ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ከ2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ
 7ቱ ጥያቄዎችና ማብራሪያዎቻቸው  ጥያቄ 1፦ በሕገ-መንግሥት፣ በፖለቲካ ማኒፌስቶ፣ በመደበኛ ትምህርት፣ በሚዲያና መሰል መንገዶች ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮንና ኦርቶዶክሳዊያንን ለጥቃት የሚጋልጡ መልዕክቶች በአስቸኳይ በሕግ እንዲታገዱ ። የተዛባ ታሪካዊ ግኑኝነት የሚል ቃል የተጠቀሙት ሕገ-ምንግሥቱን ያዘጋጁ የብሔር ፖለቲከኞች ናቸው። የብሔር ፖለቲከኞች የተዛባ የሚሉት በሕገ መንግሥት ያጸኑት ታሪክ አላቸው፤ ኮሚኒስቶች ለሺ ዘመናት እሥራት ውስጥ ነበረች እንድተፈታ የቀደመውን ማጥፋት አለብን ይላሉ፤ በዚህ መሠረት ትምህርቱን፣ኪነቱን፣ ሚዲያውን፣ መዋቅሩን ተቆጣጠሩት፣ “ተዛባ” የባለው “ታሪክ” ከታሪካዊት ኦርቶዶክስ ክርስትና ክርስቲያን ማኅበረሰብ፣ ቅርሥ፣ ሀብት፣ ታሪካዊ ጀግኖች፣ መጽሐፍት፣ አስተመህሮ ጋር ተጣምሮ የማስወገድ ዒላማ ተደረገ፤ ኦርቶዶክሳዊነት ሀብት ለማደለብ፣ ለዲሞክራሲ የአስተዳደር ሥርዓት፣ ለዘመናዊ አኗኗር፣ ለሥራ ስነ-ምግባር እንቅፋት የሆነ፣   የድኽነት ምክኒያት ናት፤ በቁስ የደኸየ በሰማይም ተስፋ የለውም የሚል አስተምህሮ የሚያራምዱ ብዙዎችን አሳስተው ኦርቶዶክስ-ጠል ለማድረግ ሠሩ፤ ከኮምኒስት የመደብ፣ የብሔረሰብ እና የተጨቋኝ-ጨቋኝ የፖለቲካ ትግል ፅንሰ ሀሳብ ጀምሮ እሰክ ብልጽግ ፓርቲ እስተሳብ ድረስ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊነትን ዒላማ አደረጉ፤ የአሁኑ ዘመን ፖለቲካም ኦርቶዶክሳዊና አገር በቀል እሴቶችን በጀርመኑ ሉተርና በማክስ ዌበር ትምህርት መተካት መበልጸግን እንደሚያስገኝ ይናገራሉ።   ከዚያ ለውጥ ሁሉ ነባሩን ማጥፋት ወደሚል ያዘነብላሉ በውስጥና በውጭ ይህን ዝንባሌ ተከትለው ነባር ኦረቶዶክሳዊነት ላይ የተመሠረቱ ኢትዮጵያዊ እሴቶችንና ክርስቲያኖችን በማጥፋት የሚሳተፉ   ሌሎች እምነቶችና...

የህልውና ትግል ሃይማኖትን አይመለከትም ለምትሉ ጥያቄ እና ሤራችሁን የማጋልጥበት መለእክት አለኝ

የህልውና ትግል ሃይማኖትን አይመለከትም ለምትሉ ጥያቄ  እና ሤራችሁን የማጋልጥበት መለእክት አለኝ፦ 👉 የህልውና ትግላችን ሌሎች ፍላጎቶችን አያስተናግድም  ማለት ምን ማለት ነው? 👉 የሃይማኖት ነገር አይነሳ ማለት ምን ማለት ነው? 👉 ህልውናን መታደግ የማኅበረሰቡን ሥጋዊ አካል ብቻ ነው?  👉 ህልውና ሃይማኖት፣ ታሪክ፣ ርስት፣ ቅርሥ፣ ትውልዳዊ ተስፋ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር፣ ዓለም አቀፋዊ ትሥሥር፣ ቀጠናዊ ሰላም አይጨምርም? 👉የህልውና ተጋድሎ በምእራባውያን ፍልስፍናና ይሁንታ ብቻ የሚትረጎም ነው? ከእኔ ዐሳብ የትሻል የሙስሊሙና ክርስቲያኑ የሃይማኖትና የታሪክ ልሂቃን ይህን ሰውር ሤራ ማክሽፍ የጠበቅባችኋል። ============================================ በአንድን ክፍለ-ሕዝብ ላይ እየተሞከረ ያለው ድምሳሴ  ከተሳካ የሚያጠፋው የማኅበረስቡን፡- 1) አባላት (ሰዎችን) እና የትውልድ ቀጣይነትን 2) ባህሉን 3) ሃይማኖቱን 4) ታሪኩን 5) የስነ-መንግሥትና የእምነት አሻራ የሆኑ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሦቹን 6) ማኅበረ-ሰበእ-ፈለቅ ዕውቀቶቹንና ጥበቦቹን 7) ቋንቋዎቹን 8) ርስቶቹንና ማኅበራዊ ትሥሮቹን ወዘት ሁሉ ነው። የህልውና ተጋድሎ የሚታደገው 8ቱንም ለማዳን ነው።   ዛሬ ላይ  ግን በአማራ የህልውና ጠላቶችን አጥፊ ፍልስፍናዎች  የወረሱ ወይንም ባለማወቅ የጠላት ሤራ ሰለባ የሆኑ አንዳንድ የፋኖ ልሂቃንና መሪ ካልሆንን ሞተን እንገኛለን የሚሉ ሰዎች "የአማራ ህልውና በ1ኛው  ተራ ቁጥር ላይ የተገለጸውን ብቻ የመለክታል---  --- የተቀረው  ግን ያረጀ፣ ያፈጀ፣ የጃጀ ስለሆነ እኛ በምንበይነው ይተካልና  ትግላችን ለሌሎች ፍላጎቶች ዝግ ...

