፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት
ከሰው ልጅ መበደል
በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ.
11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡
ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡
በበደል የመጣውን
ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ
ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን
ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡
የክርስትና ጉዞ ወደ
ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡
በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ
እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር
ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት
ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን
አባቶችን በቋንቋ መመደብና በዘውግ ማንነታቸው መሠረት ማስላትና ስታስቲክስ መሥራት ኢክርስቲያናዊ ነው፡፡ ጌታችን የመረጣቸው ቅዱሳን
ሐዋርያት ከአንድ የአይሁድ ሕዝብ ውስጥ ብቻ ያውም ብዙዎቹ ከአንድ የገሊላ አካባቢ ነበሩ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ የሮም መንበር የመጀመሪያው
ፓትርያርክ ነው፣ በትውልድ ግን አይሁዳዊ፣ አገሩም ፍልስጥኤም ነበር፡፡ የኢትዮጵያው አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን በትውልድ ሶርያዊ
ነበር፡፡ ከእስክንድርያ ፓትርያርኮች መካከል ቢያንስ 3ቱ ሶርያውያን ነበሩ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በቅድስናቸው ከሚታወቁት አባቶች
ብዙ የውጭ አገር ዜጎች ነበሩ - አቡነ አረጋዊ፣ አቡነ ገሪማ (በአጠቃላይ 9ኙ ቅዱሳን)፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ አቡነ ዮሐንስ
ዘጠጋሮ፣ አቡነ ክፍለ ማርያም ዘዋታዎ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከግብጽ ሲመጡልን የነበሩት ጳጳሳት - ቋንቋቸው፣ ዜግነታቸው፣ - ሌላ ነበር፤
ግን አባቶቻችን ናቸው፤ ዛሬ ያሉት ግብጻውያን ጳጳሳትም አባቶቻችን ናቸው፡፡
አንድ ሰው ካህን ሲሆን አባትነቱ ለሃይማኖቱ ተከታዮች ሁሉ ነው እንጂ ለሥጋ
ዘመዶቹና በቋንቋ ወይም በሌላ መንገድ ለሚቀርቡት የተወሰኑ ማኅበረሰቦች አይደለም፡፡ እንደዚያ የሚያደርግ ከሆነ ያ ሰው ካህን አልሆነም
ማለት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ዐለም አቀፋዊት/ኩላዊት እንጂ መንደራዊት/ሰፈርተኛ
አይደለችም፡፡ አምላካችን “ሑሩ ወመሀሩ ኩሎ ዓለመ”( ትርጓሜው በአማርኛ) አለ እንጂ ወንዝና ሰፈር ቁጠሩ አላለም፡፡ a
ክርስትና አንድነት ነው
ክርስትና እንኳንስ በምድር ካሉ ሰዎች ጋር በሰማይ ካሉትም ጋር አንድ የሚያደርግ
