#ፋኖነት የሙሉ ሰብእና የማንነት መገልጫ እንጂ እንጂ የፖለቲካ ቁማር ወይንም የተውሶ ልብስ አይደለም!
---- ብልጦችና ቁማረተኞች ወደ ላካችሁ ጌታችሁ ተጠቃላችሁ ቶሎ ቶሎ ተመለሱ!!!
ኢትዮጵያ የጠፋቸው፣ ክፍለ-ሕዝቡ የህልውና አደጋ ላይ የወደቀው በትውሶ ስሑት ርእዮት በተመሩ ተላላኪዎች ነውና ----
#ጠላትን ለማሸነፍ #የጠላትን #መልክ መንሳት #መርከስ ነው!! በእርግጥም #ድውይነት ነው!!
በርግጥ "ፋኖ" ከተባሉ በኋላ እጅ መስጠት የለም። የዚህን ምክንያት በሌላ ጽሑፍ እመለስበታለሁ።
የራሱ እሤት፣ የራሱ ሃይማኖት፣ የራሱ ታሪክ፣ የራሱ የሰውነትና የሕዝብ ተርጉም፣ የራሱ የፍትሕ ትርጉምና አፍጻጸም፣ የተደራጀ አኩሪ ታሪክ ያለው ሕዝብን የህልውና አደጋ እታደጋለሁ ብሎ ራሱን ለሞት ከሰጠ ብኋላ ገና እንደ ሕጻን ከጣላት ትምህርት እንውሰድ ብሎ ወደ ሢራና ጎጥ የሚወርድ ግለስብና ቡድን "ፋኖ" ተብሎ ሊጠራ አይገባዉም።
#የጠላትን #አርአያና #አምሳያ እየናፈቀ የሚኖር፣ እሤቱንና ማንነቱን በሥልጣን ፍተወት፣ በቁማርና በሤራ፣ በጠላት ምክር፣ በህሜት ኔትዎርክ፣ በፈጠራ ክስ አጋርና ተከታይን ግራ ማጋባትና መጠቀሚያ ማደርገ፣ በጸረ ኦርቶዶክስነት እና በባዕዳን የፖለቲካና የአስተዳደር ቀምር/ሀልዎት የናወዘ ግለስብም፣ ቡድንም #ፋኖ ሊባል አይገባዉም።
ፋኖነትስ የማይቀያየር --- ሰዋዊነት፣ ፍትሕ፣ እውነት፣ ነጻነት፣ መስዋትነት፣ ጀግንነት፣ እውነተኝነት ---- እንደ ካህን ከሌብነት፣ ክዝሙት፣ ከቅጥፈት፣ ከዘረኝነት፣ ከክህደት የተጠበቀ የቅድስና ጉዞ ነው። አሁን ግን ጸረ-ኦርቶዶክስ መሪዎችን የሚያዝል ሠራዊት፣ ጸረ ፍትሕ፣ ደም አፍሳሽና ረሻኝ፣ ውሸታም፣ ለህልውና አጥፊ እጅ የሚሰጥ፣ ባህር ማዶ ጌታ የሚያበጅ --- ሤረኛና የቁስ ሀብት ፍተወት ምርኮኛ ሠርጎ የገባበት ሆኗል፣ ነውም። ---
ነገር ገን ---- ለሚያምኑት፣ እንደ ፈቃዱ ለሚሄዱት ሁሉም የሚሆነው ነገር ለብጎ ነው እንዲሉ --- #እግዚአብሔር #ይመስገን --- እርሱ አፍቃሬ-ሰብእ አምላካችን የእርሱ ያልሆኑትን በሥራቸውና በውሳኔያቸው፣ ለአንድነት ፈጽመው እንቅፋት በመሆን እና ከሕዝቡ ህልውና የበለጠ ለግል ፍተወታቸውን፣ ለተላላኪነታቸው ባደረጉት የተራዝመ አሳፋሪ ተጋድሎ ራሳቸውን እያጋለጡ እየትንገዋለሉ ነው።
--- አንዳንዶቹ --- በቀጥታ ጸረ-ኦርቶዶክስ ክርስትና ለመሆናቸው በሞዐ ተዋህዶ ላይ በከፈቱት አሉታዊ ሁለገብ ዘምቻ ተጋልጠዋል። ይህ ዘምቻቸው ከቤተ መንግሥቱ ዴማስና ከኦሮ-ዉሃብያው ጋር የተናበበ ሆኖ መገኘቱ "ድንቄም የህልውና ታጋይ" አሰኝቷቸዋል። ተለኮአቸውም ታውቋል። --- በታሪካችን አገራዊ ለውጥ እንመራለን ያሉት ከተማሪ ንቅናቄዎች፣ ከአብዮተኞች፣ ከደርግ፣ ከኤርትራ ነጻ አውጭ እስክ ሲዳማና ኦጋዴ ያሉት ንቅናቄዎች ተጥቃለው --- "ለውጥ" ማለት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና በእርሷ አስተመህሮ ላይ የተመሠረት ማንኛውንም ስነ-መንግሥታዊ፣ ማኅበራዊ፣ ፍልስፍናዊና ታሪካዊ ነገሮች መቃውምና ማፈርስን ቅድሚያ ያደረጉ ነበሩ።
---- #ፋኖንም በዚሁ ልማድ ጸረ-ኦርቶዶክስ በማድረግ 99.9% ክርስቲያን ተዋጊ ወጣትን ደም ለተጻራሪ ግብ ለማዞር የጣሩትን ጸረ-ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር ባዘጋጀው ሞዐ ተዋህዶ የተባል ግልጽ 7 ጥያቄዎች ይዞ የተንሳ ንቅናቄ በመጻረር ተጋልጠዋል። ለዚህም እግዚአብሔር የመስገን!!!
