ታሪክ እንደሚነግረን በባእዳን የሚደገፍ፣ በባእዳን የሚወደስ አፍሪካዊ መሪ ሁሉ የአገሩ ጠላት ነው!!
ትድረስ:
፩) ለጎጠኞች፣
፪) የአማራን ሕዝብ ትግል የኪሳችሁ ንብረት አድርጋችሁ ለጸረ-ኢትዮጵያ፣ ለጸረ - ኦርቶዶክስ ክርስትና፣ ለጸረ-ነባርነት "የአዲሱቷ ኢትዮጵያ" አቀንቃኝ የባእዳን ፈረሶች፣ ለጸረ-አማራ አካላት ለረባችሁ ነጋዴዎች ሁሉ፤
፫) የሕዝብን ደምና መስዋእትነት እንደ ተራ ቁስ መረማመጃ በማድረግ ለስግብግብ ስነ ልቦናችሁ ማስታመሚያ ላደረጋችሁ፤
፬) የሕወሃት፣ የኦነግ፣ የኦፒዶኦ/ብልጽግና የቁማርና የሤራ ፖለቲካ የሚያስቀናችሁና የተቀደሰ አማራጭ የትግል ስልት መቀመር ተስኖአችሁ በተመሳሳይ መንገድ ላይ ያላችሁ ሁሉ
==========
እጃችን ላይ ያለው የተጋድሎ ኃላፊነት የአንድን ታሪካዊ ክፍለ ሕዝብ እንደ ሰው በምድር ላይ በክብር የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ነው። የዚህ አማራ የተባል ክፍለ ሕዝብ ጠላቶች ድንገት ዝናብ ሲጥል በፍግ ላይ እንደሚበቅል ሙጃ ብቅ ብለው፣ በወር ውስጥ በጸሓይ ሙቀትና በነፋስ የሚጠወልጉ ሥር-የለሾች አይደሉም። በትንሹ ፪፻ ዘመናት የፈጀ ዝግጅትና ተከታታይ ጥረት ተደርጎ በ፲፱፻፵፪ በትምህርት ሥርዓት ደረጃ ተዋቅሮ በ፲ ዓመት ውስጥ መንግሥቱ ንዋይና ወንድሙን ግርማሜን ማፍራት የቻለ፣ እነ ዋለልኝ መኮንን በእንጭጭ አእምሮአቸው ያደሩት ባዕዳን በአንደበቱ "ኢትዮጵያ የብሔረሰቦች እሥር ቤት" በሚለው የሲዖል በር መክፈቻ ለወጣቴ መስጠት የቻሉበት ሂደት ነበር። ሂደቱምንእነ አጼ ምንሊክና ብልህ አማካሪዎቹ ከፈረንሳይ፣ ከጣሊያን፣ ከእንግሊዝ፣ ከቱርክና ሌሎች ከበባ ባተረፉት ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ማበብ ችሎና በአድዋ ተገልጾ የነበረውን አንድነትና ቤተሰብአዊ ተዋህዶ ያናጉበት ደረጃ ደረሰ።
በዚህ የጥፋት በር የገባው የጠላት ርእዮት ገንጣይ፣ አስገንጣይ፣ ከፋፋይና የሐሰት ትርክት ፋብሪካ መሥርቶ ሻዕብያን፣ ሕወሃትን፣ ኦነግን፣ ኦብነግን፣ ሲነንን፣ ወዘተ ፈለፈለ።
ለመንግሥትነት የተፋለሙ ኢሕአፓና ደርግን በዘረኝነት ባንከሳቸውም በጸረ-ኦርቶዶክስ ክርትስትና እና በአንጻሩ በጸረ-አማራነት ሁሉም ልዩነት የላቸውም።
