በሞዐ ተዋህዶ ስም ሊቃውንትና ኦርቶዶክሳውያን አርበኞችን አድኖ መግደል የማን ፕሮጄክት ነው?
ኦርቶዶክስን ዒላማ የሚያደርግ ንቅናቄ ከ1960ዎቹ ባልተለይ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሲካሄድ የኖረውን የ55 ዓመታት ሁለገብ ጥቃት በሚያስቀጥል መንገድ የሚጠናቀቅና መጭውን ስነ-ምንግሥት እንደተለመደው ጸረ-ኦርቶዶክስ አድርጎት እንዳይቀጥል --- የፋኖ ሠራዊትና የአማራ ሕዝብ፣ በሌላም መንገድ ትግሉን የምትደግፉ ሁሉ ልትመክሩበት፣ በትግሉ መካክለ ያቆጠቆጠውን ጸረ-ኦርቶዶክስ ኃይል እንደሚገባ እንድትገሩት (እንደታስተካከሉት) እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ የአንዲት የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አካል ብልት ጥሪዬን አቀርባለሁ።
በፋኖ መካከል ፀረ-ኦርቶዶክስ ችግኝን ያበቀለው ማነው?
በአጭሩ ግን ያለኝ ጥሪ ፦ ሁሉንም ከጫጫታና ከብልጣብልጦቹ ፕሮፓጋንዳ ነፃ ሆኖ በማሰብ ጥያቄዎችን የመልስ። ቲፎዞነት፣ ጭፍን መንጋነት፣ ስሜታዊነት ለአገር፣ ለቤተ ክርስቲያን፣ ለትውልድ ዘለቄታዊ ሰላም አይበጅም። ይህ የቼልሲ የኳስ ጨዋታ አይደለም።
ይህ ሕይወት የሜከፈልበት፣ ከሁሉም በላይ የሰማይርስታችን መግቢያ መረከብ ቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተቃጣና በውጭ ጠላት ምክር "በምሥራቅ አፍሪካ የክርስቲያን ጽንፈኝነት ያሰጋናልና መሰቀላችሁን ከአንገታችሁ አውልቁ" በማለት ለተላላኪዎቻቸው ተዕዛዝ በመስጠት ያሰጀመሩት አደገኛ ፀረ-ኦርቶዶክስ ንቅናቄ መሆኑን ሁሉ ክርስቲያን ይወቀው።
#በሞዐ #ተዋህዶ ስም ሊቃውንትና ኦርቶዶክሳውያን አርበኞችን አድኖ መግደል የማን ፕሮጄክት ነው?
ኦርቶዶክስን ዒላማ የሚያደርግ ንቅናቄ ከ1960ዎቹ ባልተለይ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሲካሄድ የኖረውን የ55 ዓመታት ሁለገብ ጥቃት በሚያስቀጥል መንገድ የሚጠናቀቅና መጭውን ስነ-ምንግሥት እንደተለመደው ጸረ-ኦርቶዶክስ አድርጎት እንዳይቀጥል --- የፋኖ ሠራዊትና የአማራ ሕዝብ፣ በሌላም መንገድ ትግሉን የምትደግፉ ሁሉ ልትመክሩበት፣ በትግሉ መካክለ ያቆጠቆጠውን ጸረ-ኦርቶዶክስ ኃይል እንደሚገባ እንድትገሩት (እንደታስተካከሉት) እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ የአንዲት የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አካል ብልት ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ሥጋቱ የሚታያችሁ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ ይህን ጥሪ በተሻለ መንገድ አብራርታችሁ በማስተጋባት በፋኖ መካከል የተሰነቀረውን ጸረ-ኦርቶዶክ ንቅናቄ በማጋለጥ ሕዝቡ እንዲቆጣጠራቸው እንድትጠቁሙት እጠይዋለሁ።
