የመንግሥት 10 ዋና ተግባር እና ቀዳሚ ኃላፊነት
1) የዜጎችን ደኅንነት ማረጋገጥ፣
2) ከሁለገብ ሥጋት መከላል፣
3) የማንኛዉም ዜጋ አካልና ነፍስ፣ ሞራልና ህሊና እንዳይቆስል መከላከል፤
4) የታወቁ መሠረታውያን መብቶችን መጠበቅና ማስጠበቅ፣ የ
5) ተረጋጋ የዜጎችና ማኅበራዊ መስተጋብሮቻቸው በታውቁና ተገማች፣ ተአማኒ የሕግና የፍት ሥርዓት ማረጋገጥ፣
6) የምጣኔ ሀብት እደገት፣ የማኅበራዊ ልማት፣ ትምህርትና ጤና ወዘተ በሚፈለገው ፍጥነት፣ ስፋት፣ ነጻነት እንዲሄድ መሥመር ማሳየት እና --- ለሚፈጽሙት ዜጎች እድል ማመቻቸት --- የግልና የወል ጥረቶችን መደግፈና መጠበቅ
7) ከውጭ ጠላት መከላከል
8) የዓለም አቅፍ ግኑኝነቶችንና ጂኦ ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን በጠበበ ጠቃሚ ማድረግ
9) ሕግ ማስከበር
10) ብዝኃነትን ማመጋገብና ጠቅላይ፣ አናባቢ የጋራ ትርክትና እሤቶችን ማጠናከር፣ አፍራሾቹን መከላከል
ለምን እነዚህ 10ሩ አስፈላጊ ሆኑ?
ምክንያቱም ያለ አተቃላይ የዜጎችና የማኅበራዊ መስተጋብሮቻቸው ድኅንነት፡
1) ሰዎች መሥራት፣ መማር፣ ቤተ ሰብ መመሥረትና ማስተዳደር አይችሉም
2) ነጋዴዎችና አራሾች፣ ተመራማሪዎችና የፈጠራ ሰዎች ውጤት ተስፋ አድርገው መዋዕለ ንዋያቸውን፣ ጉልበታቸውንና ዕውቀታቸውን አያፈሱም፣ ቢያፈስሱም መተግበርና መፈጸም አይችሉም፤
3) ማኅበረሰቦች እርስብርሳቸው አይተማመኑም፣ የጋራ ግብና ርእይ ላይ አይተባበሩም፣ ለውስጥ ቀውስና ለውጭ ወረራ የተጋለጡ ይሆናሉ
4) መንግሥታዊና ማኅበራዊ ተቋማት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የሚያስችላቸው አፈጻጸም ማረጋገጥ አይችሉም፤
5) ማኅበረሰባዊና አገራዊ ልማት አዳጋች ይሆናል፣
6) የእምነቶችና የባህሎች መናቆርና መለያየት፣ የተገዳዳሪና አፍራሽ ትርክቶች፣ በጠላትነት የመጠባበቅና የመጠፋፋት ዝግጅቶች ይጠናከራሉ፤
7) በግጭትና በመለያየት ላይ የተመሠረቱ አሰላለፎችን የሚያተናክሩ ስግብግብ፣ ጠባብ፣ ራስ ወዳዶች በተከፋፍለውና በሚፈራራው ማኅበረስብ መሣሪያነት ወደ ምንግሥት ሥልጣን በመምጣት ውድቀቱን ዘለቄታዊ ሂደት ያደርጉታል፤
ስለዚህ የአንድ ዜጋ ድኅንነት መረጋገጥ የሁሉ አገራዊ ጽናትና እድገት መሠረት ነው። ይህ ኃላፊነት የአንድ መንግሥት ዋና ግዴታው ነው።
የማንኛዉም የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መንግሥት የደኅንነት መጠበቅ 7ኃላፊነቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦
1) አካላዊ ድኅንነት፡ ፖሊሲያዊ/የጸጥታ እና የአድጋ መከላከል ሥርዓትና አገልግሎት
2) ሕጋዊ ድኅንነት፡- የፍትሕ ሥርዓትና ዕቀበተ ሕገ-ሕዝብ
3) ምጣኔ ህብታዊ/ስነ-በዕላዊ ደኅንነት፦ ንብረት ጥበቃና መከላከል፤ የካባቢ ብክለት የጥራት ማሽቆልቆልን እና የተፈጥሮ ሀብታትን ዘለቄታዊነት ከመጎዳት መከላከልና ጥበቃ፤