ነው፡፡ ክርስትና ወደ ታላቁ ክርስቶሳዊ ኅብረት መግባት ስለሆነ ይህ መስፋትን እንጂ መጥበብን አይቀበልም፡፡ ክርስቲያን መሆን ማለት
ከምናያቸው በምድር ካሉ ሰዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከስውራን ቅዱሳን ጋር፣ ከቅዱሳን መላእክት ጋርና በዐለመ ነፍስ ካሉ ሁሉ ጋር ያለ
ኅብረት ስለሆነ ከዚህ ሰፊ አንድነቷና ኅብረቷ ወጥቶ በቋንቋና በአጥንት ልቧደን ማለት ለክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ባሕርይ ተቃራኒ
ነው፡፡ “ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፣ በሕያውና ለዘላለም
በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ” እንደ ተባለ
ከመንፈስ ቅዱስ ከተወለዱ በኋላ ወደ ሥጋዊ ልደት መመለስ ከክርስትና መንፈስ
ጋር መቃረን ነው፡፡ 1
ጴጥ. 1፡23 እንዲሁም “አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፣ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፣
ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና” ተብሏልና፡፡ ገላ. 3፡28
በቋንቋም ሆነ በመሰል የንዑስ ማንነት ጉዳይ ሰፈርተኛና መንደርተኛ መሆን የክርስትና
ሳይሆን የጣዖታውያን ጠባይ ነው፡፡ ከዛ አልፎ ተርፎ ክርስቲያንን በቋንቃቸው ማግለል ማጥቃት ማሳደድ፣ ክርስቲያኖችን ሆኑ እስላሞች ሲታረዱ “፣እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን” ብሎ አለማውገዝ ስህተት ሳይሆን የሰይጣን ስራ ነው።
በቋንቋ መስፈርትነት መጓዝ ክርስትናን ሰፈር ተኮር ወደ ነበሩ ጥንታውያን የጣዖት
አምልኮዎች ለመጎተት መሞከር ነው፡፡ ይህ በየሰፈሩና አካባቢው ብቻ ይመለኩ የነበሩ አማልክት እምነቶች ጠባይ እንጂ የክርስትና ጠባይ
አይደለም፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ይህን ሲያብራራ እንዲህ ብሏል፡-
ሌላው
አስደናቂ ነገር፣ ይመለኩ የነበሩት ጣዖታት በጣም ብዙ ዓይነትና የተለያዩ የነበሩና በአንዱ አካባቢ እንደ አምላክ ይመለክ የነበረው
ጣዖት በሌላው በአካባቢው የሚኖሩ ሌሎች ሰዎች ያመልኩት ዘንድ እነርሱን ለማሳመን ተጽእኖውን ማስፋፋትም ሆነ ኃይሉን መግልጥ አይችል
የነበረ ሲሆን፣ እያንዳንዱ የራሱን ጣዖት እንጂ የሌላውን አካባቢ ጣዖት የሚያመልክ ማንም አልነበረምና፡፡ በሁሉም ዘንድ በአንድነት
የሚመለከው ግን ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ የጣዖታት ድካም ማድረግ ያልቻለውን ማለትም በአቅራቢያቸው ያሉትን ሰዎች እንኳ ወደ ራሳቸው
አምልኮ ማምጣት ያልቻሉትን፣ ክርስቶስ ግን ይህን አደረገ፡፡ በቅርብ ያሉትን ብቻ ሳይሆን ዓለሙን በመላ አንድና ብቸኛ አምላክ የሆነውን
እርሱን እንዲያመልኩ አሳመናቸው፣ ወደ እርሱ አምልኮ ሳባቸው፡፡[1]
ስለዚህ
ክርስቲያኖችን በቋንቋቸው መሠረት ለመክፈልና ክህነትንም በዚሁ መስመር ለማስኬድ መሞከር በበዐለ ሃምሳ የተገኘውን አንድነት ለማፍረስ
