ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

በቄስ አስተርአየ ጽጌ ፡ በህዝበ ክርስቲያኑ ላይ መንግሥት ለሚፈጽመው ዘር ጥፋት ተጠያቂው ተወቃሹና ተከሳሹ ፓትርያርኩ ናቸው!

በህዝበ ክርስቲያኑ ላይ መንግሥት ለሚፈጽመው ዘር ጥፋት ተጠያቂው ተወቃሹና ተከሳሹ ፓትርያርኩ ናቸው!

ነሐሴ 2 ቀ 2016 ዓ/ም ቀሲስ አስተርአየ nigatuasteraye@gmail.com

በህዝበ ክርስቲያኑ ላይ መንግሥት ለሚፈጽመው ዘር ጥፋት ተጠያቂው ተወቃሹና ተከሳሹ ፓትርያርኩ እንደሆነ ቀኖናችን አጉልቶ ቢነግረንም፦ ቡራኬዎ ይደርብን የሚለውን ቄስና ዲያቆን በተለይም በጥጉ ከበውት ያሉትን ቀሳውስት ከተጠያቂነቱ ነጻ አያደርጋቸውም ፡፡ እንዴት? ምን ማድረግ ይችላሉ?

የሰው ልጅ መንግሥት ባለመሠረተበት በPrimitive ዘመን ከውጭ በመጣበት ወራሪም ሆነ በእርስበርስ እልቂት የሞተው ሞቶ የተረፈው እንደገና በመባዛት ከማንሰራራት በቀር ለጠፋው ንብረት ተጠያቂ ካሳ ከፋይ የለውም፡፡ የፈሰሰውም ደምም ተጠያቂ የሌለው ደመ ከልብ ሆኖ ይቀር ነበር፡፡ በዚህ Primitive ዘመን savage በሚባለው ባህል ከላይ የጠቀስኩት አሰቃቂ ጥፋት ለረጅም ዘመናት በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ሲፈጸም ኖሯል፡፡ ከሚያጎራብቷት አገሮች ድንበሯን እየጣሱ በሚመጡት አረመኔወች አልፎ አልፎ ከሚደርሱባት ውዝግቦችና ቀውሶች በቀር ቀደም ብለው በመሰልጠን ከዚህ አስቃቂ ጥፋት ነጻ ከወጡት አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ነበረች፡፡    

በምን ሂደት ነው ከሺዎች ዘመናት አረመኔዎች ሁሉ የባሱ የጎሣ ድርጅቶችና መንግሥት በኢትዮጵያ ሊፈጠሩ ቻሉ?

ሕዘቡና ቤተክርስቲያን ከነባር ባህላቸው ያፈነገጡ አረመኔዎች አገሩን ሲቆጣጠሩ ምን አዘናጋቸው?

 

ኢትዮጵያ ከዐለምም ሆነ ካጎራባች አገሮች ይካሄድ ከነበረው ጸረ ሰብዕ ባህል ከረዥም ዘመን በፊት ቀድማ ልትላቀቅ የቻለቸው፦ ሕዝቦቿ በቋንቋቸው ቢለያዩም የተቀረጹባቸው መንፈሳውያን እሴቶቻቸው ከጎረቤት አገሮች የተለዩ በመሆናቸው ነበር፡፡

ካጎራባች አገሮች ህዝቦች ስነ ልቡና የኢትዮጵያውያን ስነ ልቡና የበለጠ ከፍ እንዲል እድል ያገኘው፦ ፊደል ቀርጻ ቀኖና ጽፋ በሕዝቦቿ መካከል ምሳሌ ሆና በኖረቸው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያ ነበር፡፡ በወራሪወች ተንኮል በሚገፉ መንፈሰዲቃሎች ልጆቿ ከውጭ ተቀብለው በሚፈጥሩት የትርክት ፈጠራ ቅብብሎሽ ቅድሳት የሆኑትን እሴቶችን ቢያደበዝዙትም የኢትዮጵያ ሕዝብ እስከኔ ዘመን ድረስ በልቡ ላይ በተቀረጸበት ልዕለ ሕሊናው “በሕግ አምላክ” ማለቱን አላቆመም ነበር፡፡ እርስ በርሱ ግጭት ውስጥ ሲገባ “እግዚአብሔር ያሳየዎ ክርስቶስ ያመልክተዎ” እያለ ሊፈርድበት የተሰየመውን ዳኛ ያስጠንቀቅ ነበር፡፡

