የድንቁርናና ሕሊና-ቢነስት ያነገሣቸው የጎሣ ልሂቃን "የምሥራች" ትርጉም አምባገነን፥ ቁማርተኛና የወሮበሎች መንግሥት የሚመራውን ሕዝብ መከራ "የምሥራች" እያለ ያለማምደዋል። የሕወሃት/ኢሕአዴግና ብልጽግና በዚህ ሞትና መከራን ድልና እድገት አድርገው በማቅረደብ አንድ አይነት ናቸው። ስዩም መስፍንና አሊ አብዶ የሕወሃትና የሻዕብያ የዘረፋ ሀበት ክፍፍል ግጭት በባድሜ እንደ ምክንያት ትርጉም-የለሽ ከ120 ሺህ ሕዝብ በላይ ወገን አስፈጅተው፥ ይግባኝ በሌለው የአልጀርስ ስምምነት "የምሥራች፥ እንኳን ደስ ያላችሁ" ብለው ሕዝቡን አስጨፍረዉታል። የፈረደበትን ዐመሓራና ኦርቶዶክስ ክርስትናን በማጠፋት አጀንዳ ላይ ቢስማሙም ነገር ግን በተለመደው የሀብት፥ የብሔር ግዛት በሰስፋት፥ ዲሞግራፊ በመቀየር፥ አሰስ አገር የመፍጠር እና የበላይነት ለማስፈን ባደረጉት ግጭት ሕወሃትና ብልጽግና በየበኩላቸው ወደ ጦርነት የመሩትን ወገን ድል አግኝተናል፥ የባሰ አደጋ እንዳይመጣ አድርገናል ብለው "የምሥራች" ብለዋል። ብልገግና የአባይ ግድብ ከደ ጋየወረደው የክረምት ጎርፍ ስለ ሞላ የምሥራች በሚ ልሕበቡን በተለይ አሰስ አበባ ውስጥ አስጨፈሩ ፥ ግን የኢትዮጵያን ባንዲራ ያውለበለቡ ወጣቶችን የኦሮሙማው ፖሊስ ሠራዊት ቀጠቀጠው፤ አብይ አህመድ የአዲስ አበባ፥ የደብረ ዘይት፥ የናዝሬትና ሌሎች ከተሞች ነዋሪችን የሕዝብ አሠፋፈር ለመቀየር ኦርቶዶክስ ክርስቶያቸኖችን፥ ጉራጌዎች፥ ኮንሶዎች፥ ወላይታና ጋሞዎች ወዘተ ዒላማ ያደረገ ማፈናቀል እያካሄደ "ከተሞቻችን እያማሩ ነውና የምሥራች" ብሏል። የአማራን ሕዝብ በምድርና በረር ኃይል ሕዓናትን፥ ካህናትን፥ ገዳማውያንን፥ ገበሬዎችን በመጨፍጨፍ ላይ የሚገኘው የአብ...
This is a spot where I post and share part of my daily reality. I would love to hear from others too to learn how differently we interpret daily encounters including our imaginations. ይህ ሥፍራ የየዕለት ገጠመኞቼን፣ እንዴት በዕለቱ እንተረደሁትና የማስበውን ለሌሎች ያማጋራበት ነው፡፡ የሌሎችን በመስማትና ምን ያህል ዓለማችንን በተለያየ መንገድ እንደምንመለከታት ለመማር እጓጓለሁ፡፡