ከአማራ የህልውናና የፍትሕ ተጋድሎ ውስጥ እንዴት ጸረ-ነባርነት ሊበቅል ቻለ? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ዕለታት የሚፈጅ ጥናት አይጠይቅም።
ከ1960ዎቹ የጸረ-ኢትዮጵያዊነት፣ የጸረ-ኦርቶዶክስ ክርስትና፣ ከጸረ-አማራነትናና በአጠቅላይ ሲነነገር ከጸረ-ነባርነት ንቅናቄዎች ጀምሮ የለውጥ ንቅናቄዎችን የሚታዘብ ሰው እና የፋኖን ትግል አጀማመር የሚያውቅ ሁሉ እውነተኛ ከሆነ በቀላሉ የሚመልሰው ጥያቄ ነው።
ማንኛውም በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ፣ ነጻነት፣ እኩልነት፣ ራስን በራስ ማስተዳደር የሚሉ ውብና አጓጊ ቃላትና የመታገያ መፈክሮች ይዘው የተነሱ ሁሉ አንዳቸውም የሚሉትን ለማምጣት አገር-ፍልቅ ዕውቀትን፣ እሴቶችን፣ ማኅብራዊና መንፈሳዊ ትቋማትን፣ ነባር ስነ መንግሥትን እና የሕዝብን የዘመናት መስተጋብራዊ ውህደት ሳይቃረኑ ያመጡት አዲስ የፅንሰ ዐሳብ፣ የፍልስፍና፣ የጠቃሚ ርዮትና የትግል መርህ አምንጭተው አያውቁም። ሁሉም ትግላቸውን የሚጀምሩትም የሚፈጽሙትም በሚከተሉት ኢትዮጵያዊ እሴቶችና ሀብታት ላይ በመዝመት ነው።

ሁሉ ንቅናቄዎች በጋራ የሚታወቁበት ዋና ዋና ጉዳዮች፦
(1)-- ሁሉም የኢትዮጵያ ኦቶድክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ፣ ታሪክ፣ ማኅበራዊ ተጽእኖ፣ የፍትሕና የአስተዳድር አሻራዎችና አገራዊ ተሳትፎ ለማክሰም አብዝተውና በርትተው ይደክማሉ፤
(2)-- ሁሉም አማራነትን (ርዥም የጋራ አገራዊ ታሪክ ትርክት፣ ፍትሕ፣ ክብረ ስብእ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር፣ የጽሑፍ ምስክርነት፣ ቅርሥና ውርስ፣ ርስት፣ አንድነት፣ ነጻነት፣ ማኅበረሰባዊ የሕብር ተመጋጋቢነትና ውህደት) እና የማራነት እሴቶች፣ ታሪክ፣ የአገርና የሕዝብነት ፅነሰ-ዐሳብ ተጋሪ ማኅበረሰቦችና ተቋማትን እንደ ጠላት ይፈርጃሉ፤
(3)-- ሁሉም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍትን፣ ታሪክን፣ ቅዱሳን፣ ተያያዝ ስነ ምንግሥታዊ ትርክቶችን፣ ነገሥታትን በማጥልሸት ይተባበራሉ፤
(4)-- ሁሉም ኢትዮጵያን ለርዥም ዘመናት በቀጥታና በተዝዋዋሪ፣ በጦር መሳሪያና ትውልድን በጸረ-አገር አስተምህሮ ዓእምሮ በማጠብ፣ በቀይ ባህርና በአባይ ወንዝ ምክንያት፣ በሃይማኖት ምክንያት፣ በድንበር ይገባኛል ውዝግብ ሲውጉ ከኖሩት ጋር የወዳጃሉ፣ ይተባበራሉ፤
(5) ሁሉም የኢትዮጵያን የሃይማኖት፣ የታሪክ፣ የቅርሥ፣ የስነ-መንግሥት፣ የሕዝብ አሰፋፈር፣ የአገር ሉዓላዊነት አንድነት፣ ከዘመነ ምሳፍንት ወዲህ ለአገር አንደነት የደከሙ የፄ ዮሐንስ፣ ቴዎድሮስ፣ ምንልክ፣ ኃይለ ሥላሴን አዎንታዊ አስተዋጾ በምካድና ስሕተቶችን ወይንም በፈጠራ በሚያመነጩት ክስ በማጠልሸት አንድ ናቸው፤
