ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ኦርቶዶክሳውያን ለምን የጎሣ ፖለቲካ ፓርቲዎችና መንግሥት ዒላማ ተደርጉ

ጎሰኝነት/ኑዑስ ብሔርተኝነት ባለ ረዥም ታሪኳ ኢትዮጵያ ውስጥ ሳይቀር እንዴት ተፈጠረ፣ እንዴትስ በአፍራሽነቱ ጸና? የሀገራችን ዋና የመከራ ምንጭ፤ የስደት፣ ዘር ማጥፋት  ደረጃ  መድርስ 1. በማኅበራዊና ተፈጥሮአዊ ሰንሰለታዊ መስተጋብር የሚፈጠሩ ታሪካዊ አሻራዎች፦   በዓለም ውስጥ፣ በተለይ በአፍሪካችን  ጎሣዎች የኖራሉ። ለዩ ቋንቋዎች፣ ልዩነት የሚያሳዩ ባህሎች፣ በተወሰነ ደርጃ በአስተዳደርና ፍትሕ ሥርዓት ለዩነታቸው እየተዋሐደ ሳይሆን እየደመቀ መቆየቱ ይታያል።  ይህ ንዑስ ማንነት  ጤናማ ሆኖ የሚኖረው ፖልቲካዊ መሣሪያ፣ የምጣኔ ሀብት  ሽሚያ ምክኒያት ሲሆን ጎጅ፤ በተፈጥሮው ተከብሮና ተመጋጋቢ ህብረት አስገኝቶ ለእድገትና ለአቅም ምንጭ ይሆናል። 2. የቅኝ ገዥዎች ተጸኖ፦  በከፋፍለህና አዳከመህ ግዛ የቅኝ ግዥዎች ስልት በቀጥታ በአካል ተገኝተው ባርያ ያደረጓቸው የአፍሪካ ሀገራት፣ እንደ ኢትዮጵያ በትምህርት ስም አእምሮ አጠበው ባርያ ያደርጉት አገር ውስጥ ያሉ ታሪካዊና በማኅበራዊ መስተጋብራዊ ዝግመተ ለውጥ የተፈጠሩ ኑዑሳን-የጎሣ ማንነቶች  ከህብረታዊ አንድነትና ከተዋህዶ በተቃራኒ እንድ ሕወሃትና እንደ ኦነግ ባሉ የባዕዳን የአእምሮ ባሪያ ልሂቃን ጠላትነት አፍርተዋል። ከመዋሀድ በተቃራኒ መራራቅና መጠፋፋትን ሳይቃወሙት ለልሂቃኑ የጥፋት መሣሪያነት ተሰልፈው ቀጥለዋል።  3. የቋንቋና የባህል ብዝኃነት፦  አፍሪካ ውስጥ በአጠቃላይ  በአንድ ሀገረ-መንግሥት ውስጥ ብዙ ቋንቋ ተናጋሪዎችና ልዩ ልዩ  ባህሎች አሉ። እንዚህ ልዩነቶችን ወደ ሀገራዊ የጥንካሬ ምንጭ ለማሳደግ ከሚደረገው ጥረት የበለጠ በቱሪስት ሸቀጥነት፣ በየጎሣ መሪዎችና የየጎሣው አባ...

