ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ከኦገስት, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ
 7ቱ ጥያቄዎችና ማብራሪያዎቻቸው  ጥያቄ 1፦ በሕገ-መንግሥት፣ በፖለቲካ ማኒፌስቶ፣ በመደበኛ ትምህርት፣ በሚዲያና መሰል መንገዶች ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮንና ኦርቶዶክሳዊያንን ለጥቃት የሚጋልጡ መልዕክቶች በአስቸኳይ በሕግ እንዲታገዱ ። የተዛባ ታሪካዊ ግኑኝነት የሚል ቃል የተጠቀሙት ሕገ-ምንግሥቱን ያዘጋጁ የብሔር ፖለቲከኞች ናቸው። የብሔር ፖለቲከኞች የተዛባ የሚሉት በሕገ መንግሥት ያጸኑት ታሪክ አላቸው፤ ኮሚኒስቶች ለሺ ዘመናት እሥራት ውስጥ ነበረች እንድተፈታ የቀደመውን ማጥፋት አለብን ይላሉ፤ በዚህ መሠረት ትምህርቱን፣ኪነቱን፣ ሚዲያውን፣ መዋቅሩን ተቆጣጠሩት፣ “ተዛባ” የባለው “ታሪክ” ከታሪካዊት ኦርቶዶክስ ክርስትና ክርስቲያን ማኅበረሰብ፣ ቅርሥ፣ ሀብት፣ ታሪካዊ ጀግኖች፣ መጽሐፍት፣ አስተመህሮ ጋር ተጣምሮ የማስወገድ ዒላማ ተደረገ፤ ኦርቶዶክሳዊነት ሀብት ለማደለብ፣ ለዲሞክራሲ የአስተዳደር ሥርዓት፣ ለዘመናዊ አኗኗር፣ ለሥራ ስነ-ምግባር እንቅፋት የሆነ፣   የድኽነት ምክኒያት ናት፤ በቁስ የደኸየ በሰማይም ተስፋ የለውም የሚል አስተምህሮ የሚያራምዱ ብዙዎችን አሳስተው ኦርቶዶክስ-ጠል ለማድረግ ሠሩ፤ ከኮምኒስት የመደብ፣ የብሔረሰብ እና የተጨቋኝ-ጨቋኝ የፖለቲካ ትግል ፅንሰ ሀሳብ ጀምሮ እሰክ ብልጽግ ፓርቲ እስተሳብ ድረስ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊነትን ዒላማ አደረጉ፤ የአሁኑ ዘመን ፖለቲካም ኦርቶዶክሳዊና አገር በቀል እሴቶችን በጀርመኑ ሉተርና በማክስ ዌበር ትምህርት መተካት መበልጸግን እንደሚያስገኝ ይናገራሉ።   ከዚያ ለውጥ ሁሉ ነባሩን ማጥፋት ወደሚል ያዘነብላሉ በውስጥና በውጭ ይህን ዝንባሌ ተከትለው ነባር ኦረቶዶክሳዊነት ላይ የተመሠረቱ ኢትዮጵያዊ እሴቶችንና ክርስቲያኖችን በማጥፋት የሚሳተፉ   ሌሎች እምነቶችና...