4) ማኅበራዊ ደኅንነት፦ ኃይለኛው በደካማው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳይኖረው መጠበቅና መከላከል፤
5) አገራዊ ድኅንነት፦ መከላከያና መረጃ፣ ቀጠናዊና ዓለም ዐቀፋዊ ግኑኝነትና አሰላለፍ፤
6) የባህልና የሃይማኖት ድኅንነት፦ ማኅበረሰባዊና አገራዊ አለመተማመን፣ መለያየትን የሚፈጥሩና ለውጭ ጠላት መግቢያነት፣ ለትውልድ ራስን መጥላትና ውጭ ናፋቂነት፣ የአእምሮ ፍልሰት ከሚፈጥሩ የትምህርት፣ የረእዮተ ዓለም፣ የእምነትና የባህል ወረራ ጥበቃ ማድረግ፤
7) በይነመረባዊ ድኅንነት፦ ዲጂታል መሠረተ ልማቶችንና የዜጎችና ዲጂታል መረጃዎች መጠበቅና መከላከል፤
መንግሥት ከእነዚህ ከ7ቱ የደኅንነት ዘርፎች አንዱንም ቢዘነጋ ዜጎችና ማኅበረስቦች ለተለያዩ አደጋዎች ተጋላጭ ይሆናሉ።
አንድ መንግሥት 10ሩን ቀዳሚ ኃላፊነቶችና 7ቱን የጥበቃ ገዴታዎቹን ካልተወጣ መንግሥታዊ ዕውቅና ሊያገኝ አይገባዉም። በመንግሥት ስም ወሮበሎችና የባዕዳን አገልጋይ ባሮች አገርን ጠላትን ወክለው ቅኝ የሚገዙበት የጥፋት መሣሪያዎ ናቸው።
በ10ሩ የቀዳሚ መንግሥታዊ ኃላፊነቶች ሚዛን
1) የዜጎችን ደኅንነት ማረጋገጥ፦ ዜጎች በመፍናቀል፣ በመሰደድ፣ በመሞት ላይ የገኛሉ፤
2) ከሁለገብ ሥጋት መከላል፦ ዜጎች በዘር ፖለቲካ፣ በውጭ ገብ ርእዮቶችና እምነቶች፣ በጽንፈኞች ከበባ፣ በዘረኞች አግላይ ፖሊሲና ድርጊት ሁለገብ ሥጋት ውስጥ ገብተዋል፤
3) የማንኛዉም ዜጋ አካልና ነፍስ፣ ሞራልና ህሊና እንዳይቆስል መከላከል፦ መንግሥት በካል የሚሞቱ፣ በትርክትና በማጠልሸት የሚቆስሉ፣ በእሥራትና ቶርቸት በሚሰቃዩ ዜጎች የሚደሰት ሆኗል፤
4) የታወቁ መሠረታውያን መብቶችን መጠበቅና ማስጠበቅ፦ ሁሉም የዜጎች መብቶች (ሰባዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሃያኖታዊ፣ ማኅበራዊ፣ ሕጋዊ፣ ትርክታዊ፣ ርስታዊ) ተደፍረዋል፤
5) ተረጋጋ የዜጎችና ማኅበራዊ መስተጋብሮቻቸው በታውቁና ተገማች፣ ተአማኒ የሕግና የፍትሕ ሥርዓት ማረጋገጥ፦ ዜጎች በሥጋትና ስደት፣ ርሃብና ስቃይ ላይ ናቸው፣ መርጋጋት የለም፣ ተአማኒ የሕግና የፍትሕ ሥራአት ጠፍቶ በአብይ አህመድ የተደራጅ የከተማና የጫካ አፋኝና ገዳይ ቡድን ዜጎች ጭንቀት ውስጥ ናቸው።
6) የምጣኔ ሀብት እደገት፣ የማኅበራዊ ልማት፣ የትምህርትና ጤና ወዘተ በሚፈለገው ፍጥነትና ስፋት እንዲሄድ መሥመር ማሳየት እና --- በተግባር ለሚፈጽሙት ዜጎች እድል ማመቻቸት --- የግልና የወል ጥረቶችን መደግፍና መጠበቅ ነበር፦ የሁንና በብልጽግና መንግሥት አንጻር ሁሉም በተቃራኒው የፈጸማል፤ የውጭ ብድር ሳይቀር ትርፋማ ባልሆኑ ብልጭልጭ የፖለቲካዊ ግጽታ ግንባታ ፕሮጄክት የሚባክኑበት፣ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው የሚፈልሱበት፣ የግልና የወል ጠረቶች በጎሣ እና በሃይማኖት መሥፈርት በቡድን እና መዋቅር የሚታገቱበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