መሞከር ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን አስተምህሮና ታሪካዊ ትውፊት ጋር ግልጽ ተቃርኖ ነው፡፡ በክርስቶስ አምነን ያገኘነውን አንድነት
ወደ ኋላ ለመመለስና ከመንፈሳዊ ልደት ወደ ሥጋዊ ልደት ለመመለስ መሞከር ነው፡፡ አዳምና ሔዋ ከመበደላቸው በፊት ወደ ነበረውና
ከዚያም ከፍ ያለ ወደ ሆነው የሰው ልጅ ሁሉ እርስ በርሱ እና ከቅዱሳን መላእክት ጋር ወደሚኖረው በጋራ የመግባባት ሰማያዊ ሕይወት
የምታደርገው ጉዞ ለማሰናከል መሞከር ነው፡፡
ክርስትናን
በቋንቋና በመሰል ንዑስ ማንነት ለመከፋፈል የሚደረጉ ጥረቶች በዐለም አቀፈ ደረጃ ምን እንደሚመስሉ ለመገንዘብ ይረዳ ዘንድ በቅርብ
ዘመን ከሆኑና አሁንም እየሆኑ ካሉ ኩነቶች ሁለቱን ብቻ በአጭሩ እንመለከታለን፡፡
፪. አጭር ዐለም አቀፋዊ ታሪካዊ ዳሰሳ
1. የናዚ ፓርቲ
በጀርመን አገር የፈጠረው “የጀርመን ክርስትና” አጭር ዳሰሳ 5312
1933
ዓ.ም. (እ.ጎ.አ.) ለጀርመን
ትልቅ የታሪክ እጥፋት ዓመት ነበር። ይኽ ዓመት በአዶልፍ
ሂትለር የሚመራው
የናዚ ፓርቲ የጀርመንን
መንግሥት መቆጣጠር
የቻለበት ነበር።
ሂትለር ሥልጣን እንደ ያዘ መጀመሪያ ካደረጋቸው ነገሮች አንዱ ጀርመናዊ “ክርስትና”
መፍጠር ነበር፡፡
ፓርቲው በሂትለር
እየተመራ ወደ ሥልጣን በመጣ በአጭር ጊዜ ውስጥ “ሁሉን ወደ መስመር ማስገባት” ግሌይሽሻልቱንግ - Gleichschaltung (bringing everything into line) የተሰኘ ፖሊሲ አስተዋወቀ። የፖሊሲው ዓላማ የጀርመንን ማኅበረሰቦች ልዩ ልዩ ማንነቶች ሁሉ ከፓርቲው ርእዮተ ዓለም ጋር ስምሙ እንዲሆኑ ማድረግ ነበር፡፡ በሌላ አነጋገር መላውን የጀርመን ማንነት ናዚያዊ (ናዚፋይ)
ማድረግ ማለት ነው። የፕሮቴስታንት ቤተ
ክርስቲያንም ናዚያዊ ከሚደረጉት ክፍሎች መካከል አንዱና ዋነኛው ነበር።
ናዚዎች ለዓላማቸው ማስፈጸሚያ ሲሉ የፈጠሩት አዲሱ ሃይማኖት “የጀርመን ክርስትና” ተብሎ ይታወቃል፡፡
ይህ “የጀርመን ክርስትና” የጀርመንን ዜጋ ከሌሎች
የሰው
ልጆች ሁሉ ልዩ እንደሆነና እንደሚልቅ ለማሳየት የግድ አዲስ አስተምህሮ በማስፈለጉ የተፈጠረ ነው። ስለዚህም ልዩ የጀርመን ዝርያን (German Volk)
ለመስበክ የተመቸ “የጀርመን ክርስትና” የተሰኘ አዲስ ኑፋቄ ተወለደ።[2] ስለዚህ “የጀርመን ክርስትና” ንቅናቄ ለአዲሱ የናዚ ፓርቲ ርእዮት ማለትም የጀርመን ንጹሕ ደምና የላቀ ዘርኝነትን ማዕከል ያደረገ በቀዳማዊው ፕሮቴስታንትም ሆነ በካቶሊክ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ነበር። ምክንያቱም የክርስትና አስተምህሮ ከናዚ የጭካኔና
ከጥንካሬ አስፈላጊነት አስተምህሮ ጋር ስለሚጋጭ እርሱን የሚመስል አዲስ “ክርስትና” መፍጠር አስፈለጋቸው፡፡
ይህ
የናዚዎች ትርክት (ቴሲስ) የፕሮቴስታንት ቸርቾች የናዚ ርእዮት አቀጣጣይ እንዲሆኑ በታቀደው መሠረት በፍጥነት ተሠራጨ። ይህን የናዚ
ቤተ ክርስቲያንን የመጥለፍ ዘመቻ የሚቃወሙ የክርስቲያን ንቅናቄዎች በጀርመን ውስጥ ተፈጠሩ። ይህ ኑፋቄ በፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን
ውስጥ መከፋፈልን ፈጠረ። ስለዚህ በፕሮቴስታንት ቸርች ውስጥ በአንድ በኩል ራሳቸውን ለናዚ ፓርቲ ተልእኮ
አስፈጻሚነት ባዘጋጁት “የጀርመን ክርስትና” እና በሌላ በኩል ደግሞ ክርስትናን ከናዚ
መጫወቻነት ለመከላከል በሚታገሉት “ኮንፌሲንግ ቸርች” መካከል ትግል ተጀመረ።
ሪቻርድ ኢስቲግማነ-ጋል የተባለ አጥኚ “ቅዱሱ
መንግሥት፡ ክርስትና በናዚ አረዳድ - The Holy Reich: Nazi Conceptions
of Christianity) በሚለው መጽሐፉ እንደ ገለጸው፣ “የጀርመን ክርስትና” ንቅናቄ ግብ የፕሮቴስታንት ክርስትናን
በጸረ-ክርስትና
በማጥመቅ ከእናት
ፕሮቴስታንት አስተምህሮ
መለየት ነበር። “የጀርመን ክርስትና” ንቅናቄ ልሂቃን ሂትለርን ለማስደሰት ሲጣደፉ ቀደም ሲል ያልነበረ “ለጀርመን ክርስትና” ብቻ ልዩ የሆኑ አዳዲስ ኑፋቄዎችን በአስተምህሮዎቻቸው ማምረት ጀመሩ።
በናዚዎች
የተፈጠረው አዲሱ “የጀርመን ክርስትና” ንቅናቄ ሲፈጠር አንደኛው መሠረታዊ እሳቤው ዘረኝነትና በዋናነት ደግሞ የሴማዊነት-ጥላቻ (Anti-Semitism) ነበር፡፡ “የጀርመን ክርስትና” አይሁዳዊ ዝርያ ያላቸውን ክርስቲያኖች ሁሉ እያደነ ከቸርችና ከማናቸውም ክህነታዊ ተሳትፎ ሁሉ ያባርራቸው ነበር።
“የጀርመን ክርስትና” ንቅናቄ የመጨረሻ ግብ ጀርመን እንደ አገር ከሌሎች የማትጋራው የሆነ የራሷ
ዓይነት ብቻ የሆነ “ጀርመናዊ ክርስትና” መፍጠር ነበር። “የጀርመን ክርስትና” ልዩ ኑፋቄ የተፈለገው አዲሱን ጀርመን ለመፍጠር የግድ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነው ተብሎ ስለታመነ ነበር፡፡ አንዳንድ የጀርመን ታሪክ ምሁራን ልዩ-ጎዳና (Sonderweg)
የሚለውን ጽንሰ ሀሳብ እጅግ በመለጠጥ የጀርመን
ታሪክ ከአጠቃላይ
የአውሮፓ አገራት
ሁሉ ጎዳና የተለየ ነው ወደሚል ደርሰው
ነበር።[3]
“የጀርመን ክርስትና” ማዕከላዊና መሪ የሆነው ዶክትሪናቸው የጀርመን ዝርያ (German Volk) ጉዳይ ነበር። “የጀርመን ክርስትና” አቀንቃኞች መስቀልን ከቤተ ክርስቲያን ማዕከላዊ ትኩረትነት አንስተው የእምነታቸውን ዋና ማዕከል በጀርመን ዘረኝነት ተኩት። ናዚ ፓርቲም፣ “የጀርመን ክርስትናም” ሁለቱም ንቅናቄዎች የተመሠረቱት በዘርና ዘረኝነት ላይ
ነበር። ይህንም የነገረ መለኮት ምሁሩ ካርል ባርዝ (Karl Barth) ሲገልጸው “የጀርመን ክርስትና ከመጽሐፍ ቅዱስ ቀጥሎ ሁለተኛው መገለጥ የጀርመን ዝርያ ልዩ ነው ብሎ ማመኑ ነው” ብሏል፡፡[4]
ዘረኝነት” በጀርመን ክርስትና” ውስጥ የሁሉ ጉዳይ ማጠንጠኛና መወሰኛ ሆነ። “የጀርመን ክርስትና” አቀንቃኞች የዘር ሕጎችን በእምነታቸው ውስጥ ከፍ አድርጎ መደገፍ ከእግዚአብሔር የተጣለባቸው የመገለጥ አደራ እንደሆነ ይሰማቸዋል። በጀርመን ክርስትና ቸርች 10 ነጥቦች ያለው መመሪያ ሲያሳትሙ ማዕከል ያደረገው ዘረኝነትን ነበር። ሰባተኛው ነጥብ እንዲህ ይል ነበር፡- “እግዚአብሔር ዝርያን፣ አገርን፣ ብሔራዊ ሕጎችን እንድንጠብቅ አደራ ሰጥቶናል። . . . ስለዚህ የዝርያ መቀላቀልን አጥብቀን መቃወም አለብን።”
እንዲሁም ነጥብ ዘጠኝ፡- “አይሁድ ለዝርያችን ጥራት ከፍተኛ አደጋ ሆነው ይገኛሉ። ተልዕኳችን
እንግዳና ባዕድ የሆነ ደም ወደ ዘራችን
እንዳይገባ መጠንቀቅና
መጠበቅ ግዴታችን
ነው። መዳቀል ደማችንን የመበከል እድል ስለሚፈጥር የአይሁድን የጀርመን ዜግነት የሚፈቅድ ሕግን እንቃወማለን። በጀርመንና በተለይ በአይሁድ መካከል የሚደረግ ጋብቻ ፈጽሞ ሊከለከል ይገባል” ይላል፡፡[5] በ1933
