ለሊቃነ #ጳጳሳት ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ፦
የሕወሐትን የጎሣ ሕገ-መንግሥት ተራክቦ አጠናክሮ የቀጠለበት የኦነግ/ኦሮሙማ የብልጽግና መንግሥት በትግራይ ሕዝብ ላይ የፈጸመውን አስነዋሪ እልቂትና ሁለገብ ጥፋት ፤ ሕወሐት በበኩሉ በአማራና በአፋር ሕዞቦች ላይ የፈጸመውን ተመሳሳይ ጥፋት ባለማውገዛችሁ ፤ የጥምቀት ልጆች በዘር ፖለቲካ እንዳይሳተፉና እንዳይጠፋፉ ባለማስተማራችሁና ባለማውግዛችሁ ቤተ ክርስቲያናችን ተዋርዳለች ፤ ልጆቿ ከእምነት እየፈለሱ በሥጋ እየተደመሰሱ ይገኛሉ።
አሁንም ቢሆን አረመኔው የዓብይ መንግሥት በአማራ ክልል እያደረሰ ያለውን የንጹሐን ጭፍጨፋና አቢያተ ክርስቲያናት ውድመት ፥ በአንድ ገዳም ብቻ ከ570 መነኮሳትና ገዳማዊያን ማጥፋቱን እስከአሁን አንደሚገባ አላወገዛችሁም። ይህ የምእመናንን በሥጋም ሆነ በነፍስ ስለሚጎዱ ምእመናን እንደሚገባ ያለመቆርቆር ልማድ ከቀጠለ በቤተክርስቲያን ላይ እስከአሁን ከደረሰው መከፋፈል እና ጥፋት የከፋ ችግር ይዞ ይመጣል።
በመላው የአማራ ክልል፥ በአዲስ አበባ፥ በአዳማና ሌሎች ከተሞች በኦርቶዶክሳዊያን ላይ የሚካሄደውን የማጥፋት ዘመቻ በማስታረቅና በማረቅ ሚናችሁን ከከፍ ካላደረጋችሁና እምቢተኞቹን ካላወገዛችሁ በቤተክርስቲያን አንድነት ላይ የሚፈጠረውን ተጨማሪ ፈተና ፥ የምእመናን እልቂት ዳር ቆማችሁ እንደተለመደው ሰላም ዘመን ሁሉ የበዓላት ዝግጀት ፣ ሕንፃ ምርቃ ፣ የአባቶች ሽኝትና ድግስ ፣ ወዘተ መቀጠል ምእመኑ እንደ እረኛ አባቶች ሊቀበላችሁ የሚቸገርበት ደረጃ ላይ ይደርሳል። በመሆኑም ከተለመደው የሰላም ጊዜ ልማድ በመውጣት አገርና ቤተክርስቲያንን በሚያድኑ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ እንድታተኩሩ በትህትና እናሳስባለን"
አስተያየቶች