ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

የምመኛት ኢትዮጵያና ሕዝቧ

Let's dialogue about the Orthodox ምን አይነት ኢትዮጵያ ትመኛለህ ? እኔ፦ 1.        የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ የምከበርባት አገርና ይህን የሚያስከብር መንግሥት የሚመራት አገር፤   2.       ሃይማኖት፥ ባህል፥ ጾታ፥ ቋንቋ፥ ያለፈ ታሪክ፥ አሠፋፈርና የኑሮ ዘይቤ ሁሉ የሰውነትና የዜግነት ማንነቴ ላይ ምንም ተጽእኖ የማያሳድሩብተ ሥርዓተ መንግሥትና ሥርዓተ ማኅበር የሚገለጽባት አገር፤ 3.       የአገር አስተዳደር አከላለል ከቋንቋና ከፖለቲካ ነጻ ሆነው በልማት ቅልጥፍና፥ በንዑስ ማንነት መዋሃድ መሳለጥ ሚዛን ብቻ የሆነባት አገር፤ 4.       ፖለቲካ መንግሥት ከሃይማኖት፥ ከጎሣ ቡድን፥ ከቋንቋ፥ ከፖለቲካ ሠራሽ ማንነትና አግላይ ትርክቶች ነጻ ሆኖ ለሰው ክብር፥ ለፍትሕና ለሕዝብ ሰላምና መዋሀድ የሚሠራ የሆነባት አገር፤ 5.       ወታደር ትጥቅ ይዞ አገር ውስጥ የማይታይባት፥ ድንበር ብቻ በወታደር የሚጠበቅባት አገር፤ 6.       ፖሊስ ሀብታምና መንግሥት ዱላ ሆኖ ከማገልገል ወጥቶ  ሕዝብ የሚጠብቅባት  አገር፤ 7.       ፍትሕ በማሥበራዊ፥ በምንግሥታዊ፥ በሃይማኖታዊና ባህላዊ መዋቅራት ውስጥ ሁሉ እውቅና አግኝቶ የሚተበርበት አገር፤ 8.       አገርና ሕዝብ ለምግብ፥ ለመድኃኒት፥ አገርን ከውጭ ወረራ ለመከላከል በሚያስችላቸው ግብአቶችና እውቀቶች...

ዐመሓራነት ሰብአዊነትና ፍትሕ፥ እኩልነትና እውነት ነው!! "ብሔርተኝነት" ከሆነ ጠላቶቹን ማሸነፍ ሳይሆን ወርሷቸው ይጠፋል!