መነሻቸው ከነባር እሤቶችና መልክ ሁሉ የተቃረነች "አዱሲቷ" የምትባል ነገር ግን ምን እንደምትመስል በቅዠት መልክ መሪ ነን ባዮች ከሚስሉት ብዥታ ውጭ በማንም ልትገለጽ ያልቻለች ሀገር መፍጠር ነበር። አዱሲቷ የተባለችዋን አገር በታወቀ መሠረት ላል አቁሞ በሂደት መተካት ሳይሆን ያለውን እና የተጨበጠውን አጥፍቶና ደምስሶ ከምን እንደሚጀመር የማይታወቅ ወደ "አዲሲቷ" ኢትዮጵያ መጓዝ ነበርና ማፍረስ ጀነሩ፤ ነገር ግን የቃዡለት አዲስ እፕገር ፋናው ሲጠፋቸው ደግሞ የቋንቋ ዘውጋችንን ከሌላው አዋግተንና ለይተን በምንፈጠረው የአዲስ ሀገር ሕዝብ ላይ እንነግሣለን ወደሚል ጠባብ ግብ ፊታቸውን አዞሩ። ይህንንም ለማድረግ ተከታይ መንጋ በማበጀት ትናንሽ ሀገር መፍጠር "ነጻነት" ወይንም "የራስን እድል በራስ መወሰን" ብለን እንጠራዋለን ብለው ተነሱ።
እንደ ኦነግና ሻዕብያ አይነቶቹ ደግሞ ቅኝ ተገዝተናል እንበልና "የነጻነት ትግል" የተባለውን ግጭት እንጀምር በማለት ፶ ዓመት ዘልቆ የቀጠለውን በሐስት ትርክት፣ በተውሶ ርእዮትና ድንቁርና በወለደው ሰብአዊ ክፋት ደም ማፍሰሱን፣ ሕዝብ ማፈናቀሉን፣ በእቅድ ማደኸየቱን፣ ታሪክ መበረዙን፣ ርስት መንጠቁን፣ ሃይማኖት ማፍለሱን፣ በባእድልን ድጋፍ ባርነትን እንደተሻለ አዲስ ሕይወት የሚቀበል ተሰዳጅና አሳዳጅ ትውልድ ፈጠሩ።
በዚህ ሁሉ “ነጻ የሚወጣው ጭቁን” የተባለው፣ “ቅኝ ተይዟል” የተባለው ወገን ተባለ። ቅኝ ገዥው፣ ወራሪውና ነጻነት ነፋጊው አማራ ነው ተባለ። የአማራ ርእዮታዊ ምንጭ ደግሞ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ቤተክርስቲያኒቷ ናቸው ተብሎ ተበየነ። ከነባሩ የሺ ዘመናት ሀገር-ፈለቅ የአስተዳደርና የፍትህ ሥርዓት ቀርቶ በየአካባቢው ሕዝብን አስተሳስሮና አከባብሮ የሚኖረውን ሽምግልና ሳይቀር ጠላት በማድረግ የአድዋ ድል ቁስለኞችን የመረቀዘ ሕመም የሚበቀሉ ከውጭ ጠላት የከፉ የውስጥ ደዌ ሆነው ተከሰቱ።
"አዲሲቷ" ለሚሏትም ይሁን "ነጻ አውጥተን ሀገር እናደርጋለን" ለሚሉት መንደር እዉን መሆን የተውሶ ርእዮት ላይ የተመሠረተ ጸረ-አማራ፣ ጸረ-ኦርቶዶክስ፣ ጸረ-ነባር እሤቶ ጸረ-ኢትዮጵያዊነት እና ፓን-አፍሪካንዝምን መመሪያቸው አድርገው ጥፋትን በአገራችን ላይ አውጁባት።።
እንዲህም የጥፋት መልእክተኞች ፈጥረውና ደግፈው መከራችንን ያስቀጠሉት እነዚያው አፍሩካን ጓሮአቸው፣ ሕዝቡን ባሪያቸው ማድረግ የወደዱ አገራት ናቸው።
እንደሚታወቀው ፴፭ቱም የአፍሩካ አንድነት ድርጅት ጥንሳሽና ጀማሪ መሪዎች ሕወሃትን፣ ሻዕብያንና ኦነግን ፈጥረው ያሳደጉ አገራት ስለላ ድርጅት መሪነት የተገደሉና ከሥልጣን የተወገዱ መሆናቸውን ምልስትልወስ ይገባል።
