ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

አማራን ተሸናፊ - ኦርቶዶክስን ጠፊ ለማድረግ ሞዐ ተዋህዶን ግበረ ኃይል እንደ ጦስ ዶሮ ያቀረበው የፋኖ የውስጥ ጠላት


#አማራን #ተሸናፊ - #ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን #ጠፊ ለማድረግ #ሞዐ ተዋህዶን ግበረ ኃይል እንደ #ጦስ #ዶሮ ያቀረበው #የፋኖ #የውስጥ #ጠላት ይጋለጥ!! ማነው? ለምን ዓላማ? እያልን እጠይቅና መልሱን እናግኝ። እንደ ቦይ ውሃ ወዳፈሰሱን አንፍሰስ!!! በሽታውን ያልተናገረ መድኅኒት አያገኝም። እውነቱን መረዳት የምትፈለጉና የዩቲዩብ ቅንጨብጫቢ የሤራ ፕሮፓጋንዳ ግራ ያጋባችሁ ታግሣችሁ አንብቡት። ================== #ፋኖነትን #ከሽፍትነት እና ከጠላት ተላላኪነት አጥርቶ የማውጣት ተጋድሎ ከፊታችን ቆሟል! ማስመስልና ብልጣብልጥነት፣ ቁማርና ሤራ ከፋኖነት እሴቶች ሁሉ ተቃራኒ ነው። በቀላሉ የፋኖን ስሙን ሳይሆን ግብሩን አይቶ ሽፍታውን፣ ሠርጎ ገቡን፣ ሌባውን፣ ተላላኪውን፣ ባንዳውን መለየት ይቻላል። ፋኖ ያልሆኑ የስም ፋኖዎች መለያ ተግባሮች፦ 👉ሐሰተኝነት፣ 👉ሤረኝነት፣ 👉ማጋጨት፣ 👉 ከአማራ እና ከአገር የህልውና ጠላቶ ጋር መጣመር፣ 👉 ንጹሕ ደም በርሸና ማፈሰስ፣ 👉 በወገን ሞት መካከል ሀብት ማግበስበስ፣ 👉 ጎጠኝነትና የአንድነት እንቅፋትነት፣ 👉 ፈሪነት፣ 👉 የባዕዳን ተመካሪነት፣ 👉 ፍረጃናና የሐስት ክሶች መፍጠር፣ 👉 እጅ መስጠት፣ 👉 በሌሎች ታጋዮች ላይ አደጋ መጣል፣ 👉 ጀግኖችን መግደል፣ 👉 እሰከ ውጭ አገራት ድረስ በሐሰት መረጃ ወገንን ማሳሳት፣ 👉 ገንዝብና ሎጂስቲክ በፍትሓዊነት እንዳይዳረስ ማድርግ --- የመሳሰሉትን የሚያደርግ ግለሰብ፣ ቡድንና አደረጃጀት ሁሉ ፋኖ አይደለም፣ የፋኖም ወገን አይደለም። --- ሌላ ነገር ነውና #ሠራዊቱ ይጠንቀቅበት!!! #ፋኖ ራሱን በራሱ እንዲያጥፋ --- ሰይጣን አዲስ መላ መቷል። የፋኖ ሠራዊት ሞቱ፦ 👉 ከክርስቶስ ሞት እንዳይተባበርለት፣ 👉 እውነቱ የእግዚአብሔር እንዳይሆን፣ 👉 ትግሉ በፈቃድ እግዚአብሔር፣ በፈሪሃ እግዚአብሔር፣ በክብረ-ሰብእ፣ በፍትሕ እና በአገራዊ አንድነት እንዳይመራ --- ---- በሤራ በተለይ ራሱን ኦርቶዶክሳዊ ክርስትናን ጠላት አድርጎ እንዲቆም በሴኩላሪዝምና ሌሎች "ትግሉ የሃይማኖት ጦርነት አድርገው ፕሮፓጋንዳ ይሠሩብናል" በሚል ስንኩልና መሠረተቢስ አምክንዮ የሚመስል ሽፍጠኝነትና የባእዳን ተመካሪነት እንዳያሸንፍ ደባ እየተፈጸመበት ይገኛል። ከእግዚአብሔር ተለይቶ ድል እንጀጀሌለ ሰይጣን ያውቃል። አሁን