7) ከውጭ ጠላት መከላከል፦ የሰሜኑን ወገን አማራና ትግሬን፣ ኦርቶዶክስ የሆነውን ኦሮሞና የደቡቡን ማኅበረ ሰብ ለማስጨንቅና ከጎረቤት ወዳጅ ለማሳጣት ሲባል የአግሪቷ ድንበር ተቆርሶ ልሱዳን ታድሏል፤ አምራና ትገሬን ለማፋጀት በምእራባውያን ዳኝነት፣ በሐወሃት ሕገ መንግሥት ማኅቀፈ የፕሪቶሪያ ስምምነት የሚባል በናድ ሉዓላዊ አገር ውስጥ ጊዳይወረዳና አውራጃ የመደልደል ሥልጣን ለባእዳንና ለላኪዎቻቸው ተፈቅዷል።
8) የዓለም አቀፍ ግኑኝነቶችንና ጂኦ ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን በጠበበ ጠቃሚ ማድረግ፦ ለአሜሪካ ሞታለሁ፣ አርበ ኢሚሬት ኢትዮጵያን ትውረስ፣ ለጦርነት ገንዝብና ትጥቅ የሚሰጠኝ ሁሉ መሬት የቀራመት የሚለ መሪ ወደ ጥፋት የሚመራት አገርና ሕዝብ ተፈጥሯል፤
9) ሕግ ማስከበር፦ ሕግ ማስከበር የጥፋት ሥልጣንን ማስከበር፣ የጥፋት የሕወሃትና የኦነግ አግር ማፍረሻ ሕገ-መንግሥትን ማስከብር በሚል ተተርጉሞ መደበኛና መደበኛ ያልሆነ ሠራዊት በሕዝብ ላይ ዘምቷል፣ በተለየ ሁኔታ ኦርቶዶክሳውያንና አማራን ዒላማ በማድረግ፤
10) ብዝኃነትን ማመጋገብና ጠቅላይ፣ አናባቢ የጋራ ትርክትና እሤቶችን ማጠናከር፣ አፍራሾቹን መከላከል፦ ብዝኃነትና የሚቃርኑ ተላቶች በማስመሰል የማንነት ፖለቲካን ሕጋዊ በማድረግ ተገዳዳሪ ትርክቶችን ማልማትና የጋራ አገራዊ ተርከቶችን በማዳከም ሕዝብ ማጠፋፋት ላይ የገኛል።
ይህ መንግሥት በ10ሩም መሥፈርት የወደቀ ነው። ስለዚህ መንግሥት ተብሎ ሊጠራ የማይገባ የሽፍታ ቡድን፣ የኢትዮያውያን ሁሉ ጠላቶች አገልጋይ ነው። ኢትዮጵያውያን የሚመጥናቸው መንግሥት ለመፍጠር ከዘር ፖለቲካ ወጥመድ እና በትርክት ላይ ከተመሠረተ የጥላቻ ነጽሮተ-አገር መላቀቅ አለባቸው።
ይህ መንግሥት በ7ቱ የደኅንነት ምሥፈርቶች ሲመዘን፦
1) አካላዊ ድኅንነት፡ ፖሊስና ጸጥታ ተቋሙ የጎሣ ፖለቲካ ጠባቂና አገልጋይ ሆኖ በመዋቅሩ ዜጎችን ሳይሆን ቡድኖችን የበላይ ለማድረግ የሚደረገውን ግፍና ሕገ-ውጥ፣ ኢሰባዊና ጸረ-አንድነት እንቅስቃሴዎችን የሚያመቻችና የሚጠብቅ ነው፤
2) ሕጋዊ ድኅንነት፡- የፍትሕ ሥርዓቱ እና ዐቃቤ ሕግ ጥበቃው ለዜጎችና ዜጎች በነጻነት ለፈጠሯቸው ማኅበራቂ ተቋማት መሆኑ ቀርቶ የጎሣ ፖለቲካ ለሥልጣን ያበቃቸው ቡድኖችን፣ ይካድሬዎችን እና የአገልጋዮቻቸውን ጥቅም መጠበቅና ማጠናከር ነው፤
3) ምጣኔ ህብታዊ/ስነ-በዕላዊ ደኅንነት፦ የዜጎችን ቤቶች ማፍርስ፣ ርስት ማፍለስ፣ ንግድና ግብርናን በጎሣ እና በሃይማኖት የነዑስ-ማንነት ሚዛና ማዛወር፣ ለአጭር ግዜ ጥቅምና ለገጽታ ግንባታ የተውልድን የተፈጠሮ ሃብታት ዘልቄታዊነት አደጋ ላይ የሚተሉ ኢንቨስትመንቶችን ለባእዳን መፍቀድና፣ ዜጎችን በአግራቸው ባሮች ማድረግ፤
