ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ
👉 "አለን" የሚል ከአለ በዚህ ጽሑፍ መጨሻ ላይ የተቀመጡና ለእኛ አንገብጋቢ ከሆኑት ጥያቄዎች አንዱን በምክክር ኮሚሽኑ 8ቱ አጀንዳ መካከል ያሳየን!!
=========================================
ስማዕታቱ የዚህን የምክክር ኮሚሽንና የአብይን የምድር ላይ #ሽፍጥ ይታዘባሉ!! ወደ እግዚአብሔርም እንዲህ እያሉ ይካሰሳሉ፦
"ሁሉን የምትገዛ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፤ እስከ መቼ አትፈርድም? እስከ መቼስ ደማችንን በምድር በሚኖሩት ላይ አትበቀልም?" (ራእይ ዮሓንስ 6፡10)
===============================================
የ"አገራዊ" #ምክክር #ኮሚሽን ፋይዳው ምንድነው?
ግልጽ መልስ የሚሆነው፦ የ50 ዓመታት መርዛማ የሐሰት ትርክትን ከፍ በማድረግ የሚከተሉትን የሕወሃትና የኦነግ፣ ኋላም ብልጽግና የተረከባቸውን ግቦች እንዲሳኩ ሕጋዊ ሽፋን መስጠት ነው፦
(1) በሕወሃት፣ በኦነግ፣ ብጽንፈኛ ዉሃብያዎች፣ በአድዋ ቁስለኛ ወራሪዎች ደብዛው እንዲጠፋ ከ50 ዓመታት በላይ የተዘተመበትን ኢትዮጵያዊነት፣ ነባር የስነ-መንግሥት እና የሕዝብ ታሪክ፣ በተለይ ኦርቶዶክሳዊነት እና አማራ የተባለውን ክፍለ-ሕዝብና የእርሱን እሤቶች የሚካሩ ነገዶች ሁሉ ላይ የሚካሄደውን ጥቃት ሕጋዊ ማድረግ፤
(2) የኢትዮጵያን ታሪክ በኦነጋዊ የ150 አመታት ትርክት፣ "የአገር ባለቤትነት" ጥያቄ በሚል ሽፋን ሌላውን አገርና ታሪካ የማሳጣት ነውረኛ እና ኢሰባዊ ፋሽስታዊ ዘመቻ፣ ዘር የማጽዳት ሙከራዎችን ሕጋዊ ማድረግ፤
(3) በአብይ አህመድ ስሌት፣ በሕወሃት የ50 ዓመታት ድካም፣ በሮማኖ ቻውስካን እና ሄንሪ ኪሲንጀር ኢትዮጵያን የማጥፋት ምክር መሠረት ኢትዮጵያን ወደ ትናንሽ አገር ለመክፋፈል ቀላል እንዲሆን ሕዝብን የምታስተሳስር፣ ታሪክን ሰንዳ ያኖረች፣ ኢትዮጵያዊ ስበናና ማኅበረሰብ የገንባት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን አገራዊ ሚና ማሣጣት፤
(4) አማራን መምታት፣
(5) ጽንፈኞችን በነባር እስልምና ላይ ማንገሥ ኢትዮጵያን አረባዊ ማድረግ፣
(6) ታላላቅ የሚባሉ የትግራይና የኦሮምያ ሪፐብሊኮችን ለመመሥረት የጋራ ምልክቶችን "ከነጠላ ትርክት ወደ ህብረ-ትርክት" ማሻገር በሚል የጎሣ ፖለቲካኞች ስንኩል እና አፍራሽ የባዕድ ሤራ ማስፈጸሚያ ፖለቲካ ቀመር መሠረት ኢትዮጵያን የማጥፋቱን ሂደት ሕጋዊ ማድረግ፤
(7) ከ30 ዓመታት የወያኔ-ኦፒዲኦ/ኢሓዴግ የዘር ማጥፋት ፕሮጄክት ቀጣይ የሆነውን የብልጽግና መንግሥት ወንጀል ለማደባበስና ሂደቱን ሕጋዊ ለማድረግ --- ናቸው።
በአጭሩ፦
