ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ኦርቶ-አማራ ብሎ የሰየመ ማነው? ዓላማውስ?

 ነጋትና እውነት እያደር ይጠራል!
"ኦርቶ-አማራ" የሚለውን ቀምሮ እልቂቱን ያስቀጠለ ማነው?
የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይገርመኛል። አልነቃ ላለው ተገፊ ወገን በገፊው አንደበት "ላጠፋህ ነው፣ ታሪክህም፣ ማንነትህም ዳግም አይታወስም" እንዲባልለት ፊቱን ጠፍቶ አፉን ከፍቶ አናግሮለጣል። ይህ ለመተባበር ብቂ መለእክት አይሆንመእ? አይበቃም!!
===================
አልነቃ ያለውን አንድ ሰንፍ የገዛ ምራቁ ትን ብሎት ዘሎ ሲነሳ ተመልክቼ "ምነው ኦሮቶዶክሱ ማኅበረሰብ እና ሌላውም በእሣትና በስለት እንኳ አልነቃ አለ?" ብያለሁ።
በእውነት ኦርቶዶክሳዊው ሕዝብ ለምን እየሞተና እየተሰደደ ነጭ ለብሶና ሜዳ ሞልቶ በአጭበርባሪዎችና አደንዛዦቹ የሃሰት አባቶችና ሰባኪዎች ፊት ቆሞ እልልል ሲል ውሎ ያድራል?
ለምን የወገኖቹ ሞትና ስደት፣ ረሃብና ሰቆቃ አልሰማው ብሎ በሰላም የሚኖር ለማስመስል ሕይወቱን የቲያትረ ቤት ትወና አስመስሎ አጠግቡ የቆሙትን ጠላቶቹን መመልከትና ራሱን ከአደጋ ለመታደግ መንቀሳቀስ አልፈለገም?
------ የሚሉ ጥያቄዎች አሉኝ። እናንተስ? ያልደነዘዛችሁትን ነው የምጠይቀው። ሌላውማ እንደ ሽባ ቆሞ ነጻ አውጭና መፍትሔ ሰጭ እየጠበቅ ስለሆን ሀሳብ ሳይሆን እልልታና ስድብ ነው ወይንም የሰፈሩን ጀግና ግለሰብ በማወደስ ተጥምዷል።
===============
ወገኖቼ
ትርከቱ ቀድሞዉኑ "ኢትዮጵያ የአማራ፣ የኦርቶዶክስ በላይነት የንበረባት ነበረች" ትብሎ በአድዋ ድል ቁስለኞች ተሰምሮ የተሰጣቸውን በሕወሃት፣ ኦነግ ዳብሮ፣ የግራኝን አይነት ጥፋት የኒናፈቁትና የአቡዱል ወሃብ አስተምህሮን ተከትሎ በውጣት ዑስታዞች ከመካከለኛው ምሥራቅ አራጁ ጽንፈኛ ቡድን የተቀሰመውን መንፈስ አንግቦ እና በብሔር ፖልቲካ ሥር አድፍጦ የቆየው ጽንፈኛ የሚተባበረው መንግሥት ሲያገኝ አደባባይ ወጣ።
ዛሬ የምትሰማው ኦርቶዶ-አማሐራ (የአማራና የኦርቶዶክስ) በሚል ስያሜ "ንፍጠኛና የነፍጠኛ ሃይማኖት" ከሚለው ኦሮ-ዉሃቢዝምና ኦነጋዊ ትርክት ጋር ተደጋግፎ እያደገ የመጣ ነው። ዛሬ ላይ በድፍረት እየተገለጠ ያለው ከብዙ ዓመታት የውስጥ ለውስጥ ዝግጅትና የማጥቃት እቅም ግንባታ በኋላ የተገለጠ ነው። እናድውም የ3000 ታሪክህን ደምስሰን አረብ ልናደርግህ ለብልጽግና መንግሥት ጋር ውል አለን አሉ ማለት ነው። ይህ የማንኛውም የጽንፈኞች ጂሃዳዊ ዝግመተ ለውጥ ጠባይ ስለሆነ አያስገርምም።