ክርስቶስን ጥሎ የህልውና ትግል ድል ሳይሆን ሞትን መጥራት ነው!!

"መድኀኒታችንን አምላካችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እርሱት" የሚል የህልውና ታጋይ የአማራ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጆችን ሁሉ የዘላለም ሕይወት የሚቃወም የዲያብሎስ ዋና ሠራተኛ ብቻ ነው ‼️ =============== የምንሞትለትን አገር እንደ እንግዳ ሳይሆን እንደ ባለቤት ልንኖርበት ይገባል!!! አባት እናቶቻችን አገር ያስረከቡን የውጭ ጠላት ውክልና ወስደን እንድንጠፋፋና እንድንገፋፋ ሳይሆን በእነርሱ የተቀደሱ እሤቶች በነፃነትና በእኩልነት፣ በአንድነትና በእምነት ኖረን የሁለት ሀገር ባለቤቶች እንድንሆን ነበር። ==============  ኦዶክሳውያን የጥምቀት ልጆች ለሁለንተናዊ  መብቶቻችን እንቁም!!! ጥምቀታችን ከቋንቋና ሥጋ ወገንተኝነት የላቀ ክርስቶስን መሆኑን አንዘንጋ!! ይህ ኢትዮጵያ የሚባለው አገር በአባት እናቶቻችን ሁለንተናዊ መስዋእትነት እና በእግዚአብሔር ቸርነት ያገኘነውን የተጠበቀ ርስታችን እንጂ ዘረኛ ፖለቱከኞች የሚያድሉን ድርጎ፣  ሲሻቸው የሚነሱን ንብረታቸው እንዳልሆነም ታሳቢ እናድርግ!! እንነሳ!! ===≠====================  እኔ እንደዚህ ከታች እንደጻፍኩት አምናለሁ፣ ለማምንበት እታገላለሁ። እናንተስ? ========= በውስጥ መስመር ስለምንሠራው ተግባር ተመካከሩ። ይህ መንግሥት ሲወድቅ የወደቀችዋን አገር በኦርቶዶክሳውያእ እልቂት እንዲደመደም የዘር ነጻ አውጭዎች ነን ባዮች የኢትዮጵያና የነባርነታችን ጠላቶችን አጀንዳ ለማስፈጸም በስሑት የባዕዳን ርእዮትና በሐሰት ትርክት ያሳሳቱትን  የሕወሃት እናንየኦነጋውያን፣ የወሀብያውያን፣ የናዚያዊ ፕሮቴስታንት ጥምረት ያሳሳቱትንና ያስታጠቁትን ነፍሰ ገዳይ ታጣቂ ያሰማራሉ። ተሰልፎ ከመጨፍጨፍ አሁኑኑ መነጋገርና መዘጋጀት፣ ሰብአዉነትናንህሊና ያተለያቸውን ለይቶ ...

