ጎሰኝነት/ኑዑስ ብሔርተኝነት ባለ ረዥም ታሪኳ ኢትዮጵያ ውስጥ ሳይቀር እንዴት ተፈጠረ፣ እንዴትስ በአፍራሽነቱ ጸና?
የሀገራችን ዋና የመከራ ምንጭ፤ የስደት፣ ዘር ማጥፋት ደረጃ መድርስ
1. በማኅበራዊና ተፈጥሮአዊ ሰንሰለታዊ መስተጋብር የሚፈጠሩ ታሪካዊ አሻራዎች፦ በዓለም ውስጥ፣ በተለይ በአፍሪካችን ጎሣዎች የኖራሉ። ለዩ ቋንቋዎች፣ ልዩነት የሚያሳዩ ባህሎች፣ በተወሰነ ደርጃ በአስተዳደርና ፍትሕ ሥርዓት ለዩነታቸው እየተዋሐደ ሳይሆን እየደመቀ መቆየቱ ይታያል። ይህ ንዑስ ማንነት ጤናማ ሆኖ የሚኖረው ፖልቲካዊ መሣሪያ፣ የምጣኔ ሀብት ሽሚያ ምክኒያት ሲሆን ጎጅ፤ በተፈጥሮው ተከብሮና ተመጋጋቢ ህብረት አስገኝቶ ለእድገትና ለአቅም ምንጭ ይሆናል።
2. የቅኝ ገዥዎች ተጸኖ፦ በከፋፍለህና አዳከመህ ግዛ የቅኝ ግዥዎች ስልት በቀጥታ በአካል ተገኝተው ባርያ ያደረጓቸው የአፍሪካ ሀገራት፣ እንደ ኢትዮጵያ በትምህርት ስም አእምሮ አጠበው ባርያ ያደርጉት አገር ውስጥ ያሉ ታሪካዊና በማኅበራዊ መስተጋብራዊ ዝግመተ ለውጥ የተፈጠሩ ኑዑሳን-የጎሣ ማንነቶች ከህብረታዊ አንድነትና ከተዋህዶ በተቃራኒ እንድ ሕወሃትና እንደ ኦነግ ባሉ የባዕዳን የአእምሮ ባሪያ ልሂቃን ጠላትነት አፍርተዋል። ከመዋሀድ በተቃራኒ መራራቅና መጠፋፋትን ሳይቃወሙት ለልሂቃኑ የጥፋት መሣሪያነት ተሰልፈው ቀጥለዋል።
3. የቋንቋና የባህል ብዝኃነት፦ አፍሪካ ውስጥ በአጠቃላይ በአንድ ሀገረ-መንግሥት ውስጥ ብዙ ቋንቋ ተናጋሪዎችና ልዩ ልዩ ባህሎች አሉ። እንዚህ ልዩነቶችን ወደ ሀገራዊ የጥንካሬ ምንጭ ለማሳደግ ከሚደረገው ጥረት የበለጠ በቱሪስት ሸቀጥነት፣ በየጎሣ መሪዎችና የየጎሣው አባል ልሂቃን የግል ጥቅሞች አገልግሎት ከማዋል ፍላጎት የመነጨና በውጭ ጣልቃ-ገብነት ምክኒያት አሉታዊ ልዩነቶች እንዲፈለፈሉ ተደርጓል። በዚህ ምክኒያ የጎሣ ማንነቶች መርዛማና አፍሪካን እጅግ የሚጎዱ ሆነው ተከስተዋል።
4. ማኅበራዎና ፖልቲካዊ መዋቅራት፦ ባፍሪካ በተለይ ሁኔታ በኢትዮጵያ እጅግ እየተዋሀደና እየተናበበ በማደግ ላይ የነበርውን የየጎሣ ንዑስ ማንነቶችን በመቀልበስ የሀገርና የሕዝብ ውድቅት፣ የአፍሪካ ሀፍረት፣ የአድዋ ቁስለኞች ደስታ ያደርጉት የሕወሃትና የኦንግ ጎሣቂ ፖልቲከኞች ናቸው። እነዚህ ፖልቲክኞች የማያስቡ፣ ባዕዳን ያስተሟራቸውን እንድ ፈጣሪ ቃል የሚያምኑ፣ ሀግራውያን ሊቃውንትንና የሃይማኖትም ሆነ የባህል አባቶችን የሚንቁ፣ ከቁስ ብልጽግና ሰውን አሳንሰው የሚመለክቱ ደናቁርት በመሆናቸው ጠቃሚ የማንነት ልዩነቶችን ወደ ተመጋጋቢ ህብረታዊ ጥንካሬ ከመቀየር በተቃራኒው የሚሞክሩተን “አሐዳውያን” ብለው በጠላትነት ፍርጀው ጦርነት አውጀውባቸው ንዑስ ማንነትን በመዋቅር ደረጃና በሕገ-መንግሥት፣ በአስተዳደር ክልል፣ በጦር መሣሪያ ታግዘው አንግሠዋል። ሰዎች ራሳቸው ለፖልቲካዊና ማኅበራዊ መዋቅራት መሣሪያ አድርገው ሌላውን እስከሚያጠፉ ድረስ ራሳቸውን በእቃነት አቅርበው ከተዋህዶ ርቀው በዝኃ ንዑስ የጎሣ ማንነትን ወደ ፍጹም የተፈጥሮ ልዩነት ወደ ማስመሰል አሻገሩት።
5. መልካዐ ምድራዊ ሁኔታዎች፦ አንዳንድ ጎሣዎች በመሬት አቀማመጥ ምክንያት ከሌሎች በቀላሉ የማይገናኙ በመሆናቸው ልዩነታቸውን ይዘው ይኖራሉ፤ ሌሎቹ በግብርና፣ በአርብቶ አደር-ዝላልነት፣ በከትሜነት ወዘተ የአኗኗር ዘይቤ ምክንያት ንዑሳን ምንነቶች ለርዥም ጊዜ በተመጋጋቢ ሕብረት ሳይዋሀዱ ቀጥለዋል። ይህንን የፖልቲካ ረዮታቸው ከሰው ልጅ ተፈጥሮ አንጻርና ለዘልቄታዊ የትውልድ ደህንነትና ልማት ሳይሆን ለከፋፍለህና አጋጭተህ ግዛ መሣሪያ አድርግው ልዩነቱን አስቀጥለዋል።
ኦርቶዶክሳዊነት ንዑስ ጎሣዊ ማንነትን እንዴት ለሰው ልጆች ውህደትና ድኅነት ታስተማራለች?