በታተመው The Handbook
of the German
Christians በሚል የጀርመን ክርስትናን አቋም በሚገልጥ ዐረፍተ ነገር ላይም “የጀርመን ዜጋ ከሌላ ጋር መጋባት ከእግዚአብሔር ፈቃድ የሚቃረን ነው” ሲል ያውጃል።[6]
“የጀርመን ክርስትና” ዘረኝነት ራሱን የሚገልጠው በዋናነት በጸረ-ሴማዊነት (ሴማዊነትን በመጥላት) ነው። ስለዚህ በዶክትሪናቸው ውስጥ ጸረ-ሴማዊነት ተደጋግሞ ይንጸባረቅ ነበር። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚታየው የጸረ-ሴማዊነት ባህል በአይሁዶች ላይ በሚፈጸም አካላዊ ጥቃት ሳይቀር ይገለጥ ነበር።
“የጀርመን ክርስትና” ንቅናቄ አራማጆች የጀርመንን ቤተ ክርስቲያን ከአይሁድ ተሳትፎ በማጽዳት የአንድ ዝርያ ቤተ ክርስቲያን በመፍጠር ላይ ተፋጠኑ፡፡
ንቅናቄው
“የጀርመንን ክርስትና” ሕይወት ከአይሁድ ተጽእኖ ነጻ ማውጣት በሚቻልበት መንገድ ላይ የምርምር ኢንስቲቲዩት መሠረተ።[7] “የጀርመን ክርስትና” ንቅናቄ አባሎቻቸውንና ዝርያቸውን በአይሁድ
ዝርያ “ከመቆሸሽ” ለመከላከል ከፍተኛ
ጥንቃቄ ያደርጉ ነበር።
ለዚህም “የጀርመን ክርስትና” ንቅናቄ አባልነትን ለማግኘት ወሳኙ መስፈርት የጀርመን አርያን ዝርያ መሆኑ በመሐላና በምስክርነት መረጋገጥ እንዲሆን አድርጓል።[8] በ1935 አዲስ የውጊያና የእምነት ንቅናቄ (Combat and Faith Movement) በሚል የሚታወቀው በጀርመን ክርስትና ውስጥ የአባልነት መስፍርት ተመዝጋቢው “እኔ የአርያን ደም አለኝ፣ ሁለቱም ወላጅ እናት አባቴ እና አያቶቼ የአርያን ንጹሕ
ደም ያላቸው ናቸው” የሚለውን መመስከርና መፈረምን ያስገድድ ነበር።[9]
ከቤተ
ክርስቲያን
የአይሁድ ዝርያ ያላቸውን ክርስቲያኖች የማግለሉ ሂደት ከናዚ እርምጃ ጋር እየተናበበ እርምጃ በእርምጃ እየተጠናከረ ሄደ። በ1935 ናዚ በኑረንበርግ አዋጁ አይሁድነትን የተለየ ዝርያ ተብሎ እንዲታወቅ አሳወጀ። ከኑረንበርጉ ሕግ በኋላ ብዙ “የጀርመን ክርስቲያኖች” የተጠመቁ አይሁዶች የሚያመልኩበት ቦታ የተለየ እንዲሆን መጠየቅ ጀመሩ።[10] የኑረንበርጉ ሕግ አይሁዶች በሕግ ከጀርመን ማኅበረሰብ የተገለሉ አደረጋቸው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥም ተግባራዊ መደረግ ጀመረ።
ከ1935ቱ የኑረንበርግ ሕግ በኋላ
“የጀርመን ክርስትናን” ለተፈለገው አዲስ ንቅናቄያቸው እንዲስማማ አድርገው የራሳቸው ኢየሱስ ለመሣል ሞከሩ።[11] ለዚህም “ኢየሱስ የአይሁድ ደም የለውም፣
ኢየሱስ
አርያን (ጀርመናዊ) ነው” ብለው ደመደሙ። ንቅናቄው ትምህርቱ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ “ኢየሱስ በገሊላ ከሚኖሩ አርያን ጎሣ የተወለደ ነው” እያሉ እንደ ኢማኑኤል ሂንሪሽ (Emanuel Hirsch) እና ሁስተን እስቲዋርት (Houston Stewart) ያሉ ምሁራን ማስተጋባት ጀመሩ፡፡ የጀርመን ክርስትና የነገረ ክርስቶስ ማዕከሉን “ኢየሱስ ሴማዊ አይደለም” በማለት ብቻ ሳይገደብ “ኢየሱስ ዋናው ጸረ-ሴማዊ