ዛሬ የሀገር መከራ ቀፍቃፊዎቹ በእነዚሁ የአፍሩካን አንድነትና እድገት በትጋት የሚያሰናክሉ አካላት ሱሄኑ የዛሬዌቹ አገር በቀል የኢትዮጵያ አፍራሾች በጠላት የተሰሩ አገልጋዮች መሆናቸውን እንረዳለን) በተለይ መንፈስ ያለው የፔለቱካ ማኒፌስቶ፣ የትግል ስልት፣ የፕሮፓጋንዳ ቀመር፣ የሀሰት ትርክት፣ የባእድ ወዳጅነት አበጅተው በሚችሉት ሁሉ ጸረ አማራ ትግል ጀመሩ።
በአማራ የኮድ ስያሜ ነባርነት፣ ክርስትናን ፣ ኢትዮጵያዊነትን በማጠቃለል የኦሮሞና የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ነን በሚሉት ተታልሎ የራሱን ታሪክ፣ ሀገርና እምነት እንደሚወጋ እንዳያውቅ እታልለው የጠላት መሣሪያ አደረጉት።
በባእዳን የተወገዱ የአፍሪካ ባለራእይ መሪዎች
[ለታሪክ መታሰቢያነት ከሀገር አንድነት አልፈው ለአህጉር አንድነት በመታገላቸው እንድ ሕወሃትናንኦነግ ባሉ የባእዳን አገልጋዮችና ሰላዮች ህልማቸውን ሳያሳኩ የተገድሉና ከሥልጣን የተወገዱ የአፍሪካ መሪዎችን እጠቅሳለሁ:-
፩) ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፣ በሄንሪ ኪሲንጀር ፖሊሲናንበአውሮፓውያን ሤራ ወደ ተራንየባዕዳን እቃነት በተለወጡ ምሁራን ተብዬዎቹና ወታደሮች ከሥልጣን ተወግደው የተገደሉ።
፪) ከዋሜ ንኩርማህ (ጋና) የፓንንአፍሪካንጽንሰ ሀሳብ ዋና አቀንቃኝ እና የአንዲት አፍሪካ ሀገርነት ህልመኛ በመሆኑ የበ፲፱፻፷፮ በሲአይኤ የተወገደ።
፫) ጁሊየስ ኔሬሬ (ታንዛኒያ) የአፍሪካን ሶሻሊዝም ለማስተዋወቅ በመሞከሩንየተወገደ።
፬) ጆሞ ኬንያታ (የኬንያ ነጻነት አባት) የአፍሪካን አንድነት መፈጠር በጽኑ በመደገፉ የተቀጣ።
፭)) ጋማል አብደል ናስር (ግብጽ) የአፍሪካ አንድነት አራማጅና ጸረ ኢምፔሪያልስትነቱንያስገደለው።
፮) አህመድ ቤን ቤላ (አልጄሪያ)_ ድህረ ቅኝ ግዛቶች ራሳቸውን እንዲችሉ በሰሜንብእፍሪካንንቅናቄ በመፍጠሩ በ፲፱፻፷፭ የተወገደ።
፯) ሊዮፖልድ ሴዳር ሴንጎሆር (ሴኔጋል)፣ ምሁርና መሪ የነብረ፣ የእፍሪካን ባህላዊ ውህደት በማራማዱ በጠላትነት ተፈርጆ የተወገደ፣
፰) ሚልቶን አቦቶ +ዩጋንዳ) የአፍሪካ አህጉራዊ ዲፕሎማሲኔ እውነትኛና ሁለገብ ነጻነት ዙሪያ በማቀንቀኑ በ፲፱፻፸፩ እና ፹፭ መፍንቅለ መንግሥት የተደረገበት።
፱) ፓትሩስ ሉሙምባ (ኮንጎ) ፣ በአፍሪካ ላይ የጸናውን እጅ አዙር ቅኝ አገዛዙን በመቃወሙ በ፲፱፷፩ የተገደለ።
፲) ቶማስ ስንካራ (ቦርኪ ናፋሶ) የኦምፕሪያሊስትና የአብዮተኛ ብጥበጣ ለውጦችን በመቃወሙ በ፲፱፻፹፯ በመፈንቅለ መንግሥት የተገደል።