እንደምመለከተው ለአማራነት እና ለኢትዮጵያዊነት ጠላት ያፈራላቸው በኦርቶዶክሳዊነት ላይ የተመሠረቱ እሤቶቻቸው፣ ነባርና ሺዎች ዘመናትን የዘለቀው ከእግዚአብሔር ጋር የኖሩት ታሪካቸው፣ ለነጻነት የከፈሉት የክብረ-ሰብእ ምስክርነታቸው ነው። ጠላት ሆነው የተነሱት ተዋንያን እውነትን በሐሰት ለለውጥ፣ ፍትሕን ለማዛባት፣ ክብረ-ስብእን ለማርከስ፣ የሕዝብና ለአገር ሉዓላዊነትን ለመግሰስ ብዙ ደክመው የከሸፈባቸው ባዕዳን በምትካቸው እንዲያጠፉን በአምሳላቸውና በአራያቸው የፈጠሯቸው አገር በቀል ወራሪዎችና የባንዳ ልጆች ናቸው። አዲሱ የሰይጣን ወጥመድ እነዚህ የጠላት ተወካዮች ነቅንቀው ያመጡትን የጥፋት ጎርፍ በመገደብ የአግርና የሕዝብን ህልውና ለመታደግ የተነሱትን፣ ነፍሳቸውን አባቶቻቸው ለኖሩላቸው የክብረ-ሰብእ፣ የእነት፣ የክብረ-አገርና ሕዝብ፣ ለአንድነት እና በእግዚአብሔር ንግሥና ሥር የመኖር እሴቶችን ለመታደግ አሳልፈው በመሰጠት ጦርሜዳ የገቡትን የማራ ፋኖዎችን በማሳሳት የእሴቶቻቸው ምንጭ ብቻ ሳትሆን የንፍሳቸውም ዋስትና የሆነችዋን #ቤተ #ክርስቲያን እንዲዋጉ ማሳሳት ነው። ቤተ ክርስቲያንን የመውጋት ሤራ ግልጽ እንዳይሆን ሰይጣን የመረጠው አንድ የሐሰት ትርክት ሞዐ ተዋህዶ የተባለ ንቅናቄ በሚከተሉት ነጥቦች የአማራ የህልውና ትግል ጠላት ነው የሚለ ነው፦ 👉 አባላቱ ዳዊት ያነግታሉ፣ መስቀል ያንጠለጥላሉ፣ ጸሎት የጸልያሉ፣ 👉 አባላቱ የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች አንድ እንዳይሆን እንቅፋት የሆነው እርሱ ነው፤ 👉 ሞዐ ተዋህዶ በአገር ውስጥና በውጭ አገር በፋኖ ስም ገንዝብ ሰብስቦ እና እርሱን እንደ መሣሪያ በመጠቀም በእኛ ንቅናቂ ዕዝ ሥር የግድ መጋባት የኖርባቸዋል በማለት ፋኖን የከፋፍላል፤ 👉 ሞዐ ትዋህዶ የራሱ ድብቅ ማኒፌስቶ በማዘጋጀት የአማራን የህልውና ትግል ጠልፎ የሃይማኖት ትግል እንዲመስል በማድረግ በክርስቲያንና በሙስሊም መካከል አለመተማመንን ፈጥሯል፤ 👉 ሞዐ ተዋህዶ የብልጽግናና የሌሎች የማራ ጠላቶች ተልዕኮ ተሸካሚ ነው፣ 👉 ሞዐ ተዋህዶ እንደ መእዋቅር የሚንቀሳቀስና በፋኖ አደርጃጀቶች መካከል አለመጋባባት ሲከሰት ከማስታረቅ በተቃራኒ መለያየትን ያባብሳል፤ --- የሙሉ ከሶችን በከፍተኛ ትጋት ፈጥሮ እያሰራጭ የገኛል። ሰይጣ ምክሩን ለማጠናከር "ሞዐ ተዋህዶ ፋኖን የፈጠርኩት እኔ ነኝ" በማለት በፋንታሁን ዋቄ በኩል በሚዲያ ያሰነገርው ከድል በኋላ ለምናልመው የፖለቲካን የቤተ ክህነት ሥልይጣን ተገዳዳሪያችን ሆኗልና ምኝም ቢሆን ስሙን በማጠልሸት በአማራ ትግል ጠላትነት እናስፈረጅው የሚል እኵይ ዐሳብ የሚያመነጩ ጥቂት ሰዎችን መሣሪያ አድርጎ ከአገር ውስጥ እስከ ውጭ አገራት በጎጥና በቡድን መረባዊ ግኑኝነት አዝምቷል። ይህን ከሕውሃትና ከኦነግ በቀጥታ የተቀዳውን የሐስት ትርክት ፈብርኮ ሕዝብ በማሳሳት የወጣቱን የትግል መስዋዕትነት ለጥቂት ሰዎች ለዚያዉም ከትግሉ ዋና ዓላማ አስበልጠው የግል ጠባብ የሥልጣን ፍተወታቸውንና የአማራ የህልውና ጠላቶችን ተልዕኮ በተሸከሙ ሰዎች መጠቀሚያ በማድረግ ከንቱ ለማድረግ የተሰለፉ ግለሰቦች ናቸው። በዚህ መንግድ የሄዱት የሕወሃትና የኦነግ መሪዎች ያሳሳቱትን ሕዝብ በትርክት እሥረኝንት፣ በማይገባ ኢፍትሐዊ በሆን ምኞች በሌሎች ላይ ለመሠልጠን እንዲነሳሱ ማድረጋቸው መከራን እንጂ "ነጻነት" የተባለውን ትርጉሙ ያልታወቀ ማርክሲስት እስተሳስብ ውራጅ የአምሮ ባሮች ሃይማኖት መሰል ድንቁርና ያተረፈላቸው ሞትና ስደት፣ ርህብና እርዛት፣ አገርን አጥጦ በአንድ የዘር ጎረኖ መከተት ብቻ ነው። ይህንን የአማራ፣ የኦርቶዶክስ፣ የኢትዮጵያና የነባር እሴቶቻችን የህልውና አደጋ ያመጣውን የሤራ መንገድ ለመከተል የመረጠ ፋኖ ማወቅ ያለበት አግልግሎቱ ለአማራ ጠላቶች የሆናል፤ መስዋዕትነቱም ከንቱ ነው፣ ወጤቶም ህልውናንን ማርጋገጥ ሳይሆነ #ለሌላ #ዙር #የማይቀለብስ የህልውና አደጋ የተበደለውን ሕዝብና አገሩን ማድረግ ይሆናል። ስለዚህ እውነቱን ለማንሳት ማመንታት ይህን ግልጽ ጥፋት በዝምታ መመልከት ስለሚሆን በእኔ በኩል ማለባበስ እዚህ ላይ #አብቅቷል!!! 👉 ግልጽ የሆነው ጉዳይ --- የአማራ ፋኖን ሠራዊት መስዋዕትነት ከንቱ የሚያደርግ የጸረ-ኦርቶዶክስ ንቅናቄ በሞዐ ተዋህዶ ስም ተሸፍኖ የሚካሄድ የህልውና ተግሉ ጠላቶችና የጠላት ሠራተኞች በፋኖ መካከል የገኛሉ!!! ---- መርምሩ --- አትደንዝዙ --- ድማችሁና አጥንታችሁ ለጠላት መጠቀሚያ እንዳይሆን እንደሚገባ ፈትሹ!!! --- ሞዐ ተዋህዶ የሚባል በመዋቅር ደርጃ ተደራጅቶ ፋኖን የሚረብሽ ተቋም የለም!! 👉 እኔ የማረጋግጥላችሁ አንድ ነገር ቢኖርና መታወቅ ያለበት፦ --- ኦርቶዶክስ ላይ የሚካሄደውን መንግሥታዊ የዘር ማጥፋት ዘመቻ የተገነዘቡ እና ራሳቸውን እንደ አማራ፣ እምነታቸውን እንደ ኦርቶዶክስ፣ አገራቸውን እንደ ኢትዮጵያ፣ ሌሎች ማኅበረሰቦችን ሁሉ እንደ ቤተ ሰብ የሚያስቡ ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ መንፈስ በሁሉም የተጠመቀ እና አምላኩን እግዚአብሔርን ባለካድ እውነተኛ የፋኖ ሠራዊት ደም ውስጥ የሚመላልስ የማይደርቅ የሕይወት እስትንፋ አለ!!! ========================== ============ እኛን #ኦርቶዶክሳውያንን #እንጭርሳችሁ #አትናገሩ የሚሉ እና #የሚከሱን #7ቱ #ጸረ- #ኦርቶዶክስ ክርስትና እና ጸረ-ኢትዮጵያ አካላትን መጋለጥ የሁላችንም ለሰባዊነት፣ ለፍትሕ፣ ለእውነት፣ ለአገር ሉዓላዊ አንድነት፣ ለሰላም፣ ለፍቅር እና ለሰውን ልጅ እኩል የአገሩ ባለቤት መሆን የምንጨንቅ ሰዎች ሁሉ ነን!!! ======================= ቤተ ክርስቲያንን በሞዐ ሽፋን ዒላማ ያደረጉ በፋኖ ጉያ ውስጥ የተሰነቀሩ ቡድኖች ምንጫው ምንድ ነው? አጋሮቻቸው እነማናቸው? ብንል፦ 7 ወገኖች ናቸው። 7ቱ ጸረ-ኦርቶዶክስ ክርስትና እና ጸረ-ኢትዮጵያ አካላት እነማናቸው የሚለውን ከሁሉ አስቀድሞ #እኩል #ግንዛቤ #መያዝ የሚገባን፦ 👉 ውድ እና አንዲት ነፍሱን ለህልውና ትግሉ የሰጠ #የአማራ #ፋኖ ሠራዊት፤ 👉 ላቡን፣ ዕውቀቱ፣ ጉልበቱን ሳይሰስት ለዚህ ትግል የሚደክም ገበሬ፣ የአገር ውስጥ እና የውጭ አግር የሚኖር ምሁርና ሠራተኛ ሁሉ ናቸው። ✏️ እነዚህ ለጋር ግብ የሚደክሙ ወገኖች #እውነቱን #በማወቅ ራሳቸውን በትግሉ ውስጥ ከተሰገስጉት፦ 👉 አሰልቺና ዓይናአውጣ ሌቦችና አጭበርባሪዎች ፕሮፓጋንዳና በሤራ ተፈብሮኮ ከሚርጭ #አሳሳች #የሕሰት #መረጃ አደረጃጀቶች፤ 👉 የባእዳን ዕሳቤ ተቀላቢዎችና በገራችን በተለይ በአማራና በነባር እምነቶች ላይ የህልውና አደጋ መጋረጥ ምክንያት ከሆኑ የጎሣ ፖልቲካ አርማጆች ጋር አዙሪቱን ለማስቀጠል ለሕዝቡ ግልጽ ባልሆነ መርህና ግብ የሚጎዳኙትን፤ 👉 በጸረ-ኢትዮጵያ፣ ጸር-አንድነትና ጸረ-ኦርቶዶክሳዊነት አውቀው በሤራ፣ ሳይውቁ በመታለልና በቅንነት ትግሉን እያጓተቱና ዓላማ በማሳት ሌላ ዙር #አጠቃላይ #የሲቪል #ጦርነትና #የማይቀልበስ #የህልውና #አደጋ የሚጋብዙትን፤ 👉 በሞዐ ተዋህዶ ግብረ-ኃይል ሽፋን ኦርቶዶክሳውያንን የሚያሳድዱትን --- እንዲጠበቅ አለማሳሰብ በደልም፣ ኃጢአትም ይሆናል። ✏️ ይህን ሐቅ መግለጥ ያስፈለገብት ምክንያት፦ የትግሉ መጨርሻ ግብ ለኢትዮጵያ ዜጎች ሁሉ እኩልነት፣ ሰላም፣ ፍትሕና የተዋረደውን ሰብአዊ ክብር ዋስትና በሚሰጥ፣ የተፈናቀሉትን ወደ ቀያቸው የሚመልስ፣ የተበደሉትን የሚያስክስ፣ አጥፊዎችን ለፍትሕ አደባባይ የሚያበቃ፣ በሕዝቦች መካከል መተማመንና መተባበርን በማስፈን ህልውናን ዘልቄታዊ መሠርት ላይ የሚያቆም እንዲሆነ --- የትግሉ ደጋፊዎች፦ 👉 አጥፊዎችን ከአልሚዎች ለይተው በመረዳት እንዲረዱ፣ 👉 በሤርኞችና ርለማቆም አውጭ መንገድና ዐስተሳሰብን ከሤረኞች አካሄድ ለመለይት በእርጋታ ይመርመር። ================================== #7ቱ ጸረ-ኦርቶዶክስ ክርስትና እና ጸረ-ኢትዮጵያ አካላት በመሆን