ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

የተኛህ ንቃ

የጂሀዳዊ ሚዲያ  ሥልጠናው በመጠኑም ቢሆን ሠርቷል ልበል?  ኦርቴዶክሳውያን ገምግሙት።
===========

ሰው ሰይጣንን ሳያውቀው በሰው  ተመስሎ ሲመጣ እስኪያውቀው ተቀብሎ አብሮት ይከርማል። ሰይጣን ማንነቱን ከገለጠ ግን ይሸሸዋል፣ ወደ እግዚአብሔር ይጣራል። በስመ ሥላሴ ያማትባል።

ኦርቶዶክሳውያን ግን ዓይኑን አፍጦ ጥርሱን እግጦ የመጣውን የዉሀብያ ጽንፈኛና የአብይ አህመድን ዘር አጥፊ ሥርዓት ራሱን ገልጦ እያዩት እንኳ እንደ ደነዘዙ ቆመዋል።  የነቁትን ጥቂት ክርስትያኖች  እንኳ እያዋከቡና እየወቀሱ አጥፊያቸውን እያወዳደሱ መገኘታቸው ይደንቃል።

አሳፋሪው፣ ነውሩና ራስን እንደ ማጥፋት የሚቆጠረው ነገር ------
ህልውናውን ለመታደግ የተነሳውን አማራ ስንኳ "እምነትህን እርሳው፣ መከታህን እግዚአብሔርን በትግልህና ፖለቲካክ ውስጥ አታውሳው፣ " ሴኩላር ሁን" ብለው የሚወተውቱት  ብዙ ናቸው። እንደዚህ የዉሀብያ ሤራና የአድዋ ድል ቁስለኞች የሸረቡት ወጥመድ በገቡ ጥቂት የፋኖ ተከፋይ ሚዲያዎችና ናርሲሱስቶቹ የሥልጣን ጥመኞች በኩል ደምቆ ይነገራል። 

ትግሉን  ከእግዚአብሔር ለይቶ ሊበትነውና መከራውን ለማስቀጠል ዓላማ ያለው ብቸኛ ጠላት ሰይጣን ዲያብሎስ ብቻ ነው። 
====================
ልብ ብልን ስናስተውል ብዘውን ጊዜ #እውነትኞች #በሤረኞች ይታለላሉ። ምክንያቱም  ሙሉ ሰብእና ሲኖርህ፣ እምነትህ የሰው ልጆችን ሁሉ በሰውነታቸው ብቻ እንድታከብርና እንድታፈቅር ሲያስተምርህ፣ አገር የሁሉም ናት ብለህ ሁሉን ስታገለግል ትኖራለህ።  

በተቃራኒው እንደ ውጭ ገብ እምነቶችና ርእዮቶች ተከታዮቹ  ከጀርባህ  ተደብቆ  የ፳፭ አይደለም የ፭ ቀን ሤራን ከውጭ አጥፊዎች ጋር  ተባብረህ በማቀድ እልቂትና ስደትን መፈጸምና እንዳይነገር ሌላ አጀንዳ መፈብረክ አይሆልህም።  ይህ ግን በወሀብያዌቹ ተችሏል (የ፳፭ ዓመት እቅዳቸው የዛሬ ፮ ዓመት ገደማ ተጋልጧል፣ እርሱን ተመልከት)።

ታዲያ ይህን ኢትዮጵያዊ ነባር መልካምነት እንደ ጅልነትና አላዋቂነት የቆጠሩት ጽንፈኛ ዉሀቢስቶች ከብልጽግና ወንጌል፣ ከኦነጋውያን እና ሌሎች የዘር ፖለቲካ ንቅናቄዎች ጋር በመተባበርም ይሁን በሥራቸው በመደበቅ ብዙ ዓመታት ተዘጋጅተዋል። 

===========
 "ማተብ የሚያሥር ቄሮ አናውቅም" የሚሉ ኦፒዲኦዎች የዉሀብያዎች መሣሪያ ነበሩ፣ ዛሬም ናቸው።  በሕወሐት የተመራው  የዩጎና(የሶማሌ ወጣቶች)፣ በኦሮምያ ሤረኞች በተለይ በጀዋር የተመራው የሲዳማ ኤጄቶ በክርስቲያኖች ላይ  ያደረሱት ጥቃት ከጀርባ ዉሀብያዎችና አብይ እህመድ እና የሕወሃት መረብ ነበረበት፣ አሁንም አል።  

