ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ቤተ ክርስቲያን ላይ ቅሬታ አለኝ የሚል እርሱ ማነው?

በቤተ ክርሲያን ላይ ቅሬታ አለኝ የሚል ሰው ማነው? ስድቡ ይገባዋል? አምላክ ላይ መቂጣቱን ይረዳል? አንድ ሰው #ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ላይ ጥላቻ ቀርቶ #"ቅሬታ አለኝ" ከአለ፣ "በእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ቅሬታ አለኝ" ማለቱ ነው። ቤተ ክርስቲያን ሰማያዊው አምላክ የክርስቶስ ሰማያዊ መንግሥቱን በመስቀል ላይ በፈቃዱና በፍቅረ-ስብእ በፈጸመው ሞቱ ለምድራውያን ገልጠ። ይህ መገለጥ ለተቀበሉትና ወደፊትም እስከ ዳግም ምጽዐቱ ለሚቀበሉት ምድራውያንን ከሰማያውያን ያወሐደባት፣ እርሱ ክርስቶስ ራስ በሆነላት በአካሉ በቤተ ክርስቲያን (በከርስቲያን አንድነት) የአካሉ ብልቶች ያደረገባት ናት። ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ራስነት እና በተቀበሉት ብልቶቹ አንድነት ምክንያት መጉደል፣ መወየብ፣ ማነስ፣ መለዋወጥ፣ መወሰን የላባትም። ለውጥ፣ መጉደል፣ ማነስ፣ መወይብ፣ መጥቆር ከታየ፣ የእርሷ አይደለም። በስሟ የሚጠሩ፣ በስሟ የተካኑ ነገር ግን ከማይለወጠው ራስ ተለይተው የተቆርጡና በሌላ ሙት ራስ ስር የተኮለኮሉ ሙታን ጉባኤ ነው። በርግጥ በዚህ ምድር ያለን የአካላቱ ብልቶች ከታላቁ ሰማያዊ ማኅበር አንጻር ስንታይ ጥቂቶችና በእንድ የግዙፍ ሰው አካል ላይ ከሚገኙ ብልቶች እንደ እንድ ጣት ልንቆጠር የምንችል ነን። እንደዚሁም ሆኖ በቁጥር የዚህ ማኅበር አባላት መቶ ሚሊዮኖች ነን። በአህጉረ ስብከት አሥራ ሙሊዮኖች፣ በአጥቢያ አሥራ ሺዎች እና አሥራ መቶዎች፣ ብሎም በስደት ስንበታተን መቶዎችና አሥራዎች እንሆናለን። ከሕያው ግንድ ከክርስቶስ የአካል ብልትነት ቡድን ሆነን እንዳንከፈልና ለሕይወት ባእዳን ነገር ግን ለሞት ደቀ መዝሙር እንዳንሆን፣ ኢአማኒም ሆነን በግል ተቆርጠን እንዳንርቅ የሚጠብቁን ክርስቶስ ልዩ የሆነ ሥልጣን የሰጣቸው ግለሰቦች እና ስብስባቸው አለ። እርሱም ካህናትና ቆሞሳት ናቸው። ስልጣናቸውን የሰማያዊ አምላክ በትርና መሪ ብርሃን እንዲሁም ሕይወትና ሰይፍን ያጣመር ልዩ መገለገያ #ክህነት ነው። ክህነት የዘላለም ሕይወት በትር ናት! የቤተ ክርስቲያን ህልውና መሠረት፣ የማኅበሩ መደምሪያና መዋሐጃ አማራጭ የማይገኝለት የመንፈስቅዱስ ጽጋ የሚናኝበት የክርስቶስ እጅ ናት። በትሯን ሳይዙ የያዙ መስለው ሞትን በዓልም ያንሰራፉትም በዚሁ ስም የተጠሩና በዲያብሎስ የተውሰዱ ጥቂት መናፍቃን፣ ከሃዲዎች፣ ምንደኞች፣ ቅድስና የጎደላቸው ከንቱዎች ናቸው። በአገራችን ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም፣ ዘንድሮና ድሮ በቻ ሳይሆን ከጥንት ጀምሮ ወደዚህ ልዩ አግልግሎት ከሚመጡት መካከል ጥቂት አጥፊዎች ሰረገው ገብተው ከይሁዳ እስከ ዛሬው ሠረቀ ብርሃንና ሳዊሮስን የመሰሉ የጎሣ ፖለቲካ ርእዮት ተልእኮ ተሽክመው ከታላቁ የዘልዓለም ሕይወት ግንድ ላይ እየቆረጡ ከሙት የጎሣ፣ የኑፋቄ፣ የፍቀረ ንዋይ ማኅበር ጋር የሚደምሩ ነበሩ። ዛሬም ተንሰራፈተዋል። በዚህ እይነት መንገድ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች ከሳቱ ሙታን የዓለማውያን የፖልቲካ መሪዎች ጋር በመጣመር ዓለምን አሠዝመዋል (እንደ ምሳሌ የቤዛንታይን ክርስትና ወደ ሮማ ካቶሊክ፣ ኑፋቄ፣ ክፍደት፣ ሴኩላር በማድረግ ለዳርዊን፣ ለማርክስ፣ ለፈረንሳይ አብዮተኞች፣ ለሜንሼቪክ እና ቮልሼቪክ) መፈጠር በቻ ሳይሆነ ዘረኝነትን፣ ቅኝ ገዥነትን፣ ባሪያ ፈንገላን፣ ዘር ማጥፋትን፣ ስግብግብነትን በዓለም እንዲሠራንፋ ምክንያት የሆኑ መንግሥታትና የፖለቲካ ርእዮቶችን እንዲነግሥ ያስቻሉት ወደክህነት ገብተው በትቃራኒ ሚና የተገኙት ናቸው። ይህ አውሮፓን አጥፍቶ ወደ ተረፈችዋ ኢትዮጵያ በስፊ እጁ የመጣው በዘመነ መሳፍንት እና ራሱን በመንግሥትነት የሰየመው በንፈሰ ገዳዩ ጄኔራል መንግሥቱ ንዋይና ወንዱም ግርማሜ ንዋይበር ከፋችነት እሰክ ዛሬ ለደረስንበት ነፈሰ ገዳዮችንና ዘረኞችን "ብፁዕ" የሚል ሲኖዶስ እና ክርስትናና በመዋቅር የሚያጠፋ የብልጽግና መንግሥት እደረሰን። ሰይጣን ከሁሉ ተንኮሎቹ በላይ ወጤታማ የጥፋት መንግደ ሆኖ ያገኘው ሰዎች የቤተ ክርስቲያንን ብርሃን እንዳያዩ እንዳይረዱ "ቤተ ክርስቲያ፣ ክርስቲያን፣ ካህን፣ አባት፣ ዘማሪ፣ ሰባኪ" በሚሉ ሽፋኖች ወስጥ የሚኖሩ አስመሳይ ሙታንን ሕያዋን አስመስሎና ዝናቸውን ናኝቶ ምእመናንን በሚሊዮኖች በጭፍን መንጋነት መንዳት መቻሉ ነው። አንዳዶች እውነትና ተናጋሪ አባቶች ሲታዩ ተስፋ ያጭራሉ። ያደፈጡት ወንጀለኞች ቢባሉ ክሱ አይበዛባቸዉም፤ ምክንያቱም እረኛ ሆኖ በጎቹን በማድፈጥ የሚያስበላ፣ መብራት ይዞ ብዙኃንን በጨለማ ውስጥ ጥሎ የሚደበቅ፣ እውነትን ይዞ ሐሰት ከግለ ሰቦች ስሕተትነት ወደ መንግሥታዊ ሥርዓት ስታድግ ያልሞገት፣ በጎቹን አሰልፎ በትኩላዊ ፊት ዘምሩ እያለ የሚያስበላ "ካህን" ነኝ ማለት አይችልም። ክህነቱ ክርስቶስን ሳይሆን የከርስቶሳውያንን ጠላት የሚያገለግል የሞት በትር ሆኗልና። እስቲ ብዙ አስተራየ ጽጌዎችን እግዚአብሔር እንዲያስነሳልን እንጸልይ። https://youtu.be/fAKXR9mdQLA?si=b0NX7CpysXtksG3H

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...