ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

መከላከያ ውስጥ የምትገኙ ሁሉ በእነዚህ ጥያቄዎች ራሳችሁን መርምሩ!!!

#መከላከያ ውስጥ የምትገኙ ሁሉ በእነዚህ ጥያቄዎች ራሳችሁን መርምሩ!!!

👉🏾 የአገር መከላከያ ማለት ማንን ነው የሚከላከለው? አሁን በያዘው ተግባሩ ስሙና ግብሩ ይገናኛል?  

👉🏾 የኢትዮጵያዊያን ወይስ አብይ ሥልጣን አስጠባቂና የኢትዮጵያ መሠረቶች ለመናድ የተዘጋጀ መሣሪያ?

👉🏾 " የአገርን ድንበር ሱዳን  ተጥሷል፥ ዜጎች ከእርሻ መሬታቸው ላይ ተፈናቅለዋል። መከላከያ ምን አደረገ? ዜጎችንና ድንበሩን ተከላከለ?

👉🏾 ምሥራቁን ለአልሸባብ ክፍት አድርጎ አማራን ለመውጋት እጓጓዛል፤ ይህ ቀዳሚ ተግባሩ ነው?

👉🏾 የሽመልስ አብዲሳና የአሻድሊ ሐሰን አራጆችን እንደ ፈቃዳቸው በየክልሎቻቸው ውስጥ አሠማእተው በአማፅያን ተፈፀመ የሚል ሽፋን እየሰጡ ሺዎችን በጅምላ ሲያስፈጁ፥ ሚሊዮኖችን ሲያፈናቅሉ  5 ዓመታት አልፎ ቀጥሏል። መከላከያ ምን አደረገ?

 👉🏾 አማራ ክልል የገባው መከላከያ  #የአብይአህመድን #PMAbiyAhmed ትዕዛዝ ተቀብሎ አማራን፥ ጋሞን፥ ጉራጌን ለማጥፋት ከተማ ለከተማ ንጹሐንን ይረሽናል (አርባ ምንጭና በመላው አማራ) ወንድ ይሰለባል (ላሊበላ) ሕጻናት ሴቶችን ይደፍራል፥ ሴቶችና ወጣቶችን ይረሽናል (ወገል ጤና፥ ላሊበላ፥ ባህርዳር ቆቦ)። ይህን እያደረገ መከላከያ ማንን እየተከላከለ ነው?  

👉🏾 መከላከያ በአማራ ክልልውስጥ  ሀስፒታልና ቤተክርስቲያን፥ ዩኒቨርሲቲና ትምህርት ቤቶች ቅፅር ውስጥ  ይመሽጋል፥ (ወገል ጤና፥ ባህርዳር፥ ላሊበላ፥ አጣዬ፥ ደብረ ማርቆስ-- ወዘተ)፥ ከዚያም ወደ ሕዝብ መኖሪያ ቤት ይተኩሳል። ይህን እያደረገ ማንን እየተከላከለ ለነው?

👉🏾 መከላከያ ገዳማት ላይ ተኩሶ ከ570 በላይ መናኒንን በአንድ ቦታ ብቻ በምሥራቅ ጎጃም ደብረ ኤሊያስ ፈጅቷል፤  በከተሞች  ዜጎችን ንብረት፥ ገንዘብ  ይዘርፋል፥ አንደ ማፍያ ከሕግ ውጭ ሰው እያሠረ ብር እያስከፈለ ይፈታል ያሥራል። ይህን እያደረገ መከላከያ ማንን ይከላከላል?   

👉🏾 መከላከያ የማነው? ማንን ነው የሚከላከለው?

👉🏾 መከላከያ የዜጎች ሁሉ ጋሻ ከሆነ ለምን አሁን የሚያደርገውን ወንጀል በቀጥታ ከአብይ አህመድ ትዕዛዝ ተቀብሎ ያለ ጥያቄ መፈጸሙን ቀጠለበት?

👉🏾 የኢትዮጵያ ሕዝብ መከላከያ ነው ወይስ ነበሯን ኢትዮጵያ አጥፍተን አዲሲቷን ኦርቶዶክስ ክርስትና እና አማራ የሌለባት አገር እንፈጥራለን በለው በውጭ አገራት እየታገዙ ሊያጠፉን ለሚሠሩ የፖለቲካና የጽንፈኛ ውጭ-ገብ እምነቶች መሣሪያ ሆኗል?

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...