ሕምሌ 12 ቀን 2018
ከፋንታሁን ዋቄ
=============================================
የኢትዮጵያ ሕዝብ የመከራ በር መክፈቻ ቁልፍ ያለው በሕወሃታዊ እና ኦነጋዊ አስተሳሰብ በተለከፉ የትግራይና የኦሮሞ ልሂቃን እጅ ነው።
ሕዝብን ከመከራ ለመገላገል፦
================================================
ይህች መራራ መልእክት ሕወሃት ለተባል የዘር ፖለቲካ ጣዖት ዋጋ ሲከፍልና ለኢላውንም ሲያስከፍል ለኖር፣ ለሚኖር የአዲሱ "ትጋራዋይነት" የጣዖት እምነት ለተንበረከከ የትግራይ ወጣት፣ ልሂቅና ባለማወቅ በጭፍን እልሚከተሉ ምስኪን የጥምቀት ወገኔ ሁሉ ትድረስልኝ።
መራራና ጨካኝ መሆኗ ሁላችንም ተያይዘን እንድንድን፣ ክፋትን እንድንተው፣ ከፖለቲካ ትርክት የሚመነጭ ዘረኝነትን ተተን ክርስቶስ የሰጥንን የጥምቀት ልጅነት፣ በፍጥረት ያገኘነውን ሰባዊ ክብር፣ በታሪክ ሂደት ያፈራነውን ኢትዮጵያዊነት ገንዘብ አድርገን ለ55 ዓመታት አካባቢ አገር ለማስቆረስ፣ አዳዲስ መነድሮችን አገር ልማደርገ ታላቋን ኢትዮጵያ ማፈራርስ ላይ የሙጥኝ ያለውን ሕወሃትንና በሰው ደም የተጨማለቀውን ኦነጋዊ ኦሮሙማ የተባል አዲስ የፖለቲካ የጣዖት እምነት ሁሉ ከማኅበራሰባችን ነቅለን በሰውነት ለመኖር ይጠቅማል በማለቴ ነውና --- ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሜቆራርጡ ሕወሃታውያንን እንደሌሉ ቆጥሬአቸዋለሁ።
=======================
እውነቱን እንጋፈጠው ከአልን የሕውሃት መከራ መፈልፈያ እና ማሰራጫ ማእከል ከትግራይ ሕዝብ የተገኝ ልሂቅና ለምገደል፣ ለመዋሸት፣ አገር ልማፍርስ፣ ከርስቶስን እንኳ በነግደ ትርክት ለመቀይር፣ ወግኖቹን ለመውረር የማያቅማማ ትውልድ ነው።
በሕወሃት የሚፈለፈለውና የሚሰራጨው መከራ ለመላው የኢትዮጵያ ቤተሰቦቹ በመዋቅር ደርጃ ለ30 ዓመታት ሲከፋፈልና ሕጋዊ ሲሆን ቆይቶ በተመሳሳይ የኦነጋዊው የአብይ አህመድ ምንግሥት ተረክቦት ለትግራይ ሕዝብ ድርብ እጥፍ አድርጎ መከራዊን እየጋተው ነው።
የትግራይ እናቶች ጦርነትን፣ የሌላውን መዋርደ ደግፈው ሲጨፍሩ ታይተዋል። በዚያው ልክ መከራው ጽንቶባቸው ሲያለቅሱና ሲጽልዩም ታይተዋል።
እናቶች ልጆቻቸውን አበረታትው "ትግራይ ትስእርርርር!!!" ብለው ለሌሎች ጥፋት ያዘመቷቸው ልጆች የተጠበቀው፦ ሌላውን የማዋረድ፣ ኢትዮጱያን አፍርሶ ትግራዋዮችን ብቻ ከሁሉ ዜጎች ከፍ አድርጋ የምታኖር አዲስ ሪፐብሊክ አገር የመፍጠር ህልም ሲቀር፣ ልጆቹም ራሱን በሚከላከል ወገን እጅ ሲያልቁ እጅግ አንጀቱ ያርራል፣ የሽማቀቃል፣ ደምም ፈስሶ ወጤቱ ተቃራኒ ሲሆን ሀዝን የበረታል።