ለዚህ ማስረጃው አንድምንየተከሰሰ ወጥፊ፣ የተካሰ ተጎጂ አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን ፕረጀክቱ ጭራሽ በመደበኛ ሠራዉትና በኦሮምያ ክልል ልዩ ኃይል ጭምር መቀጠሉ ነው።  ሌላው ይህንን የዘር ማጥፋት ሂደት ኦፑዲኦ፣ ሕወሃት፣ ብልጽግና፣ ዉሀብያ፣ የጀርመን ናዚ ክርስትናው ጴንጤ፣ የሃይማኖት ተቋማት ተብዬው የመንግሥት ዕቃ ሁሉም በግልጽንአያወግዙትም፣ ሚዲያዎች አይዘግቡትም፣ ፓርላማው አጀንዳ አድርጎ እልባት አይሰጠዉም፣ ዐቃቤ ሕግ ክስ ግፈኞች ላይ ክስ አይመሠርትም። 

አሁን የምንመለከተው በጂሀዳዊ ሚስኢንፎርሜሽንና ዲስኢንፎርሜሽን የሠለጠኑና  (ለምሳሌ የሚዲያ ጂሀድ ሥልጠንና ቪዲዮ ማየት ( https://t.me/Fantahun_Wakie/5650 )  መዋሸት በእምነታቸው አስተምህሮ የተፈቀደላቸው ወገኖች በተግባር  ተረባርበው እውነት እንዳይነገር ዘመቻ ላይ በመገኘታቸው እየመሰከሩ ነው። 

በዚያ ላይ  ውሸታቸውም ተግባራቸውም ከአብይ አህመድ  አዳዲስ አገራትና ማንነቶችን በትርክት የመፍጠር እቅድ " (grand narration/ታላቅ ትርክት፣ ነጠላና ሕብራዊ ትርክት" የተሰኙትን መልእክቶች ልብ ይሏል )ፕሮጄክት ጋር በቀጥታ ስለሚስማማ ሕጋዊ የሚመስል ሽፋን  በመንግሥት ይሰጠዋል። ለምሳሌ 
" የአረብ ሊግ አባል እንሁን ብላችሁ ጠይቁኝ፣ ለሀገራዊ ምክክር ኮምሽኑ ፍላጎታችሁን ሕጋዊ ሽፋን እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቡ፣ የምትፈጽሙትን ግፍ በሸኔና ሌሎች ግጭቶች ሥር ሰውሩ፣ ኢኮኖሚውን እንድትቆጣጠሩ  ልዩ እስላማዊ ባንክ ጠይቁኝ ፥ ወዘተ"  በሚል መግባቢያንሁሉም እንደታቀደው እየተከናወነ ነው። 

በሌላ በኩል መንግሥት እንዳቀደው ክርስቲያን የሚበዛባቸውን አካባቢዎች በጦርነት ማድቀቅ፣ አናሳ በሆኑበት ማስጨፍጨፍና ማፈናቀል፣ ፍትሕ መንፈግ ተጠናክሯል። 

በአዲስ አበበባ አፈሳና እሥሩ፣ ቤት ማስጣትና ማደኸየት በእቅድ (ሽመልስ ከ፬ ዓመት በፊት irrelevant እናደርጋታለን ባለው መሠረት)  ክርስቲያኖች ላይብወተኩሮ እየተከናወነ ነው። 

የቤተ ክህነቱ ምንደኛ  የሆድ ሎሌ በበኩሉ ከመንግሥት የተቀበለው  ድርሻው በማዘናጋትና በማስጨብጨብ ክርስቱያኑን ለሥጋና ነፍስ ሞት አሰልፎ  ማቅረብ ነው።

 ለምሳሌ አርሲ ሰው እየተጨፈጨፈ ቤተ ክህነቱ #ትዝታው ሳሙዔል የተባለ ከሀዲ እብድ ፍርድ ቤት ከስሻለው የሚል ተራ ነገር አጀንዳ ያደርጋል፣ ቄስ #ታጋይ ሚሊኒየም አዳራሽ ተገኝቶ ስለሚያልቁት ምእመናን ጉዳይ  መፍትሄ ማወያየት ወይንም ጸሎት ማድረግ  ሲገባው  የሕዝቡን ትኩረት ለማዛባት በተሰጠው ተልእኮ መሠረት  "ይህን በዓል በመስቀል አደባባይ እናክብራለን" ብሎ  የፈረደበትን ድንዙዝ ምእመን ያስጨበጭባል። 