የአማራና የኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ላይ ባልፉት 37 ዓመታት በተለያዩ መደበቂያ ሰበቦች የሚፈጸመው መጨፍጨፍና መፈናቀል "ይገባቸዋል" የሚለው የኦሮ - ዉሃቢዝም ተግባራዊ አሰላለፍ እና ጫጫታው ጭፍጨፋው እንዲቀጥል ባላቸው እቅድ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ነው። ለዚህ ማስርጃው አንድም ቀን ጭፍጨፋውንና ከፋፋዩን ሥርዓት ሲቃወሙ አይሰሙም።
በትቃራኒው ትጋታቸው ታሪክ መገልበጥና ጠላት ያሉትን የበለጠ ማጠልሸት፣ ማስገደል፣ ማፈናቀል፣ ንብረታቸውን መውርስ፣ ክርስቲያኖችን እንደ አብዱል ጀሊል ትርክት "አማራ ይበተናል፣ የቅማንት፣ የአገው፣ የወሎ ኦሮሞ ጉዳይ" እያለ የሕወሃትንና የኦነግን ፖልቲካዊ ርእይ ለማሳካት መድከም ማን እና ማን እየተባበሩ አገርን ወደ መንደሮች መቀየር ብቻ ሳይሆን ክርስትናን በብሔር ፖለቲካ መሣሪያነት ለመደምሰስ እንደሚተባበር ግልጽ ያደርገዋል። በዚያውም ላይ በጎሣ ብቻ ሳይሆን የዛሬ 5000 ዘመን የኖህ ልጆች መስመርን ተከትለን እና ከናዚ ጀርመን በቀሰምነው ጸረ ሴምነትን በማቀንቀን ኩሽና ሴም በለን የኦርቶዶክሳውያንን አንድነት አላልተን አምቺ ሲሆን የተሸነፈውን የ16ኛውን ክፍለ ዘመን ተላላኪ ጂሃዲስት በ21ኛው ክፍለዘመን አዲስ የግራኘ አህመድ ፈጥረን በሰይፍ አገሩን እንወርሳለን የሚል ድምጸት ያለው ድፍረት ይታያል።
እነዚህ ድፋርና የሰው ልጅ ደም የማያሰቅቃቸው ሰዎች (የሊቢያን አራዊታዊ ድርጊታቸእውን ልብ ይሏል) በስህተትም ቢሆን በምንም መልኩ ዛሬ ስለሚሞተው የሰው ልጅ አጀንዳ አድርገው አያውቁም። እንዳዉም አጀንዳ እንዳይሆን የሚቻለውን ሁሉ ተጋድሎ ለማደረግ አውዛጋቢ ትርክት በምፍጠራና በአንጻሩ የሚፈጸመው ጥፋት እንዲጠናከር ሲደክሙ፣ የጥፋት ሥልጠና ሲሰጡ ይታያሉ። አንድም ቀን በስሕተትም ቢሆን ስለ ሰባዊነት፣ ፍትሕ፣ እውነት፣ የሰው ልጆች ክብር ሲናገሩ ተስምተው አይታወቁም። ምናልባት ጽንፈኝነት ከመግደልና ከማጥፋት፣ ከማፍረስና ነባርነትን ነቅሎ ከለወጥ ጋር የሚቆራኝ በምሆኑ ማንነታቸውን ሊቃርኑ ስለማይገባቸው ሊሆን ይችላል። የዘወትር መዝሙራቸው ከኦነግ፣ ከሕወሃት፣ ከብልጽግና ጋር ሙሉ በሙሉ አንድ አይነት ነው፤ "እርሱም እኛና እነርሱ፣ ተበድለን ነበር፣ ነባሩ ጠላታችን ነው" የሚል ነው። ይህን በሁሉም የዉሃብያ ዑስታዞችና በአብዱል ጀሊል አይነቶቹ በስኮላርሺፕ/ሳይናሳዊ ልሂቅነት ስም በተመርጡና በተጠመዝዙ የወሀቢ ማጣቀሻዎች እና የፈጠራ አተራርኮች ዒላማ የተደረገው የዋሁ ወገን ሳያስተውል ለርዥም ጊዜ የተካሄደ የሤራ ሂድት እድገት ሥልጣንና ሀብቱን ተቆጣጥሮ በግልጽ መጥቷል።