የሕግ አምላክ እግዚአብሔር በተካደበት፥ ሕግ አስከባሪ መንግሥት ከሐዲና አረመኔ በሆነበት ሁኔታዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአገሪቱ ማኅበረሰቦች የባህልና የእምነት መሪዎች እንዴት ሕዝባቸውን ለመከላከል አልተንቀሳቀሱም?

ይህን ልዕለ አዕምሮ በሕብረተሰቡ ሕሊና ላይ የቀረጹት “ልሣኑ ይነብብ ጽድቀ፡፡ወሕገ አምላኩ ውስተ ልቡ” (መዝ 36፡30) የሚለውን የዳዊትን መጽሐፍ የሚደግሙ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናችን ያፈራቻቸው የመሠረቱት ያለፓትርያርክ ይመራ የነበረው የሊቃውንት መንፈሳዊ ጉባኤ ነበር፡፡

ከውጭ በአረማውያን (savage) እየተመሩ በሐሰት ትርክት ኢትዮጵያዊውን ስነ ልቡና የሚበክሉ እንደሚከሰቱ አባቶቻችን ሊቃውንት አስቀድመው በመረዳት “መተርጉማነ ፈጠራ ይህድጉ ወእመ አኮሰ ይሰደዱ”(ፍ አ 11 ቁ 468) ማለትም “የፈጠራ ትርክት አሰራጮች ያቁሙ! የማያቆሙ ከሆነ ከህዝብ ጋራ ወደማይገናኙብት ቦታ ይሸኙ(ይባረሩ)” ብለው መመሪያ አስቀምጠው ነበር፡፡ ይህን መመሪያ የሰሩ የጥንት አባቶቻችን ሊቃውንትብዝሑ ወተባዝሁ ምልእዋ ተገበርዋ ለምድር” (ዘፍ 1 28) የሚለውን ሕገ ተፈጥሮ ሳያዛቡ ለሕብረተ ሰቡ በቀለለ መንገድ የተጠያቂነቱን ሰሰለት በጥንቃቄ ሰርተውልን ነበር፡፡

ሕብረተ ሰቡ ዓለምን እያበጃትና በመባዛት እየሞላት እንድትቀጥ በመጠመድ ከውጭም ሆነ ከውስጥ ድንገት የሚነሱበትን አጥፊ ጠላቶችን አስቀድሞ ለማየት ትኩረቱ እንደሚቀነስበት የተረዱ አባቶች፦ የሚመጣበትን ተግዳሮት አስቀድመው አይተው የሚያስጠነቅቁትና የሚጋረዱለት መንፈሳውያን ሊቃውንት እንዲኖረው አደረጉ፡፡ ለሚያስጠነቅቁትና ለሚጋረዱለት መንፈሳውያን ሊቃውንት ጉባኤሕዝባዊ ያስተሐምም በእንተ ነፍሱ አንተሰ ጾርከ ጾረ ክቡደ”( 5120) ፡፡ የሚል መመሪያ አስቀመጡለት፡፡ ይህም ማለት፦ ህዝብ የፈጣሪውን ተክህኖ መመሪያ አደርጎ በመውለድ በመዋለድ ዘር እያስቀጠለ ዐለምን ለመሙላት በጥረት ላይ ሳለ፡ በጉልበትህ ጥረት ዐለምን ከማበጀትና በመዋለድ ዓለምን ከመሙላት ሕግ ራስህን አግልለህ ሕዝብ ለመምራት በመንፈሳዊ ክህነት የተሰማራህ አንተ ግን፡ ሕዝብ በተልእኮው ውጥረት የሚመጣበትን ጎጅ ነገሮች አስቀድሞ ለማየት ትኩረት ስለሚያጥረው አስቀድመህ አይተህ ለማስጠንቀቅ ተላልፈህም የመሞት የእዳ ሸክም አለብህእንደየ ክሂሎቱ ተሰማርቶ በውጥረት ላይ ባለው ህዝብ ላይ መንግሥት ቢያምጽ በመንበሩ ላይ የሚሰየመውን ፓትርይርክ በህዝብና በመንግሥት መካከል ጣልቃ እንዲገባ የገባው ቃል ኪዳን ያስገድደዋል፡፡ ለማስቆም ያለውን ሁሉ መንፈሳዊ ኃይል ይጠቀማል፡፡