(6) ሁሉም “አንድ አገር፣ አንድ ሕዝብ” በተዋህዶ ጽንቶ እንዳይኖር ከውጭ ጠላት በከፋ ወገንን በቋንቋ እና በአካባቢያዊ ነጠላ ትርክክቶች በመከፋፈልና በማጋጨት፣ አገር በመገንጥልና በማስገንጠል፣ አማራና ኦርቶዶክስ ክርስቲያንን በማሳደደ የተባበራሉ።
ከእነዚህ አፍራሽና አሁን ለምንገኝንበት የእልቂት፣ የስደትና የአግር መፍረስ ሁኔታ ያደረሰንን ፖለቲካዊ አቅጣጫ በመቃወም፣ ይህ አቅጣጫ የህልውና አደጋ ደቅኖብኛል በሚል የተነሳው የአማራ ሕዝብ የህልውናና የፍትሕ ተጋድሎ ጫፍ ፋኖ እና ፋኖ ብቻ ነው።
ይሁንና በፋኖ ውስጥ ነባር ጠልነትን ከቀዳሚዎቹ የህልውና አድጋ አምጭዎች በመቅዳት መልሰው የተክሉ ቡድኖች አሉ። የእነዚህ ቡድኖች መገለጫዎች ፋኖነትን የሚቃርን፣ የአማራን እሴት የሚንድ፣ የህልውና አደጋውን የሚያጠናክርና የማራን ተጋድሎ ብቻ ሳይሆን አገሪቷንና ሌሎቹን ማኅበረሰቦች፣ በተለይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ለህልውና አደጋ የሚያጋልጥ ሆኖ ታይቷል፦
(1)—እገሌ ወይንም የተወሰነ ቡድን “ሞዐ ተዋህዶ ነው” በሚል ፍረጃ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት፣ መምሀራንን፣ የአብነት ተማሪዎችን፣ የፋኖ መሪዎችና አርበኞችን እያሳደደ ስም የሚያጠፋና የሚገድል ቡድን፤
(2)---እኔ ካልንገሥኩ፣ እገሌ ከተባል የውጭ አገር አካል ጋር ካልተባበርኩና ትዕዛዞቻቸውን ካልተቀብለኩ የፋኖን አደረጃጀት አንድነት አልፈቀድም በሚል አንድነቱን ሲያደናቀፍ የኖር፣ አሁንም የሚሞክር፤
(3)--የህልውና አደጋ ምንጭ የሆኑ ርእዮቶችን በመከትል፣ መርዛማ የሐሰት ትርክት በማመንጨት፣ አማራን ከአገራዊ ተሳትፎ በማግለልና ከፋፋይ ሕጎችና ፖሊሲዎችን በመደንገግ፣ የጎሣ ሠራዊትና መዋቅር በመዝርጋት፣ ኢትዮጵያን በመቆራርስና በምፋፈራረስ፣ አማራን ከጎዴ እስክ ሁመራ፣ ከጋንቤላ እስከ ራያ በማፈናቀልና በመግደል፣ በማምከንና በበሽታ በማስጠቃት፣ በማደኽየትና ርስት በማሳጣት በመጭረሻም ግልጽ የጅምላ ጭፍጭፋ ከሚያካሄዱ አካላት ጋር --ምንም አይነት የፖለቲካ ርዮታቸውን፣ የተመሠረቱበትን አገር የመገነጣጠል ግባቸውን በአደባባይ መተዋቸውን ሳያውጁ፣ አማራን ዒላማ ያደረገውን ለ55 ዓመታት የንዙትን መርዛማ አሉታዊ ትርክቶቻቸውን መልሰው ሳይውጡና ይቅርታ ሳይጠይቁ “የአማራ የህልውና እና የፍትህ ተጋድሎ አጋሮቻችን ናቸው” በሚል ለአማራ ሕዝብ የመስዋእትነቱ ዋጋ እንዴት እንደሚከፍለ ግልጽ ለማድረግ ፈቃደኛ ያልሆኑ፤
(4)-- በ3ኛ ደርጃ የተገለጸውን አሉታዊ ጉድኝት የሚቃወሙ በመምሰል፣ ግልጽ አማራጭ መንገዶችን፣ የተቃውሞ ምክንያቶችን፣ አዋጭ ስልቶችን ሳያቀርቡ በተለመደው ፕሮፓጋንዳ ትብብሩን የሚደግፉትን የሚያሳድዱ፤ በአመክንዮአዊ ተጠየቅ ከመከራከርና ሁሉን አሰባሳቢ አማራጭ ከማቅረብ ይልቅ ለከፋፋይነትና ለጥቃት የሚተቀሙ የታጋዮች መሪዎች፤