ምክክሩ ለኢትዮጵያ ሰላም፣ ልሕዝቦቿ ውሕደት፣ ለጠፋው ታሪክ እርምት፣ ለተፈጸምው ግፍና እልቂት ፍትሕና ካሳ፣ ለተፈናቀልው መልሶ መቋቋም አያመጣም። በአንጻሩ የሕወሃት እና የኦነጋውያንን አገር የማፍረስ ሂደታዊ እድገት አዲስ ደረጃ ነው። በአምጽና በየድርጅቱ የደረግ የነበረውን አገር አገር የማፍርስ ፕሮጄክ መንግሥታዊና ሕጋዊ ማኅቀፍ ከመሥጠት አያልፍም።
አጀንዳዎችን ስንመለከትና ተሳታፊዎቹን ራስ ገዝነትና በህሊና የመመራት ሁኔታ አጠራጣሪ መሆኑ፣ በአብይ ቁጥጥር ሥር መሆኑ የክርስቲያን ዘር የማጥፋት ግቡ አገር አፍርሶ የትግራይና የኦሮምያ ሪፐብሊኮችን የመፍጠር የሂደት አንጓ ነው።
አጀንዳዎቹ በሙሉ ያለንበትን መከራና የጎሣ ነጻ አውጭዎችን፣ የጽንፈኞችን ትርክትና ድምጽ የተሸክም እንጂ የኢትዮጵያን ሕዝብ በተለይ ኦርቶዶክሳውያንን አይመለከትም ብቻ ሳይሆን ጎጂሽቸው እንደሚሆን አያስጠርጥርም።
የሐሰት ትርክትን የ የአብይ አህመድና የጽንፈኛ ዉሀብያን ፍላጎቶችን እንደ ድሪቶ ከምሮ "አገራዊ አጀንዳ" በሚል ከሰው ልጆች ውርደትና እልቂት፣ ከታሪክ ድለዛና ቀጣይ የመጠፋፋት ብልጽግናዊ ሴራ የከፋና ወንጀልን የመቀደስ፤ ፍተሕን የመቅበርና ወንጀለኛ ተቋማትን የማንጻት የክፋት ሁሉ ቁንጮ ነው።
ኦርቶዶክሳዊውን ማኅበረሰብ የሚወክል በሌለበት፣ በኦርቶዶክስ ስም በግል የሕይወት ስብራትና ነውር የሚሳቀቁ፣ መንግሥት መረጃ ይዞባቸው እንደ እቃ የሚጫወትባቸው፤ በጸራራ ፀሐይ በጅምላ የተጨፈጭፉ የጥምቀት ልጆችን እንኳ መረጃ ለመዘገብ እና ለዓለም ለማጋለጥ እምቢኝ ያሉ የወንጀለኛ ተባባሪ ሙሰኞች፣ እውነትን የሚፈሩ የሐሰት መኖኮሳትና ጳጳሳት በምክክሩ ውስጥ መጎለት ውጤቱ አደገኛ ነው።
እየተካሄደ ያለው ክርስቲያንን በሁለንተናው የማሳነስ ከተቻለ የማጥፋት መንግሥታዊ ወንጀል ሳይሞግትና አጀንዳ አድርጎ ሳያቀርብ ጠላቶቹ በቀመሩት አጀንዳ ዙሪያ እንደ ጥምብ አንሳ መሥፈር የካባና የወርቅ ሽልማት ለወንጀለኞችና ታሪክ ሸቃጭ ቁማርተኞች እያድለ ቅዱስ ገጽታ ሲሰጥ ከኖሩ ሰዎች ምን ይጠብቃል? መሳተፋቸው በግልጽ ሞታችንና ስደታችንን፣ የታሪካችን በሐሰት መጠልሸትና ከአንድ እንደ ጠላት ተፈርጆ ከሚጠቃው የማርኛ ተናጋሪ ክፍለ-ሕዝብ ጋር በማቆራኘት አብሮ ሁለቱንም ሲያጠቃ የኖረ ሥርዓት፣ ሕገ መንግሥቱን እከላከላልሁ በሎ ፕሪቶሪያ ድርስ አሜሪካንን ጋብዞ በአንድ አገር ሕዝቦች መካክለ ወርዳና አውራጃ የሚያቃርጥ፣ ሕግ አስከብራለሁ ብሎ ከአርበ መግደያ እየተዋሰ ፍጅት ከሚፈጽም መሪጋ ተባብሮ ቀኖና ሐዋርያትን ከሚሽር ቡድን የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች አጀንዳ እና የቤተ ክርስቲያን ፍላጎት ውክልና ያገኛል ብሎ መጠበቅ አላዋቂነት ብቻ ሳይሆን ከቁም ሬሶች ብቻ የሚጠበቅ ነው።
ተሳትፎው እንደተለመደው በጅምላ የሚገደለውን ክስቲያን ለሚብስ እልቂት አደንዝዞ እና አፈሰዝዞ በባዶ ተስፋ ማቆየት ይሆናል።
