ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

መከላከያ ውስጥ የምትገኙ ሁሉ በእነዚህ ጥያቄዎች ራሳችሁን መርምሩ!!!

#መከላከያ ውስጥ የምትገኙ ሁሉ በእነዚህ ጥያቄዎች ራሳችሁን መርምሩ!!! 👉🏾 የአገር መከላከያ ማለት ማንን ነው የሚከላከለው? አሁን በያዘው ተግባሩ ስሙና ግብሩ ይገናኛል?   👉🏾 የኢትዮጵያዊያን ወይስ አብይ ሥልጣን አስጠባቂና የኢትዮጵያ መሠረቶች ለመናድ የተዘጋጀ መሣሪያ? 👉🏾 " የአገርን ድንበር በ ሱዳን   ተጥሷል፥ ዜጎች ከእርሻ መሬታቸው ላይ ተፈናቅለዋል። መከላከያ ምን አደረገ? ዜጎችንና ድንበሩን ተከላከለ? 👉🏾 ምሥራቁን ለአልሸባብ ክፍት አድርጎ አማራን ለመውጋት እጓጓዛል፤ ይህ ቀዳሚ ተግባሩ ነው? 👉🏾 የሽመልስ አብዲሳና የአሻድሊ ሐሰን አራጆችን እንደ ፈቃዳቸው በየክልሎቻቸው ውስጥ አሠማእተው በአማፅያን ተፈፀመ የሚል ሽፋን እየሰጡ ሺዎችን በጅምላ ሲያስፈጁ፥ ሚሊዮኖችን ሲያፈናቅሉ  5 ዓመታት አልፎ ቀጥሏል። መከላከያ ምን አደረገ?   👉🏾 አማራ ክልል የገባው መከላከያ  # የአብይአህመድን #PMAbiyAhmed ትዕዛዝ ተቀብሎ አማራን፥ ጋሞን፥ ጉራጌን ለማጥፋት ከተማ ለከተማ ንጹሐንን ይረሽናል (አርባ ምንጭና በመላው አማራ) ፥ ወንድ ይሰለባል (ላሊበላ) ፥ ሕጻናት ሴቶችን ይደፍራል ፥ ሴቶችና ወጣቶችን ይረሽናል (ወገል ጤና፥ ላሊበላ፥ ባህርዳር ፥ ቆቦ)። ይህን እያደረገ መከላከያ ማንን እየተከላከለ ነው?   👉🏾 መከላከያ በአማራ ክልልውስጥ   ሀስፒታልና ቤተክርስቲያን ፥ ዩኒቨርሲቲና ትምህርት ቤቶች ቅፅር ውስጥ   ይመሽጋል፥ ( ወገል ጤና፥ ባህርዳር፥ ላሊበላ፥ አጣዬ፥ ደብረ ማርቆስ -- ወዘተ )፥ ከዚያም ወደ ሕዝብ መኖሪያ ቤት ይተኩሳል። ይህን እያደረገ ማንን እየተከ...

ለብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት አስቸኳይ

ለሊቃነ #ጳጳሳት ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ፦    የሕወሐትን የጎሣ ሕገ-መንግሥት ተራክቦ አጠናክሮ የቀጠለበት የኦነግ/ኦሮሙማ የብልጽግና መንግሥት በትግራይ ሕዝብ ላይ የፈጸመውን አስነዋሪ እልቂትና ሁለገብ ጥፋት ፤ ሕወሐት በበኩሉ በአማራና በአፋር ሕዞቦች ላይ የፈጸመውን ተመሳሳይ ጥፋት ባለማውገዛችሁ ፤ የጥምቀት ልጆች በዘር ፖለቲካ እንዳይሳተፉና እንዳይጠፋፉ ባለማስተማራችሁና ባለማውግዛችሁ ቤተ ክርስቲያናችን ተዋርዳለች ፤ ልጆቿ ከእምነት እየፈለሱ በሥጋ እየተደመሰሱ ይገኛሉ።   አሁንም ቢሆን አረመኔው የዓብይ መንግሥት በአማራ ክልል እያደረሰ ያለውን የንጹሐን ጭፍጨፋና አቢያተ ክርስቲያናት ውድመት ፥ በአንድ ገዳም ብቻ ከ570 መነኮሳትና ገዳማዊያን ማጥፋቱን እስከአሁን አንደሚገባ አላወገዛችሁም። ይህ የምእመናንን በሥጋም ሆነ በነፍስ ስለሚጎዱ ምእመናን እንደሚገባ ያለመቆርቆር ልማድ ከቀጠለ  በቤተክርስቲያን ላይ እስከአሁን ከደረሰው መከፋፈል እና  ጥፋት የከፋ ችግር ይዞ ይመጣል። በመላው የአማራ ክልል፥ በአዲስ አበባ፥ በአዳማና ሌሎች ከተሞች  በኦርቶዶክሳዊያን ላይ የሚካሄደውን የማጥፋት ዘመቻ  በማስታረቅና በማረቅ ሚናችሁን ከከፍ ካላደረጋችሁና እምቢተኞቹን ካላወገዛችሁ በቤተክርስቲያን አንድነት ላይ የሚፈጠረውን ተጨማሪ ፈተና ፥ የምእመናን እልቂት ዳር ቆማችሁ  እንደተለመደው ሰላም ዘመን ሁሉ የበዓላት ዝግጀት ፣ ሕንፃ ምርቃ ፣ የአባቶች ሽኝትና ድግስ ፣ ወዘተ መቀጠል ምእመኑ እንደ እረኛ አባቶች ሊቀበላችሁ የሚቸገርበት ደረጃ ላይ ይደርሳል። በመሆኑም ከተለመደው የሰላም ጊዜ ልማድ በመውጣት አገርና ቤተክርስቲያንን በሚያድኑ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ እንድታተኩሩ በትህትና እናሳስባለን"

በአማራ ህዝብ ላይ የሚነሱ የተፋለሱ የጭቆና ትርክቶችን ስለመሞገት1 (unknown author) ክፍል 2

በአማራነታቸው የተጠቁ ሰወች ‘ዜጎች’ ናቸው ወይስ ‘አማሮች’?     ሰብዐዊነት የተፈጥሮ ስጦ ነውና ሁሉም ሰው በሰውነቱ እኩል ነው። መንግስት የተፈጥሮ መብቶችን ለያንዳንዱ ግለሰብ የሚያስጠብቅበትን ህግ ታሳቢ በማድረግ በተለምዶ ‘የዜግነት መብት’ ብለን እንጠራቸዋለን። ዋናው ቁምነገሩ ሰው በተፈጥሮ     ያገኛቸውን መብቶች መንግስት የመጠበቅ ሃላፊነት አለበት የሚለው ነው፡፡ ይህን ሃላፊነት የሚወስድ መንግስት የሌላቸው ሰወች፣ ዜግነት አልባ (ስቴትለስ) ሊሆኑ ይችላሉ። በማይንማር 600000 የሚደርሱ ሮሂንጋ የሚባሉ ጎሳ አባላትን መንግስት የእኔ ዜጎች አይደሉም ስላላቸው ዜግነት አልባ ሆነዋል።   ወደሃገራችን ስንመለስ በህግ “ኢትዮጵያዊ አይደለህም” የተባለ ስለሌለ በማንነት የሚጠቁ ሰወች ችግር ለጊዜው የዜግነት ችግር አይደለም። አማራም ይሁን ትግሬ፣ አፋርም ይሁን ኦሮሞ ወዘተ ሁሉም ዜጎች በሁሉም የሃገሪቱ ቦታ ያለዐድልዎ የመኖር መብት እንዳላቸው በህገመንግስቱ ተደንግጓል። ሆኖም ወደተግባራዊነቱ ስንመለስ፣ ይህ የግለሰቦች መብት ከብሄሮች ሉዐላዊነት ስር ወድቋል። ህገመንግስቱን ተከትሎ በተደራጀው የብሄርተኝነት ርዕዮተአለም ሳቢያ፣ በአማራ ህዝብ ላይ እንደዜጋ ሳይሆን እንደአማራነት የተፈጠረ ማፈናቀልና ግድያ ተፈጥሯል። ግድያው አንድ ወቅት ብቻ የተከሰተ ሳይሆን፣ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ፣ እጅግ ዘግናኝ ግፎች የተፈጸሙበትና በበርካታ ቦታወች የተከሰተ ነው። በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ በገለምሶ፣ በጋራ ሙለታ፣ በወተር፣ በሃብሩ፣ በአጋሮ፣ በአሰቦት፣ በሸቤ፣ ወዘተ በገደል በመወርወር፣ በቢላዋ በመታረድ፣ በእሳት በመቃጠል፣ በጥይት በመደብደብ አማራ ማንነት ባላቸው ላይ አሰቃቂ ግፍ ተፈጽሟል። የአገዳደል ዘዴው ራሱ በማንኛውም ንጹህ ዜጋ...

