና ምክር ቤት፣ ገዳ ለሚባሉ ሽማግሌዎች፣ ለሁሉም እምነቶችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁሉ የተደራጀውን መረጃ በሸኝ ኦፊሴላዊ ደብዳቤ በመላክ መንግሥት የክርስቲያኖችን ደኅንነት እንዳያረጋግጥ ቀግልጽ ጫና በማድረግና በታወቀ የግዜ ገደብ አዎነታዊነታቸውን እንዲያሳዩ ጠይቁ፤

(፮) 👉 አሁን እልቂት የሚፈጸምባቸው አርሲና ወለጋስ በካል ሄደው በማጽናናትና አዲስ አበባ ባንክ ያጨናነቀውን ገንዝብ እርዳታ ይስጡ፣ ለዓለምም የመልሶ መቅቋምና አጥቂዎችንን በማውገዝ የድጋፍ ጥሪ ያቅርቡ፤

(፯) አባቶች ከአስተዳደር ሥራ ይውጡና ለባለሙያ ይስጡ፣ በመንፈሳዊ አገልግሎት ይወሰኑ፣ 

(፰) ለሞቱት ክርስቲያኖች የሰማዕትነት ዕውቅና ይስጡ፣ የክብር ቀን የወሰንላቸው፣ ስንክሳር የዘጋጅላቸው፣ በመላው ዓለም በአንድ ዕለት ይከበር፤

(፱) ሊቃውንትን በእቅድ በማዝመት በዘር ፖለቲካ የተከፋፈለውን የጥምቀት ልጆችን የሚሰብስብ የትምሀርት ዘመቻ ያድርጉ፤ በዘር ፖለቲካ ተሳትፎ ወንድሙን የሚጠላውን ሁሉ አውግዘው ይለዩ፣

(፲) በገዳም ተወስነን ልጆቻችንን በጸሎት፣  የመረዳዳትና ራስን የመከላከል፣ የቡራኬ አገልግሎት ጦማሮችን በመላክ ስለምናገለግላችሁ ከዛሬ ጀምሮ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን።፣ በካህናት፣ በተፈተኑ ፅኑ ቆራቢያን ክርስቲያን ምእመናን አንድነት እየተመራችሁ ሀገራችሁንና ቤተ ክርስቲያናችሁን ከመጥፋት እንድትታደጉ ጥሪ እናቀርባለን ቡሉና ከእሥር ፍቱን፤

ይህን በዚህ በጥቅምት ጉባኤ ሳትወስኑ ብትበተኑ ላለፉት ፰ ዓመታት እንዳስፈጃችሁን ፱ኛውንም ዓመት በዓላት በማድመቅ፣ ሕንፃ በመመረቅ፣ ገዳዮቻችንን በመሸለም ልትቀጥሉ እንደወሰናችሁ እንቆጥራለን? ቤተ ክርስቲያንን ለሚያጠፋ ሥርዓት ደጋፊና አጋፋሪ ብቻ ሆናችሁ #ለመቀጠል #ፍላጎት #እንዳላችሁ #ታረጋግጣላችሁ።

=======================

የዚህን 2 ቀን የእልቂት ዜና እያደመጣችሁ በማይጠቅምና ሞት በማያስቀር አጀንዳ አትድከሙ። #የአርሲ #እልቂት #ናሙና👇👇👇👇👇

በሽርካ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ በተመለከተ

በቀን 14/2/2019 ዓ.ም በአርሲ ዞን ሽርካ  በቢርቦና ጮሌ  በተፈጸመው ጅምላ ጭፍጨፋና ውድመት
👉 ለጊዜው የ46 ሟቾች ስም ዝርዝራቸው ደርሶኛል (ገና  ያልደረሰኝ አለ  )
👉ከተገደሉት መካከል 25ቱ የኦሮሚያ ክልልዊ መንግሥት መዋቅር በሚመራው በሪጴ ሎላ(ሽምቅ ተዋጊ) የተጨፈጨፉ ናቸው