የዐመሓራነት   የህወሃትና የኦነግ አይነት “ ብሔርተኝነት ” እይደለም ! ዐመሓራነት ሰብአዊነትና ፍትሕ፥ እኩልነትና እውነት ነው !! ተጻፈ ከፋንታሁን ዋቄ መስከረም ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓለም ዐቀፍ ዝና የነበረው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት በወራዳ ድንክ አእምሮዎች፥ አገርና ሕዝብን ከሆድና ከሕጻን ቅዠታቸው አሳንሰው በገዛ ወገኑ ላይ አዘመቱት። እንደዚህ አድርገው አዋረዱት።  ላም እሣት ወደለች አንዳትልሰው እሣት ሆነባት፥ እንዳት ተወዉ ልጅ ሆነባት እንዲሉ  የዐመሓራ ሕዝብ ራሱን ከታወጀበት የ50 ዓመታት የዘር ማጥፋት ሁለገብ ጥቃት በኋላ  በሕወሃትና ኦነግ ሕገ አራዊት መሠረት የተወለደው ብልጽግና በይፋ በተመሠረተው የኦነግ-ኦሮሙማ የብልጽግና አመራር ቀጥተኛ ፍጅት ተካሄደበት፤ ማፈናቀል፥ እያደኑ መግደል፥ ማደኸየት፥ በበሽታ ማስጠቃት፥ ከትምህርትና ከፖለቲካ ተሳትፎ ማራቅ ወዘተ እየተፈጸመበት ታገሰ፤ በመጨረሻም ለመታገስ የማይመች በጦእ ሠራዊት ቀጥታ ፍጅት ተከፈተበት።  ፍጅቱን የሚፈጽመው በአብይ አህመድ የጠቅላይ ጦር አዛዥነት የሚመራው ይከበር የነበረው የአገር መከላከያ ጦር ሠራዊት ነው።  እናም ለዐመሓራ የቀረበለት አማራጭ ራሱን መከላከል፥ እያለቀሰ በራሱነ ወገን ላይ መተኮስና እያዘነ መማረክ ነው።   እነርሱ የቆሎ ተማሪ ከጎጆ እየጎተቱ ሲረሽኑ፥ መነኩሴና ሕጻን ሲደፍሩ፥ ሰብል ሶያቃጥሉና ከተማ ሲያፈርሱ ሰውነቱን ዛሬም አስከብሮ የኖረው በዓለ ሕሊና ዐመሓራ (ባንዳ፥ ዘረኛ፥ ስስታምና ሸቃጭ አማራን አይመለከትም)  ግን የማረከውን በጠላትነት ያሰለፉበትን "ጠላት" ወገኑን እየደባበሰ እና እያጽናና፥ ጫማ ሳያስወልቀው፥ ግፍ ሳይፈጽምበት   ወንደሜ "ጥላችን ከሥርዓት ...

የፋኖን ትግል በሚመለከት ለአማራ ምሁራን የተሰጠ የግል ምክረ ሀሳብ

L እንደግዲህ ጎጠኞች ምን አገባህ እንዳትሉኝ እንጂ እኔ ለአማራ ምሁራን  ምክረ-ሀሳብ አለኝ፦ የአማራ ምሁራን ሚና  በአማራ በህልውና ትግል ውስጥ ማንኛዉም የህልውና ትግል ውጤታማነቱን ማረጋገጥ የሚችለው ዘርፈ ብዙ የህልውና መሠረቶችን ታሳቢ ያደረገ ጉዳዮች ተንትኖና በሁሉም አቅጣጣ ተመጋጋቢ ድሎችን ማስመዝገብ ሲችል ነው። የአማራ የህለውና ተጋድሎም እንደዚሁ አሁን በፋኖ ከሚካሄደው የጥትጥቅ  እኩልና ጎን ለጎን፥ ብሎም ከትጥቅ ትግሉ መጠናቀቅ መኃላ በአጭር፥ በመካከለኛ ግዜ (ከአሁን እስከሚቀጥሉት ፭ ዓመታት፥ ከ፮-፲፭ ዐመታት፥ ከ፲፮ እስከ ቢያን ፴ እና ከዚያ በላይ ዓመታት የሚመዘገቡ ድሎች፥ በየድል ምዕራፉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአጠቃላይ ምን የተሻለ ሕይወትና የትውልድ ሰላማዊና ሁለገብ የሰብአዊ ክብር ሁኔታ እንዲሚያረጋግጥ የሚያመለክት የድል ጉዞ ፍኖተ-ካርታን ከወዲፉ በጭናጭልም ቢሆን ማሳየት አለበት/ ይህ ተግባር በአብዛኛው በሜዳ ላይ ውድ ሕይወቱን አስይዞ ለመጀመሪያው ድል፥ ማለትም የአመራን ሕዝብ ከጥፋት የመታደግ ተጋድሎ ላይ ከተሰለፈው ተዋጎ ኃይል የሚጠበቅ አይደለም። ይህ ፍኖተ-ካርታ፥ ፍኖቱ ላይ ለመሄድ የሚያስፈልገው መርህ፥ አቅምና አደረጃጀት፤ አደረጃጀቱ የሚመራበት ፖለቲካዊ፥ አስተዳደራዊና ማኅበራዊ አመራር ምን መሆን እንደሚገባው፥ በወዳጅነትና በጠላትነት የተሰለፉ አካላት በፍኖቱ ላይ በሚደረግ ጉዞ ውስጥ የሚኖራቸው ሚና እንዴት መስተናገድ እንደሚገባው፥ የትጥቅ ትገሉ መጠናቀቂያ መሥፈርቶችና ቀጣይ ተጋድሎዎች አይነትና አመራር ወዘተ ሁሉ በምሁራን ሊታሰብባቸውና ግልጽነት እያገኑ መሄድ የሚገባቸው ናቸው።  በአመራ ሕዝብ የህልውና ትግልም ይሁን የትግሉው ውጤቶች ዘለቄታዊ ዋስትና ለማስገኝ በሚደረጉ ተያያዥና ተከታታይ ከትጥቅ ው...

