ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ፋኖ፣ ሞዐ ተዋህዶና ብልጽግና

"ሞዐ ተዋሕዶ የለም" ካላችሁ ሰለሌለ ነገር የሚያንጫጫችሁ ምንድነው? ዘወትር የሚገርመኝ ነገር አለ። እርሱም የሰው ልጆች ግብዝነት፣ ትዕቢት፣ በአለማወቁ እየኮራ ታላላቅ ነገሮችን ሳይቀር ከአቅሙ በላይ ሲናገር ነው። ለምሳሌ ኤቴይስቶች እንde Bertrand Russell (1872–1970) , David Hume (1711–1776) , Friedrich Nietzsche (1844–1900), Jean-Paul Sartre (1905–1980) , Christopher Hitchens (1949–2011) , Richard Dawkins (1941–present) , Charles Darwin (1809–1882), Albert Einstein (1879–1955) , Carl Sagan (1934–1996) , Stephen Hawking (1942–2018), Alan Turing (1912–1954) , Mark Twain (1835–1910), George Orwell (1903–1950), Salman Rushdie (1947– ወዘተ ያሉ ፍልስፍናን በክህደት ላይ የመሠረቱ የክርስትና ትጻራሪዎች ሕይወታቸውን ሙሉ የሠሩት "እግዚአብሔር የለም" የሚለውን መላምታቸውን ለማሳመን ነው። እንዚህ ሰዎች ብዙ መንጋ ምሁራንና ጨቅላ ተከታይ ወጣትና ትውልድ በማፍራታቸው የዓለምን ፖልቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ጂኦ ፖልቲካዊና ዲፕሎማሲ ሁሉ ቀይረዉታል። ብዙውን ጊዜ የዋሓንን ለማስከተል የሚተቀሙት --- ሃይማኖት ወይንም በእግዚአብሔር ማመን ለሥልጣኔ፣ ለሰላም፣ ለእውቀት ልማት፣ ለቀና ዲሞክራሳዊ ሥርዓት፣ ራስን እንደሚገባ ለመግለጽ እንቅፋት ነው። እኛን ከሰማችሁ ነጻ ትወጣላችሁ" የሚለ ነው። በእኛ አገርም ልጆች ተወልደዉላቸዋል። የ60ዎቹ ትውልድ፣ ሻዕብያ፣ ወያኔ፣ ኦነግና መንጋዊ የዚህ ሂደት ሰለባዎች ናቸው። የሰ ልጅ አንዴ ከሳተና ስሕተቱን በሃይማኖት ደርጃ መከተለ ከጀመረ ይታወራል። እግዚአብሔርን "የለም!" ብሎ ሲከራከር ዓይኑን አያረገብግብም። ዝምም አይልም፣ ለዚህ ሐሳቡ ተከራክሮ መጽሕፍት ያሳትማል። የሚከተለውም ያገኛል። አንድ ሰው ውይንም ቡድን ስለ አንደ ሌለ ነገር "የለም" በሎ ከበየነ በኋላ መልሶ ስለ ነግሩ መልሶ መላልሲ ለምን ይናገራል? ለምን ሚዲያ ያዘምታል? ለምን ማሰልጠኛ ሰነድ አዘጋጅቶ ጸረ- ኦርቶዶክስ አቋሙን በሞዐ ተዋህዶ ስም ያናፍሳል" እነዚህ ቀንና ሌሊት በጎጥና በቡድን ምሪዎቻቸው በኩል ልክ ሕውሃትና ኦነግ የሕሰት ትርክት ፈጥረው ኢትዮጵያን ለማፍርስ በምሥራት ዛሬ ላይ በማራ ሕዝብና በኦርቶዶክሳውያን ላይ የህልውና አደጋ እንደ ጋረጡት ሁሉ --- የህልውና አአደጋዊን ልቀለብስ ጫካ የግባውን ውድ እና ጀግና ወጣት ደም እያሰፈሰሰ --- መልሶ የሐሰት አመንጭቶ ጸረ-ኦርቶዶክስ ትርክትን በሞዐ ተዋህዶ አንጻር ማሰራጨት ጀመረ? ውድ ሕይወቱን በኦርቶዶክሳዊነቱ እንዳይተባብርና በቋንቋ ጎሣ ተከፋፍሎ እንዲበታተን ከተደረግ በኋላ "በነፍጠኛ/አማር" ኮድነት እንዲጠፋ የ50 ዓመታት አሰቀድሞ የተጀመረውን የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ዘር የማጥፋት ጉዞ ለመቀልበስ ተሰልፎ ሕይወቱን እየገበር መልሶ የሞዐ ተዋህዶ ጠላት አድርገው ሲሰብኩት ሠርጎ ገቦቹን የማራና የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች እንዴት ሊታገሥ ቻለ? #ለምንስ ለክሳችሁ #የሚቆጠር #ማስርጃ #አቅርቡልኝ የሚል ጥያቄ ሳያነሳ ቀረ? --- ምክንያቱም ከ50 ዓመት ወዲህ የተነሳው ትውልድ በአብዛኛው ፍለጋው እውነት፣ ፍትሕ፣ ሰባዊ ክብርና ቅድስና አይደለም። ስሜትን አሁን እና እዚሁ ማርካት፣ ለዚህ ያደርሰኛል የሚለውን ጀግና በጭፍን መንጋነት መከተል ሆኗል። አጀንዳና ግቡን አሳንሶ ግለሰብና ዝነኛን ወደ አምላክነት የማጎን ባህልን ወርሷል። እግዚአብሔርን የሁሉ ነገር ማንጸሪያ አለማድረግ ለዚህ አይነት ግራ መጋባት ይዳርጋል። እግዚአብሔርን የለም የሚል ሰው አንድ ጊዜ "ናና አብርነ እናምልከ" ለሚሉት ሰዎች "አላምንም" እና አልመጣም ማለት የበቃው ነበር። ከተናገረም አንዴ ለራሱ ብቻ የተናግሮ የካደውን አምላክ እንደ ሌል አድርጎ በመኖር አለ ወይንም የለም የሚል ክርክር ሳያነሳ ያለመረብሽና ያለመስበክ መኖር ይችላል። ነገር ግን የእግዚአብሔር መኖር በፍጥረቱና በህሊናው እየጮኸበት፣ ያዩትና የሚያመልኩት ተረጋግተው ሲኖሩ እያየ የጨንቃል፤ እናም ያላማቋረጥ ይንጫጫል። በሞዐ ተዋህዶ ንቅናቄ አንጻር ኦርቶዶክሳውያን ክ50 ዓመታት ወዲህ ለምን መንቃት ጀመሩ የሚለውም ጠላይ ይንጫጫል። ጫጫታውን የጀመረው ብልጽግና፣ ዉሃብያና በተለይ ዳኔል ክብረትና መንግሥት የመደበለት የሚዲያ መንጋ ነው። --- አሁን ግን ፋኖ ውስጥ ሠርገው የገቡት የጠላት ተላላኪዎችም ዳኔል ተከትለው ጸረ ኦርቶዶክስ ድብቅ አጀንዳቸው ፍንድቶ ወጥቷል። የቤተ ክርስቲያናችን የውስጥ ጠላቶችም ሆኑ የአብይ አህመድ የአእምሮ ባሪያ ዳኔል ክብረትን ተከትለው እንደ ዕቃ የሚመላለሱ ሰዎችም እንቅልፍ አጥተው እርሱ "ጽንፈኝነትን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት ውስጥ መዋጋት" በሚል የዛሬ 3 ዓመት የጀመረውን ዘመቻ አስፋፍቶና አጠናክሮ በታዬ ቦጋል፣ በናትናኤል መኮንን፣ በሲሳይ አጌና፣ በአብበ ቶላ ላይ ጭኖ ከማንጫጫት ፋኖ መካከል ብልጽግና፣ ሕወሃት፣ ጽረ ኦርቶዶክስ የሆነው የውጭ አካል ተባብረው ጸረ-ሞዐ ተዋህዶ መዝሙር ሲዘምሩ ቆይተዋል። የሐሰት ትርክታቸውና ማጠልሸታቸውን ከዉሃብያ ጋር አስተባብረው በአብዱል ጀሊልን የአሸባሪዎቹ መንገር ጠራጊና አመቻች ዑስታዞችም በኩል አስጩኸዉት ---- ውሉ ሲጠፋቸው አዲስ ዘፈን ጀምረዋል። እርሱም "ሞዐ ተዋህዶ የለም" የሚል ነው። ስለሌለ ነግር ምን ያንጫጫቸዋል? ጥያቄው ከሌለ ለምን በዘምቻ ማጠልሸቱ አስፈለገ? ከሌለ የለም ብላችሁ ለምን ዝም አትሉም? የሚለው ነው። ሞዐ ተዋሕዶ የሚያሳምማቸው የኦርቶዶክሰ ተዋሕዶ ክርስትና ጠላቶች ከግርማሜ ንዋይ እስከ ዛሬው የፋኖ ውስጥ ሠርጎ ገቦች ድርስ ክርስቲያኖች አግራቸውንና ቤተ ክርስቲያናቸውን ተነጥቀውና ዒላማ ተደርገው እንደ በግ ሲታረዱ --- በአንድነት