በሐሰት የሚክስሱን፣ የሚያሳድዱን፣ የሚያፈናቅሉን፣ የሚገድሉን፣ ፍትሕ የሚነፍጉን፣ ታሪካችንን የሚያነውሩ ጠላቶቻችን እነማናቸው? (1) #ማርክሲስት የተማሪዎች ንቅናቄ/የገር ገንጣታይ እና አስገንጣይ ነጻ አውጭዎች፦ "ሃይማኖት የማኅበረሰብ አሽሽ/ማደንዘዣ ነው ፣ ወዛደሩን ነጻ ለማውጣት ሕዝብ ከእግዚአብሔር ተለየቶ በቁሰአካላዊ የተቃርኖ ግጭት እና የመደብ ትግል ማመን ሲችል ነው" ብለው የሚያምኑ ማርክሲስቶች በኋላቀርነት፣ በጭቆና መሣሪያነት፣ በአደንዛዥነት፣ በግዥ መደብ አገልጋይነት ይከሱናል። (2) #የጎሣ -ንዑስ #ማንነት ፖለቲካ ውልዶች ሕውሃት፣ ኦነግ/ኦፒዲኦ/ብልጽግና፦ ከማርክሳዊ ዕሳቤ በመወለዳቸው በ1ኛ ተራ ቁጥር በተግለጸው ተመሳሳይ ክስ ላይ በተጨማሪ #የነፍጠኛ/የአማራ፣ #የቢሲኒያውያን (አምሐራና ትግሬ ተብሎ አስቀድሞ ይተረካል) ሃይማኖት፣ የብሄረሰቦች መጨቆን ምክንያት፣ የድህነትና ኋላቀርነት ምክንያት ናት ብለው ይክሱናል (3) #የአይሲስ መንፈስ ወራሽ ጽንፈኛ #የኡስታዞችና #የአልሸባብ #ሥልጠና ውስደው በመመለስ አገር ውስጥ ሕዋስ የዘረጋው ጂሃዳዊ ዉሃቢዝም፦ ኦርቶዶክስ ጭቁናናለች፣ አገሩን በብቸኝነትና በበላይነት ይዛለች፣ ነገሥታቶች በቤተ ክርስቲያኒቷ ቡራኬ በደል ፈጽመውብናል፣ መብታችን ይከበር በሚል የእልቂት ሂደትን ከአጀዳነቱ ለማውረድ የሚረባረቡ፤ (4) #የሂትለር መሸነፍ ኅቡዕ ያስገባቸው ወለጋ ከትመው በየጸሎት ቤቱና ሚሽነሪ ት/ቤቶች ውስጥ የተፈለፈሉ የኦነግ ውላጅ ተረፈ-ናዚ ፕሮቴስታንት፦ ኦርቶዶክስ ታሳደደናልች፣ እኩል አይደለንም፣ ሃይማኖታዊ መንግሥት በድሎን ነበር፣ አሁን በቀል ይገባታል፤ (5) እውነት ሁሉ የሚታወቀውና የሚመዘነው ከሴኩላር ሳይንሳዊ፣ ፍልስፍናዊና መላምታዊ የተጠይቅ ምእራባዊ የትምህርት ስልት በቻ ነው የሚሉ ጭፍን-ገልባጭ እና የባእዳን ዕሳቤዎች ማኅደር የሆኑ ምሁራን፦ ኦርቶዶክስ ሥልጣኔን መክታለች፣ የእድገት እንቅፋት ናት። መወገድ አለባት የሚሉ። (6)ነባርነትን መጣልን የባእዳን መከተል ሥልጣኔ የሚመስላቸው፣ ሆድና ድሎትን የሚከተሉ የቤተ ክህነት መዥገሮች፦ 👉. ዓለም እና አግር ከየት ወዴት እንደሚሄድ መመርመርም አቅጣጫው ላይ ተጽእኖ ለማሳደር ዐሳብ የሌላቸው፣ 👉 ድሎትና ምቾትን እንደ ነፍስ ሥራና ሃይማኖት የሚመለከቱ፣ የሞተውን ፖለቲካ ሁሉ የሚያገልግሉ፤ 👉 አሁን ላይ የጎሣ ጎሬው ውስጥ ገብተው ምእመናን ከክርስቶስ እቅፍ ወደ ጎሣ ፖለቲካ የሞት እቅፍ የሚገፉ የተወሰኑ ሤረኞች አቅም ካለው ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ጠላት ጋር "ተግባብተን እንምራቸሁ" በሚል