ነው” በሚል እሳቤ ላይ አደረገ።[12] በንቅናቄው ውስጥ የሚሳተፉት ብዙዎች የሂትለር ርእዮት ፕሮፓጋንዳ አባት የሆነውን የዮሴፍ ጎቤልስን (Joseph Goebbels) “ኢየሱስ የመጀመሪያው የአይሁድ ጠላት ነው” የሚለውን ጥሪ የተቀበሉ ነበሩ።[13]
ዘረኝነትን ከእምነታቸው ጋር ለማስማማት ሲባል “የጀርመን ክርስትና” ንቅናቄ አይሁዳዊ የሆነውን የመጽሐፍና የአስተምህሮ ይዘት ሁሉ ከክርስትናቸው ለማጽዳት ሞከሩ። ከዚህ
የተነሣም አንዳንዶቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን ኢቀኖናዊ ናቸው ብለው ሲክዱ[14] ሌሎቹ ደግሞ የብሉይ ኪዳንን ቀኖናዊት ሳይክዱ ጸረ-ሴማዊነታቸውን እንዲደግፍላቸው በማድረግ በራሳቸው መንገድ አመሰቃቅለው ይጽፉትና ይተረጉሙት ነበር። ሌሎች ደግሞ ጸረ-ሴማዊ
አቋማቸውን ለማጠናከር ብሉይ ኪዳንን የሚጠቅስ ጌታ ለአይሁድ እውቅና የሰጠባቸውን የሐዲስ ኪዳንን ጥቅስ ሁሉ እያስወገዱ ወንጌልን እንደ አዲስ ጽፈዋል። [15]
ሴማዊነትን መጥላትንና መጸየፍን ሁሉንም ጀርመናዊ በአንድነት የሚያሰባስብ የጋራ አጀንዳ አደረጉት፡፡ ኦቶ ብሮክልሸን (Otto
Brokelschen) ይህን “የጀርመን ክርስቲያን” አቋም እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡-
“የጀርመን ብሔራዊ የክርስቲያኖች አንድነት ለጀርመን ቤተ ክርስቲያን ባዕድ ናቸው ተብለው የሚታመንባቸውን ማንኛውንም ትምህርትና የአይሁድ የሚመስሉትን ነገሮች ሁሉ ከቤተ ክርስቲያን ጠራርጎ ማጽዳት አንድነትን የሚፈጥር ድል አድርገው ወስደውት ነበር።”[16]
ጀርመናዊ አንድነት መፍጠር በሚል ስም ማንኛውንም ዶግማና አስተምህሮ ሙሉ በሙሉ ተካደ።
“የጀርመን
ክርስቲያኖች” በአይሁድ ላይ ሉተር የነበረውን ጥላቻ በሁሉም ክርስቲያኖች ላይ እንዲኖር እጅግ ከመናፈቃቸው የተነሳ በ1940
ሉተርን ጠቅሰው እንዲህ ሲሉ በእምነት መጻሕፍት ደረጃ አቅጣጫ ይሰጡ ነበር፡- “የአይሁድን ምኩራቦች በያሉበት አቃጥሏቸው፣ በእሳት
ለማቃጠል አስቸጋሪ የሆኑትን ደግሞ ቆሻሻ ከምሩባቸው።”[17]
ያለዚህ ረዥም ታሪካዊ መሠረት “የጀርመን ክርስትና” ንቅናቄ መቆምም መኖርም አይችልም ይሉ ነበር።
በሌላ
በኩል ሂትለር የጥላቻና ዘር የማጥፋት ዝንባሌ መነሻው የፐሮትስታንት መሥራች የሉተር አስተምህሮና ድርጊቶች ነበሩ። ሉተር በዘመኑ
ለሕዝቡ አቅጣጫ ሲሰጥ “አይሁዶችና ውሸቶቻቸው /"On the Jews and
Their Lies" በሚል ርዕስ በ1543 እ.አ አ ጸረ አይሁድና እና ጸረ ሴመቲክ
ጽሑፍ ጽፏል።[18] ሉተር
በጽሑፉ አንዲህ ይላል “የአይሁድ ትምህርት ቤቶቻቸው፥ ምኩራቦቻቸውና የንግድብ ቦታቸው በእሣት መቃጠል አለበት”፥ የፈሎት መጽሐፍቶቻቸው
መውደም ይገባቸዋል፥ ቤቶቻቸውና ያለቸው ሀብት ሁሉ መወረስ አለበት።
ሉተር ለአይሁድ ምንም አይነት ሐዘኔታ፥ የሕግ ከለላና ርኅራኄ ማድረግ አይገባም። እነዚህ
መርዞች አካባቢውን ሁሉ ስለበከሉት ("these
poisonous en”venomed
worms" ) ተጭነው ወደ አስገዳጅ
የጉልበት ሥራ ስፍራ መታቀብ ወይንም ለዘላለም ከዚህ አገር ተጠርገው መባረር አለባቸው። እንዲሁም በአይሁዳውያን
ላይ አልቂት እንዲታወጅ ጥሪሳያቀርብ “እንዚህን በጅምላ መርዞ አለመጨረሳችን የእኛ ስህተት ነው/ "[W]e are at fault
in not slaying them" ይላል
.