በ30 ዓመታታ የሕወሃት የአግር ዘረፋ ገንዘብ የተገንባው መሠረት ልማት ይፈርሳል፣ ሕጻናት ይሞታሉ፣ ወጣቶች ይሰደዳሉ፣ ጎበዛዝቱ ከሞት የተረፉት ወንጀለኛ ይሆናሉ፣ ሌሎች ተፈናቃይ ሆነው ይራባሉ---- በዚህ ሁሉ ውስጥ የሕወሃት ባለሥልጣናት ለሌላ ዙር ጦርነት፣ ለሌላ ሴራ፣ ለሌላ ዘረፋና መርዛማ ተርክት፣ ለሌላ የባእዳን ጣልቃ ገብነት ይራወጣሉ።
ሀፍርት፣ ፀፀት፣ ማስተዋል የጎደላቸው የሕወሃት መሪዎች የላካቸውን መራባዊ አገር ሳያፍሩ ጠርተው፣ እንርሱ ራሳቸው የፈጠሩት ኦርንጋዊ አገር አፍራሽ አጋራቸውን ኦነጋዊ ብልጽግና እንደ መንግሥት ቆጥረው አንድን ሉዓላዊት፣ ታሪካዊት እና ጋናና የአፍሪካ እናት ኢትዮጵያን ለመቅበር ፕሮቶሪያ ወርደው ወረዳና አውራጃ ይደራደራሉ። ----
በዚህ ሁሉ ጥፋታቸው ወስጥ እንደተዘፈቁና ሳይታረሙ አሁንም የሚሰማቸው፣ የሚደግፋቸው፣ ዲፕሎማሲ የሚሰራላቸው፣ ቤተ ክርስቲያንን ሳይቀር አፍርሶ የጎሣ ጣዖትን ክርስትና በሎ የሚዘምርላቸው ሰው ከዚያው ከትግራይ ሕዝብ መካከል ይመነጫል።
በዚህ ወር ግን እናቶች በጽሎት፣ በምህላ፣ "ለጆቻችን ለሌላ ጦርነት አይወስዱም" በሚል ተቃውሞ ሲያሳዩ አደባባይ ላይ ታየትዋል። ይህ የሚያበረታታ ነው። የሕወሃት መቅስፍትነት፣ ኢትዮጵያን የማፈርስ እኵይ ዓላማው፣ አማራን የመጥላትና በሁሉም አስከብቦ የማጥቃት አሳፋሪ ተግባሩ፣ ታሪክን የመሸቀጥና የጋራ አገርን በመንደር ትርክት ማቆሸሹ፣ ራስን ከሰው በላይ ነኝ የሚያሰኝ ሐሰተኛ ትርክት ከ50 ዓመታት በላይ በትውልድ አእምሮ በመዝራት ከተፈጥሮው እና ከእውነት ውጭ የሚንጠራራ ከንቱ ስነልቦና በትግራይ ወጣት መካከል መፍጠሩ፤ ከሁሉ በላይ የመነግሥተ ሰማይመግቢያ መክፈቻ ቁል የሆነውን ክህነት በማርክስና በወሮበሎች ሲኖዶስ ፈጠርኩ ብሎ ሕዝቡን በንፍስም እንዲጎዳ ማድረጉ --- ሁሉ ግልጽ ሆኖ እያለ ---- ዛሬም ሕወሃትን እና ተመሳሳይነተ ያላቸው የነገድ ነጻ አውጭዎች ነን ባይ ድርጅቶችን አባልና ደጋፊ የሚሆን ሰው ትግራይ ውስጥ መገኘቱ ---- ሕዝቡ እንደ ሕዝብ ቁጭ በሎ ራሱን የሚመረምርበት ዘመን ላይ ይገኛል።
----- ሕዝቡ በአንድ ድምጽ በክልል መወሰንን አውግዞ ፦
----- እያለ በግልጽ ንስሐ ግብቶ የራሱንም መከራ፣ በሌላው ወገኑ ላይ የተነዛውንም መቅሰፍት በአጭር ግዜ ላማስቆም እድል ይፈጥራል።
================
ከላይ ያነሳሁትን ከባድ ውሳኔ ለመውሰን እስቲ 55 ዓመታት ወደኋላ ተመልሰን የፖለቲካ ሽፍጥ ጥንሥሥ እናስታውስ፦-