4) ማኅበራዊ ደኅንነት፦ በንዑስ-ማንነት ጎሣዊ ፖለቲካ የሃብት፣ የፖለቲካ ሥልጣን፣ የአደረጃጀትና የትጥቅ፣ የሚዲያና የትርክት የበላይነት እንዲያገኝ የተደረገው ኃይለኛው በተቃራኒው ፖለቲካው እንዲዳከምና እንዲጠፋ በብየነበት ወገን ላይ ከማፈናቀል እስክ ጅምላ ግድያ የሚፈጽምበት ሁኔታ ተፈጥሯል፤
5) አገራዊ ድኅንነት፦ መከላከያው ድንበር ክፍት አድርጎ አገር ውስጥ ለፍጅት የሚዝምንትና የመረጃ አቅም ለዜጎች ድኅንነት ሳይሆን ዜጎችን ለመሰለልና ለመቆጣጠር ውሏል፣ ቀጠናዊና ዓለም ዐቀፋዊ ግኑኝነትና አሰላለፍ ግልጽ በሆነ አገራዊ ግብና ርእይ የማይመራ፣ በግለሶቦች አስተሳስብና ፍላጎት ሥር የወደቀ ሆኗል፤
6) የባህልና የሃይማኖት ድኅንነት፦ ማኅበረሰባዊና አገራዊ አለመተማመን፣ መለያየትን የሚፈጥሩና ለውጭ ጠላት መግቢያነት፣ ለትውልድ ራስን መጥላትና ውጭ ናፋቂነት፣ የአእምሮ ፍልሰት የሚፈጥሩ የትምህርት፣ የረእዮተ ዓለም፣ የእምነትና የባህል ወረራ በመንግሥት አመቻችነት ከምቼውም ዝመን በከፋ ደረጃ ተጠናክሯል፤
7) በይነመረባዊ ድኅንነት፦ ዲጂታል መሠረተ ልማቶችንና የዜጎችና ዲጂታል መረጃዎች መጠበቅና መከላከል ሳይሆን ከአገር ውስጥ እስከ ውጭ ተቃዋሚና ነጻነት ጠያቂ ዜጎችን ለመሰለል፣ መልሶ ለማጥቃት፣ የፕሮፓጋንዳ መሣሪያነቱ እግጅ ያደላበት ሆኗል፤
የዳንኤል ክብረት ቃለ መጠይቅና የመንግሥት ነጽሮተ ዓለም ገመና
ከላይ በግለጽናቸው 10ሩ የመንግሥት ቀዳሚ ኃላፊነቶችና 7ቱ የድኅንነት ሚዛኖች መርምረን የአብይ አህመድ መንግሥትና የአብይ አማካሪው ዳንኤል ክብረት “መንግሥት” የዜጎች፣ የማኅበረስቦችና የአገር አጠቃላይ ድኅንነት ጠላት መሆናቸውን አንድ በአንድ መዝነን አርጋግጠናል።
እንደ ማሳያ እንዲያገለግለን ይህን ከአብይ አህመድ መንፈስ ተቀድቶ በካድሬ ዳንኤል ክብረት በኩል የተላለፈውን የቪዲዮ ይዘት በንመረምር 10ሩንም የመንግሥት ኃላፊነቶችና የጥበቃ ግዴታዎች ፈጽሞ የማይጠቅስ፣ በተቃራኒው ‘ሰው’ የተባለውን ሰማይና ምድር የተሰቀሉለትን፣ መንግሥት የሚመሠረትለትን ዜጋ ዘንግቶ ስለቁስና ቁሳዊ ውበት ብቻ የሚገልጽ ሆኖ የገኛል።
ዳንኤል ክብረት በቤተ ክህነታችን ብልሹ እና አድርባይ ሰዎች ጋር ውሎ በማደር ካካበተው የስነ-ኃዳሪነት ልምዱ ስለ አለቃውን አሰትዋይነት እና ስኬታማነት ለመግለጽ ያቀረበው ምሳሌ “የአንድነት ፓርክ” የተባለውን የአብይ አህመድን ነባር ኢትዮጵያዊ አሻራ የመደምሰስ መሠሪ ፕሮጄክት ነው። እስቲ የአብይ አማካውን ሰው ንግግር በአሥሮ ኃላፊነቶችና 7ቱ የደኅንነት ግዴታዎች እንመዝናቸው፦
ዳንኤል ክብርት በቪዲዮ ቃለ መጠይቅ የተናገሩት እንደ ወረደ፦ “ዛሬ በየጎሬው ያለው ሰይጣን የተለቀቀበት ግዜ ነው። አንዱ ምንድነው ነጻነት የሚያመታው ችግር ሁሉም ከየዋሻው የወጣል፤ እሳቸው በተደጋጋሚ እንደሚሉት አንድ ዝግ ቤት ሁለት አማራጭ ነው ያለው፤ ወይ ክፍተሽ አድሰሽ ማጽዳት፣ እንደርሱ ስታደርጊ የሻገተው፣ የሚሸተው ምን የሚለው እስክታውጭው በጣም አደጋ ነው፤ አያስፈልግም ካልሽ ደግሞ አፍርሶ መሥራት። አገር ሲሆን የምትመርጭው አፍርሶ መሥራት አይደለም፤ አገር ሲሆን በሩን ክፍተሽ ችለሽ፣ ውስጥ ገብተሽ፣ ትንፋጉን