ጠላቶቻቸውን በውል አውቀው፣ መዋግኒያውንም ተስማምተዉበት ቢነሱ እንዚህ አሁን ምድር አይብቃን ያሉቱ ሁሉ በሳምንት እንደሚበንኑ ያውቁታል። ሞዐ ተዋህዶ የሚያስፈራቸው ይህን ንቃት ይፍጥራል የሚል ክፍተኛ ጭንቀት ነው። በተለይ በተለይ ብልጽግና ውንጌሉ መንግሥት፣ የዘር ድርጅቶች፣ ዉሃብያ የሽብር ኢንኩቤተር፣ ኦርቶዶክስን ለዘመናት አድበተው ሲወጉ የኖሩ አካላት ዛሬ ላይ --- "ኦርቶዶክስን ለማጥፋት፦ * አማራን ማዳከም፣ * የትግራይን ሕዝብ አእምሮ አጥቦና ከክርስትና ለይቶ በሃይማኖታቸው ምትክ "ትግራዋይነት/ሕወሃትነት" በምትባል አዲስ ከክርስቶስ የምትበልጥባቸው "እምነት" በመፍጥር ማስካድ፣ * ኦሮሞ ክርስቲያኖችን "ኦሮሙማ ከእምነቶች ሁሉ በላይ ነው" በሚል የጨለማ መፈክር ሕዝቡን ከኦርቶዶክሳዊነት ማስወጣትና ማዳከም፣ --- በመጨረሻም አሁን እንደሚያደርጉት እርስ በርሱ ማጫርስ ዓላማ አድርገው የሚሠሩት ቡድኖች ---- #ሞዐ ተዋህዶን መርጃ በማይደርሳቸው #የፋኖ አባላትና በባእዳን ትልእኮ ተሸካሚነት ወደ ፋኖ አመራር የወጡ ጮሌዎችን በመጠቀም ጸረ-ኦርቶዶክስ ንቅናቄን በፋኖ መካክል ለመትከል እየዋተቱ ይገኛሉ። ዉሃብያው ስንኳንስ ኦርቶዶክሳዊ ክርስትና የግዕዝ ፊደል "ሃይማኖት" ነው ብሎ እስከመቃውም ስልደረሰ አያስገርምም። የሚያስገርመው ፋኖ ውስጥ ሠርገው ገብተው በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላየ በሞዐ ተዋህፎ አንጻር የዘመቱን ናቸው። እነዚህ ጥቂት ለጠላት የሚሠሩ አካላት ያስከተሉትና ለህልውናህ እናታግልሃለን ብለው ያስከተሉት ወጣን 99.9% በእምነቱ ኦርቶዶክሳዊ ነው። የህልውና አደጋውም የትጋረጠበት በማንነቱ ነው። ማንነቱ ሃያማኖቱን፣ ርስቱን፣ ባህሉን፣ ማኅበራዊ መዋቀሩን፣ ታሪኩን፣ ቅርሱን ሁሉ ያጠቃልላ። "ተሰውተህ ለሥልጣን አብቃኝ፣ ነገር ግን ለህልውና አደጋ ከዳረጉህ የማንነት መሠረቶችና ዋናው የሆነውን ኦርቶዶክሳዊ ከርስትና ጠፍተህ አጥፋው" የሚል በሚመስል ነውረኝነት ጸረ-ኦርቶዶክስነትን በጸረ-ሞዐነት ሲገልጽ --- ወጣቱ ለፕሮፓጋነዳው የሚጨበጥ አንደ ማስረጃ አምጣልኝ አለማለቱ --- ኢአሕፓንና ወያኔን፣ ኦነግና ሻብዕአን ተከተሎ በከንቱ ተሰውቶ በመጨረሻም --- ማንነቱን፣ አገሩን፣ ሃይማኖቱን፣ ሀብቱን አጥቶ አገሩን የደም ግብር እያስከፈል የሚገኘው የማይጠይቅ እና በዕቀት ስም ያነበበውን የባዕድ ግሳንግሥ ሁሉ እንደ ሃይማኖት ተቀብሎ የተሰዋዉን፣ የባከነውን የ60ው0ቹን ትውልድ ያሳስበኛል። የፋኖ --- ሠራዊት ከአንዳንድ መሠሪና የጠላት መሣሪያ ፕሮፓጋንዲስቶችና የሥልጣን ጠመኞች ራስህን ጠብቅ። ለመስዋትነትህ አግባብነት ያለው ዋጋ ለማግኘት ከፈለግህ --- ፕሮፓጋንዳ ከመመገብህና ከመንዳትህ አስቀድሞ የተጨበጠ ማሰርጃ፣ ተከራካሪ የሚቀርብበትና የሚብራራ ጉዳይን መምረጥ ተማር። የዳኔል ጸረ-ኦርቶዶክስነት የመጀምሪያ ጥይትና ለአብይ አህመድ ታማኝነቱን ያረጋገጠበት የሐሰት ትርክት እንሆ ለማስታወሻ--- ጽንፈኝነት ብሎ የፈረጃቸው 7ቱ የኦርቶዶክሳውያን ጥያቄዎች እነሆ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...