የጽንፈኛው ቡድን በወለጋ እና በመላው ኦሮምያ፣ ቤኒሻንጉል፣ በከሚሴ፣ ዛሬም በአርሲ የሚፈጸመው የኦርቶዶክሳውያን ጭፍጨፋ አሳያሳምማቸውም። ለምን ቢባል ፕሮጄክታቸው ነዋ! ወለጋ ውስጥ በአማራ ክርስቲያኖችና በሙስሊሞች ላይ ለተፈጸመው ጭፍጨፋ የሚያነሱት በሰውነት ክብር ደርጃ ሳይሆን በእምነቱ ብቻ እንደተጥቃ በማስመሰል ነብረ። ሸፍጣቸውን የሚገልጠው ሰሞኑን "ፋኖ ስለሚጠቃው ክርስትናም ይመለከተዋል ብላችሁ መናግራችሁ ኃጢአት ነው" ብለው ዘምቻ በማድርግ ሕዝቡን ከእምነቱ ነጥለው አሁን ላዘጋጁት የጥፋትና አገርን አርባዊ የማድርግ እቅዳቸው ጥብቅና ቆመው ታዩ።
የወለጋ ሙስሊሞች ሞትን በሚመለከት የተናገሩትም አጋራቸውና መደበቂያቸው የሆነውን የብልጽግና ሥርዓቱን ለመውቀስ ሳይሆን እና በሰውነት ደርጃ ክብር መጠበቅ ሳይሆን በሃይማኖት ብቻ እንዲጠራ አድርገው የውጭ አጋሮቻቸው በኢምባሲዎቻቸው በኩል መግለጫ እንዲወጡ፣ በሰባዊ መብት ደርጃ ሆኖ የክርስቲያኖችን እልቂት እውቅና እንዳይሰጥ አደርጉ። በዚህም ዓለም ዐቀፍ የጂሃዲስቶች ተኩርተና ትብብር ለመሳብ ሞክርው ነበር። በተመሳሳይ የጎሣ ፖለቲካ የሚፈጥረውን ግጭቶች ክርስቲያኖች በእስልምና ላይ እንድሚፍጽሙት በማስመስልና ተባባሪያቸውን የዘር ፖለቲካን ከተጠያቂነት ለማዳን ሠርተዋል።
እንደምሳሌ ለማንሳት ደንበጫ ለተቃጠለ መስጊድ ተጠያቂውን አማራና ኦርቶዶክስ ክርስቲያን አድርጎ በመሳል አጥፊውን እና አጋራቸው የሆነውን መንግሥታዊ ሥራዓት ነጻ አውጥተው እና የመንግሥትን ሕግ ያለማስከብር ሰውረው በምንም መልኩ ክጎጃሙ ደንበጫ ጋር ግኑኝነት ያልነበረውን ጉዳይ በስልጤ ዞን እና በሌሎች አካባቢ የሚኖረውን ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያንን ማስገደልና ቤተ ክርስቲያንን በዘረጉት መረብ በኩል ማቃጠል ነበር።
የዚህ ጥፋት አስተባባሪና ተባባሪ አብይ አህመድ ደሴ ሄዶ "የቦሩ ሜዳ" ታሪክናስትውሱ" በማለት ግጭት ለማቀጣጠል ሲሞከር እጁ እስኪቀላ ያጨበጨበው የእነ አብዱል ጀሊል የአእምሮ አጠባ ውጤት የሆነው ነባር ጠሉ መንጋ ሲሆን ከብልጽግና ወንጌል ሃይማኖታዊ መንግሥት ጋር ያላቸውን አጋርነት ግልጽ አድርገዉት ነበር።