ተቋቁመሽ ነው የምታድሽው፤ አሁን ገብተው ያዩት ሰዎች ምንድነው ይኼ ቤት ብለው ሊያማርሩ ይችላሉ አሁን ባለበት ሁኔታ፤ እኔም እርሳቸውም የሚታየን የአሁኑ ጠረን አይደለም፤. ጠረኑን ተከትሎ የሚመጣው መዐዛ ነው፤ አሁን ያልውን ጠረን አየተሽ ቤቱን ከገመትሽው በፍጹም --- ያ ማለት ምን ማለት ነው? ያኔ እርሳቸው ወደ ለውጥ በመጡበት ግዜ አንድነት ፓርክ የተባለውን እንደማየት ነው፤ እኔ አስታውሳለሁ፣ እኔ እርሳቸው አቶ ለማ መገርሳ ከቢሮ ኑ ኑ አንድ ነገር ላሳያችሁ ብለውን ሄድን፣ መንገድ ላይ አቆሙና መኪና በእግር ግማሹ ቦታው ገደል ነው፣ ገደልነቱ ገደል ብቻ አይደለም ለወታደሮች የተሠራ መጽዳጃ ቤት ሆኖ የእንጨት ርብራብ ሆኖ ውስጡ ሁሉ ልትገቢ ትችያልሽ፣ አንዳንዱ የፈረሰ ቆርቆሮ ቤት ነው፣ አስታውሳለሁ፣ ቅድምም እየተናገርኩ ነበር፣ ኑ በዚህ በኩል ተሻገሩ በለን ስንሄድ ለጥቂት ነው የተረፉት በገደሉ በኩል አልፈው ለጥቂት --፣ አለ ህሊናዬ ውስጥ ሁል ግዜ አለ እርሱ ነገር (የዘገነነውና ያዘነ ፊት እያሳየ)፤ እንደዚያ አይነት አስጠሊታ ግቢ ውስጥ ነው የነበርነው፣ ግን ያንን ሽታ፣ አፈር እየወጣ የወጣ ቆሻሻ እኮ እኔ አስታውሳለሁ፣ ዛሬ የሚያየው ሰው እኮ ሌላ አንድነት ፓርክ እኖ ነው የሚያየው፣ ያንን የት ያያል? ያኔ አንች ብትሄጂ እዚህ ግቢ አልመጣም ነው የምትዪው፤ በቃ ይኼን ግቢ አታሳዩኝ ነው የምተዪው። እዚህ ግቢ የምትመጭው መች ነው? ነገ የሚሆነውን ካወቅሽ ነው፣ ነገ ምን ሊሆን እንድሚችል ካወቅሽ ትችይውና ገደልም ውስጥ እየወድቅሽም ቢሆን፣ ቆርቆሮ እየቆረጠሽም ቢሆን ተሠሪዋለሽ። አንድ ቀን ቤተ መንግሥት ገብቶ የማያውቀው ሁሉ የምንልክን ቤተ መንግሥት ሊያፈርሱ ነው ነው ይላል፤ አፍርሰን ብንጠብቀውም እኮ የሚያውቅበት እድል እኮ የለዉም፣ የት ያየዋል? አይቶት አኮ አያውቅም፣ በዚያ በኩል እንደዚህ ሲዞር በል እየተባለ አይደል እንዴ ሰው ሁሉ ሲያልፍ የነበረው? ግን ሊያፈርሱ ነው ብሎ ያወራል። ያን ሁሉ በመቋቋም እንዲወጣ ተደረገ። ከዚያስ የነበሩትን ቅርሦች ማንበር፣ ሜይንቴን ማድረግ፣ የግብር አዳራሹን፣ ዙፋን ችሎቱን፣ ቀዳማ ኃየለ ሥላሤ የነበረውንና በኋላ አቶ መለስ የኖሩበተን፣ የእንቁላ ቤቱን፣ የንግሥት ዘውዲቱ ማነው አዎ የንግሥት ዘውዲቱን፣ የእቴጌ ጣይቱን፣ የአፄ ምንልክ ቤት የነበረውን እነዚህን እነዚህን ደግሞ ባሉበት ማንበር። እርሱ ብዙ ዋጋ የጠየቀ በዙ ገንዘብ የጠየቀ -- ሶስተኛ ድግሞ አዲስ እሴት መጭመር፤ ብዙ ሰው ሁል ግዜ የምንልክን ቤተ መንግሥትና የግብር አዳራሽ ለመጎብኘት አይመጣም፤ እዚያ ምግብ ቤቶች ተከፍተዋል፣ የመጽሐፍት መሽጫዎች ተከፍተዋል፣ የመዝናኛ ሜዳዎች ተከፍተዋል፣ የኢትዮጵያን ክልሎች የሚያሳዩ እልፍኞች ተከፍተዋል፤ እነዚህን ደግሞ መጨመር፤ እነዚህ በደርስሽበት ስታይ እኮ ሌላ ኢትዮጵያ እኮ ነው የምታዪው፤ ተጠርጎ ስትመጭ ያኼ ነገር ንጹሕ ሆን ትያልሽ፣ ተጥግኖ ስትመጭ አረ የኼ ነግር ሊያልፍለት ነው ትያለሽ፣ አካባቢው