ይህን የሁላችንንም ሽፍጥና አድርባይነት፦
እኛ በአካለ-ሥጋ የቆምነው ነገር ግን ከክርስትና ከመራቃችን የተነሳ ለእውነት ክርስቶስ፣ ለቤተ ክርስቲያን ልዕልና፣ ለፍተህ እና ለክብረ ሰብእ መሟገት ብንፈራም በእምነት ጸንተው ሰማዕት የሆኑት የአርሲ፣ የወለጋ፣ የከሚሴ፣ የሐረርጌ፣ የጅማ፣ የባሌ፣ የኦጋዴን፣ የጉምዝ ሰማዕታት ከላይ ሆነው ይፋረዳሉ።
እውነትን በድግስና በፕሮፓጋንዳ መቅበር አይቻልም።
እውነተኛ ምክክር እና እውነተኛ ተወካይ ቢኖረን ኖሮ የሚከተሉትን ቁልፍ አጀንዳዎች ከማያነሳ የምክክር ኮምሽንና ጉባኤ ጋር የሚተባበር ቤት ክህነትና ሲኖዶስ አይኖርም ነበር ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳውያን አንድ ሆነው እንዲቃወሙት ጥሪ ያስተላልፋል፣ ለዓለም ማኅበረ ስብም ይህንን አዲስ የአደጋ መንገድ ያጋልጣል፦
(1) ታሪከን የሚመልከት አጀንዳ፦
👉. የሐሰት ትርክቶች በገለልተኛና በማስረጃ፣ በአርኪዮሎጂና በጥንት አገር በቀል (በወራሪ የአውሮፓ ሊቃውንት ተጣመው የተጻፉትን ሳይጨም) ይስተካከል፤
👉 በኦነግና በሕወሃት፣ በጽንፈኛ ዉሃብያ፣ በአድዋ ድል የቆሰሉና አገር አሳሽ ወይንም ሚሽነሪ ተብለው ሕዝቡን ለመክፋፈል የፈጠሯቸው ትርክቶች፣ የሰጧቸው ትምሀርቶች በዝርዝር ተቆጠረው ሳይንሳዊ ምላሽ እና መስተካከል እንዲደረግባቸው፣
👉 በግራኝ አህመድ ወረራ፣ በኦሮሞ የመስፋፋት ጉዞ፣ በዮዲት ጉዲት ወረራ፣ በማርክሲስት አብዮት፣ በዘር ናጻ አውጭዎች የ38 ዓመታት የውስጥ ነውጥ የደረሰው የማኅበረሰብ ታሪክ መዛባት፣ በሂደቱ በጋራ ያዳበርናቸው አዎንታዊና አሉታዊ የውህደትና የመሰንጠቅ ምልክቶች፣ የበላይ ለመሆን በተለያዩ ወገኖች በሐሰት ተፈብርከው በትውልዱ ላይ የተጫኑ ትርክቶች፣ አገራዊ የታሪክ አዘጋገብን አተናን ዘዴዎች እንዲመረመሩ፣ አስተዳደራዊ ጥፋትን ለቋንቋና ለሃይማኖት ወገን የማሸከሙን የሕወሃት፣ የኦነግና ይጽንፈኛ ዉሃብያ አካሄድ አውዳሚነት ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ እልባት መሥጠት፤
(2) ርስትን በሚመለከት፦
👉 በትርክት ላይ የተመሠረተ ወይንም በጎሣ ፖለቲካ ስሌት የሚፈጠሩ የመሬትና የተፈጥሮ ሃብታት ነጠቃና ድልድል፣ እንደ አውሮፓው የአፍሪካ ቅርምት የበርሊን ኮነፈረንስ ሕወሃትና በኦነግ የጋራ ሤራ አገርን በጣሊያን ወራሪ መንፈስ በጎሣ የመሸንሸን፣ በአንድ አገር ውስጥ መጤና ነባር የሚል ትርክት መፍጠርና ታሪክን በመቶዎች ዓመታት ብቻ የመጉመድ፣ ቀጥሎም የማፈናቀል፣ የመውርስ ሂደት (ለምሳሌ ከዲሬ ሼክ ሁሴን (አኔሬዎስ ገዳም) ጀምሮ እውነቱ ተነግሮ ቀዳሚ ባለቤቱና የዛሬው ባለቤቶች ተማምነው ለወደፊት የተዘገብ ታሪክ፣ አብሮ የመኖር ወሳኝ ድምዳሜና ስምምነት፣ ሕጋዊና ታሪካዊ ብያኔዎችን በመስጠት የግጭ፣ የመገፋፋትና የመካሰስ ሂደት እንዲቋረጥ፤
