ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ የሚለው የሀገሬ ብሂል የወ/ሮ መዓዛን የኤል ቲቪ ቃለመጠየቅ ተከትሎ ተመላለሰብኝ፡፡ እንዲሁም የቤተክርስቲያን እና ኢትጵያዊ ምነነትን በሁሉመ ዘርፍ የመድፈር ሂደት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ታየኝ፡፡ አንዴ በማርክሲዝም፣ ሌላ ጊዜ በፌሚኒዝም፣ ሌላ ጊዜ በካፒታሊዝም፣ ሌላ ጊዜ በተሐድሶ፣ አንዴ …. በስንቱ እንደፈራለን!!! ይህ ሁለንተናዊ ድፍረት አሳሰበኝ -- እናንተስ? ----የሚያሳስባችሁ ሁሉ የ ዚህ መፍትሔው የክርስቲያኖች ከጥልቅ እንቅልፍ መንቃት ነውና !!!! ነቅተን በትምህረትና በእውቀት ልዕልና፣ በህግ፣ በጸሎት፣ወዘተ መከላከል መጀመር ነው፡፡ ጊዜ የለንም፡፡ ይህ ካልሆነ ባዕድ አምልኮ፣ ሰዶማዊነት፣ የሰው ልጅ አካል እየበለቱ ለመለዋወጫ መጠቀም፣ አሁን በኢትዮጵየ የተፈቀደው ውረጃ ሰውን መብት ነው እያሉ ራሱን አንዲገድል መፍቀድ፣ ወዘተ ተማርን፣ ሠለለጠንን በሚሉ የሀገራችን ልጆች ጀርባ ተጭኖ ከምዕራባዊያን የሚፈሰው የርኩሰት ጎርፍ ነገ አስገዳጅ ሐገራዊ ሕግ ሆኖ ይቀርብልናል፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን የተደፈረችባቸው ዘርፎች፡ እና የሁላችንንም ጥረትና ተሳትፎ የሚጠይቁ ጉዳዮችን ከማንሳቴ አስቀድሞ በዚህ መልዕክቴ ቤተክርስቲያን ብዬ የምጠራው፡ ---- ክርስቲያን ግለሰብ ሰው፣ ---- የክርስቲያኖች ስብስብ፣ ---ክርስቲያናዊ እምነት ያመነጫቸውና ክርስትና የሚገለጥባቸው የግልና የማኅበራዊ ኑሮ ዘይቤዎች ማጠበቂያ ማኅበራ ዊ አደረጃጀት ፤ --- ክርስቲያኖች አምልኮ የሚፈጽሙባቸው ቦታዎችና ለአገልግሎት ተለይተው የሚሠሩ ቁሳቁሶች፤ ---የክርስቲያኖች መልዕክት የሚለዋወጡባቸውና አምልኮአቸው...
This is a spot where I post and share part of my daily reality. I would love to hear from others too to learn how differently we interpret daily encounters including our imaginations. ይህ ሥፍራ የየዕለት ገጠመኞቼን፣ እንዴት በዕለቱ እንተረደሁትና የማስበውን ለሌሎች ያማጋራበት ነው፡፡ የሌሎችን በመስማትና ምን ያህል ዓለማችንን በተለያየ መንገድ እንደምንመለከታት ለመማር እጓጓለሁ፡፡