ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ከኦክቶበር, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጳጳሳት ከፈለጉ የኦርቶዶስ ክርስቲያኖች እልቂትን ማስቆም ይችላሉ

ለጳጳሳት ካልለገማችሁ በስተቀር ሥርዓታዊ የክርስቲያን ፍጅቱን ማስቆ  ትችላላችሁ‼️ ===================== እንዴት❓ ይኼው ምክረ ሀሳብ፦ ጳጳሳት ሥርዓታዊውን የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ዜጋ ዘር የማጥፋቱን ያፈጠጠ ያገጠጠ ሂደት በጉባኤቸው የሚከተሉትን በመወሰን ማስቆም ትችላላችሁ:- (፩)👉 ከአጥቢያ ጀምሮ በክርስትናቸው በመንግሥት መዋቅ ግብር የተጨመረበት፣ ግፍ ተፈጽሞበት ፍትሕ የተነፈገ፣ የተፈናቀለ፣ የተገደለ፣ ንብረት የተቀማ ከ፩-፪ ሳምንት ውስጥ ማሰባሰብ፤ በቀጣይ ፪ ሳምንት ውስጥ ማሳተምና ለዓለምና ለምእመናን አሰራጩ፤ (፪) 👉 "የክርስቲያን ሁለገብ (ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርሥ፣ ማኅበራዊ መዋቅር፣ ኢኮኖሚ፣ በአካል መግደል፣ ማምከን፣ ማፈናቀል፣ ጅምላ ፍጅት፣ ፍትሕ መንፈግ) ዘር የማጥፋት ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ፕሮጄክት ተዘርግቶ ፍጅት እየተፈጸመብን ነው" መግለጫና የድረሱልን ጥሪ ለመላው ዓለም አግባብነት ላላቸው ተቋማትና መንግሥታት ኦፊሴላዊ ጥሪ ከማስረጃው ጋር አያይዛችሁ  ጠይቁ፤  (፫) 👉 በመላው ዓለም የተሰራጨው የኦርቶዶክስ ምእመንና አጥቢያ ሁሉ ቸዘር ማጥፋት መከላከል ግብረ ኃይል በመመሥረት የሁለገብ ዘር ማጥፋቱይ መረጃ በመያዝ ከሕግ ባለሙያ፣ ከወትዋቾችና ከዲፕሎማቶች፣ ከሌሎች አቢያተ ክርስቲያናት ጋር ንቅናቄና ክስ መመሥረት እንዲችሉ ትዕዛዝ ስጡ፤ (፬) 👉 መንግሥት ያወገዝነውን ከአጥቢያዎቻችንና ከገዳሞቻችን ስለማያግድ፣ በጎሳ እንደንሾም ቀኖናችን ውጭ  ከጫና አልፎ በወታደር መንበረ ጵጵስና ለመገልበጥ ደም እስከማፍሰስ ደርሶ ኦርቶዶክስን ስላገለለ፣ ኦርቶዶክሳውያን በአገራቸው የፖለቲካ ሥልጣን እንዳይሳተፉ በመደረጉ፣ ላለፉት ፰ ዓመታት ለተካሄዱት ግፎች ሁሉ ፍትህ ስለነፈገን፣ ፍጅቱን ለማስቆም ፈቃደኝነት ስለ...