ፖልቲካ-ሠራሽ ከሰውነት ከሚያሳንስ ኑዑስ-ጎሣዊ-ማንነት መገላገል መከራችንን ይቀንሳል

 የጎሣ ልሂቃንና ጭፍን ተክታዮቻቸውን የምመክርው ነገር አለኝ፦ በቋንቋ፣ በትርክትና ፖልቲካ-ሠራሽ ከሰውነት በሚያሳንስ ኑዑስ-ጎሣዊ-ማንነት የአእምሮ መዛባት ራሳችሁን ማዳን ጥቅሙ ለራሳችሁ ነው! ክርስቶስን በመዘንጋት ጎሣቸውን እንደ ጣዖት የሚያገልግሉ የፓርቲ አገልጋየ አባት መሰል ግለሰቦች ሲገኙና ሲወቀሱ እጅግ የሚያማቸው የኦነግ ኦሮሙማ   የፋሺዝም አእምሮዎች እጅግ ይንጫጫሉ። ስሞኑን አቡነ ገብርኤል በሚያሠራጩት ኑፋቄ ምክንያት መወቀሳቸውን ከሚመለከታቸው ከሊቃውንት ጉባኤ፣ ምሥጢር ካደላድሉ መምህራን፣ ከሲኖዶስ ቀድመው   ተቆጭተው የሚይውለበለቡት ኦነጋውያንና የብልጽግና ወንጌል አራማጆችና  ጸረ-ነባር እሤት እንዳላቸው ላልፉት 50 ዓመታት ሀገር በማመስ የሚታወቁት ናቸው። #OMN የተባለው ቀንደኛ የዘ*ር ማ*ጥ**ፋት  አዋጅን ያለ ድካም የሚለፍፈው ሚዲያ ይህንኑ የተለመደ አሉታዊ ጣልቃ ገብነቱን ቀጥሎበት የሃይማኖትን ጉዳይ ለኦሮሞ ፖለቲካ ማድመቂያ ተጥቅሞበት ታይቷል።  በዚህ ሚዲያ "አማራን ከ30 ሚሊዮነ ውድ 120 ሺ መቀንስ፣ manegable በማድረግ ሰሜን ሸዋ  መንዝ ማስቀመጥ"  የሚል ፕሮፓጋንዳ ጋዚጠኛ ደጀኔ በሚባል ግለሰብ አቅራቢነት የቀረብ ተወያይ ለተከታዮቹ ሲመክር  የሚዲያው ባለቤቶች ስለተስማማቸው እርምት አልወስዱም፣ ይቅርታም አልጠየቁበትም።  በተግባር ድግሞ በአማራ ስም ኦርቶዶክሳውያንን፣ ኦሮሞ ኦረቶዶክስ ክርስቲያኖችን ጨምሮ ማጽዳቱ በአርሲና ወለጋ ቀጥሏል። ይህ ሚዲያ ስለዚህ አይዘግብም። በታሪክ እንደምናውቀው፦- የጎሣ ፖለቲካ ከፋሺዝም አምልጦ አያውቅም።  በሀገራችን ኦነግና ሕወሃት የተከሉት የፋሽዝምና አፓርታይድ  ርእዮት እውር ድንብ...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ትንሳዔን የምናከብረው እኛ ራሳችን ልንነሳ ነው! አዘቅት ውስጥ ሆነው ክንፍ ስላበቀሉት መዘመርና በዓል ማክበር በእግርም አያራምድም! በንስሐ ለመብረር መነሳት ይቀድማል!

ትንሳዔን የምናከብረው እኛ ራሳችን ልንነሳ ነው! አዘቅት ውስጥ ሆነው ክንፍ ስላበቀሉት መዘመርና በዓል ማክበር በእግርም አያራምድም! በንስሐ ለመብረር መነሳት ይቀድማል! በ2014 ተጽፎ የተሰራጨ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀዳማዊ ቃል ነው፥ ያቃል እግዚአብሔር ነው፥ ያቃል በአግዚአብሐየር አብና በአግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ዘንድ ነበረ። ያ ቃል ሰው ሆነ። ለምን?        እኛ በገዛ ፈቃዳችን ከሕይወት አልባውና በሐሰቱ ራሱን ካጠፋው ከሰይጣን ጋር ተወዳጅተን፥ የሕይወት ምንጭና መሠረት ከሆነው ከእግዚአብሔር በአመጻችን ተለይተን  ሙታን ሆንን። ከዚህ አይነት ከሕይወት ምኝጭና መሠረት ከእግዚአብሔር በመለየት  ሚሞቱት ሞት  በፍጡር ኃይልና ጥበብ፥ ተጋድሎና ምልጃ መዳን አይቻልም።  ከዚህ አይነት ሞት መዳን  የሚቻለው በማይሞት፥ በጥበቡ በሞት ላይ ሥልጣን ባለው፥ በደልን መሰረዝ በሚችል፥ ሙቶ ሞትን ድል በሚነሳ፥ በሁሉ ላይ ሥልጣን ባለው አካል ብቻ ነው። ይህ ደግሞ እግዚአብሔር ብቻ ነው። እርሱ ከሶስቱ አካል አንዱ ቃል ከባርሕይ አባቱ ከአግዚአብሔር አብ እና ከባሕርይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፍስ ቅዱስ በመለኮት ሳይለይና ሳይንስ በተለየ አካሉ ቃል ከእመቤታችን ከቅድሰት ድንግል ማርያም ሞት የሚስማማውን የእኛን ሥጋና ነፍስ ነስቶ በመዋሀድ ስለ እኛ ለመሞት ፈቀደ።  ከአዳም በደልና ጉስቁልና ነጻ አድርጎ ከጠበቃት ከእናታችን ሰው ሆነ፥ አርሱን የሚመለከት አንዳች ኃጢአትና በደል ሳይኖርበት እኛ በነፃ ፈቃዳችን መርጠን ስለሞትንበት አመጽ አርሱ እኛን ተገብቶ መከራ ተቀበለ፥ ታመመ፥ ሞተ፥ መለኮት በተዋሐደው ሥጋው ወደ መቃብር፥ መለኮት በተዋሐዳት ነፍሱ ወደ ሲዖል ወርዶ  ከሞ...