1. የሰው ልጅ በግዚአብሔር አምሳልና አርአያ በመፈጠሩ ያለው መሠረታዊ ማንነት (ዘፍ 1:27) ፦ በታሪክ ሂደት፣ በአኗኗር፣ በመልካዐ ምድራዊ ምክንያት፣ በማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተጸእኖ፣ በቋንቋና ባህል ልዩነቶች ምክንያት የሚፈጠሩ ንዑሳን ማንነቶች ሁሉ በእግዚአብሔር አርአያ መፈጠሩ ጠቅላይ ማንነቱ ስለሆነ ልዩነቶችን እንደ ማኅበረሰብ ዘርፈ-ብዙ ደካማ ጎኖች የሚያሞላላ እንጂ የሰውነት ልዩነት አይፈጥርም በሚል አስተምህሮ የሰው ልጆችን በእኩልነት፣ በቤትስብነት፣ ክርስቲያን የጠምቅት ልጅ ሲሆን ደግሞ ከፍጥርት ያለፍ የግዚሽብሔር ልጅነት ያዋሐዳቸው እንደሆኑ ታስተምራለጭ። በዚህ አስተምህሮዋ ንዑሳን ማንነቶችን እንደ አንድ አካል ብልቶች እንጂ ራሳቸውን እንደቻሉ አካላት ለየብቻ አቁሞ ማበላለጥን ፈጽሞ የሚቃወም አስተምህሮ ነው።
2. የምሥጢረ ሥላሴ አስተምህሮ፦ አንድነት ባለው ሶስትነት አስተምህሮዋ፣ በአብ እና በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ሶስት በመለኮት፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ማለት ልዩነት በተዋህዶ አንድነት መገለጥ ሕይወት፣ ህልውና ፍጹምነት ነው ስትል ብዝኃነትን ህብረታዊ አንድነት ለሕይወት ነው።
3. የክርስቶስ አካል ብልቶች የሆኑ የጥምቀት ልጆች አንድነት፦ ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያዊ 1ቆሮ 12፡12-27 ቤተ ክርስቲያን የአንድ የክርስቶስ አካል ልዩ ልዩ ተግባራት፣ ቅርጽና አቅም ያላቸው ብልቶች ብላ ከግዚአብሔር የተቀበለችውንና ያየቸውን በማጽናት ብዝኃነትን የማይለያዩ የሕያውነት መሠረት እንደሆነ ታስተምራለች። ሙሉነት የልዩነቶች ትብብርና የሕይወት መሠርት መሆኑን በማጽናቷና ለዚህ በመድከሟ እንደ ሕወሃትና ኦነግ ያሉ የጎሣ ልዩነትን ወድ ተፈጥሮ ልዩነት አይነት የመጠፋፋት መንገድ የሚኖሩ ወገኖች “አሓዳዊ” በሚል ትርጉሙን በማይረዱት ጽንሰ ዐሳብ ኦርቶዶክሳዊነትን ጥርሳቸውን ነገሰው ይዋጓታል።
4. በፍጹም የክርስቶስ ፍቅር የሚመራ ማኅበራዊ ፍትሕ እና ይቅርባይነት፦ ኦርቶዶክሳዊ ክርስትና የነጽሮተ ዓለም ምንጭዋ የክርስቶስ ትምህርትና አራያነት፣ የግዚአብሒር ፍትሓዊነትና ምህረትን መሠረት ያደርጋል። ቀዱስ ጳውሎስ በገላቲያ 3፡28 እንደተብራራው ባህል፣ ቋንቋ፣ የኖሮ ዘይቤ፣ ፖልቲካዊ ልማድ፣ ቀዳሚ ፍልስፍና ሁሉ ሰውን ከሰውነቱ፣ የጥምቀት ልጅን ከክርስቶስ አካል ብልትነትና የእግዚሽብሔር የጸጋ ልጅነት የሚለየው እና ብልጫ ያለው ንዑስ ማንነት ፈጽሞ የለም በሚል አስተምህሮዋና ተግባራዊ ኑሮዋ ታሳያለች። በዚህ አቋማ በዘርኞችና ከፋፋዮች እጅግ ትጠላለች፣ ተጠቃለች።
በዛሬዋ ኢትዮጵያ በዘርኞች ፓርቲዎችና መንግሥታት ለምን እንደምንጠላ እንርዳ! የሚግባውን መፍትሔ እንሻ!
አስተያየቶች