ጥፋትና ያባብሳሉ። (7) የኢትዮጵያና የኦርቶዶክስ ትንሳዔ የሚያስፈራቸውና በፋኖ ትግል ውስጥ ስርገው የገቡ የሕወሃትና የብልጽግና ትክሎች፣ የባእዳን ተመካሪዎች፣ የግል ሥልጣን ጥመኛ ናርሲስቶች፦ 👉 በቀጥታ ኦርቶዶክሳዊነትን ቢነኩ 99% የሆነው በእምነቱ ኦርቶዶክሳዊ ሠራዊት እና ቀሪው ከጽንፈኝነት የፀዳ ነባሩ ሙስሊም አምሐራ ስለማይ ቀበላቸው ፣ 👉 ጸረ-ኦርቶዶክሳዊነታቸውን ለመደበቅ ሞዐ ተዋህዶን እንደ ትግል ጠላት በማቀረብ ስፊና ሩቅ እይታ ያላቸውን ሊቃውንት፣ የትግል አመራሮችን የሚያሳድዱ የውስጥ ባንዳዎች፦ 👉 ሞዐ ተዋህዶ የማራ ትግል የህልውና ጠላት ነው፣ ትግሉን የሃይማኖት በማስመስል ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን ይከፋፍላል፣ 👉 ሞዐ ተዋህዶ አደረጃጀቶች ወደ አንድነት እንዳይመጡ እንቅፋት ሆኗል፣ 👉 በፋኖ ስም ሀብት ሰብስቧል፣ በሚል ከብልጽግና መንግሥት፣ በዳንኤል ክብረት በሚመራው የፋኖ ሠርጎ ገቦችና በገንዝብ እየተደራደሩ ፍርፋሪ በሚቃርሙት የማኅበራዊ ሚዲያ ጀግኖች እና አሁን ባህርዳር በተቀመጥው አደራዳሪ በኩል እጅ ለመስጠት የተሰለፉት ከህዲዎች የቤተ ክርስቲያን አጀንዳን ከትግልና ከፖለቲካ አውድ ለማስወጣት የሚሠሩ ሤረኞች ኦርቶዶክስን ከብልጽግና ባልተናሰነስ የሚከሱት ናቸው። ===================== ቤተክርስቲያናችን እና በሃይማኖቱ ተከታዮች ላይ የሚካሄደው ሁለገብ ዝረ የማጥፋት ዘመቻ በረቀቀ መንገድ የቤተ ክርስቲያን ተላቶችን ሊያነበረክኩ ይችላሉ ተበልው የሚጠብቁትን ፋኖዎች በማታለል በራሳቸው ህልውና ላይ እንዲነሳሱ ሞዐ ተዋህዶን እንደ ጭዳ ፍየል በመጠቀም የራሱን እናት የሚወጋ ፋኖ ለመፍጠር እየጣሩ ነው። ነገር ግን አይሳካላቸውም። ሤርኞች ሲሽነፉ እንጂ ሲያቸንፉ አየተን አናውቅም። ድላቸውም ግዜአዊና አጥፊ ነው። ክርስትናን እና አማራን የማጥፋት ዘመቻው በፖለቲካ መዋቅር የሚደገፉ ዘርፈ ብዙ ስልቶችን ያቀናጀ ብቻ ሳይሆን በመንግሥት ፀጥታና የሥራ አስፈጻሚ መዋቅር በጀት ተበጅቶለት፣ ሠራዊት በመደበኛና በጫካ ተድራጅቶለት የኃይል እርምጃን ያካተተ ነው። ይህን እውነታ የሚያረጋⶓጡት ትገባራዊ እና ነባራዊ ተጨባጭ ተግባራት መገለጥ ከጀመረ 52 ዓመታት ወዲህ ባለፉት ስምንት የጠቅላይ ሚኒስቴር #አብይ #አህመድ አሊ የብልጽግና መንግሥት በከፍተኛ ፍጥነትና ስፋት የሚካሄድ ሆኗል፡- 1. የአገሪቱ መንግሥትና የፖለቲካ ዝንባሌ ነባር አገራዊ እሴትን፣ ባህልና ታሪክን በተለይ ከኦርቶክስ ቤተክርስቲያን የነገረ መለኮትና ትውፊት፣ አኗኗርና ማኅበራዊ መስተጋብር ጋር ፈጽመው የሚቃረኑ የፖለቲካ ርእዮተ ዓለማትን የሚከተል ነው። ይህንን የሚያረጋግጠው በመደበኛ ትምህርት፣ በፖለቲካ ማኒፌስቶ፣ በፖለቲካ ካድሬና የፀጥታ ኃይል ኢዶክትሪኔሽን ትምህርት፣ በኪነጥበብ፣ በመገናኛ ብዙኃን ውስጥ በማካተት የሚያስፋፋ መንግሥት መሆኑ። 