👉 ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተነተቁ የግዳማት፣ የአድባባያ አግለግሎት ቦታዎች ተቆጥረው እንዲመለሱ ብቻ ሳይሆን፣ የአግር እኩል ባለቤትነትን በሚያረጋግጥ ሕጋዊ ማኅቀፍ ቤተ ክርስቲያን የልጆቿን ሃይማኖቶአዊ አገልግሎት እንደ ልጆቿ ብዛት፣ እንደ እምነቱ ሥርዓትና ስተምህሮ ፍላጎት መሬትን በልማና ሳይሆን በታወቅ ሕግ የምታገኝበትና የምታስተዳድርበት ሥርዓት ማበጀት፤
(3) ፍትሕን በሚመልከት፦
👉 ለ38 ዓመታት እንዲመክክንና የመዋለድ ፍጥነቱ እንዲቀንስ፣ በሤራ ለአርብ ገርድ እንዲሆን እየተመለመለ የተሸጠው የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ወላድ ሴቶች ጉዳይ፣ በመንግሥት መዋቅር የተፈናቀለው ክርስቲያን፣ በሥርዓትና በፖለቲካ ሕይወቱን እንዲያጣ ከጎዴ እስከ ማርያም ደንጎላት፣ ከሚሴና በሻሻ፣ አርሲና ቡራዩ፣ አዲስበብባና ኮፈሌ ወዘተ ተቆጥሮ ተጥያቂነት፣ ካሣ፣ የወደፊት የደኅነነት ዋስትና ሥርዓት ጉዳይ፣
👉 በብልጽግና መንግሥት ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት እና በሕወሃት የተራዘም ሤራ በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ የሚደረገው ተጽእኖ፣ የጎሣ ጳጳሳት መሾም፣ የሳዊሮስ በአብይ ወታድሮች ታጅቦ ሻሸመኔ ላይ ፍጅት መፈጸም ጉዳይ፤ የመንግሥት በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት፣ የገዳማት "ነፍሰ ገዳይ ማሰልጠኛ ናቸው" ሐሰተኛ ክስና እርሱን ተከትሎ መንኮሳት መረሸን ጉዳይ፤
👉 የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥትና ኦፒዲኦ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ "አማራ/ነፍጥኛ" በሚል ኮድ ያካሄዱት የ38 ዓመታት ሁለገብ ጥቃት ጉዳይ፤
👉 በአብይ ጦር እና መዋቅር በሸዋ፣ በወሎ፣ በጎጃም፣ በወለጋ፣ በአርሲ፣ በሐረርጌ፣ በኦጋዴን፣ በትግራይ፣ በጎንደርና ባሌ በገዳማት፣ አድባራት፣ ካህናት፣ የአብነት ትምህርት ቤቶች ላይ የደረሱ ማቃጥል፣ ማፍልስ፣ ጭፍጨፋና ስም ማጥፋት፣ ይርስት ነጥቃ ጉዳይ፤
👉 በኦጋዴን በሕወሃት ጄኔራሎችና በክልሉ ምክር ቤት መሪነት በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ሰለትከአሄደው ዘር የማጽዳት ወንጀል ጉዳይ፤
የአገራዊ ምክክር አጀንዳዎች ተጠቃለው የፒዲኦ/ብልጽግናና የጽንፈኛ ዉሃብያ የጋራ አጀንዳ አለምሆናቸውን፣ ሌላውንም ወገን ማካተታቸውን ይመስክር ነበር። አሁን ግን እኛ የለንበትም።
(ፋንታሁን ዋቄ)


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...