ከ6ኦዎቹ አብዮት ጀምሮ መላው የኦትዮጵያ ልሂቅና ተማሪ እብደት በዙ ውጥንቅጥፈጥሯል። ውጥንቅጡን ከማርክሲዝም ወደ ጎሣ ነጻ አውጭና የኤርትራ ግንጠላ የቀየረውና በሻዕብአ ባርነት የመጀምሪያውን አገር አፍራሽ መርዝ የተከልው ሕውሃት ሲሆን፣
ታናሽ ወንድሙ የጀርመን ሥሪት ያለው ኦነግ ነው። ሌሎቹ እነዚህን ሁለቱን እንደ ምሳሌ በመውሰድ ወይንም እንደተላላኪ የተፈጠሩ ናቸው።
በዚህ ሂደት በደርግ ግዜ የሕወሃትን መሠሪ አካሄድ የተረዱ ጥቂት የትግራይ ወጣቶች "የዘንዶ ጦር" በሚል ስያሜና በደርግ ደጋፊነት ትግል ጀመረው ቢሆንም መሠሪው እና በውጭ የኢትዮጵያ ጠላቶች፣ በሻዕብያና በግብጽ መደገፍ አጥፏቸው። ከዚያን ወዲህ የትግራይ ሕዝብ የማሰብ፣ የመወስን፣ ራሱን የመሆን እድሉንና አቅሙን ሁሉ ተነጥቆ የሕወሃት የአእምሮ፣ የኢኮኖሚ፣ የመኖር ዋስትና ባሪያ ሆነ። ይህ ሂድት ቅሰ በቀስ ራሱን የቻል "ትግራዋይነት" የሚባል አዲስ ሃይማኖት መሆን ጀመረ።
እልልታና ዋይታ፦
የ55 ዓመታት የትግራይ ሕዝብ የእልልታና የለቅሶ፣ የስቃይና የደስታ ተቃርኖአዊ ሕይወት---ይመርመር!!
ግንቦት 20 ቀን 1983 ሕወሃት ግብስብስ የአማራና የኦሮሞ ፈረሶቹን አየጋለበ ከሻዕብያ ጋር ተጣምሮ፣ በአሜሪካና አውሮፓ ሴረኛ አስተዳደሮች ተባርኮ አዲስ አበባ ከገባበት እለት ጀምሮ ቀበሌው፣ ካንፑ ሁሉ በትግርኛ ዘፈን፣ ከበሮ፣ እልልታ የተዋጠ ነበር። ከዚያ ቀን ጀምሮ ዒላማ የተደረገ የሃይማኖትና የቋንቋ ወገን ከአሶሳ፣ በደኖ፣ አርባ ጉጉ፣ መላው ሐረርጌና ባሌ ሙሉ ዋይታ፣ ለቅሶ፣ ሞትና ስደት ጀምሮ ዛሬም በአጋሩ በኦነግ ልጅ በብልጽግና ቀጥሏል።
የዚህን የ8 ዓመቱን ለቅሶ ልዩ የሚያደርገው የትግራይ ከበሮ መቺዎች እኩል 30 ዓመታት ካስለቀሱት ማኅበረሰብ ጋር ደረት መድቃታቸው ነው።
38ቱንም ዓመት በዘፈንና በዘረፋ በብቸኝነት የቀጠሉት ኦነጋውያን የዘረፋ፣ የማፈናቀልና የመግደል ፕሮጄክቱ ተጠቃሚ "ኦሮሞ ነኝ" በሚል ፖለቲካዊ የዘር ማንነት የገንቡ ቡድኖች ናቸው። የ የቀድሞ የሕወሃት አጋር የዛሬዎቹ ጠላቶች ኦነጋውያን ብልጽግናዎች ሕወሃት በጠላትነት ከሶማሌ እስክ ወልቃይትና ራያ ሲያፈናቅልና ሲገድል፣ ሲያደኽይና ሲያዋርደው የኖረው የማርኛ ተናጋሪው ኦርቶዶክሳዊ ወገኑ ጋር ተደምሮ ማልቅሰ ላይ ይገኛል።
---- ማልቀስም፣ ማስለቀስም፣ መዋረድም ማዋርደም፣ መፈናቀልም ሆን ማፈናቀልም እንዲቀር ከተፈለገ የትግራይ ሕዝብ ከሕወሃት፣ የኦሮሞ ሕዝብ ከኦነጋዊ/ብልጽግና አስተሳሰብና ትርክት፣ ከስግብግብነት፣ አገር አፍርሶ የራስን መንደር አገር የማድርገ እውርነት፣ ከሐሰተኛ ተርክት፣ ራስን ከሌላው ልይቶ የመሳል ዘረኝነት፣ በባእዳን ፍላጎትና አጀንዳ በባንዳነት ከማገልገል፣ " ሌሎች" በሚል የቋንቂአ እና የእምነት ቤተሰቦቹን በጥላትነት ከምፈረጅ፣ ከኢሰባአዊና ኢፍትሓዊነት ከተጸናወተው ፖለቲካ ስነልቦና ---- መላቀቅ ግዴታ ነው። --- መላቀቅ ብቻ ሳይሆን በቁርጠኝነት መዋጋት ሰላም፣ እርፈትታ መግባባትን ያመጣል። ይህን መርዝ ታቅፎ "አገራዊ ምክክር፣ የድንበር ኮሚሽን፣ ምርጫ፣ ፕሪቶሪያ ስምምነት፣ መንበረ ሰላማ፣ ወዘተ" ዋጋ ቢስ ቅዠት ነው።