 

መንግሥት ተግሳጹን ባይቀበልና በአመጹ ቢቀጥል ፓትርያርኩ ከመንበሩ ላይ ቁጭ ብሎ እነደ እመጫት እናቶች እንዲያለቅስ ቀኖናችን አይፈቅድለትም፡ ፓትርያርኩ በራሱ ላይ በደፋው ዘውድ፡ በትክሸዋ ላይ በደረበው ላንቃ በጨበጠው አርዌ በትር ተሰውሮ ያለውን መንፈሳዊ ኃይል ባይጠቀም ቀኖናችን ተጠያቂ ያደርገዋል፡፡

 

የፓትርያርኩ ተጠያቂነት የሰው ልጅ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዳይፈጸምበት የሚቀጣበት ዓለም አቀፍ ሕግ ሠርቶ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ከመሰየሙ በፊት፦ ቀደም ብሎ በመንፈሳዊ ልዕልና ይኖር የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጠያቂ አልባ ሆኖ፡ ዛሬ በአቡነ ማትያስ ዘመነፕትርክና፡ የብልጽግና መንግሥት በቆፈረለት አዘቅት ውስጥ ወደቀ፡፡ዘነሥአ ክህነተ እምእግዚአብሔር ከመ ይዕቀብ ሥጋ ወነፍሰ እም ኀጉል በከመ ነፍስ ትከብር እምሥጋ ከማሁ ክህነትኒ ትትሌዐል በክብር እመንግሥት

 

ወይእቲ ተአሥሮ ለዘይደልዎ ኩነኔ ወትፈትሆ ለዘይደልዎ ፍትሐት( 9289)፡፡ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ እገሌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የአክሱም ሊቀ ጳጳስ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትተብሎ በተደራረቡ ተቀብኦ ስሞች የሚሰየመው ፓትርያርክ ግለሰብነቱን በምንኩስና ግድሎ ለመንፈሳዊ ልጁ ሕይወት ለመሞት የተዘጋጀ አድርጎ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይመለከተው ነበር፡፡ በዚህ ቅድስና ፓትርያርኩን የሚመለከተው ሕዝብ በፍርድ ወንበር ላይ ወደ ተሰየመ ዳኛ ሲቀርብእግዚአብሔር ያሳየዎ ክርስቶስ ያመልክተዎእያለ ዳኛውን በማስጠንቀቂያ ሕሊናዊ ልዕልና እርከን ላይ የደረሰ ነበር፡ በዚህ ልዕለ አእምሮ እርከን ላይ የደረሰውን ሕዝቡን ሊመራ በመንበረ ፓትርያርኩ ላይ የተቀመጠው ቅዱስ አባትበትረጽድቅ ወበትረ ምንግሥትከ አፍቀርከ ጽድቀ ወአማጻ ጸላእከእያለ በሚደግመው በዳዊት ቃል በትረ መንግሥቱን የጨበጠውን መንግሥት እየመዘነ ይታዘበው ነበር፡፡

 

ህዝቡን የሚጎዳውና የሚበድለው አመጸኛ መንግሥት ሲሆን ጭቆናው ከብዶት ሕዝቡ ተቆጥቶ ከመነሳቱ በፊት መንግሥትን ያስጠነቅቀዋል፡፡

 

መንግሥት ምክሩን ንቆ በአመጹ ቢቀጥልና ፓትርያርኩ በሰላም ጊዜሰላም ለኩልክሙእያለ በጸሎቱ የሚመራውን ሕዝብ ሕዝብ ተቆጥቶ ቢነሳ፡ መስቀል አደባባይ ብለው አባቶቻችን በሰየሙልን ሜዳ ፓትርያርኩ ቁጣና ተግሳጽ በታጀበ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲመራው ነበር፡፡ በሚመራው ሰላማዊ ሰልፍ መንግሥት ከእመጹ የምይገታ ከሆነንጉሦቻቸውን በሰንሰለት አለቆቻቸውን በእግር ብረት ያስሩ ዘንድ በሰወች መካከል ቅጣትን ያደርጉ ዘንድ የተጻፈውን ፍርድ ያደርጉበት ዘንድ ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት”(መዝ 1497_9)፡፡