መልከዐ ምድሪ ተሠርቶ የማሳመር ሥራ ተሠሮ ስትመጭ የኼ ነገር የተለይ ነገር ሆነ ትያለሽ፤ የሚለው፤ ይህ ነጻነት የሚያመጣው ችግር ነው፤ የጽዳ ነው፤ መንበር ያለበት ሜይንቴይን መደረግ ያለበት እየተደረገ ነው፤መጠረግ ያለበት እየተጠረግ ነው፤ እንደ አረንጓዴ መሠራት ያለበተ እየተሠራ ነው፣ መጨመር ያለበት እየተጨመር ነው፤ በየቀኑ ስታዩት ከዚያ እየወጣ ነው። በአሁኑ አትፍረዷት ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያ በመሄድ ላይ ናት፤ ለእኔም የሚታየኝ እንደዚያ ነው፣ እርሳቸዉም የሚታያቸው እንደዚያ ነው።”
የብልጽግና ቡድን የመንግሥት፣ የሕዝብ፣ የልማት፣ እና የአገር አረዳድ ውድቀት
የብይ አህመድ የመንግሥት ኃላፊነትና ግዴታዎች አረዳድ በዳንኤል ንግግር ውስጥ በቻ ሳይሆን የብለጽግና ጋድሬዎች፣ ፓርላማ ላይ የሚቀርቡ ዘገባዎች፣ አብይ የሚመሠርታቸው ማዘናጊያ ኮሚሽኖች፣ ሚዲያዎች፣ የብልጽግና ፓስተሮች ከሚነገሩን ምን የተለየ አይደለም። የዳንኤል ክብረት ቃለ መጠይቅ የአንድነት ፓርክ አልሚ ኮንትራክተር ወይንም አንድ የቱሪዝም ልማት ባለሥልጣን ቢናገረው በዙ አግባብነት ያላቸው ይዘቶች አሉት። ነገር ግን ጠቅላይ ምንስትሩን፣ መንግሥትን፣ አሁን ሕዝቡ ያለበትን ጉስቁልና፣ መፈናቀል፣ የጅምላ ፍጅት፣ መታፈን፣ መንግሥታዊ የአገር ውስጥ ዘር የማጥፋት ጦርነት የቤተ ክርስቲያን አንደነት ላይ አብይ አህምደ በቀጥታ እነሳዊሮስንና ዳንኤልን ራሱን በመጠቀም የሰነዘርው የመበተን ጥቃት የሕዝብ ቀዳሚ ጥያቄ ሆነው በሚገኙበት ይህ ንግግር በ10ሩም የአንድ መንግሥት ተቀዳሙ ኃላፊነቶችና 7ቱ የድኅንነት ሚዛኖች ውድቅና እጅግ ይህን መንግሥት ተብዬ የቁስና የብልጭልጭ ትኩርት ከማጋለጥ ያለፈ ፋይዳ የለውም።
እስቲ ንግግሮቹን አልፈን አልፈን እንድምታቸውን እንመልከት፦
ዳንኤል፦ “ዛሬ በየጎሬው ያለው ሰይጣን የተለቀቀበት ግዜ ነው። አንዱ ምንድነው ነጻነት የሚያመጣው ችግር ሁሉም ከየዋሻው ይወጣል፤--“
ብልጽግና ለኢትዮጵያ ዜጎች ሁሉ አየተዉት የማያውቁትን እኩል ነጻነት ስለሰጠ፣ ነጻነት ያለመደውና ሰይጣን የሆነው ዜጋ ከተደበቀበት ብቅ ብሎ ጥያቄ መጠየቅ ጀመረ ይለናል “ሙሐዘ ጥበባት”። በአብይ አህመድና የዳንኤል ክብረት የብልጽግናና የመደመር አስተሳስብና ፍልስፍና ሲተረጎም፦
• አዲስ አበባ አትገባም፣ ልዩ መብትና ባለቤት ነት ያለን እኛ ነን፣ እናንተ እጣ ፈንታችሁ በየመንገዱ መታፈንና መዘርፈ መገደልና መሰደድ፣ መደኽየትና መታሰር ነው።
• ይህ ተጨባጭ ሁኔታ የማይመለከታቸው ጥቂት የሥርዓቱ ተጠቃሚዎችን አሳዳጆች የሚያድርጉት ጥቃት የነጻነት ምልክት ነው።
• የተጠቂዎች ማጉረምረም የሰይጣን ከየጎሬው መውጣት መገለጫ ነው። ቤተ የፈረሰባቸ፣ እድርና ሰንቤቴያቸው የተበተንባቸው፣ የለመዱት ትሥርና አነስተኛ ንግድ የተፈናቀሉት እና የሚያለቅሱት ሰይጣኖች ናቸው።