ይህንን የዉህብያና የብልፍግና ትርክት ለማድመቅ እና ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግ የተቀጠረው እምነትና ህሊና የከዳው ግለሰብ ደግሞ ፲፯ ዓመታት ሙሉ ክርስቲያኖችን ሲጨፈጭፍ፣ ገዳማትን ሲያወድም፣ ሰውን እየሰበሰበ ለአረብ ባርነት እየሸጠ በጠመንጃ ሲቀይር የነበረውን የአረቦችና የቱርክ የጂሀድ ጫፍ ግራኝ አህመድን ከግራኝ ታሪክ ጸሓፊ ከአረብ ፈቂህ እንኳን ያልተነገረንን በበሬ ወለድ ክህደት "ግራኝ አህመድ ቅዱስ ንጉሥ" በሉ እና በትቃራኒው ደግሞ የእነ አህመዲን ጀበል ትርክት አጽድቃችሁ "አጼዎቹ ርኩሳን ናቸው" በሉ አለን።
ይሁን -- ይህ ሁሉ የጠላት እቅድ አፈጻቅጽም ነው። የሚገርመው ግን
የክፉዎች መናበብና የመልካሞች መደንዘዝ ጉዳይ ጉዳይ ነው።
1) ጳጳሳቱ ቀኖና ሓዋርያትን በአብይ አህመድ ደብዳቤ ሽረው ለምእመንነት ስንኳ ቀኖናው የሚከለክላቸውን ዘርኞችና ከህዲዎች "ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል" ብለው የጥፋት ማኅበር ሲያጥናክሩ
2) ሕንጻ ስላሤ ሲፈርስ በዝምታ አልፈው የድንጋይና የሲሚንቶ ሕንጻ ዜና ሲያሰራጩ
3) ምእመኑ አጥፊው ሥራዓት የሚያወድስ፣ ጠንቋይና ሌባ አሰማርቶ በጸበልና በአስተዳደር ስም ሀብት የሚያከማች፣ በስብከት ስም ተውልድ የሚያደነዝዝ ምንደኛ ሰባኪን ተከትሎ ወገኑ እያለቀ፣ ተውልደ ከእምነት እየፈለስ --- ማዘንና ማልቀስ ሲገባው ነጭ ለብሶ በእልልታና በጭብጨባ መደንዘዙ፣
4) ወትሮ ከሁሉ ቀድሞ ነቅቶ ወላጆቹንና አካባቢውን ሲያነቃ፣ ግፍና ሌብነትን ሲቃወም የኖረው የሰንበት ተማሪ በዚሁ መንፈሳዊ ያይደለ ቱሪስታዊ መስህብ በሚመስል መዝሙርና አለባበስ እየተወዛወዘ መንፈሳዊ ነቃት ማጣቱ
5) በኦርቶዶክሳዊነቱ የሚጨፈጭፈውን ቤተሰቡን ለመታደግ ፈቃደኛ ያልሆነ የሠራዊት አባል
ወዘተ ---- 37 ዓመት ሙሉ መቀጠሉ ነው።
አሁን ግልጽ ሆነዋል፣ እንዲህም ይላሉ፦ "አረብ ስናደርግህ፣ ታሪክህን፣ ቋንቋህን ስንደመስስ፣ "የክርስቲያን ደሴት፣ ሰለሞናዊ ትርክትህን ፊትህ ላይ ስናከስመው፣ ፋኖን እንኳ እምነትህን አትጥቀስ ብለን ስናወዝግበው ያንተ የክርስቲያኑ ድንዛዜ እኛንም ይገርመናል " በለው ኦሮ-ዉህቢስቱ፣ ጂሃዲስቱ፣ ብልጽግናዊው፣ ናዚያዊው ክርስትና ወዘተ በአንድ ቃል የሚናገሩ ይመስለኛል።
የአማራ፣ የቢዛሞን፣ የኦሮሞ፣ የጉራጌ፣ የኾንሶ፣ የጋምቤላ፣ የትግራይ ወዘተ የህልውና ትግል ሰውን ከእነ እምነቱ፣ ታሪኩ፣ ባህሉ አጠቃላይ ሙሉ ክብሩን ለማዳን እንደሆነ ይታመናል። ይሁን እንጂ አንዳንድ አሥጊ ምልክቶች በፋኖ መሪዎች መካከል የታያል። ምልክቶቹ በአማራና በኦርቶዶክስ ጠላቶች ፍላጎትን ለማሳካት የተዘጋጁ ሰዎች አሉ ወይ የሚል ዐሳብ ያጭራል። የሰሞኑ የዉሃብያዎች ጩኸትና "አማራን ከእምነቶቹ ለዩልን" የሚሉ ድምጾች ለኛ አዲስ ቢመስሉም እነአብዱል ጀሊል ከ7 ዓመታት በፊት የመከሩበት መሆኑ ነገሩ ሥር የሰደደ የጽንፈኞች ሤራ እናዳለበት ይጠቁማል።