 

በሚለው ቃል ሕዝቡ በምንግሥት ላይ ያነሳውን የጽድቅ ብትር በጨበጠው በትረ ክህነት አጠናክሮ በመነሳት አመጸኛውን መንግሥት በህዝብ ሥልጣን ስር እንዲንበረከክ የማድረግ ግዴታ ነበረበት፡፡ በሕዝብ ምርጫ በእግዚአብሔር ፈቃድ ተመርጦ ቅዱስ በመባል በመንበሩ ላይ የሚቀመጠው ፓትርያርክ ቤተ ክርስቲያን ክልል ላሉት ክርስቲያኖች ብቻ ሳይወሰን በእግዚአብሔር አርያ ለተፈጠረ ሰው ሁሉ እኩል ይሟገትለታል ይቆምለታል ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡ወኩሉ ዘኮንከ አንተ ሊቀ ላዕሌሆሙ እምነ እደው ወአንስት ወሕጻናት ዘታቃወም ምክንያተ በንቲአሆሙ፡፡

 

ታስተጋብእ አፍሐመ ዲበር እርስከ ዘመጥነዝ ዐቅሙቅዱስ ተብለህ በመንበሩ ላይ የተሰየምከው በአገርህ ለሚኖሩ ሁሉ ሰወች ለወንዱ ለሴቱ ለደካማውና ለብርቱ ለእናቶችና ለሕጻነት ሁሉ ለሚድርስባቸው መከራ ተከላክይ እንድትሆን ነው፡፡ በአካባቢህ የሚኖረው ህዝብ እየተሰቃየ ሳለ አንተ ዝምታን ከመረጥክ ችግሩን የፈጠረው አመጸኛው ከሚከፍለው ፍዳ በላይ ተጠያቂ፡ ነህ፡፡በእንተ ግዕዘጠባይ ዘለባውያን ይሕሥሡ ሊቀ ዘይመርሆሙ ኀበ አእምሮ ፍኖተጽድቅ ወገቢረ ሠናይ ወምትወፍዮት ኀበ ርዕስ ዘእይከሎኦሙ እምዐምጽኦት ወይፈትህ ማእከሊሆሙ በእንተ ተጋእዞት ወተጻላኦት”(465) በቅዱስነትህ በምትመራቸው ሰወች መካከል ውዝግብ ቢከሰት ለተነሳው ውዝግብ ፈጥኖ መፍትሔ ለመስጥት እችላለሁ ብለህ ወደ ዚህ ቅድስና ገብተህበታል፡፡ የገባህበትን ቅዱስ ተልዕኮ ሳታፈጽም ብትቀር ተጠያቂ ነህ፡፡እምከመ ወጻት እሳት ወአውያቶሙ ለካልዐን እስመ እግዚአብሔር ይትሐሠሥ ነፍሳቲሆሙ እምእዴከ፡፡ ወለመ ኢኮንከ አንተ ዝንቱ ዘወደይከ እሳተ አላ ተዳደቀ ምስለ ዘወገራ፡ ሰመርከ በግብረ ዚአሁ ታስተጋበእ እሳተ በርእሰ ዚአከራሳህ የስህተቱ ጀማሪ ባትሆንም ከምትመራቸው ሰወች ባንዱ ስህተቱ ተከስቶ እያየህ እያወክ ዝም የምትል ከሆነ ስህተቱን ከፈጠርው አካል ጋራ እኩል ይፈረድብሀል፡፡

 