• በአርሲ፣ በወለጋ፣ በከሚሴ፣ በባሌ፣ በሀረርጌ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ የሚፈናቀሉትና የሚጨፈጨፉት፣ በትግራይ በሕውሃት ቡድን እኵይ ሤራና በአብይ ሥራአት አገር መምራት አለመቻል በርሃብና በጦርነት የሚረግፈው ሕዝብ ድምጽ ማሰማቱ ሰይጣንነት ነው።
እነዚህ ለሥቃይ የተዳረጉት ወገኖቻችን ዳንኤልና አለቃው አብይ አስተሳሰብና እምነት መሠረት እንዲህ ይገለጣል፦ “እሳቸው በተደጋጋሚ እንደሚሉት አንድ ዝግ ቤት ሁለት አማራጭ ነው ያለው፤ ወይ ክፍተሽ አድሰሽ ማጽዳት፣ እንደርሱ ስታደርጊ የሻገተው፣ የሚሸተው ምን የሚለው እስክታወጭው በጣም አደጋ ነው፤ አያስፈልግም ካልሽ ደግሞ አፍርሶ መሥራት። አገር ሲሆን የምትመርጭው አፍርሶ መሥራት አይደለም፤ አገር ሲሆን በሩን ክፍተሽ ችለሽ፣ ውስጥ ገብተሽ፣ ትንፋጉን ተቋቁመሽ ነው የምታድሽው፤ -- አሁን ባለበት ሁኔታ፤ እኔም እርሳቸውም የሚታየን የአሁኑ ጠረን አይደለም፤. ጠረኑን ተከትሎ የሚመጣው መዐዛ ነው፤ “ --- ሲል እየነገርነ ያለው፦
• ኢትዮጵያ የምትሽት፣ ትፍገቷ የማያስቀርብ፣ የሻገተች ናት፤ ላልፉት 50 ዓመታት ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑት የባእዳን ተላላኪ የጎሣ ፖለቲካ ልሂቃን እና ውጭ-ግቦቹ የቅኝ ገዥዎችና የጂሃድ ደም ጥመኞች በፈጠሩት የጥላቻና አፍራሽ የሐሰት ትርክታቸው ሲሰብኩን እንድኖሩት ሁሉ ኢትዮጵያ ጠረኗ የከፋ ነው። ስትታደስና መልሳ እንርሱ በሚሹት መልክ ሲሰሯት መልካም መዐዛ ይኖራታል ይሉናል።
• በጅምላ ፍጅተው በቡልዶዘር የሚቅብሩ፣ ከአረብና ከተሸናፊዎችይ የውጭ ወራሪዎች እርዳታ ተቀብለውና ተመክርው በቦንምብ የሚፈጁት ሕዝብ የሥጋቸው ብስባሽ፣ ከተማ ቦታ ለይተው እንደ ደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ልዩ ጥቅም የሚሰጡትና የሚነፍጉት ሕዝብ ምሬትና ልቅሱ ለአብይን አህመድና ለዳንኤል ክብረት አይነቶቹ መልካም መዐዛ ለማሽተት የሚደረግ ጉዞ ነው።
• መግደል ማፍናቀልና ማሳደድ፣ ታሪክ መደልዝና ብልጭልጭን ገባያ ማውታን በእንዚህ ሰዎች ስሌት የሻገትና የሸተተ ያሉትን ኢትዮጵያዊ ማንነት፣ አንድነት፣ እምነት፣ ታሪክና አሻራ መደምሰስ ነው።
ዳንኤል ገጽታ ግንባታውንና በቻለው መጠን ማደናገሩና፣ ያለፈውን እያጣጣለ በአንድነት ፓርክ ከመሠራቱ በፊት በነበረው የካባቢው ጉስቁልና ኢትዮጵያን እየመሰለ፣ ፓርኩ ካለቅ በኋላ የበለጽግና መንግሥት ኢትዮጵያን የወደፊት ተስፋን ምሳሌ እየመሰለ ሲቀጥል እንዲህ ይላል፦
“ አሁን ያለውን ጠረን አየታየሽ ቤቱን ከገመትሽው በፍጹም --- ያ ማለት ምን ማለት ነው? ያኔ እርሳቸው ወደ ለውጥ በመጡበት ግዜ አንድነት ፓርክ የተባለውን እንደማየት ነው፤ እኔ አስታውሳለሁ፣ እኔ እርሳቸው አቶ ለማ መገርሳ ከቢሮ ኑ ኑ አንድ ነገር ላሳያችሁ ብለውን ሄድን፣ --- ኑ በዚህ በኩል ተሻገሩ በለን ስንሄድ ለጥቂት ነው የተረፉት በገደሉ በኩል አልፈው ለጥቂት --፣ አለ ህሊናዬ ውስጥ ሁል ግዜ አለ እርሱ ነገር (የዘገነነውና