ይህ ጽሑፍ ከ500 ዓመታት በኋላ ለተነሳው ሂትለርና ሌሎች
የጸረ አይሁድና ጸረ ሱሜቲክ ንቅናቄዎችን መሠረት ሆኗል። ሂትለር
በተነሳበት ዘመን መጽሐፉ በአስተሳሰቡ ደጋፊዎችና በፓርቲው ዘንድ
በብዛት ተሰራጭቶ ይነበብ ነበር። በ2ኛው ዓለም ጦርነት መጽሐፉ
በሰልፈኞች እጅ ተይዞ ይታይ ነበር፥ ምናልባተም ለአይሁድ እልቂት ዋና ሞተር የሆነው የዚህ የሉተር አስተምህሮ እንደሆነ ይታመናል።[19] ለተጨማሪ ጥናትና ንባብ ---[20]
“የጀርመን
ክርስትና” ኑፋቄያዊ ንቅናቄ ለናዚ ፓርቲ የፕሮቴስታንት ቸርችን ሰብሮ “ናዚያዊ ፕሮቴስታት” በመፍጠር የራሱ ዓላማ ማስፈጸሚያ ማድረጉ
መንገዱን ቀላል አደረገለት። በዚህ ሂደት ራሳቸው ቸርቾቹ ወንጌላውያንና መምህራን ከናዚ ፕሮፓጋንዲስቶች ባልተናነሰ አገልጋይ ሆነው
ተገኙ።
ስለዚህ ለናዚዎች ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት
ከመታገል ይልቅ በመቀየር (ውስጧ ገብቶ በመቆጣጠርና ሪፎርም በማድረግ) መጠቀሙ ትርፋማነቱ ልቆ ተገኘ።[21]
በዚህ ስሌት መሠረትነት ሂትለር የቻንሰለርነት ሥልጣኑን ባገኘ በሰባት ወር ውስጥ ሐምሌ 23፣ 1933 በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አደረገ። ምርጫው የተፈለገው ለናዚ ፓርቲ
ምቹ የሆነች ጀርመናዊት የሬይክ ቸርች (Reichskirche
- Reich Church) ለመመሥረት ነበር። በጥንቃቄ በታቀደ ስልት ምርጫው ለሂትለር ግብ እንዲያገለግል ተደርጎ ተከናወነ። የቦንሆፈር ግለ ታሪክ ጸሐፊ
ኤሪክ ሜታክሳስ (Eric Metaxas) የሂትለርን የቸርች ምርጫ እንደሚከተለው ያጠቃልለዋል፡- “በምርጫው ሂደት ላይ ምንም አይነት አሉታዊ ተጽእኖ ለማሳደር የሚሞክር
ሁሉ በጀርመን ክርስትና ንቅናቄ “በአገር ክህደት” ይከሰሳል። ትርጉም
ያለው ተቃውሞ እንዳይደራጅ የምርጫ ጥሪው በተላለፈበት ቀን እና በምርጫው ዕለት መካከል የነበረው ጊዜ አንድ ሳምንት ብቻ ነበር።”[22] በሂትለር
በተመረጡ ሰዎች አማካይነት ከ28ቱ የፕሮቴስታንት አህጉረ ስብከቶች ከሦስቱ በስተቀር ሁሉም ቸርቾች ከምርጫው በኋላ በናዚ ርእዮትና
መርሆዎች መስመር ገቡ።[23] እዚህ ላይ በአገራችን “ሃይማኖቶቹ ሁሉ ከኦሮሙማ
በታች ናቸው”[24] በሚል የብልጽግና
መንግሥት አሠራር የኦሮሞ፥ የትግራይ ወዘተ የዘር ሲኖዶስ ለመፍጠር ብያኔ ተሰጥቶ ሰው እስኪጨፈጨፍለት የደረሰ ተመሳሳይ ጉዞ መኖሩና
ማስታወስ ለማገናዘብ ይጠቅማል።
የሂትለር እቅድ እንደታሰበው ተሳካ። የጀርመን
ቸርቾች የተዋረዳዊ መዋቅራት አመራር አዲስ በተመረጠው “የጀርመን ክርስትና” መሪዎች እጅ ወደቀ። ከዚያም ዋና ሥራቸው የናዚን ርእዮተ
ዓለም ማስተማር ሆነ። የተለያዩ ሰልፎችና ንግግሮችም ይደረጉ ጀመር፡፡ ከራውስ የተባለ ተናጋሪ “በክርስትና ውስጥ ያለው የአይሁድ
ተጽእኖ ተቀባይነት የለውም”፣ “ብሉይ ኪዳን፣ ሐዋርያ ጳውሎስ፣ የመስቀል
ምልክት ሁሉ በናዚ ርእዮት መሠረት ተቀባይነት የላቸውም”[25] ሲል ሃያ በሺህ
ሰዎች ፊት በአደባባይ ተናገረ።
ክራውስ የጀርመን ክርስትናን ለማስተዋወቅ