ወዑቅ እንከ ከመ ህዝብ ይድኅን እምግብር እኩይ ዘይበዝህ ላዕሌሁ ዘእንበለ ሊቅ”(ድርሳ 34) ማለትም፦ህዝብ የደረሰበት መከራ ሲከብደው የአንተን አመራር በትዝብት እንደሌለ ተረድቶ ራሱን የሚያድንበትን መንገድ ለመፍጠር እንደሚገደድ ተረዳ፡፡ በቅዱሱ መንበር ላይ ቅዱስ በመባል ተሰይመህ የቀድስናህን ሀላፊነትህን ላልተወጣህ ላንተ ግን ወዮልህ፡፡ በማለት ቀኖናችን የመጨረሻውን ተጠያቂነት በብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርካችን በአቡነ ማትያስ ላይ ያሸክመዋል፡፡

ፓትርያርኩ ባይችልስ? ሕዝብ በመተርጉማነፈጠራ እርስ በርሱ ግጭት ውስጥ ሲገባ፡ ፓትርያርኩ ሕዝባዊ ሀላፊነቱን መወጣት ከማይችልበት አቀም ላይ ወድቆ እንደ ዛሬው ተጠያቂ ሲጠፋ ቀኖናችን የኢትዮጵያን ሕዝብ ያለአንዳች መውጭ ቀዳዳ አይተወውም፡፡ ዛሬ በኛ ላይ በመፈጸም ላይ ያለውን ዘግናኝ የመከራ አይነት በጥንት ክርስቲያኖች ላይ ከደረሰው መከራ ጋራ የምናነጻጽርበትን ስንክሳሩን ወደምናነበው በየደብሩ ወዳለነው ቀሳውስት ሐላፊነቱን ያወርደዋል፡፡ ሳይቀየር ሳይጨመርበትና ሳይቀነስለት ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፈው መጽሐፈ ቅድሴያችን ከንጽጽር በላይ እጅግ የከፋውን መከራ እኛ በህዝቡ መካከል የምንኖር ቀሳውስት ለሰውም ለአምላክም እንድናደርስበት የተዘጋጀ ነው፡፡

ለአምልኮት የምንጠቀምበት መጽሐፈ ቅዳሴያችን ወቅታውያን ክስተቶችን በደስታና በመከራ ጊዜ በዜማ ወይም ለሕዝብ ጆሮ አድራሽ በሆነ ከፍ ባለ ድምጽ መነበብ በሚገባቸው ሀሳቦች የተሞላ ነው፡፡ በምትሰቡበት ጊዜ ሁሉ አድርጉት ያለውን ቁርባኑን በምናከናውንባቸው ሰአታት ምእመናኑ ትኩረቱን ሰብስቦ በቅዳሴው አማካይነት ብሶቱን ምኞቱን ለአምላኩ እንዲያቀርብ ይረዳው ዘንድ ወቅቱን የሚያንጸባርቁትን ለይተን ከፍ ባለ በተለየ ድምጽ እናነባቸዋለን፡፡

ወይም እናዜማቸዋለን፡፡ በወንጌሉም የሚንጸባረቀው ትምህርት የተዜመውን ወይም የተነበበውን ብቻ ማብራራት ነበር፡፡ እኛ የዘመናችን ካህናት ሕዝቡ ትኩረቱን ሰብስቦ ወቅታዊ ብሶቱን ምኞቱን ስሜቱን ለአምላኩ እንዲያቀርብ የተዘጋጀውን ቅዳሴ፡ ህዝቡ ተረድቶት በተገቢው መንገድ እንዲጠቀምበት ከማድረግ ይልቅ ለመተዳደሪያነት የተከፈተልን ድርጅት አስመስለን የገቢ ምንጭ አድርገነዋል፡፡