---- እውነተኞቹ ፋኖዎች ሁሉ የግዚአብሔር ልጆች ናችሁ! ጽኑ! ህልውና ማርጋገጫው፦
(1) የህልውና አደጋውን የደቀነውን ፖለቲካዊ ርእዮት፣ መዋቅር ተሸንፎ ሲያርፍ --- እነዚህ እንደ መቁያ የሚጠቀሙ ጸረ-ኢትዮጵያ፣ ጸረ-ኦርቶዶክስ፣ ጸረ-ማራነትን ከመቶ ዓመታት በላይ የተጠቀሙ የውጭ አካላት እጀታ (ጠማማ ዛቢያ) ሲያጡ፣
(2) የጋራ አገራዊ ተርክትን በማኮሰስና ተጻራሪ የጎጥ የሐሰት መርዛማ ተርከቶችን አምርቶ በመንዛት የትውልድ አእምሮ በመበከል ለእኩይ ግባቸው ማሣሪያ ያደርገኧቸውን በአዋሐጅ እውነተኛ ትምህርትና ትርክት በማሥረጽ አእምሮ ማቃናት፣
(3) በስሑት ርእዮትና ሐሰተኛ ተርክት ላይ የተመሠረተውን ከፋፋይና አገር-ጠል ትምህርት፣ ሕገ-መንግሥት፣ ፖሊሲዎች፣ የሕዝብ አሰፋፈር አሰነዋሪ ለውጦች፣ ሁሉ ታርመው፣ ሕጋዊና መንግሥታዊ ጥበቃ ሲደረግላቸው፣
(4) በስሑት ርእዮት፣ ሐሰተኛ ትርክት፣ በተላላኪነት፣ በስስትና ስግብግብነት፣ በድንቁርናችን ላደረስነው ጉዳት ካሣ፣ ለወንጀላችን የፍርድ አድባባይ፣ ለጥላቻችን ይቅርታና መስተካክል ችለን እንደ ቤተ ስብ የሚያኖረን፣ ከዘርና የባእዳን የአእምሮ ባሪያ መሁራን ነጻ ሆነን መኖር ስንችል፣
(5) ሰው ከሰውነቱ አንሶ ቡድንና የቡድን መሪዎቹ ባርያ የማይሆንበትን ክብረ-ስብእ የአግሪቷ አስተሳሰብ፣ ሕግ፣ ፖሊሲ እና መደበኛ ትምህርት ሲኖርን ----
----- ጠፋኖ ሠራዊት ደም ክቡርና የትውልድ መድኃኒት ይሆናል። ---- ጮሌዎች በፕሮፓጋንዳና በብልጣብልጥ ቃላት የሚጫወቱበት ደም ከንቱ ነው!!! ---- ሠራዊቱ ማን እንደሚመራው አውቆ ይወስን።
እስቲ በምን መርህ ብንመራ የበጀናል? እንደ እኔ
👉 "ከክብረ-ሰብእ፣
👉 ከፍትሕ፣
👉 ከእውነት፣
👉 ከፈሪሃ እግዚአብሔር፣
👉 ከአገር ዜጎች ቤተሰብአዊ አንድነት ----- መሠረት የተነቀለ ምንም አይነት ክብር የሚገባው #ተጋድሎ በዓለም ላይ ሊኖር አይገባም" ብለን መሐላ ምግባት። ሌላ ግሳንግሥና ፕሮፓጋንዳ አያስፈልግም። ለአጭበርባሪዎቸ ምላሶች እድል አይሰጥም።
ማንኛውም ትግል ልምራ የሚል ግለሰብ፣ ቡድን የሚከተሉትን ጥያቄዎች በትክክል መልሦ ካላሳመናችሁ ፋኖዎች #አትከተሏቸው!!
(1) ህልውና ተረጋገጥ የሚባለው ምን ሰባዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ስነ-መንግሥታዊ ሁኔታ ሲሟላ ነው?