በአማራ ህዝብ ላይ የሚነሱ የተፋለሱ የጭቆና ትርክቶችን ስለመሞገት1 (unknown author) ክፍል 3

  የአንዳንዱ ሰው ምክንያት ደግሞ የማንነት ስነልቦና ቀውስን ለማስቀረት ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ በአማሮች ላይ የሚደርሰው የግድያ አይነት እጅግ የሚዘገንን ስለሆነ ራሱን ‘ጀግና ነኝ’ የሚል ሰው ወይም ‘የኔ ብሄር አረመኔ አይደለም’ የሚል ሰው አገዳደሉ የውርደት ስነልቦናን የሚጭንበት መስሎ ይሰማዋል። ይህ ጥቃት እኔ ላይ ደረሰብኝ ወይም የእኔ ብሄር አደረሰው ብሎ ከሚያስብ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ መካዱ ወይም ማድበስበሻውን መቀበሉ አቋራጭ አማራጭ ይሆንለታል። ታዲያ እየቆየ ሲሄድ ይህ እሳቤ የሰው ህይወትን ዋጋ ከብሄር ማንነት በታች አሳንሶ የሚያስቀር ሊሆን ይችላል።     አንዳንዶች “አማራ እንዲህ ሆነ የማንለው ብሄርተኝነትን ላለማስፋፋት ነው” ይላሉ። ይህ ከላይ እንዳልሁት ህግንና ፖለቲካን ከማደበላለቅ የሚነሳ ስህተት ነው። እንደውም የአማራን ሰቆቃ ማደፋፈን የብሄር ፖለቲካን የበለጠ አስፈላጊና ብቸኛ አማራጭ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ለምሳሌ ሰላማዊው የኦሮሞ ህዝብ በአማራ ወገኑ ላይ የሚደርስበትን ጥቃት ተገንዝቦ ድርጊቱን ለማስቆም እንዳይነሳ ያደርገዋል። ይልቁንም፣ ድርጊቱ በጽንፈኞች ብቻ ትርጉም እንዲሰጠው ስለሚያደርግ በሁሉም ዘንድ አደገኛ አማራጮች ተገቢ እየመሰሉ መታየታቸው ይቀጥላል።   አንዳንዶች አማራ እንዲህ ሆነ የማንለው ጉዳዩ እንዲረግብ ለትዕግስት ተብሎ ነው ይላሉ። እኔም ግጭት እንዳይባባስ፣ ዕልቂት እንዳይከሰት የሚደረግን ጥንቃቄ እደግፋለሁ። ግን ሰላማዊና ጠንካራ ጥረት ከተደረገ እኮ የኦሮሞ ህዝብም ሆነ የቤንሻንጉል ወዘተ ውስጥ በድርጊቱ የሚያዝኑና ክፋቱን ለማስቆም የሚፈልጉ ብዙ ሰወች አሉ። እነዚህ ሰወች የሚያሰባስባቸው መድረክና የጋራ አጀንዳ ይፈልጋሉ። በህልውና መብት ላይ የተመሰረተ ንቅናቄ ይህን እድል ሊፈጥር ይችላ...