በስደተኛው መካከል በውጭ የምንኖር ካህናት ከጥቂት ካህናት በቀር በቅዳሴአችን በተመዘገበው ህዝቡን በዋይታውና በሀዘን አልተባበርነውምና በህዝቡ ላይ በደረሰው በደል ተገፍተን አለመሰደዳችን እንዲያውም በተሰደደበት ቦታ ሁሉ እየተከተልን ገንዘቡን በመዝረፍ ላይ እንደሆን በገሀድ እየተገለጸብን ነው፡፡የገብያ ግርግር ለቀጣፊ በጀውእንዲል፡ ቤተ ክርስቲያናችን የገባችበትን ውዝግብ በመጠቀም ራሳችን በፈጠርናቸው ስሞች ከሊቃውንቱ በላይ ራሳችንን በማላቅ በታላላቅ አድባራት ራሳችንን ሰይመንና ከቀኖናችን ውጭ ጽላቶች እየደራረብን ገንዘብ ከመዝረፋችን በላይ ሕዝቡ ከችግር የሚወጣበትን የተጻፈውን በመሸፈናችን እጽፍ ድርብ ተጠያቂነት አለብን፡፡ በስደት በውጭ ዓለም የሚኖረው ሕዝብ ከአገሩ በመራቁ ስደተኛ ቢባልም፡ በአገር ውስጥ የቀረው ህዝብ ስደት እጅግ የከፋ ነው፡፡

 

የህዝቡን ወቅታውያን ሁኔታወች ማለትም መሰደድ መደብደብ መገረፍ መገደልና መበዝበዝ ከፍ አርገው ከሚያሳዩት በቅዳሴ ጊዜ መነበብ ካለባቸው ግን ከሸፍናቸው ለማሳያ ያህል ጥቂቶችን ለመጥቀስ እሞክራለሁ፡፡ንሕነሰ እለ ተሰደድነ በእንተ ስምከ ወኮነ ሕብልያ እምኀቤሆሙ ለዕልዋን” (አትናቴወስ) ማለትም፦ በአረመኔዎች ከተወለድንበት መንደር ተሰደድን ሕይወታችንም ለልቂት ተዳረገንብረታችንም ተበዘበዘብሎ ቅዳሴው የሚገልጸው ስደትና ብዝበዛ አገሩን ጥሎ በስደት ላይ ባለው ሕዝብ ላይ ከሚደርስበት ይልቅ እጅግ የከፋ ነው፡፡ ተሰዶ በውጭ የሚኖረው ሕዝብ በወገኑ ላይ የሚደርሰውን መከራ እንዲዘነጋ ለማድረግ አጉልቶ የሚያሳየውን አንቀጽ በጠራ ንባብ አናቀርብለትም፡፡

እኛ ልጆቻችሁ ዘር በሚያጠፋ ንብረት በሚበዘብዝ ጠላት አለቅንእያለ የሚያሰማው የዋይታ ድምጽ አጉልቶ የሚያሳየውንናሁ ለደቂቅክሙ በልዐተነ ኃጢአት ከመ ዘእሳት ወአውያተነ ፍትወት አኮ ፍትወት ዘነፍስ አላ ፍትወት ዘሥጋ ዘእውቱ ማኅጎሊሃ ለነፍስአትና 34 የሚለውንም ሸፈነናዋል፡፡ ጥቂት ንጹሐን በመካከል ቢኖሩምአሜሃ ጽኑዓን ይደክሙ እስመ አህለቁ ሥጋሆሙ በዝሙት “(አትና 82) እንዲል መጽሐፉ፦ ብዙወች ጳጳሳት ጵጵስናቸው ብጽዕናቸው በሸፍጥ በዝሙት እንደ በረዶ የቀለጠባቸው መሆኑን ደፍረን ከመናገር ይልቅ ለምናገኘው ጥቅም ስንል ራሳችንንም ቅዱሱን ሕዝበ ክርስቲያኑንም አስረግጠነዋል፡፡ መጽሐፈ ቅዳሴአችንወለእመኒ ኖሙ አክናፈ መላእክት ይክድኖሙ ክበደ ንዋም ኢያስጥሞሙ፡፡ ዘወእቱ አምሳሊሃ ለሞት”(ዘሥ 35386) ማለትም፦በሥጋ ፈቃድ ተውጠዋል ደንዝዘዋል ነፍዘዋል በእንቅልፍ ላይ ናቸውየሚለውን አንዳንድ ጊዜ በሹክሽክታ ሌላ ጊዜ በግልጽ ሰውና ቦታ እያየን እናወራለን፡፡ ነገር ግን እኛ የተረዳውን ሳይረዳ የፓትርያርኩን መኖር በመደገፍ የሚከተለውን ህዝበ ክርስቲያን እንዲያወግዛቸውና ራሱንም እንዲከላከል አልረዳነውምና ተጠያቂወች ነን፡፡ምግባረ ካህናት ሠናይት ትበቁዖሙ ለብዙኅን እስመ ውእቱ ይትሜሰሉ ባቲ፡ ከማሁ ካዕበ ኃጢአቶሙ ለሰብእ ሀካያን እምሠናያት( 9 ቁጥ 298)፡፡ ይላል፦ ማለትም በምግባራቸው ምሳሌነት ሕዝባዊ ጥቅም የሚሰጡ ጥቂት ካህናት ቢገኙ ይጠቅሙ ነበር፡፡ ነግር ግን ምሳሌነት የሌላቸው ካህናት ስለበዙ በህዝብ ላይ ያስከተለው የጥፋት ብዛት እጅግ የሰፋ ሆነ በማለት እኛን ቀሳውስቱን የሚወቅሰንን ምንባብ ሕዝቡ በኛ ላይ ተቆጥቶ እንዳይነሳብን ከህዝቡ ሰውረነዋል፡፡ የፍልሰታን ሱባኤ ጀምረን የምንፈጽምበት አባ ሕርያቆስ የደረሱት ቅዳሴ ማርያም የተባለው መጽሐፍ የኛን የምንቀድሰውን ቀሳውስት አስመሳይ አቋም እጅግ ክፉኛ ይኮንነዋል፡፡