የኦሮሞ ሕዝብ የለቅሶ ተራ ጠብቆ እንደ ትግራይ እናቶች ከማልቀሱ አስቀድሞ የጥፋት መሪ የሆነውን ኦነጋዊ ልጆቹን ወዲያ ሂዱልኝ ብሎ ለሰብአዊነት፣ ለኦውነት፣ ለፍትሕ፣ አአንድ ሉዓላዊት አገር፣ ለጋራ አዎንታዊ ታሪክ መጠናከር ቢሠራ ይበጀዋል። "ኦሮሙማ" የሚባል ኦነግ በጅርመን ናዚ ፖለቲካ አምሳል የፈጥረለትን መርዛማ ትርክት፣ ስነልቦናና አቋም ማስተካከል የጠበቅባተላ። ከበደኖ እስክ ዛሬው የአርሲ ጭፍጨፋ ፊቱ ሲካሄድ በዝምታ መስማማቱን በግልጽ ይቅርታ ብሎ መቃወም ይጠበቅበታል።
በሁለቱም ዘመናት አንዴም እልል ያላሉት የአማራና ሌሎች ክፍለ ሕዝቦችም ለህልውና ሲታገሉ ከሐወሃትና ከኦነግ የጥፋት ስልትና ወዳጅነት መራቁን ያስቡበት። የአማራ ሕዝብ የምኖር ተፈጥሯዊ ግፊት አስገድዶት ትጥቅ ቢያነሳ የሚሰዉለትን ልጆቹን እንምራህ በለው አትልለው ለባእዳን አጀንዳ መግልገያ፣ የሕወሃትና የኦነግ አምሳል በሆነ ሤራና ቁማር የተቀደሰውን ተጋድሎ እንዳያበላሹት በቅርበት እየተከታተሉ እውነቱን መንገርም ይገባል።
የትግራይ ሕዝብ ከሰቆቃ የሚላቀቀው በስማቸው የጥፋት መክፈቻ አዝሎ ከሚዞረው ሕወሃት ነጻ ለመውጣት ቆርጦ ሲነሳ ብቻ ነው። ሌላ መላ የለም።
"ለ55 ዓመታት ታሪካዊት የነጻነት አርማ አርንጓዴ ቢጫ ባንዲራቸውን ጥለው፣ ጀግኖቻችንን አራክሰውና ወራሪው ጣሊያን የፈለፈላቸውን የባንዳ ልጆች ራስን የማርከስ ባህል ወርሰው ፣ የኢትዮጵያን ታሪክና ኦርቶዶክሳዊ ማንነታቸውን አቃልለው "ትግራዋይነት" የሚባል ፖለቲካ ሠራሽ ፋሽስታዊ የእምነት ጣዖት ተከትለው ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የመከራ በር ከፋች የሆኑት ሕወሃቶች ናቸው" ብሎ ማመን የመጀመሪያ የምፍትሔ እርመጃ ነው። የአጥፊን ትርክት እንደ ሃይማኖት እየዘምሩ፣ የእርሱን ባእድ አርማ እያውለበልቡ ማለቃቀስ ሌላ ከሕወሃት የከፋ የጠፋት አስተባባሪ ይወልዳል እንጂ ትክክለኛ ፈውስና ሰላም አያመጣምና የትግራይ ሕዝብ በነጻነት ለማሰብ --- መጀመሪያ ከዘር የፖለቲካ ጣዖት ራሱን ያጽዳ። ሰው ከሰው አይበልጥም፣ አያንስም፤ አገሪ ኢትዮጵያ ድፍን እንጂ ኦነግና ወያኔ ተቃርጠው የሰጡኝ አይደለም፣ ታሪኬ የኢትዮጵያ እንጂ የባንዳ ለጆች ፈብረከው ያሸክሙኝ የአንድ አካባባኢ ውስን ትርክት አይደለም--- እያለ መቆጣትና በተግባር ማሳየት የጠበቅበታል።
ሕወሃቶች በሙሉ የተገኙት ከትግራይ ሕዝብ ነው። ይህ ማለት የትግራይ ሕዝብ ሁሉ ሕወሃት ነው ማለት ግን አይደለም። ይሁንና ከሕዝቡ መካክለ ፊደል የቆጠርውና ልጅነት ያለው በአብዛኛው ወዶ ገብ የሕወሃት የአእምሮ ባሪያ ሆኗል ማለት ይቻላል። በስደት አግር እንጇ ሳይቀር ጥላቻ የምንዛት፣ ኢትዮጵያውያንን በክልልና በጎጥ የመክፋፈክል፣ የኦርቶዶክስን መቅደሶች የመካፈልና ክርስቶስን ለጎሣ የማሰልፍ ነውርኛ አባዜ ሁሉ የሚታየው በሕወሃት እና ኦነግ የአእምሮ ፍጡራን ነው። ይህ በሽታ መንኮሳትንና ካህናትን ሳይቀር የበከለ፣ በመጭርሻም የጎሣ ሲኖዶስ ተብዬ ክህነት ይለሽ የወሮበላ ቡድን በትግራይ የተከል፣ በኦሮምያ የሳዊሮስና የቡድኑ አይነት አሳፋሪ ሰዎችን የፈጠረ ደዌ ነው።
ይህ የትግራይ ሕዝብንና የሌላው ማኅበረሰብ የመከራ በር መክፈቻ የሆነውን ሕወሃትን ስናስብ እንደ ወላጅና ተባባሪ፣ እንደተላላኪና ላኪ የምናወሳቸው ሻዕቢያአን ጭምሮ ኦነግና ሕወሃት በጸረ ኢትዮጵያ፣ በጸረ ኦርቶዶክስነት የቀረጸቻቸውና ያሳደገቻቸው የጎሣ ነጻ አውጭዎች፣ ኮሚቴዎች፣ ሽንጎዎች፣ ጽንፈኛ የዉሃብያ ዑስታዞችና የአልሽባብ ኔተዎርክ አባላት፣ ፈጥረው የሚደግፏቸው የውጭ አገራት ዲፕሎማቶችና ቡድኖችን ማሰብ ግድ ይለናል።
ጣሊያን ባንዳነትን ያተመባቸውን የታላቋ ትግራይ ሪፐብሊክ መፈጠርና የኢትዮጵያ እንደ አገር መፈርስን ግብ ያድረጉ ንቅናቄዎች ብዙ ቢሆኑም በኃላፊነት የሚጠይቁት ሕወሃትና ኦንገ ናቸው። ሁለቱ ወንጀላቸውን መንግሥታዊ ሕግ ያደረጉና ል38 ዓመታት ደም ያፈሰሱ፣ ሕዝብ ያፈናቀሉ፣ ዛሬም እረፍት ያላደረጉ ናቸው።
የእነዚህ ሁለቱ እና አባታቸው ሻዕቢአ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና ማማሰያና መቁያ ሆነው በጠላት ጣሊያን አስተሳሰብና ትርክት ላይ የተፈጠርውን እና በባንዳ ልጆች እንደ ሕይወት ግብ የሚታየውን በነጻነት ስም አገር የማጥፋት ሤራ ያለእረፍት የሚያሰፈጽሙት ሕወሃት፣ ወለጋ ግንቢ የተፈለፈልውና ዘር የማጥፋት መንፈስ ያረፈበት የሚሽነሪዎችና የተርፈ-ናዚ ሰባኪዎች ውጤት የሆነው ኦነግ -- የዓላማ ስለሚያስተባብራቸው እርስብርስ እየተዋጉ እንኳ ሁለቱም አገር አፍሮስ የጎሣ አገር መፈጠር ህላምቸው ላይ ይተጋገዛሉ።