አንዳንድ ብዚህ እና በሌሎች የሤራ ኃይላት ተጸኖና በግል ፈተወታቸው ትልቁን የህለውና አጀንዳ ወደ ትራ የጎጥና የግለስቦች ሥልጣን ያዋርደኡ ጮሌዎች የአማራም ሆነ የማንኛዉም የህልውና አደጋ የተደቀነበት በተለይኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን የሚታገለውና ዋጋ የሚክፍለው ሆዱን ብቻ በማዳን እና ትግሉን ተጥቅመው በግላቸው ለመንገሥ የሚፈልጉ ሰዎችን ለማንገሥ፣ ከሕዝቡ

ዋና ዓላማ ውጭ ለጠባብ አረዳዳቸውና ፍላጎታቸው መሟላት ሲሉ ለህልውና አደጋው መከሰት ምክንያት ከሆኑት የውጭና የአገር ውስጥ አካላት ጋር ሁሉ ሳይቀር ተደራድሮ ለማለፍ በሚሞከሩ እና በአንጻሩ የሕዝቡን "ሃይማኖትና ነባር ትርክት እንቀብራለን" በሚል ቃል የገቡ በሚመስሉ ግብዞችና ናርሲሲስቶች ምከንያት የፋኖ አደረጃጀቶች አንድነት አዝጋሚ ሆኗል።
የአንድነት ሂድቱ መዘግየት በጎሣውም ይሁን በእምነቱ ምክንያት የጥቃት ዒላማ የሆነው ማኅበረስብ የበለጠ እንዲዳከም፣ እንዲሞት፣ እንዲሰደድ ለማድረግ ቀድሞ በሕወሃትና ኦነግ፣ አሁን በብልጽግና ወንጌል ሃይማኖታዊ መንግሥት አስተባባሪነት የዉሃብያ ጽንፈኞች፣ የጀርመን ናዚ ፓርቲ የክርስትና አይነት የተፈጠሩት የኩሽና ሴም ተራኪዎች ፣ በስግብግብ ዘርኞችና የጎሠኞች ልሂቃን መርዛማ ትርክት የአእምሮ ሰለባ የሆኑ አደረጃጀቶች መጠናከር፣ መሰባሰብና ጉዳት የማድረስ ጊዜና አቅም ሰጥቷቸዋል። ለአንድነቱ መዘግየት ምክንያት የሚሆኑ የአማራ ታግዮች ከአማራ የህልውና ጠላቶች እኩል አደጋዎች በመሆናቸው ሕይወቱን አስይዞ ለውጊያ የተሰለፈው ወጣትና ልጆቹን የሰጠው ሕዝብ ተነጋግሮ ፈጣን የማስተካከያ እርምጃ ካልወሰደ ትግሉ መደናቀፉ ነው።
ዙሪያ ገባውን ሳስበው በእቅድ ዘር የማጥፋት ማኅበር መሥርተው የሚሠሩ አካላት እንድዚህ ግልጽ ውጥተው እቅዳቸውን በሚያቀርቡበት ጊዚ እንኳ ዒላማ የተደረግው መላው የኢትዮጱያ ኦርቶዶከስና ነባሩ ሙስሊም፣ አምራውና ወላይታው፣ ትገሪውና ኦሮሞው ወዘተ በቁሙ እየሞተ ለመትባበር መዘገይቱ፣ በተለይ "ኦርቶ-አማራ" ተብሎ ለጥፋት የተለየው ክፍል የራሱን የህልውና ትግል ጥቂት ስንኩል ልጆቹ ሲያዳክሙት ቆሞ በጎጠኝነት መመልከቱ በእውነት ይህ ወገን እርግማን አለበትን? ያስኘኛል።
ኦርቶ_አማራ_የዉሃብያ ስያሜA.mp4

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...