በሕብረተ ሰቡ መካከል ስንሆን ራሳችንን ነጻ አድርገን ተጠያቅኒቱን በፓትርያርኩ ላይ ብቻ እናሸክማለን፡፡ ወደ ቤተ መቅደስ ስንመጣ በህዝብ መካከልና እርስ በርሳችን የምናወራውን እንክድና አቋማቸውን ሳያዛቡ ተልእኳቸው ለተወጡትና በመወጣት ላይ ላሉት ፓትርያርክ ብቻ የሚሰጠውን የአድናቆትና የክብር ምስጋና፡ ለምንወቅሳቸው ፓትርያርክ የሚከተለውን እናነባለን፡፡

ኧረ ምን አይነት ጉዶች ! ነን ? “ አበዊነ ንቡራነ ዕድ ሥዩማን እለ መትለዎ ሐዋርያት እስመ ነሣእናክሙ በመዋዕሊነ አስተብቋዕያነ ለነ ኀበ አግዚአብሔር”( ገጽ 164፡ቁ 10) ይህ ቃል በዘመናችን ያሉት ፓትርያርክ በሐዋርያት ቦታ ተሰይመው የሚጠበቅባቸውን በማድረግ ላይ እንዳሉና እኛም ደስ ብሎን ፓትርያርክነታቸውን እንደተቀበልናላቸው የሚገልጽ ነው፡፡

ታዲያ በቤተ መቅደስ አድበስብሰን እምናነበውን ሕዝብ ትኩረት ቢሰጠው ከፓትርያርኩ ይልቅ እኛን ቀሳውስቱን አይታዘበንም? አዲስ አበባ ካለው ከብልጽግናው መንግሥትና በትግራይ ከሚገኘው ከነደብረ ጽዮን አመራር በሚቀበሉት ጳጳሳት እየተመሩ ፓትርያርኩ ህዝበ ክርስቲያኑን ለእልቂት እንደዳረጉት ቄሱም መነኩሴውም ሁሉ በይፋ ይናገረዋል፡፡

በስሕተት ከተሰለፉበት ፈጥነው በመንቃት እንዲመለሱ መቀስቀሻ እንዲሆነን ከዚህ በታች በቅዳሴ መጽሐፋችን ላይ የተመዘገበውን ጠቅሰን አሳስበናቸዋል? “እቀቦሙ እምጌግዮ ወስሒት በመልክ ወበመለያልይ በንጻሬ ወበራእይ ሌሊተ ተኖልዎሙ ትግሀታተ ከንቱ ኢይምጾሙ እንተ ይእቲ ማሕጎሊሃ ለነፍስ(21934) ይህም ማለት፦መንፈስ ቅዱስ የተለየው መንፈሳዊ መሪ በሚያየውና በሚሰማው ውዝግብ ይሳሳታል፡፡ በሚያየውና በሚሰማው ውዝግብ እያንቀላፋ የሚመራ ፓትርያርክ በሚመራው ሕዝብ ላይ ሥጋንና ነፍስን ለሚደመሥስ ጥፋት ምክንያት ይሆናል፡፡

