የዘር ማጥፋት ሙከራዎችና ተግባራት 100% ለማለት በሚያስድፍር ደረጃ የሚካሄዱት በመንግሥት ነው!!!
(ክፍል 2)
#ሕወሃት እንኳ የፈጸማቸው ወንጀሎች በአብይ አህመድ እወቅናና ሤራ የሐውሃትን ነባር ሰይጣናዊ ዝንባሌዎችን በማነቃቃት የተከናወኑ ናቸው።
ማስረጃ፦
ዘር ማጥፋት የመንግሥትን ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ ተሳትፎ የሚፈለግባቸው ዋናዎቹ ምክንያቶች፣ ድርጊቱ በዕለት ታስቦ፣ ተደራጅቶ የሚፈጸም ሳይሆን ዓመታትን የሚፍጅ ዝግጅት የሚጠይቅ፣ ትርክት፣ ርእዮት፣ መዋቅርና አቅም የሚጠይቅ በምሆኑ ነው።
ግጭት ሲሆን በንድ ውቅትና ጉዳይ ዙሪያ የሚጋጩ ሁለት አካላት በመንደር ወይንም በቀበሌ ጊዜአዊ እና ስሜታዊ ጉዳይ ላይ ተጋጨተው በመንግሥት፣ በሃይማኖትና በባህል ጣልቃ ገብነት ያበቃል። የሐውሃትና የኦነግ ትርክትና ርእዮት መንግስታዊ ሕግና ፖሊሲ በመሆኑ በአንድ መንደር ሳይሆን በመላው አገሪቱ 38 ዓመታት ያልተቋረጠ በኦርቶዶክሳውያን ላይ እልቂት እየተፈጸመ ምሆኑ ድርጊቱ መንግሥታዊ መሆኑን ያረጋግጣል።
መፈናቀሉ፣ መገደሉና የታሪክ መጠልሽቱ፣ ዒላማ የተደረገውን ወገን በተለያዩ ስያሜዎች፣ በተልይ በማራና ነፍጠኛ ሽፍኖ ማጥፋቱ መንግሥታዊ መሆኑ የክልል ሕጎች፣ የባለሥልያናት ንግግሮች፣ መንግሥታዊ መዋቅን ሥልያን ድልድል፣ የፍትሕ መታጣትና የታቀደ ድኽነትን በዘውግ የመፍጠር ድርጊት ሙሉ በሙሉ መንግሥታዊ ነው።
ዘር ማጥፋት በጠባቡ ሲተረጎም ፡- በትከታታይነት በጅምላ መግደል እና ፍትሕ መንፈግ ፣ በተከታታይነት በጀምላ ማፈናቀልና መልሶ አለማቋቋም፣ በስልት ሴቶችን መድፈርና ተዳር መበተን፣ ቋንቋና ባህል ማዳከም፣ ከሃይማኖት ማፍልስ፣ ባህል መደምሰስ፣ በጅምላ ማሠር፣ ሕጻናታትን ከማንነታቸው አውጥቶ የሌሎች ማድረግ፣ ማምከን፣ ማደኸየት፣ በሥራ ስም በባርነት ሰዎችን ከአግር ማስወጣትን ሁሉ ይጨምራል።
ይህን ለማድረግ የግድ፡
1) የፍጅት መሣሪያና ሎጂስቲችስ ማሟላት (መንግሥት መሆንን የጠይቃል) ፤
2) በመንግሥት ቢሮክራሲ ቅንጅት ለመፈጠር አካባቢን በአስተዳድር ክልል አዋቅሮ ባለቤት የሆነ ዚጋና ያልሆነ፣ ልዩ ጥቅም የሚገባውና የማይገባው ብሎ መክፍለ (መንግሥታዊ ሥልጣን የጠይቃል)፤
3) እንዲጥፉ የተፈረደባቸው ወገኖችን ራስን የመከላከል አቅም መንሳት፣ ማምለጫና ለዓለም የሚናገሩበትን መንገዶች መዝጋት (ይህ መነግሥታዊ ሥልጣን የጠይቃል)፤
4) የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነትና መከላከልን የማገድ አቅም (ይህ መንግሥት መሆንን የጠይቃል)፤
5) ወንጀሉ በብዚኃን መገናኛ እንዳይነግር፣ ተቃዋሚዎች እና ፓርላማ አጀንዳ እንዳያደርጋቸው ማገደ (ይህ የምንግሥት ሥልጣንን መቆጣጠር የጠይቃል)
6) የአግሪቷ መከላከያ፣ ፖሊሲና የፍትሕ መዋቅሩ ስለሚጨፈጭፉና ስልሚጎዱ ወገኖች ተቃውሞ ሳይሆን ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን የዘር ማጥፋት ማስፈጸሚያ መሆን አለባቸው (ይህም መንግሥት መሆንን የጠይቃል) ----