ከሚያዝያ 20 ጀምሮ በኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክርስቲያን ከሚካሂደው ከዝክረ ኒቂያ ጉባኤ ምን እንጠብቅ?

ከዝክረ ኒቂያ ምን እንጠብቅ?    በትንሹ  ከዚህ በታች ያለውን ጉዳይ የመፍትሔ አቅጣጫና ቀኖና ነው፦ (1)  በጎሣ ፖለቲካ እየተመራ የተሾሙ ኤጲስቆጶሳትና ጳጳሳት  እንዲሁመ መለካዊነት፣ ሲሞናዊነት፣ ዘረኝነት በደዌ ደረጃ የተጣባቸው፣ በቁሳዊ ሃብት ማጋበስ ምንኩስናን ያዋረዱ ወገኖቻችን ሕይወት የሚመዘንበትና የሚታረምበት  ውሳኔና ቀኖና ማወጅ፤ (2) ምእመናንን በጎጥና በቋንቋ፣ በትርክት፣ በውጭ-ገብ የፖለቲካ ርእዮተ ዓለም ክርስቲያኖችን  መከፋፈሉን፣ እያጭራርሰ እንደሚገኝ፣ የጎሣ ሲኖዶሳት እየትፈለፈሉ በመሆኑ የተከተለውን የምእመናን መለያየት፣ መጠላላት፣ መዋጋት፣ ተበትኖ ለክርስትና ጠላት ለሆኑት አካላት የተመቻቹ  መሆናቸውን ያገናዘበ ኦርቶዶከሳዊ መመሪያና ለመእመንና ለካህናት ማስተላለፍ፤ (3) አርአያ ምንኩስናን በማራከስ በከተማ የከተሙ መነኮሳት፣ ሀብት በማፍራት ላይ በማተኮር ምእመናንን፣ ካህናትን አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን  ተልእኮን የዘነጋ አኗኗርን የሚመለከት ግልጽ  የእርምት መመሪያና ቀኖና፤ (4) ሲኖዶስ የጳጳሳት ብቻ እንጂ የካህናትና ምእመናን  ተሳትፎ የሌለበት ሆኖ መቀጠሉ ያስከተላቸውን ጥቅሞችና ጉዳቶች በመገምገም ለወደፊቱ ግልጽ የሆነ የተሳታስፊዎች፣ የአጀንዳ አቀራርጽ፣ የውሳኔ አሰጣጥና አፈጻጸም ቀኖና ፤ (5) በምእመናን ላይ በመንግሥት የተፈጸመውን ጭፍጨፋ፣ ማፈናቀል፣ ሲኖዶስ ውስጥ የሚገባውን ጣልቃ ገብነት፣ የገዳማትና አድባራት፣ መናኒያን መደፈርን፣ የነገረ መለኮት ት/ቤቶችና ማሠልጠኛዎች ከመናፍቃን መምህራን፣ ከመናፍቃን መጽሐፍትና ኮርስ የመጠበቅነ አሠራርና የሊቃውንት መዋቅራዊ ተሳትፎ መበየን፤ (6) የሚሊዮኖች መመናን ፍለሰት የውስጥና የውጭ መንሴዎችና...