እኛ በተለይም በዙሪያቸው የከበብናቸው ቀሳውስት እግራቸው ስር በመውደቅይባርኩኝ ቡራኬዎ ይደርብኝበማለት አመጸኛው መንግሥት በጫነባቸው ላይ ተጨማሪ ማደንዘዣ በላያቸው ላይ ከመካብ በቀር፡ ከላይ የጠቀስኩትን በቅዳሴአችን በተገለጹት ምንባባት ከንቅልፋቸው እንዲነቁ አስታውሰናቸዋል? ቅዳሴው በሚያዝዘን ፓትርያርኩ እንዲነቁ በምናደርገው ትውፊታዊ ቅስቀሳ የምናቆርበውን ህዝበ ክርስቲያን አዘጋጅተንና አንቅተን በፓትርያርኩ ላይ ተጽእኖ እንዲያከብድባቸው ይተባበረን ዘንድ ድርሻውን እንዲወጣ ነግረነዋል? Primitive ዘመን ከውጭ ከመጣበት ወራሪም ሆነ በእርስበርስ እልቂት የሞተው ሞቶ የተረፈው ያለተጠያቂ እንደገና በመባዛት ማንሰራራትና ደሙም ደመ ከልብ ይሆን በነበረት ዘመንበሕግ አምላክእየተባባለ እርስ በርሱ በመደኛኘት ይኖር የነበረው የኢትዮጵያን ሕዝብ ዛሬ በአረመኔወች የሚደርስበትን አሰቃቂ መከራ እንደ ውጭ ተመልካች ቆመን በመመልከት ላይ ነን፡፡

ከብዙ ዘመናት በፊት የሚፈርድ ዳኛ ከሰየመም በኋልእግዚአብሔር ያሳየዎ ክርስቶስ ያመልክተዎእያለ ሊፈርድበት ለሰየመው ዳኛ የፍርድን ሚዛን እንዳይሰብር አስጠንቃቂ እርከን ላይ ደርሶ የነበረውን ሕዝብ በዘመናችን እንዳሸን የፈሉት መተርጉማነፈጠራየፈጠራ ትርክት አሰራጮች ያቁሙ! የማያቆሙ ከሆነ ከህዝብ ጋራ ወደማይገናኙብት ቦታ ይሸኙ(ይባረሩ)” ( 11 468) የሚለውን ቀኖና ሰርዘው በሐሰት ትርክታቸው እርስ በርሱ ሲያጋድሉት ቆመ በማየት ላይ አይደለንምን? ለዚህ ሁሉ እልቂት ተጠያቂነቱ በፓትርያርኩ ላይ እጽፍ ድርብ ቢሆንም ፦በዚህ ዘመን ላይ የምንገኝ ሀላችንንም በተለይም በፓትርያርኩ ዙሪያ ያላችሁትን ቀሳውስት የክህነታችን ሐዋርያዊ ትውፊት ሰንሰለት ከፓትርያርኩ ጋራ አስተሳስሮ ተጠያቂወች ያደርገናል፡፡

ቀጥየ ለማቀርበው እዚህ ላይ ይቆየን!

=================================================

እነዚህን መገናኛዎቼን ሱበሰክራይብ፥ ማጋራት፥ አባል በመሆን፥ እንደየ አመለካከታችሁ የመወያያ ጉዳዮችን በገጾቼ ላይ በመጻፍ ለአገራችንና ለቤተክርስቲያናችን ሰላምና አንደነት አስተዋጽ እናድርግ

Telegram: https://t.me/+io2m-XA1OBE2NmM0

YOUTUBE:- https://www.youtube.com/@Orthodox_Secular_FantahunWakie/videos

ትዊተር፦ @fwakie

FB:- https://www.facebook.com/fwakie

Blog:- https://ethiopiaorthodoxchristian.blogspot.com

እግዚአብሔር ያክብርልኝ፤

ታናሽ ወነድማችሁ ፋንታሁን ዋቄ


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...