ለዚህ እኵይግባቸው የትግራይን ሕዝብ ከመንፈሳዊ ምሪቱ አስወጥቶ የጎሣ ጣዖት አምላኪ ማደርገ፣ ኦሮሞን ከፈሪሃ እግዚአብሔር ለይቶ የጽንፈኛ ዉሃብያና ዘመን ያለፈበትን አሓዛባዊ የባዕድ አምልኮ አድሶኦ ልጥፋት መጠቀም ላይ በግልጽ ሲተባበሩ ይታያሉ። በሌላ በኩል ሁሉንም ዬትዮጵያ ማኅበረሰቦች ከቋንቋና አሰፋፈር ባሻገር አጋምዷል የሚሉትን የአማራ ሕዝብ እና ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን የበሔሮች ሁሉ ጠላት አድርገው በመፈርጀ እሰከ ዘር ማጥፋት የሚደርስ ሁለገብ ጥቃት የሚያካሄዱት በጋራና በተናጥል ነው። ይህ ውንጀላቸው እንዳይጋለጥ የፍትሕ ሥርዓቱን፣ ሚዲያውን፣ ቤተ እምነቱን ሁሉ በንቅዘትና በዘር ቡድን ተቆጣጥረው 38 ዓመት ሙሉ ደም ማፍሰስ ችለዋል። አንድም ሰው በዚህ ወንጀል አልተጠየቀም።
በዚህ የጥፋት ፖለቲካ ውስጥ ገዳይና ወራሪ ወታደር፣ የዲፕሎማሲ ተለእኮ ተቀባይ፣ የሰው ልጆችን በትምህርትና በአካልም የማምከን ሥራ ላይ ባለሙያና መሪ ሆኖ መሰለፍ፣ ታሪክን መሸቀጥና አገርን ማበሻቀጥ ወ.ዘ.ት. የሕወሃት መሠራቾችና ከ50 የማይበልጡ መሪዎቹ ብቻ የፈጸሙት ሳይሆን ከአገር ውስጥ የተሰራጭው "ትግራዋይ ነኝ" የሚል አዲስ ሕወሃታዊ ማንነት የለበሰው ሰው ሁሉ በመተባበር ነው። በኦሮሞ በኩልም እንዲሁ በኦነግ አምላክነትና ጣዖትነት የተከተለው ትውልድ የወንጀሉ ተካፋይ ሆኗል።
እነዚህ በጥፋት የሚተባበሩ ወገኖቻችን የተወለዱት ከእንዚህ አንድ ግዜ ትግራይ ትስዕርርር" ብለው የሚጨበጭቡ፣ ሌላ ገዜ ለጆቻቸው ሌላ እና ጠላት በለው የፈረጁትን ወገን በመውረር እና ራሱን ከወረራ በሚከላከልው ወገን ጥይት ሲውደቁ ደረት የሚደቁት እነዚሁ እናቶች ናቸው። እዚህ ላይ ነው እንግዲ ለክፋት፣ ሊሰብአዊነት፣ ለኢፍትሓዊነት፣ ለነጥቃ፣ ሌሎችን ለማዋረድ በምቻልል እልል ማለት ወጤቱ ለቅሶና ዋይታ፣ ማፈርና መክራን ደራርቦ እንድሚያስከትል ለመማርና ለመታረም የጠቅማል።
የትግራይ ሕዝብ ለአጥፊ ልጆቹ ከማጨብጨብና ወጤቱ ሲበላሽ ከማልቀስ ነጻ የሚወጣው ከሕወሃት አስተሳሰብ፣ ከክፋት አደረጃጀት፣ ስምሪትና ተለኮ መፈጸም ፈጽሞ ነጻ ሲወጣ ነው። ነጻነቱም የሚረጋገጠው፦
በሕወሃት እና በምሳዮቹ የማንነት ፖለቲካ ዘረኛ አስተሳስብ እየተመሩ ከለቅሶ፣ ከሞት፣ ከስደት መላቀቅ አይቻለም።
ሁላችንም ቋንቋ፣ ቦታ፣ ትርክት፣ የፖለቲካ መሪዎች እንደ እቃ እዳይጫወቱብን ራሳቸንን ለመጠብቀ ልዩ ትምህርትና ሊቅነት አያስፈልገንም። ማመን፣ መቀበልና ለዚያም መቆም ያለብን ጉዳይ፦
(1) ክብረ-ሰብእ
(2) እውነት
(3) ፍትሕ
(4) የጋራ አገርና ሉዓላዊነቷ
(5) ፈሪሃ እግዚአብሔር
(6) በካድሬ ያልተሸቀጥ ረዥሙ ታሪካችንን መከላከል --- ላይ ብቻ ካተኮርን --- ከዘር ፖለቲካ ነጻ ከወጣን ---- መከራችን ያበቃል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