👉25 ለከፍተኛ አካላዊ ጉዳት ተዳርገዋል 

👉 ከ20 ቤቶች ወድመዋል
👉ብዙ እንሰሳት ተዘርፈዋል መውሰድ ያልቻሉን ጨፍጭፈዋል

1 ቃል ኪዳን ከፋለው  እድሜ 25
2 ምህረት ከፋለው    = 12
3 ቃል ኪዳን ደምሱ   = 12
4 ዳኒ  ታከለ  ከበደ    = 25
5 ከበደ ታደሰ ብሩ    = 50
6 ትርንጎ   ሲሳይ   =    45
7  ኤፋሬም ተፈሪ ዓለሙ =30
8 ሸዋን ግዛው ደጀኑ ዋቅ ቶላ =42
9 አባይ ተስፋዬ ተሰማ=45
10 ማቴዎስ ላሌ  =35
11 ውድነህ ዘውዴ በላቸው =75
12 ከበደ ማንደፍሮ ቦካን=  60
13 ሙላቱ ተሾመ ቦካን=50
14 አምዴ በሌይ ሁን=85
15 ግርማ ዓለሙ ብሩ =45
16 ከፋለው ዓለሙ  ብሩ =60
17 በጋሻው ቦጋለ =40
18 አብርሃም ስሜ ከበደ=24
19 ቀለሟ አበራ =60
20 ምናለ ጌታሁን ኃ/ማርያም45
21 ደመቅ እሸቱ ቦካን=50
22 ዘለቀ ጥላሁን እሸቱ =ቦካን
23 እንዳለ ጸጋዬ አሰፋ=42
24 ወንድሙ ለገሠ ዱላ=60
25 አባት ከበደ ታደሰ=4
26 ታመነ ታደሰ በየነ =60
27 በቀሉ ዳዲ=40
28 አበበ ጌታቸው  ዘውዴ=50
29 ባቢ ታመነ ታደሰ=10
30 ይልማ ወ/ሰንበት =70
31 ንጉሤ ማንደፍሮ ቦካን=65
32 መብራት ጌታቸው  =50
33 ገበየሁ አሳምን =35
34 ታመነ ጌታቸው=40
35 ፍራኦል ይስሙ አጥናፌ=25
36  አባይ ጌረደው ፈዬ=50
37 አቡ ደጉ ካሳ= 48
38 ታደሰ ደስታ= 80
39 አጥላው አምዴ= 39
40 መኩሪያ ሰብስቤ 45 (ሶሌ ዲገሉ ቀበሌ የሶሌ መድኃኔ ዓለም ጥበቃ)
41)መስፍን ተመነ =58
42)ወሰኔ አበራ  = 53
43)ሀና ጌታነህ=15
44)መቅደስ ከፋለው=18
45)ተሾመ መልሴ =64
46)አቢቲ ተክሌ= 32

 በጅምላ ጭፍጨፋውበፊት የነበሩ ሁኔታዎች፦

፩ "ኦርቶዶክስ የሆነ ሁሉ ፋኖ ነው" የሚሉ የሐሰት መረጃዎች ከመንግሥት ባለሥልጣናት ፍቃድ በማኅበራዊ ሚዲያ እንዲሰራጩ ተደረገ በየመስጊዱ እንዲነገር ተደረገ

፪ የሪጴ ሎላ(ሽምቅ ተዋጊ) አዛዥ ወደ ዞኑ ደውሎ ሽርካ ላይ 100% ሸኔ(ኢስላማዊ ታጣቂዎች) የሉም አሁን እያስቸገረ ያለው የኦርቶዶክስ ፋኖ ነው ያው ሕዝቡ ማለት ነው ስለዚህ  ጠንካራ እርምጃ እንድንወስድበት አዲስ ኀይል እንድትልኩልን ሲል ሪፖርት ሲያደርግ ነበር

፫  ኦርቶዶክሳውያንን ሲያስጨፈጭፍ የነበረው  የጨፌ ኦሮሚያ  አባል የነበረው አብደላ አማን(አብደላ ማይክሮ)   በአክራሪነት ከሚታወቁ ሰዎች ጋር በመሆን ሪጴ ሎላዎችን ሲገብዙና ሲያወያዩ ነበር

፬ ወደ ቢርቦና ጮሌ ለአራጆቹ የሚሆኑ ለስላሳና የተለያዩ ቁሳቁሶች ሲጓጓዙ ነበር

፭  በዕለተ ዐርብ የወረዳው ዋና ከተማ በሆነችው በጎቤሣ ከተማ በሚገኝ መስጊድ ውስጥ  ዑዝታዞች የጥቃት ዕቅድ መኖሩን የሚያሳይ ንግግሮችን ያደርጉ ነበር

በጭፍጨፋው ጊዜ፦
👉ሪጴ ሎላ ከአክራሪዎች ጋር ሆኖ ይገድል ነበር
👉 ሙስሊም ገበሬዎች ከሙስጊድ ውስጥ ሆነው ወደ ኦርቶዶክሳውያን ይተኩሱ ነበር

ከጭፍጨፋው በኋላ ፦
👉ከመሸ መከላከያ ወደ ወረዳው የገባ ቢሆንም እስከ ዛሬ 15/02/2019ዓ.ም ከሰዓት ድረስ የትም ቦታው አልተንቀሳቀሱም ነበር ።ከሰዓት ወደ ቦታው የተንቀሳቀሰው መከላከያ  ለ አንድ ሰዓት እንኳ ሳይቆይ ነው የተመለሰው
 (ዜናው ከዚህ ገጽ የተገኘ ነው👇
https://t.me/Eyo21e






አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...