በምንሞትለት አገር እንደ እንግዳ ሳይሆን እንደ ባለቤት ልንኖርበት ይገባል

በምንሞትለት አገር እንደ እንግዳ ሳይሆን እንደ ባለቤት ልንኖርበት ይገባል። ደማችሁን ስጡን ነገር ግን መብታችሁን አትጥቀሱ የሚል የሴኩላሪስቶች የሃምሳ ዘመን ሤራ የሚያበቃው ለሁሉም የሚጠቅም እውነትን በፍቅር እና በአንድነት ስነጋገር ብቻ ነው። ፖለቲካዊ ትክክለኝነት (political correctness) በቅዝቃዜ ጀምሮ በኑፋቄ አድጎ በክህደት የሚጠናቀቅ የሰይጣን ማታለያ በመሆኑ ኦርቶዶክሳውያን የሌሎችን ነጻ ፈቃድ ሳንጋፋ በአገራችን የሚገባንን መብት ሁሉ ሳናመነታና በሌሎች አጀንዳዎች ሥር ሳንወሸቅ በፍቅር ሁነን መወያየት መጠየቅና ማስከበር ይኖርብናል። አንድ ሰው አንድ እስከ ሆነ ድረስ ሃይማኖት ከፖለቲካ ሲደባለቅ አደጋ አለው የሚለው ስብከት ሳይንሳዊም፣ አመክንዮአዊም፣ ተግባራዊ ምስክርነት የለውም። እኛ የተሰቃየነው ከፖለቲካ ወጥተን በሴኩላሪዝም ወይንም በማርክሲዝም ስም ኦርቶዶክስ ጠል አካላት ሥልጣኑን ጠቅልለው እንዲይዙት  እና ኦርቶዶክስ ጠል ሥርዓት ሕግ ሲሆን ዝም ማለታችን ነው። ምንም እንኳ በሐሰት ተራኪዎችና የውጭ ጠላቶች ስብከት ቢጠለሽም የእኛ በትክክለኛው መርህ መገኘት እንደሚተረከው ስንኳንስ ሌሎች እምነቶችን ሊጎዳ ቀርቶ ለዛፎችና አራዊቶች የተረፈ ነበር። እጄ ተቆርጦ ነበር ከሚለው እምነት ተጨቁኗል ከሚለው ሐስተኛ  ዛሬ ነፍሰ ጡር ማኅፀን ከፍቶ ፅንስ እየሸለቀቀ ስለሃይማኖታችሁ አትሟገት ሲለን መቀበል "አጥፉን" ብሎ ፈቃድ የመስጠት አስሳስብ ነበር። =============================== ኦርቶዶክሳዊ  መንፈሳዊነት በዓለም ውስጥ በተጎታችነት ብቻ እየኖሩ የሚደበቁበት ሕይወት ሳይሆን   ከግበበ ምድር እስከ ሮም ቤተ መንግሥት  አሕዝባዊነትን ተዋግቶ የመቀደስ ጠቃሚ የንቃት ጉዞ ነው!! =====...

ስለ አማራ የህልውና ትግል ያገባኛልና ጻፍኩ

  የአማራ የህልውና ተጋድሎ ያገባኛል ስላልኩ --- እንዴት እና ለምን እንደሚያገባኝ እነሆ ጻፍኩ፦- አደራ አደራ፦ ያልተጻፈ የምታነቡ፣ ያልተነግረ የምትተነትኑ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌላችሁ፣ እውነት የማያስጨንቃችሁ፣ አማራ ወገናችሁ ሌላ አማራጭ ዐሳብ ባለመስማት እናንተን እንዲያመልካችሁ የምትሹ የህልውና ትግሉ ጠላፊዎች ከዚህ ገጽ ራቁ። ======================= ወደ ጽሑፉ ---- ግልጽ እንነጋገር። የእውነተኛ ፋኖነትና በፋኖነት ሥር የተደበቀ የጎጥ ሽፍትነት ይለያያል። ለትግሉ ውጤታማነት ስለሚጠቅም በማለባበስ በሽታን ታቅፎ መንፏቀቅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከሚናፈቀው በጎሣ ፖልቲካ ከመጣው አጥፊ ማዕበል ታድጎ ከእርፍት ወደብ አያደርስም። ካደረሰም አያዘልቅም። ከዘለቀም ቀጣይ መጠፋፋትን ይተክላል እንጂ በፍትሕ፣ በእውነት፣ በክብረ-ስበ፣ በፍቅርና መተማመን ላይ የተመሠረተ የአንድ ቤተ ሰብእ የሚያኖር ሰላምን ማንበርና ዋስትና መስጠት አያስችልም። አማራን ከአማራነት እሤቶቹ በሚቃረነው በጠላቶቹ ነጽሮተ ዓለም እና የፖለቲካ-ሠራሽ ማንነት ለመተካት አማራን ለህልውና አደጋ ከዳርጉት አካላት ዐስተሳስብ በመዋስና ስልታቸውን በመከተል አማራን ከአጥፊዎቹ ለመታደግ የሚመኝ ቡድን ፈጽሞ ከአማራነትና ከታሪካዊ “ፋኖነት” ጋር እጅግ የተለያየ አስተሳሰብ ነው። ፋኖነት ተውሶ፣ ቁማር፣ ወደ ዶግማነት ያደገ አግላይ ጎጠኝነት፣ ሤራ፣ ወገንን በሐሰት ፕሮፓጋንዳና በገንዘብ ኃይል፣ ሌላውን በመግደል፣ ታሪክና እምነትና በመካድ፣ ከባእዳን ተዋውሎ የሕዝቡን መስዋእትነት የሚከፈልለት ግብ በግለሰቦችና ቡድኖች ፍላጎት ማርኪያ አንጻር ቀርጸው የሚትክሉት ባዕድ ረእዮት አይደለም። ፋኖነት በሰባዊነት፣ ፍትህ፣ እውነት፣ ግልጸኝነት፣ ነባርነት፣ መተማመን፣ ቃል ...