---- እንዚህ 6 ሁኔታዎች ሳይሟሉ እንኳንስ 30 + 8 ዓመታት ለ8 ሳምንታትም ሰውን መጨፍጨፍና ማፈናቀል አይቻልም።
--- ስለዚህ
ከዓለም ታሪካ የዘር ማጥፋት ሙከራዎች የሚጠቀሱ ማስረጃዎችን እንመልከት፦
1) በአይሁን ላይ በናዚ ጀርመን የተፈጸመው ዘር የማጥፋት ዘርፈ በዙ ሙከራዎቸ፦
የናዚዋ ጀርመን አይሁድን፣ ሮማዎችንና ሌሎችን ከሰውነት የወረዱ ዘርያዎች በለው የሰየሟቸውን ወገኖች ለማጥፋት የተጠቀሙት የሚሎታርይ፣ የፖሊስ፣ የደኅንነት፣ የባቡር ትራንስፖርት፣ የኬሚካል ካምፓኒዎችን፣ የፕሮፓጋንዳ ተቋሟትን በማቀናጀት ነው። ስለዚህ ዘር ማጥፋቱ መንግሥታዊ ነው።
2) በ1915 (እ.አ.አ) የተፈጸመውና ዛሬም ደርስ በረቂቅ መንገድና በፖልቲካ የሚካሄደው የአርመን ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ዘር የማጥፋት የኦቶማን ቱርክ ድርጊት የተከናወነው በእስላማዊ መንግሥት ነው። የኦቶማን መንግሥት የጅምላ ማፈናቀልና ማባረር፣ የጅምላ ግድያ ሰልፈኞችን ማዘጋጀትና አርመን ክርስቲያኖችን መጨፍጭፍ መርቷል። ስለዚህ ዘር ማጥፋቱ መንግሥታዊ ነው።
3) በ1994 (እ.አ.አ) በሩዋንዳ የተካሄደው ዘር የማጥፋት ሙከራ በሁቱዎች በሚመራ መንግሥታዊ ራዲዮ ቀስቃሽነትና በመንግሥት መዋቅር ድጋፍ ነበር። ሚሊሺያዎች፣ ሚዲያ፣ በየሽካባቢው (ወረዳና ቀበሌ) መዋቅራትን የሚመሩ ባለሥልጣናት (እንደ ኦሮምያ ምንግሥታዊ መዋቅር ማለት ነው) ቅንጅት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ቱትሲዎች ተጭፍጭፍዋል። ሩዋናዳና ሰላም ከተመለሰ በኋላ ይህን የመሩ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ለዓለም ዐቀፍ ቲሪዩቡናል አቅርባለች።
4) በ1995 ምዕራባውያን የተዛባ ጣልቃ ገብነትና በጽንፈኞቹ ፖለቲካዊ የአልቃይዳ መንፈስ ወራስ ሙስሊሞች በክርስቲያኖች ላይ በተጀምረ ጥቃት እና ምላሽ የቦስንያ ሰርብ 8,000 ቦስኒአክ ሰርቤኒካ እልቂት ተፍጥሟል። በሌላው በኩል መረጃ እንዳይኖር የሚፈልጉት የውጭ ጣልቃ ገቢ ተዋንያን ትርክቱን አዛብተው የአንዱን ወግን ብቻ ተረክዋል። ይህ በኢትዮጵያ በጣልያን የተፈጸመው የአማራና የኦርቶዶክስ ዘርን የማጥፋት ሙከራ እንዳይዘገ እንደሞከሩትና በእግዚአብሔር ፈቃድ በኢያን ካምፕቤል ባልፈው 5 ዓመት ቅንጭብ መርጃ ከታተመው ( https://a.co/d/0ezXTW79 ) ውጭ። በሰርቢያ ክርስቲያኖች ላይ የተደፈደፈው ክስ የሚያነሳው ስሎቦዳን ሚሎስቪች የመራው ሚሊታሪ ላይ ሲሆን ሌላውን ወገንና የውጭን ሚና ድብቆታል። ያም ሆን ይህ በጅምላ ያለቁት ሰርቦች በመዋቅር መሆኑ እንረዳለን።
ማጠቃለያ