የአንድነት ሚዲያ እንመሥርት ውይንም አሁን ካሉት መካከል መርጠን እናብቃ

ረዥም ያልተቆራረጠ የሥነ መንግሥት ያላት አገራችን ኢትዮጵያ ብዙ ጠላት ያፈሩላት ጸጋዎች አሏት።  በተፈጥሮ ከምትገኝበት የመልክዐ ምድር አቀማመጥ ጀምሮ ሕዝቧ ካዳበረው የነጻነትና የጸረ ቅኝ ግዛት  ጋር ተጣምሮ  ነባር እሤቶችና የአፍሪካ መግቢያ በር፥ የአባይ ወንዝ መነሻ፥ የቀይ ባህርና የህንድ ውቂያኖስ መተላለፊያ የመቆጣጠር አቅም የሚሰጣት አቀማመጧና የገናና ታሪኳ መመለስ አስፈሪነት፥ በዓረብና በአፍሪካ ድንበሮች አካባቢ መኖሯና አፍሪካን የጓሮ አርሻቸው፥ የተለያዩ አደንዛዥ እምነቶቻቸው ማራገፊያነት እንቅፋት መሆኗ፤ እንዲሁም ልዩ የተፈጥሮና የማዕድናት ሀብት ባለቤትነት፥ የሕዝቡ ጥበብኝነትና የጀግንነት ታሪክ፥ የአክሱምና ቀዳሚ ሥልጣኔ የመመለስ እድል ሁሉ  ዓይን ውስጥ አስገብቷታል።  ፖረቱጋል፥ ኦቶማን ቱርክ፥ ጣሊያን፥ ኢንገሊዝ፥ ጀርመን፥ ፈረንሳይ፥ አሜሪካ ዛሬ የአውሮፓ ሕብረት፥ ሩሲያ፥ ቻይና፥ ግብጽ ወዘተ ወደ አፍሪካ አህጉር፥ ወደ ህንድ ውቅያኖስ፥ ወደ ቀይ ባሕር ሲመለከቱ የኢትዮጵያን  አቅምና ሚና ከጥቅማቸው አንጻር  የመበየን ፍላጎታቸውን መግታት አይችሉም። በዚህም ኢሰብአዊና ኢፍትሐዊ ፍልስፍናን ከሤራ ጋር ቀምረው፥ አገር በቀል ባንዳን መረማመጃ አድርገው  ኢትዮጵያ ያለማቋረጥ በሁለገብ ጥቃት ሥር ማኖራቸው ይታወቃል። ይህ ሂደት በትንሹ ከ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ አገሪቷን ሲያቆስላት፥ ሲቆነጻጽላት፥ ከህንድ ውቅያኖስ ባለቤትነት ወደ ባህር በር አልባነትና አሁን ወዳለዉ የክልል አፓርታይድ ሥርዓት ያደረሳት ነው።  ሂደቱ ከቀጥታ ወረራ ጀምሮ፥ የንግድ በር መዝጋት፥ አገርን አንድ ሉዓላዊ ሕዝብ በጎኃና በእምነት ዘውግ ከፋፍሎ ማጋጨት፥ በመጨረሻ በትምህርትና በእውቀት ስም ልጆቿን አእ...

ጸረ ክርስቶሱ ጽንፈኛው ሼህ አህመድ ዲዳት ያፈራቸው የኢትዮጵያ እንዳንድ ዑስታዞች አስተምህሮ

ሼህ አህመድ ዲዳት ዲዳ ሆኖ  ለምን ሞተ? ፈጣሪው ያውቃል። ሞት በክርስቶስ ሞት ድል የተነሳበት፣ መድኀኒት የምትሆንንየጌታችንንሕማም በሚታሰብበት በዚህ ቀን የጌታችን ጠላት የሆነውን ሰውዬ ተከታይ ዑስታዞችን ወደ እውነት ሃይማኖት ለመጥራት እጅግ የሳተውን ደፋር ሰው ማንሳት መልካም መስሎ ታየኝ። ስለ ዲዳት ሳስብ በግልጽ  ጸረ ክርስቶስ ሆኖ መሳዮቹን የእኛን አገር ጥራዝ ነጠቅ ጸረ ክርስቶሶችን፣ ጽንፈኞችን፣ ገዳዩን ግራኝ የሚናፍቁ ግብዞችን  በፍጥነት መፈልፈል ምክንያት ይመስለኛል። ክርስቶስ ላይ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ባልተገኘበት ሜዳ አፉን በጌታችን በመድኀኒታችን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በቁራን በጠመመው አእምሮው፣ ሰይጣን በሚጠቀምበት ምላሱ ያለ አግባብ ስድብ ሲያወርድ የነበረው ዲዳት  አንደበቱ ተዘግቶ፣ በስቃይ ከመሞቱ በፊት የሚናዘዘው ነገር እንደነበረው እገምታለሁ። እርሱም ጸረ ክርስቶስ እምነት እንዴት ከእውነት አርቆ በጨለማ እንዳኖረው እና ንስሐ ገብቶ መጠመቅ እንደሚፈልግ ነበር። ግን የጽልመት መላእክት አፉን ዘግተው እያሰቃዩ አጣድፈው. ወደዱት። የሚመኘው መቶ ደናግል ሴቶችን ጀነት አለመኖሩን አውቆ ነበር። ግን ስትናገር እየቃተተ አለፈ። ለማንኛውም ጸረ ክርስቶስ መሆኑን ሲናገራቸው ከነበሩት፣ አሁንም መሳዮቹ የሚናገሩትን በጥቂቱ በማስረጃ ላቅርብ:- * አምላክ ተወለደን ሲሰማ "አላህ አይወልድም አይወለድም" ይላል። * በመጀመሪያ ቃል ነበር፣ ያ ቃል እግዚአብሔር ነበር፣ ያ ቃል ሰው ሆነ፣ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው  የሚለውን ሲሰማ "ኢየሱስ የአላህ ባሪያና ነብይ ነው" ይላል። * እኔን ያየ አብን አየ፣ እኔና አብ አንድ ነን፣ አብ የሚያደርገውንንያንኑ ወልድም ያደርጋል የሚለውን ሲሰማ ፣ "ኢየሱስ ያለ...