ያዘነ ፊት እያሳየ)፤ እንደዚያ አይነት አስጠሊታ ግቢ ውስጥ ነው የነበርነው፣ ግን ያንን ሽታ፣ አፈር እየወጣ የወጣ ቆሻሻ እኮ እኔ አስታውሳለሁ፣ ዛሬ የሚያየው ሰው እኮ ሌላ አንድነት ፓርክ እኖ ነው የሚያየው፣ ያንን የት ያያል? ያኔ አንች ብትሄጂ እዚህ ግቢ አልመጣም ነው የምትዪው፤ --- እዚህ ግቢ የምትመጭው መች ነው? ነገ የሚሆነውን ካወቅሽ ነው፣ ነገ ምን ሊሆን እንድሚችል ካወቅሽ ትችይውና ገደልም ውስጥ እየወድቅሽም ቢሆን፣ ቆርቆሮ እየቆረጠሽም ቢሆን ተሠሪዋለሽ። ---- --- ብዙ ዋጋ የጠየቀ በዙ ገንዘብ የጠየቀ -- ተሠራ--- እነዚህ በደርስሽበት ስታይ እኮ ሌላ ኢትዮጵያ እኮ ነው የምታዪው፤ ተጠርጎ ስትመጭ ያኼ ነገር ንጹሕ ሆን ትያልሽ፣ ተጥግኖ ስትመጭ አረ የኼ ነግር ሊያልፍለት ነው ትያለሽ፣ አካባቢው መልከዐ ምድሩ ተሠርቶ የማሳመር ሥራ ተሠርቶ ስትመጭ የኼ ነገር የተለየ ነገር ሆነ ትያለሽ፤ ---- መጠረግ ያለበት እየተጠረገ ነው፤ እንደ አረንጓዴ መሠራት ያለበተ እየተሠራ ነው፣ መጨመር ያለበት እየተጨመር ነው፤ በየቀኑ ስታዩት ከዚያ እየወጣ ነው። በአሁኑ አትፍረዷት ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያ በመሄድ ላይ ናት፤ ለእኔም የሚታየኝ እንደዚያ ነው፣ እርሳቸዉም የሚታያቸው እንደዚያ ነው።”
• አለቃዬ አሁን ያለውን ኢትዮጵያዊ አስከፊና አጸያፊ ጠረናችሁን ችሎ ነው እያጸዳችሁ ያለው። መጠረግ የሚገባውን እየጠረገ ነው፤ አፈርና ቆሻሻ የሆናችሁት እየወጣችሁ ነው።
• የብልጽግናን ሥራ በተለይ ጠረጋውን፣ ማፈናቀሉን፣ መግደሉን፣ ማደኸይቱን፣ ፍትሕ መንፈጉን፣ አገር ውስጥ ጦርነት ማካሄዱን፣ የገርን ድንበር አሳልፎ ለሱዳን መስጠትቱን፣ አግርን በጎሣ ከፋፍሎ ባለልዩ መብትና ተሳዳጅ መፍጠሩን ሁሉ “ኢትዮጵያን በሁኗ ስትፍረዷት --- በመሄድ ላይ ናት፣ ለእኔ ለዳንኤል ክበረትና ለአለቃዬ ለአብይ አህመድ የሚታየን ነገ እንጂ የእናንተ የብዚኃን የዛሬው ሥቃይአይደለም” --- ነገ ጠርገናችሁ ኢትዮጵያን በኦሮ-ዉህቢዝምና በተረፈ-ናዚዎቹ የአእምሮ ባሮች በኦነጎች አምሳል የምትሥራ ኦሮምያ የምትባል አገር ትታየናለች። ሌንጮ ባቲ እንደነገራችሁ ልጅ ሲወለድ ደም ይፈሳል፣ አዲስ አገር ኦሮምያም ስትፈጠር መጠረግ የሚገባቸው ወግኖች ያልቃሉ” --- ይለናል።
የብልጽግና መንግሥት አስተሳሰብም ድርጊትም 10ሩን የመንግሥት ተቀዳሚ ኃላፊነቶችና 7ቱን የደኅነት መጠበቅ ግዴታዎችን ሙሉ በሙሉ የተቃረነ፣ መንግሥት ሊባል የማይገባው --- የወሮበሎችና የነፈሰገዳዮች ማኅበር ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት፣ በነባርነት፣ በኦርቶዶክሳዊነት ላይ ቂም ባላቸው ተሸናፊ ቅኝ ገዥዎችና ጂሃዲስቶች ተላላኪነት የተዋቀረ በአካለ ሥጋ ኢትዮጵያዊ በአእምሮ ውቅሩ የጠላትን ፍላጎት የሚያሳካ አጥፊ ሥርዓት ነው፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