(2) እያንዳንዱ የድል አንጓና ደርጃ በምን መሥፈርት የለካል?
(3) የትጥቅ ትግሉ ሲጠናቀቅ ምን አይነት መንግሥት፣ አገር፣ ርእዮት፣ ትርክት፣ የዚገነትና ስባዊ ክብር ማረጋገጫ መሥፍርቶች የኖሩናል?
(4) የኦርቶዶክስ፣ የነባር እምነቶችና ባህሎች እጣ ፈንታ አሁን ከተፈጠረው ውጭ-ገብና ነባር-ጠል ሁኔታ አንጻር ህልውናችን ሲርጋግጥ ምን አዲስ ሁኔታ ይፈጥራል?
(5) ወያኔና ኦነግ በሤራቸው የፈጠሩት ፖልቲካዊ ዘር (በሔር) እና ለህልውናው እየተፋለመ የሚገኘው ክፍለ-ሕዝብ ግኑኝነት እንዴት ይስተናገዳል?
(6) ሶማልያ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ኤርተራ፣ ግብጽ፣ ቀይ ባህር ማዶ፣ እና የሩቆቹ የጂኦ ፖለቲካ ድላጎቶች እንዴት ለህልውናችን ዘለቄታዊነት ይስተናገዳሉ?
(7) የፋኖ ተዋጊ የትጥቅ ትግሉ ሲያበቃ እንደ አንድ ጀግና ምን አይነተ ሕጋዊ ከለላ፣ ክብርና ሕይወት ይኖረዋል?
(8) ሥራአታዊና መዋቅራዊ በሎቻችን እንዴት ይካሣሉ? ---- ወዘት የሚሉትን ጥያቄዎች የመለሰ የፋኖ መንሻና መወያያ ሰነድ በሌለበት አንድነት እያሉ መጮህ በራሱ የውጭ ላኪና አምካሪ ባላቸው ለሤረኞች ለመታለልና ደምንና ድካምን ከንቱ ማድረግ ነው።
---- #ይኽን #ግልጽ ለማድረግ 3የሚያመነታ የፋኖ መሪ ከአለ --- በርግጥኝነት ድብቅ አጀንዳ ያለው #የህልውና #ትግሉ #ጠላት ነው።
ምክንያቱም ግልጽ ባለሆነ መንገድ ላይ የሚደረግ ተጋድሎ የሚያሰገኝው ድሉም ሆነ ስኬቱ መጨረሻው #ለአሸናፊም ሆነ #ለተሸናፊም ወገን #እኩል #ጥፋት ይሆናልና ነው!!!
ለፋኖዎች የግል ወንድማዊ መልእክትም አለኝ፦
* ዘረኞችን ለማሸነፍ ዘረኛ መሆን
ሤረኞችን ለማሸነፍ ሤረኛ መሆን
* ሐሰተኞችን ለማሸነፍ ሐሰተኛ መሆን
* ቁማርተኞችን ለማሸነፍ ቁማእተኛ መሆን
* ዘራፊዎችን ለማሸነፍ ዘራፊ መሆን
* ከሀዲዎዥን፣ ባንዳዎችንና የባዕዳን ጥቅም አገልጋዮችን ለማሸነፍ ከውጭ ጌታ መፈለግ
* ጎጠኞችን ለማሸነፍ ጎጠኛ መሆን
---- አያስፈልግም ብቻ ሳይሆን የውድቀት ውድቀት እና የከፍተኛ አማራጭ የማቅረብ አቅም የማጣት ዋና ማሳያ በዬ ስለማምን እንዲ ያሉትን ሰዎች ፋኖ ሳይሆን ወንጀለኛ ሽፍቶች ብሎ መፈረጅ ትክክለኛ ፍትሕ ነው።
#ጠላትን ለማሸነፍ #የጠላትን #ርኲሰትና ነውር መውረስ አይገባም።
የራስን ነባር፣ መልካም፣ ሰብአዊ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔርን፣ እውነትንና ጀግንነትን፣ ብልህነት፣ ትብብር፣ መተማመን ይዞ መገኘት ይበቃል። በዚህ መንገድ ከጠላት ወገን ወዳጅ ማፍራት ይቻላል።
እውነተኞች የግዚአብሔር እጆች ናችሁና በርቱ!!! ሐሰተኞች፣ ቁማርተኞች፣ ተላላኪዎችና ብልጣብልጦች የጠዋት ጤዛ ናቸውና አትስጉ!
ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።። 1) ሻሸመኔ ከተማ I. የተገደሉ 1. አያሌው ተረፈ ● በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ● ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ● በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ● በ ጥር 30 2015 ዓ/ም ሰማዕትነትን ተቀብሏል 2. ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ● የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ● በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ● ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ● በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም ሰማዕትነትን ተቀብለዋል። 3. ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ● የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...
አስተያየቶች