ሲኖዶሱን ከዓለማዊነት ሰመመን በመቀሰቅሱ እንተባበር

ሲኖዶሳችንን ከገባበት ዓለማዊ ሰመመን እንቀስቅስ በአሁኑ ግዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ እና የመፍትሔ ጥቆማ   ሀ. በውስጥ   1. የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ መሥፈርት ከክርስትና ቀኖና እየራቀ ወደ ጎሳ የማንነት ፖለቲካ አዘንብሏል፤  2. ኤጲስ ቆጶስነት ለአገልግሎት በቤተ ክርስቲያን አስገዳጅነት ለተምረጡ አብቶች የሚሰጥ መሆኒኡ ቀርቶ በደጅ ጥናት፣ በእጅ መንሻና በመኳንንት ድጋፍ የሚፈለግ የድሎት ቦታ ሆኗል፤   3. ካህናት አስተዳደግና አሿሿም፣ ስምሪት እና መዋቅራዊ ክትትሉ ከግል ጥቅም ካር የተቆራኝ ሆኗል፤  4. ዝሙት፣ ፍቅረ ንዋይ፣ ዘረኝነት፣ አድርባይነት እና ድሎት ማሳደድ ሥር እየሰደዱ ናቸው   5. ምእመናን ዘመኑን የዋጅ አገልግሎትና ጥበቃ በማጣታቸው አሕዛባዊ ሕይወት ተለማምደዋል፦ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ውርጃ፣ ዘረኝነት፣ ንፍገት፣ ኢፍትሐዊነት፣ መገዳደል ተስፋፍቷል፤ 6. ኑፋቄና ክህደት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምእመናንን አፍልሷል   ለ. በውጭ   1. ላልፉት 60 ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የተቀነቀነው ፖለቲካ የኦርቶዶክስ ክርስትና ጠል መሆኑና የትውልዱን ክርስቲያናዊ ዝንባሌ በተቃራኒው እንዲቆም የትምህርት፣ የመዋቅር፣ የስነ ልቦና ጥቃት እየፈጸመ መቀጠሉ፤   2. ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያን ዜጎች የመንግሥትና የተለያዩ የነገድ ነጻ አውጭዎችና የውጭ-ገብ ጽንፈኛ እምነቶች የጥቃት ዒላማ በመሆን ከእምነት መፍለስ፣ መፈናቀል፣ መደኸየ፣ ከሀገራዊ ተሳትፎ መገለል መዋቅራዊና ሥርዓታዊ መሆኑ።   1. የቀደሙት ቅዱሳን ጳጳሳት ምን ይመስሉ ነበር? እንደ ቅዱስ አትናቴዎስ፣ ቅዱስ ቄርሎስ፣ ቅዱስ ያሬድን ያስተማ...

ፀረ-ኦርቶዶክስ ችግኝ በፋኖ መካከል እንዴት በቀለ?

በሞዐ ተዋህዶ ስም ሊቃውንትና ኦርቶዶክሳውያን አርበኞችን አድኖ መግደል የማን ፕሮጄክት ነው? ኦርቶዶክስን ዒላማ የሚያደርግ ንቅናቄ ከ1960ዎቹ ባልተለይ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሲካሄድ የኖረውን የ55 ዓመታት ሁለገብ ጥቃት በሚያስቀጥል መንገድ የሚጠናቀቅና መጭውን ስነ-ምንግሥት እንደተለመደው ጸረ-ኦርቶዶክስ አድርጎት እንዳይቀጥል --- የፋኖ ሠራዊትና የአማራ ሕዝብ፣ በሌላም መንገድ ትግሉን የምትደግፉ ሁሉ ልትመክሩበት፣ በትግሉ መካክለ ያቆጠቆጠውን ጸረ-ኦርቶዶክስ ኃይል እንደሚገባ እንድትገሩት (እንደታስተካከሉት) እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ የአንዲት የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አካል ብልት ጥሪዬን አቀርባለሁ። በፋኖ መካከል ፀረ-ኦርቶዶክስ ችግኝን ያበቀለው ማነው? በአጭሩ ግን ያለኝ ጥሪ ፦ ሁሉንም ከጫጫታና ከብልጣብልጦቹ ፕሮፓጋንዳ ነፃ ሆኖ በማሰብ ጥያቄዎችን የመልስ። ቲፎዞነት፣ ጭፍን መንጋነት፣ ስሜታዊነት ለአገር፣ ለቤተ ክርስቲያን፣ ለትውልድ ዘለቄታዊ ሰላም አይበጅም። ይህ የቼልሲ የኳስ ጨዋታ አይደለም። ይህ ሕይወት የሜከፈልበት፣ ከሁሉም በላይ የሰማይርስታችን መግቢያ መረከብ ቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተቃጣና በውጭ ጠላት ምክር "በምሥራቅ አፍሪካ የክርስቲያን ጽንፈኝነት ያሰጋናልና መሰቀላችሁን ከአንገታችሁ አውልቁ" በማለት ለተላላኪዎቻቸው ተዕዛዝ በመስጠት ያሰጀመሩት አደገኛ ፀረ-ኦርቶዶክስ ንቅናቄ መሆኑን ሁሉ ክርስቲያን ይወቀው። #በሞዐ #ተዋህዶ ስም ሊቃውንትና ኦርቶዶክሳውያን አርበኞችን አድኖ መግደል የማን ፕሮጄክት ነው? ኦርቶዶክስን ዒላማ የሚያደርግ ንቅናቄ ከ1960ዎቹ ባልተለይ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሲካሄድ የኖረውን የ55 ዓመታት ሁለገብ ጥቃት በሚያስቀጥል መንገድ የሚጠናቀቅና መጭውን ስነ-ምንግሥት እንደተለ...