፲፩) ሙአማር ጋዳፊ (ሊቢያ) ፳፻፲፩ የእፍሪካን መተባበር፣ የጋራ ገንዘብ መፍጠርና ራስን መቻል እቅድ በመያዙ ኔቶን በማዝመት አሜሪካ ያስገደለችው።
፲፪) አሚልካር ካብራል (ጊኒዎ ቢሳው/ኬከ ቨርዴ) ለነጻነት በመታገሉ ከድሉ አስቀድሞ በ፲፱፻፸፫ የተገደለ።
፲፫) ሲልቫነስ ኦለንፑዮ (ቴጎ) አገሩቷ ከቅኝ ነጻ በሆነች በእፕጭር ጉዜ ውስጥ ከምእራባውያን ጎራብአልሰለፍም በማለቱ በ፲፱፻፮፫ የተገደለ።
፲፬) ፌሊክስ-ሮላንድ ሞኡሜ ምናልባት በፈረንሳይ ስለለላ አካላት ተመርዞ በ፲፱፻፷ የተገደለ።
፲፭) ሩቤን ኡም ኖዮቤ (ካሞሩን) በ፲፱፻፶፰ የሀገሩን የነጻነት ንቅናቄ በመምራቱ በፈረንሳይብሠራዊት የተገደል።
፲፮) ኤድዋርዶ ሞንድላኔ (ሞዛንቢክ) : በየፊሮሊሞ ንቅናቄ መሪ በመሆኑ በፖስታ በተጠመደ ቤምብ ፲፱፻፷፱ የተገደለ።
፲፯) ሳሞራ ማቼል (ሞዛምቢክ)፣ አውሬፕላኑ በአጠራጣሪሁኔታ እንዲወድቅ ተድርጎ በአፓርታይዷ ደቡብ አፍሪካ ድንበር አክባቢ በ፲፱፻፹፮ የተገደለ።
፲፰) ስቱቭ ቢኮ (የደቡብ አፍሪካንአፓርታይድ ተቃዋሚ መሪ፦ በ፲፱፻፸፯ በፖሊስ በጭካኔ ተቀጽቅጦ የተገደለ።
ጥያቄ እንጠይቅ!!
ሀ) ለአገራቸውና ለሕባቸው፣ ለመላው አፍሪካ መልካም ርእይ ያላቸውን ታጋዮች የሚገድል የዳርዊን ልጅ ለምን የሻዕብያን፣ የወያኔን፣ የኦነግን፣ ኦፒዲኦ/ብልጽግናን ደገፈ?
ለ) እብይ አህመድን ለምን የሰላም ኖቬል ሽልማት ለምን ተሰጠው?
፫) ታንዛኒያ ድረስ ተጉዘው ኦነግ/ኦሮሙማን ከወያኔ ያስተባበሩትና የሕወሃትን ህልውና ከመጥፋት ቆመው የተከላከሉት ለምንድ ነው?
፬) የአማራንና የኦርቶዶክስን እልቂት ችላ ብለው፣ ፪፻ በላይ በአማራ ላይ የድሮን ጭፍጨፋ፣ በገዳማት ላይ እልቂት ሲካሄድ ለምን ችላ ይላላሉ? በአንጻሩ በትግራይ ላይ ድሮን ድብደባ ሲፈጸም ለምን ከ፭ ጊዜ በላይ የጸጥታ ምክርቤት ስብሰባ ጠሩ?
፮) አንዳንድ የፋኖ መሪዎችን ከሌሎች ጓዴች ለይተው ለምን ያነጋግራሉ?
መልሱ ቀላል ነው፦ ንግግራቸውና ፍቅራቸው ከጸረ-ኢትዮጵያ፣ ጸረ-አማራና ኦርቶዶክስ ክርስትና መንፈስ ካላቸው እካላት ጋር ብቻ ነው።
ከአማራ ትግል ውጭ የነበሩት ባለ ማኒፌስቶዎቹ
የትግላቸው ዋና ምሰሶዎች ሀሰት፣ ሤራ፣ ክህደት፣ ግድያ፣ ዘረፋ፣ ተላላኪነት፣ የሀገርን ጥቅም ሳይሆን ሥልጣን ላይ አውጥቶ ያቆየናል የሚሉትን የውጭ ኃይል ማገልገል ነው።