ይህን  ግፍ የሚፈጸምበት ክርስቲያን ሕዝብ የሚመራ  #ጳጳስ ነኝ ባይ ኢአማኒ የጎሣ ጣዖት አምላኪ  ሁሉ "ብፁዕ" እየተባባለ የተከበሩ የቅዱሳን አባቶቻችን ማዕረጋትና ቅፅሎች ሁሉ ትርጉም እስኪያጡና እስኪጠሉ ድርስ  በትግባር ይቃረኑታል። ሲኖዶሱን የስንኩላን መናኸሪያ ያደረገው የሕወሃት የጎሣ ኮታ ጵጵስና ልማድ  ዛሬ ላይ በአብይ ደብዳቤ ወንበዴን ብፁ የሚል ሱኖዶስ ፈጥሯል።  "ይህ ግፍና ኡክርስቲያናዊ ሂደት  አይሆንም" ብሎ በመቃወም  ከሲኖዶሱ ወጥቶ ወደ ገዳም በመሄድ ከፈጣሪ ጋር የጸሎት ግብግብ የሚያደርግ መነኩሴ ጳጳስ አልተገኘም። 

 የሞከሩትንም የተወሰኑ ከተገኙ  "ይቅርታ ጠይቁና ለአብይ ተገዙ" የሚሉ የውስጥ ካድሬዎች  አሉ። ለምሳሌ  በአቡነ #ሉቃስ የደረሰውን ልብ ይሏል።

ይሄው እረኝነቱን የሚቃረን ሲኖዶስና ቤተክህነት ጠንቋዩን፣  በሐታዊውንና አጥማቂ ነኝ ባዩን፣ የበረኻ ትንቢት ተናጋሪ ተብሎ የቸገረውን ምእመን ሁሉ እንዲያውክ የተሠማራውን ሁሉ  ፈቃድ በመስጠት ምእመኑ ራሱን በአንድነት እንዳይከላከል እንቅፋት ያኖሩለታል።  

ንቁ የነበረው #የሰንበት #ተማሪ ተሳቅቆና ፈርቶ ለበዓላት ድምቀት እንዲዘምር ፣ መዝሙራቱ ወቅታዊ መከራን የሚያሳስቡና ምእመኑን ወደ መፍትሄ የሚያመለክቱ ሳይሆኑ በተቃራኒው  እልቂት የማረሳሳት ሚናቸውን ብቻ እየተወጣ ቆሞ እንዲቀርንየተደረገ ነው።   

በዚህ የክርስትያን ደም በሚጎርፍበት  ወቅት ወጣቱ   አልባሳት እያሳመረ ሜዳ ሞልቶ በወገኖች እልቂትና ስደት ምንም ሳይሰማው ይዘምራል። ያጨበጭባል፣ እልል ይላል።

ክርስቲያኑ እንደ ልማድ የዓብይ ጾም መጨርሻ ላይ ግን የጌታችን #ህማማት ብሎ ያዝናል። ጌታ ለሞተላቸው ማዘን ግን ከጌታ ህመም ጋር አገናዝቦ ለወገኖቹ ማዘንን ዘንግቷል። ነጭ ለብሶ ማንም እንዳልሆነ ታመመ ይተውናል። ይህንን እግዚአብሔር የሚደሰትበት አገልግሎት አድርጎ ራሱን ያጽናናል። 

#ፓትሪያሪኩ የዚህ ሁሉ ምስቅልቅል መነሻና መሪ፣ መከራን  መቀፍቃፍ እንጂ  ንስሐ የማያውቀውን የሕወሃትን ፈቃድ እያገለገሉ ነው።  ጭራሽ ሲኖዶስ ያወገዘውን የናዚ ትምህርት የሚመስል  የባለ ዲቃላና ንጹሕ ዘር ሰባኪውን የሰረቀ ብርሃንን መንበረ ሕወሃትን ይባርካሉ።

ይህን ሁሉ ስንመለከት እና ስናገነዛዝብ 
አሁን ሰይጣን ራሱን ገልጧል፣ የብርሃን መልአክ መምሰሉ ተገፏል። 

 #ማጠቃለያው 
ምእመን ራስህን ከከበበህ ጠላት አድን! ድንዛዛዜ፣ ይሉኝታ፣ ነጻ አውጭ መጠበቅ፣ የሌለ ሱኖዶስና ምንድኛ ሰባኪን መፍትሄ ይጠቁመኛል ብሎ ማሰብህን አቁም።  ታላቁን ኦርቶዶክሳዊ ሕዝብ ሲቀብሩት ቆመህ ከመመልከት ጠላት ያጠረብህን የቋንቋ፣ የቦታ፣ የመርዛማ ትርክት ወጥመድ በጣጥሰህ፣ በሥላሴ ልጅነት ባገኘኸው አንድነት ቄመህ ሰይጣንን ተዋጋው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...