(5)-- ልጆቹን፣ ህብቱን፣ ሕይወቱን ጭምር በመስጠት የህልውና ተጋድሎው ላይ የሚሳተፈውን የማራ ሕዝብ፣ የጥቃቱ ዒላማ ሆና በሁሉም ዘርፍ መከራ የምትቀበልዋን ቤተ ክርስቲያን ያቆሙ ሊቃውንትን፣ አባቶችን፣ ገዳማውያንንና ማኅበረሰቡን ከ1960ዎቹ ንቅናቄዎች ባልተናነሰ “በተጋድሎአችህ ሂደትና ውጤት እናንተን አያገባችሁም” በሚል መንፈስ መረጃ መንፈግ፣ የእሴት ተሳትፎ መገደብ ላይ የተጠመዱ፣ ነገር ግን ክርስቲያኑን ለማስተባበር የማያምኑበት መስቀል አንገታቸው ላይ አንጠልጥለው ፎቶ የሚነሱ፣ ኦርቶዶክስ-ጠሎቹ ባእዳን ሲገላምጧቸው የራሳቸውን መሰቀል ከመደበቀ አልፈው ሌላውን ባለመስቀል “ሞዐ ተዋህዶ” በማለት የሚያሳድዱ፤ ----
---- በግልጽና ሊደበቅ በማይችል ደረጃ በፋኖዎች መካክለ ይታያል።
ይህ ኦርቶዶክስን ዒላማ የሚያደርግ ንቅናቄ ከ1960ዎቹ ባልተለይ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሲካሄድ የኖረውን የ55 ዓመታት ሁለገብ ጥቃት በሚያስቀጥል መንገድ የሚጠናቀቅና መጭውን ስነ-ምንግሥት እንደተለመደው ጸረ-ኦርቶዶክስ አድርጎት እንዳይቀጥል --- የፋኖ ሠራዊትና የአማራ ሕዝብ፣ በሌላም መንገድ ትግሉን የምትደግፉ ሁሉ ልትመክሩበት፣ በትግሉ መካክለ ያቆጠቆጠውን ጸረ-ኦርቶዶክስ ኃይል እንደሚገባ እንድትገሩት (እንደታስተካከሉት) እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ የአንዲት የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አካል ብልት ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ሥጋቱ የሚታያችሁ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ ይህን ጥሪ በተሻለ መንገድ አብራርታችሁ በማስተጋባት በፋኖ መካከል የተሰነቀረውን ጸረ-ኦርቶዶክ ንቅናቄ በማጋለጥ ሕዝቡ እንዲቆጣጠራቸው እንድትጠቁሙት እጠይዋለሁ።
ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።። 1) ሻሸመኔ ከተማ I. የተገደሉ 1. አያሌው ተረፈ ● በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ● ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ● በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ● በ ጥር 30 2015 ዓ/ም ሰማዕትነትን ተቀብሏል 2. ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ● የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ● በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ● ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ● በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም ሰማዕትነትን ተቀብለዋል። 3. ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ● የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