ዘር ማጥፋት ያለ ምንግሥት ተሳትፎ ሊከወን ይችላልን? አገር ባልፈረሰብት፣ መንግሥት መዋቅራትን በሚቆጣጠርበት ሁኔታ ሁሉ ያለ መንግሥት ፈቃድ፣ ተሳትፎና መሪነት የዘር ማጥፋት ሙከራ ፈጽሞ ሊካሄድ አይችልም ነው።
በእርግጥ አንድ ግለሰብ፣ ወይንም ቡድን የዘር ማጥፋት ሀሳብና ሙከራ እንዲጀመር ቅስቀሳ ሊሠራ የችላል። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ሕወሃትና ኦነግ መንግሥት እንስኪሆኑ ድርስ ትርክትና ቅስቀሳ አድርገዋል።
መንግሥትነት እጃቸው ሲገባ ውለው ሳያድሩ ዘር ማጥፋቱን ከሐረርጌ እስከ አርሲ ብቻ ሳይሆን በማራ ክልል ውስጥም በመሠረተ ልማት አድልዎ፣ ወሊድን በመቅነስና በማምከን፣ የውባ ወረርሽኝና በሽታ እንዲስፋፋ በማድረግ፣ በጦርነቶች ሆን ብሎ ከፊት በመማገድ፣ በማደኸይት፣ ከትምህርትና ከኢኮኖሚ እደገት ውጭ በማደረግ፣ እርስ በርስ የሚያጋጩ ሁኔታዎችን በመፍጠር፣ ርስትን በጎሣ በመደልደልና አምራና ኦርቶዶክሳውያንን በሚጎዳ መንግደ በመከለል፣ የራሱ መሪዎች እንዳይኖሩት በማድረግ፣ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ከእውነተኛ የመነቱ አባቶች እጅ በማስወጣት በካድሬና ሕሰተኛ አባቶች በመሙላት፣ የጀመሩትን ሂድት የበልጽግና መንግሥት በቀጥታ በመደበኛ ሠራዊትና ታጣቂዎች የጅምላ ፍጅትና ማፈናቀል ውስጥ መግባቱ መንግሥታዊነቱን ያረጋግጣል።
ይህ ጠንካራ ማሰርጃና አሳማኝ እንዲሆን የሚያደርገው ዘር ማጥፋት ሂድት ተጀምሮ ከሳምንታት በላይ እንዲቀጥል የሚያደርገው አድራጊው፡
1) በመንግሥት ደርጃ ማቀደ ሲችል፤
2) የመንግሥት መከላከያ፣ የፖሊስ ፣ ሚሊሻና ልዩ ልዩ በምንግሥት መዋቅር ሥር የሚተዳደሩ እና በተዘዋዋሪ የሚደግፉ የተደራጁ አካላት ሲሳተፉበት፣
3) በጀትና ፕሮፓጋንዳዊ የማያቋርጥ ሆኖ ሲቅጥልና በተቃራኒዊ ያለው ተጠቂ ወገን መናገር፣ መጻፍና መደራጀት፣ መታጠቅና ለትርክቱ መቆም ሲከለክለ፣
--- ሲተባብሩ ስለሆነ መንግሥት የማይሳተፍበት ዘር የማጥፋት ሙከራ በአንድ አገር ውስት ሊኖር አይችልም። በተለይ ሕወሃትና ኦነግ ኦሮሙማ ለ38 ዓመታት በኦርቶዶክስ ክርስትናና በአማርኛ ተናጋሪዎች ላይ የጀመሩት ዘር የማጥፋት ሙከራ ሙሉ በሙሉ መንግሥታዊ፣ መዋቅራዊና ሥርዓታዊ ነው።
ይህን አሁን በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ሁለገብ የዘር ማጥፋት መንግሥታዊ ፕሮጄክት ለማስቆም ጤናም ሰብእና ያለን፣ ፈጣሪ በሌላ ፈጡር በሆነ ሰው እጅ ሰውን ያድናል እንጂ አይገድልም የሚለ የሃይማኖት አስተምህሮ ያለን፣ ፍትሕ ትርጉሙ የሚገባን፣ ነውርና አውሬነትን የምንጸየፍ፣ ሐሰትና ስግብግብነትን የመንጠላ ሁላችን --- በሃይማኖት፣ በቋንቋና በትርክት ከፋፍሎ ለሚያፋጀን መንግሥት መሣሪያ ሳንሆን ህልውናችንን፣ አገራችንን፣ ታሪካችንን፣ እውነታችንን፣ ሰባዊ ክብራችንን ለማስመለስ የድርሻችንን እንወጣ!!!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