ሻዕብያ፣ ሕወሃት፣ ኦነግ እና የጎሣ ነጻ አውጭ ነን ባዮች ሁሉ በአንድ አይነት ጸረ-አማራ፣ ጸረ-ኦርቶዶክሳዊት ቤተንክርስቲያንና ኢትዮጵያዊነት ዐስተሳሰብ ላይ የተዋቀሩ ነበሩ። አንዳቸውም የኢትዮጵያን መልካም እሤቶች፣ ታሪካዊ ሀብታት፣ ማኅበራዊ መዋቅራት፣ ጥበቦችና ሀገር-ፈለቅ ዕውቀቶች አይታዩአቸውም ነበር።
እናም ለትግል ሲነሳሱ መነሻቸው ኢትዮጵያዊ ነባር ማንነታችንና አንድነታችን በአድዋ የሰበረው የዳርዊን ዘረኛ ልጆች የሰውን ልጅ የሚከፋፍልና በክብር የሚያበላልጥ የቅኝና ባሪያ ገዥዎችን ፋልስፍና እንደ እናት የጡት ወተት ተግተው ያደጉ በሥጋ ውልደት ኢትዮጵያዊ በአእምሮ ግን ባዕድና የነባር ማንነቶቻችን ፣ መሠረታዊ አስተምህሮና ርእይ ጠላቶች ናቸው።
አፈጣጠራቸው ከስኮላ ፊደል ቆጠራ፣ ከሚሽነሪዎች ጸሎት ቤት፣ ከአብዱል ዉሀብ መርዛማ መድረሳ፣ ከውጭ ስኮላርሺፕ፣ ከማርክስ አምላክ የለሽ ርእዮት፣ ከጣሊያን ባንዳ ቤተሰብ ወዘተ የተበላሸ ሁኔታ ውስጥ የተገኙ ሰዌች ናቸው።
የአማራ ሕዝብ የህልውና ይግል መነሻ ከእነዚ ባዕድ-ድቅል ተላላኪዎች ራሱን ለመከላከል የተከሰተ ተፈጥሮአዊ የአደጋ ምላሽ ነው። ስለሆነም ሤራ፣ ሀሰት መፈብረክ፣ የባእድ ርእዮት መቃረም፣ የጎሣ ጠላት መሰየም፣ የባእድ ድጋፍና ምክር መሻት፣ የጎጥና የቋቋን ዘውግ ማቀንቀን፣ በህቡዕ የትውልድ አእምሮ በመርዛማ ትርክትና በቅዠታዊ ርእይ ማታለል አላስፈለገዉም።
ተነስቶ "ሰው ነኝ፣ ሰው ናችሁ፣ ህልው ነኝ አልጠፋም" የምትል መጽሐፍና ፍልስፍና የማትሻ ተፈጥሮአዊ የሰብአዊነትና የፍትህ ንቅናቄ ነው።
የሚያስደነግጠውና ከፍተኛ ትኩረት የሚሻው ይህን ተፈጥሮአዊ፣ ስብአዊ፣ ፍትሐዊ ንቅናቄ ጠልፈው ለግል የሀብት፣ የሥልጣንና የዝና ማጋበሻ፣ የጎጥ ስነ ልቦና መታሻ ለማድረግ ለአገርና ለአህጉር አንደነትና ውሕደት የሠሩ መሪዎችን እያደነ የሚያጠፋ፣ ተላላኪ ድውያንን ከሚሸልም ጸረ-እኩልነት መሆናቸውን ከ፬፻ ዘመን በላይ በፈጸሙት ታሪካቸው ከሚታወቁት፣ በጎሣና በእምነት ከፋፍለን ኢትዮጵያን እናጥፋብብለው የጎሣ ነጻ አውጭ ፈልፍለው ለዚህ የዳረጉንን አካላት ጋር ከሕዝብ ጀርባ እየተገናኙ የሚርመጠመጡ ድንኮች በአማራ መካከል መብቀላቸው ነው።
የህልውና ትግልን ቅዱስ የሚያስፕኘው ሤራ፣ ጎጠኝነት፣ ሀሰተኝነት፣ መግደል መቻል አይደለም። ቅዱስነቱ የሚመነጨው እውነተኝነቱ፣ ፍትሐዊነቱ፣ ክቡር የሰው ልጅን ያዋረዱትን አስተሳሰቦችና ድርጊቶችን ለማሸነፍ መነሳቱ፣ ከጎሣ አጥንትና ደም ቆጠራ በላይ ሰውነቱና፣ የከበረ ሰው የሚኖርባት የተከበረች ሀገርን ማልሙና ለዚህ መሰዋቱ ነው።
ይህን ቅዱስ ነገር ውሾች እንዳይጫወቱበት ባለቤቱ የሆነው የአማራ ሕዝብ ከፕሮፓጋንዳና አጭበርባሪ ልጆቹ የጠላትን ያህል መጠበቅ ይኖርበታል።