2. የአገሪቱ መንግሥት ለኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና አኗኗር ተፃራሪነት ያላቸውን ማንኛውንም አይነት ኑፋቄዎችና ክህደትን የፖለቲካ ድጋፍ ይሰጣል። ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን እና ማኅበረሰቡን የማዳከም ግብ ያላቸው እርምጃዎችን ለምሳሌ ከሥልጣን ማግለል፣ ምእመናንን ማደየኸየት፣ ማፈናቀል፣ ማስጨፍጨፍ፣ ሌሎች እምነቶችን በመደገፍ ትምህርታዊና አካላዊ ጥቃት እንዲፈጽሙ ማድረግ፣ የአገልግሎት መሬትና ሀብታትን መቀማጥ፣ በወራሪነት መክሰስን ያካሂዳል። 3. መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት በሚሰሩት ሥራቸው ውስጥ ኦርቶዶከሳዊያንን የሚያጠቃ ስልት አንዲከተሉ ማድረግ። ለምሳሌ የልማት እቅዶች፣ ከልማትና ጋር ተያያዥነት ያላቸው እንደ ጤና፣ ግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ልማት፣ የከተማና የገጠር ቦታ አጠቃቀም፣ የማኅበረሰብ አደረጃጀት ኦርቶዶክሳዊ ታሪካዊና ነባር አሠራሮችን በማግለል፣ በማጥላላትና አፈራርሶ በመቀየር ላይ ያተኮሩ እንዲሆኑ ማድረግ፣ ትዳርና ልጅ አስተዳደግ ከክርስትና መርህ ውጭ እንዲሆኑ ተፃራሪ ሕግጋቶችን መደንገግና መተግበር፣ አጹዋማትና በዓላትን፣ ሰንበታትን ጠብቆ ስብሰባዎችና የሥራ ዘመቻዎችን በአስገዳች ሁኔታ በማቀድ ካህናትና ምእመናንን ከምሥጢራትና አገልግሎት ማገድ። 4. መንግሥትና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃይማኖትና ፖለቲካ ይለያያል የሚል አስመሳይ ንግግርና ሕግ ከፊት በማሳየት ተግባሩን ግን ዜጎች ከሃይማኖት መለየት ይገባቸዋል ወደሚል አሠራር መሸጋገራቸው፡- ለእማኞች አስፈላጊ የሚሆኑ መገልገያዎችን ቁስና ሀብታት፣ የጊዜ፣ የትምህርት ማስተላለፊያ መንገዶችን መገደብ። አገር ቁሳዊ ድኅነት፣ ወይንም ፖለቲካው በሚፈጥራቸው መሥፈርት ልኬታ የዘመናዊነት እንቅፋት በማድረግ ቤተክርስቲያንን መክሰስና በአንፃሩ የተቀደሰ ባህልና አኗኗርን በተግባር መገደብ። 5. መንግሥት በቀጥታና በብሔር ልሂቃን በኩል ፀረ ኦርቶዶክስ ሐሰተኛ ትርክቶችን በማሰራጨትና በማጥናከር በክርስቲያኖች ላይ ጥላቻ ተስፋፍቶ ወደ ማሳደድና የጅምላ ፍጅት መሸጋገሩ፤ ሂደቱ መንግሥታዊ በመሆኑ ከእይታ እንዲደበቅ፣ ፈጸማዊቹ ለሕግ አንዳይቀርቡ፣ ተጠቂዎች ራሳቸውን እንዳይከላከሉ፣ ሂደቱ እንዳይቆም ለዓመታት በእቅድና በመዋቅር ማስቀተሉ። 