ሐሰተኛ ትርክትን ሳይንሳዊ የማስመሰል የዘረኞች ወንጀል

             ዘር ማጥፋትና የሐሰት ትርክት ቁርኝት፡- የሐሰት ትርክትን ሳይንሳዊ የማድረግ ፕሮጄክት እና ለእውነተኞች ምሁራን የቀረበ ጥሪ   የጽሐፉ መደምደሚያ አጽሕሮት ·        በኢትየጵያ ጠልነት፣ በኦርቶዶክስ ጠልነትና በአማራ ጠልነት የተሰለፉ ምሁራን የሚከተሉት ሃይማኖትና ፍልስፍናቸው በአብዛኛው ከኦርቶዶክስ ክርስትናና ከባር የኢትዮጵያ እሰልምና ውጭ የሆኑ ናቸው (ለምሳሌ ማርክሲሰት፣ ዉሀቡ ጽንፈኛና የጝራኝ አህመድ ናፋቂ፣ የናዚ ፍጡር “የጀርምን ክርስትና”-ቀመስ ፕሮቴስታንን፣ ከክርስትናና እስልምና ውጭ ሆኖ በባህል ስም የጠራና የሀሰት አምላክ የሚመልክ፣ ከማርክሲዝም የመደብ ፀንሰ ሀሳብ ተውሶ አዲስ የብሔረሰብና የጎሣ አሰላለፍን በመደብ ደረጃ የፖለቲካ ርእዮት አድርጎ የሚያምን፣ ማንኛዉም የአገሩን ሃይማኖትና እምነት ሳይማርና ሳያውቅ በምዕራባዊያን ወይንም በአረቦች እሴት ተመስጦት ሰመመን ውስጥ የገባ ምሁር) ። ·        የአገራችን የኢትዮጵያ የዘረኝነት ፖለቲካ ርእዮትና፣ ርእዮቱን እውነት ለማድረግ የሐሰት ትክትን ታሪካዊ የማድረግ ስልት ሁለቱም በአውሮፓ ቅኝ ገዥዎችና ባሪያ አሳዳሪዎች በተለይ በናዚ ፓርቲ የተሚከሩት በቀጥታ በመገልበጥ ነው ·        ዘረኝነት ላይ የመሠረተ ፖለቲካ ተቀባይ አግኝቶ ለሥልጣን የሚያበቃው ሐሰትን ሳይንሳዊ አስመስለው ማቅረብ የሚችሉ ምሁራን ሲገኙ እና ፐሮጄክቱን ሲያገለግሉ ብቻ ነው ·        ዘረኝነት ሕዝብን ከፋፍሎ...