ካልሆነ ግን ደሙን አፍስሶ፣ አጥንቱን ከስክሶ የሚያገኘው ውጤት ከሕወሃትና ኦነግ ዲቃላ ከብልጽግና ወንጌሉ ገዥ ባርነት ብየከፋ ይሄናል። በስሙ እየማሉ በሥልጣን ላይ ወጥተው ለባእዳን እየቸረቸሩ ለዘላለም ነጻ ሕዝብ እንዳይሆን በሚያደርጉት አማርኛ ተናጋሪና በ"አዲስነት" ስም እሤቶቹንና እምነቱን ደምስሰው ወደባሰ አዘቅት የሚከቱት እጅ ይወድቃል። እሤቴቹን ደብቆ ደምና እፕጥንት ለማስቆጠር “በደምና አጥንት ከሚገለጽ ብሔርተኝነት ውጭ መዳኛ የለም” የሚለው አዛኝ መሳይ ቅቤ አንጓችነት ለዘላለም ጥፋት የሚዳርግ የጠላት ምክር ነው።
ፋኖ ውስጥ እና በድጋፍ ስም ያላችሁ ሤረኞች፣ ሩቅ ዓላሚ ቅርብ አዳሪዎች የሚጠብቃችሁን ልንገራችሁ:-
፩) የህሊና፣ የታሪክ፣ የህግ፣ የነፍስ እዳ መክፈል በምትችሉበት ደረጃ የመጣባችኋል፣
፪) ህወሃትን ኦነግ ነጻ እናወጣሀለን እያሉ አገር አሳጥተው በደም ጎርፍ ውስጥ እንደሚያኖሩት የዋህ ተከታይ አማራን ለህልውናህ ቆሜያለው በሚል ማታለያ የራሳችሁን ጠባብ ፍተወት ለማርካት በምትፈጽሙት ወንጀል ትጠየቃላችሁ፣
የአማራን ትግል ቅድስና የምታረክሱ ወንጀንላችሁ ግልጽ ነው
፩) በጎጠኝነትና በበዛ ራስ ወዳድነት፣ ማን አህሎኝነት ባዘገያችሁት አንድነት፣ ታላቅ ሆኖ ሳለ ተካፍላችሁ እንደ እናሳ ስላዳከማችሁት በዘገየው ድል፣ በፈሰሰው ድም፣ በወደመው ሀብት ከትምህርታቸው በተስተጓጎሉት ህጻናት፤
፪) የአማራን ሕዝብ ትግል የኪሳችሁ ንብረት አድርጋችሁ ለጸረ-ኢትዮጵያ፣ ለጸረ - ኦርቶዶክስ ክርስትና፣ ለጸረ-ነባርነት "የአዲሱቷ ኢትዮጵያ" አቀንቃኝ የባእዳን ፈረሶች፣ ለጸረ-አማራ አካላት በማቅረባችሁ የፋኖነትን ክብር የትግሉን ቅዱስነት በሤራ ስላቆሸሻችሁ ትጠየቃላችሁ፤
፫) የሕዝብን ደምና መስዋእትነት እንደ ተራ ቁስ መረማመጃ በማድረግ ለስግብግብ ስነ ልቦናችሁ ማስታመሚያ በማድረግ ክቡር ዓላማውን ጥርጣሬ ላይ ስለጣላችሁ እና ስላላችሁት ተነሳሽነት መዳከም ትጠየቃላችሁ፤
፬) የሕወሃት፣ የኦነግ፣ የኦፒዶኦ/ብልጽግና የቁማርና የሤራ ፖለቲካ የሚያስቀናችሁና የተቀደሰ አማራጭ የትግል ስልት መቀመር ስለተሳናችሁ፣ ጠባብነትና ስግብግብነት ከአማራ ጠላቶች ጋር የአማራን ትግል በማመሳሰላችሁ የታሪክ እዳ ትከፍላላችሁ።
ከዚህ ለመዳን ሰው ሁኑ። ሙሉ ሰው ስትሆን አማራም ኢትዮጵያዊም ትሆናላችሁ። እግዚአብሔር የማይወሳበት የተሸናፊዎችን (አምላክ የለሽ ሴኩላር) መንገድ አደገኝነት ለመረዳት ዓይናችሁ ይከፈታል።
አስተያየቶች