6. የመንግሥት ሥልጣን ከቀበሌ እስከ ፌደራል ድረስ፣ የፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ የኮርፖሬሽን ኃላፊዎችና ውሳኔ ሰጭዎች፣ ስልታዊ የምጣኔ ሀብት ምንጭች ሁሉ ውስጥ ኦርቶዶክሳዊያን እንዲወገዱ ማድረግ። 7. የሐሰት ሲኖዶስ በመፍጠር ቤተክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ ማጥፋት፣ በእምነታቸው የሚጸኑትን በቀጥታ ፍጅት በእርስ በእርስ ጦርነት፣ በስደት፣ በረሃብና በሽታ የመፍጀት ሥራ መኖሩን ታሳቢ በማድረግ---- --- መፍትሔ የሚገኘው እነዚህ በፖለቲካ ርእዮት፣ በፖለቲካዊ መዋቅር እቅድ የሚካሄደው ኦርቶዶከስን የማጥፋት ሥረዓታዊ ሂደት ሊገታ የሚችለው መዋቅራዊና ሥርዓታዊ ጥያቄዎች ቀርበው፣ ኦረቶዶከሳዊያን ያለማወላወል፣ ያለመከፋፈል፣ ያለማመንታት፣ ያለቅድሚያ ተዋራጅነት ለመልሱ በሚችሉት ሁሉ በአንድነት ሲነሱ ነው። ይህን የአጀንዳ፣ የልብ፣ የዐሳብና የግብ አንድነት በማስተባበርና በማስጀመር ሁሉም ክርስቲያን በግሉ፣ በቡድ፣ በመዋቅር፣ በማኅበረሰብ ደረጃ ለሁለገቡ ክርስትናን የማጥፋት የብልጽግና መንግሥትና እርሱን የወለዱ የዘር ፖለቲካ ፓርቲዎች ሁለገብ ጥቃት ሁለገብ ምላሽ የሚያስገኝ ሁለገብ እርምጃ ላይ መሠማራት እንዲቻል የሞዐ ተዋሕዶ ኃይለ ግበር መንገድ ከፍቷል። "ይህን መንገድ ለማራ የህልውና ትጋድሎ ጠላት ነው" በሚል ፍረጃ ፋኖ ውጽጥ በቅጥረኝነት ለጠላት የሚያገለግሉ አካላትን የፋኖ ሠራዊት ለይቶ በማውቅና ከትግሉ በመነጠል የተጋድሎውን ጥራት፣ የመጭርሻ ግብና ፍሬ ጣፋጭ ማድረግ ይግባዋል። የህልውና አደጋ ያመጡብንን ሤረኞች፣ ቁማርተኞች፣ የሐሰት ተራኪዎች፣ ስግብግቦች፣ አገር-ጠሎችን ለመዋጋትና የሰውን ልጅ ክብር፣ ለዘመናት የተጓደልውን ፍትሕ ለመመለስ፣ የተነጠቅነው የአግር ባለቤትነት ለመመልሰ ብሎ ነፍሱን ለመስዋዕትነት የሰጠውን ታጋይ የገዛ ሃያምኖቱ ጠላት እንዲሆንና ራሱን በራሱ እንዲያጠፋ የሚሠሩትን መሠሪዎች መጠንቀቅ ይኖርበታል። ለፍትሕ፣ ለእውነት፣ ለክብረ ስብእ የሚቆሙ ሰዎች አምላካቸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ የቀመሱ ናቸው። እነርሱን በግብር የሚመስሉ የሌላ እምነት ተከታዮችም በሕገ-ተፈጥሮ ፍትሕና ህልውና የሚረዳቸው ክቡራን ሰዎች ናቸው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...