ባደረገው ጥረት ጥቃቱ በብሉይ ኪዳን ብቻ ሳይገደብ “ኢየሱስም ቢሆን” [አምላካችን ክብር ምስጋና ይድረሰውና] አለ፡- “ኢየሱስም
ቢሆን ሊገለጽና ሊቀርብ የሚገባው ከብሔራዊ ሶሻሊስት ፓርቲ ፍላጎት አንፃር ነው” አለ።[26]
የኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ክራዑስ “ወደ ጀግናው አርያናዊው ኢየሱስ መመለስ አለብን፣ ጀርመኖች ኢየሱስን ተዋጊ መሪ አድርገው መሳል
ይገባቸዋል” ብሎ መናገሩን ጽፏል።[27]
በንግግሮቹ “የጀርመን ክርስትና” አራማጆች የሞቀ ጭብጨባ ይለግሱት ነበር።[28]
ክርስትና ዘረኞች ለክፉ ዓላማቸው መጠቀሚያ ሊያደርጉት ሲሞክሩ ምን ሊመስል እንደሚችል የክራዑስ ገለጻ አሳይቷል።
የተመረጡት አዳዲሶቹ “የጀርመን ክርስትና” መሪዎች አርያን ያልሆኑ ዝርያዎችን ከየመሥሪያ
ቤቶች የማስወገዱን አሠራር በቤተ ክርስቲያንም ተገበሩት።[29] የመጀመሪያው የአርያን አንቀጽ “ዝርያው አርያን ያልሆነ ወይንም
አርያን ካልሆነ ሰው ጋር የተጋባ ሰው ካህን አይባልም”[30]
ይላል።
ከዚያም ስዋስቲካን አንግበው የናዚን ፍላጎት
የሚያስፈጽሙ “የጀርመን ክርስቲያኖች” የፕሮቴስታንት ቸርች ውስጥ ተልእኮ ይዘው በመግባት የናዚ ርእዮት መምህራን ሆነው በመስቀሉ
ጀርባ ተደብቅው በክርስቶስ ፈንታ ለሂትለር ታማኝ ስለ መሆንና ለጀርመን ዝርያ ልዩነት ስለ መቆም፣ ዘረኝነትንና ጥላቻን አበክረው
እንዲሰብኩ ይደረጉ ነበር።
የጀርመን ብሔራዊ ሶሻሊስት ፓርቲን ክርስትናን
የማጥፋት እቅድ ፊት ለፊት ቆመው የሚዋጉ አያሌ ጀርመናዊ ክርስቲያኖች ነበሩ። የጀርመን ፓስተሮችና ክርስቲያኖች ቡድን በአንድነት
ሆነው በዘርና በብሔር ላይ ያተኮረውን “የጀርመን ክርስትና” ንቅናቄ ተቃውመዋል። ከእነዚህ ተቃዋሚዎች መካከል አንዱ ዲይትሪች ቦንሆፈር
ነው። የናዚን ሥርዓት የተቃወሙ ብዙዎች ሰዎች ቢኖሩም ቦንሆፈር የተቃውሞው ምልክት ሆኖ ወጣ። ቦንሆፈር የአርያን አንቀጽን የሚቀበል
ክርስቲያን ሁሉ ከእውነተኛ ክርስትና የተለየና የሐሰት ክርስትና የሚከተል መሆኑን በኃይልና በቁጣ ያስተምር ነበር። በእንዲህ ዓይነት
ጊዜ እውነተኛውን ክርስትና ለመጠበቅ ሲባል መሰደድና ከእነዚህ መናፍቃን መለየት እንደሚገባም በአጽንኦት አስተምሯል።[31]
ለአርያን
አንቀጽ መታወጅን ምላሽ የፓስተሮች የአደጋ ጊዜ ሊግ (Pastor’s
Emergency League) ተመሠረተ።[32]
የንቅናቄው መሪ የነበረ ፓስተር ማርቲን ኒሞለር (Martin Niemoller) የጀርመን ቤተ ክርስቲያንን ናዚፊኬሽን
ይቃወም ነበር። ከዚህ ንቅናቄ ውስጥ የኮንፌሲንግ ቸርች ተወለደ። ቢያንስ
ግማሽ ያህሉ የጀርመን ቸርች የናዚን መስመር የማስገባት (Gleichschaltung) ዶክትሪን ተቃውመዋል። ሰነዱ ሲነበብ
የተቃውሞው መንፈስ በቃላቶቹ ግልጽ ይሆናል።
ቦንሆፈር
የጀርመን አዋጅን “የደቀ መዛሙርትነት ዋጋ” (The
Cost of Discipleship) በሚለው መጽሐፉ
ውስጥ ሲገልጸው “ቤተ ክርስቲያን እንደ ብሉይ ኪዳን እስራኤል ብሔራዊ አንድነት ልትፈጥር የተሠራች ሳትሆን ከፖለቲካና አገር
አጥር ውጭ የሆነች የአማኞች አንድነት ናት” ብሏል፡፡[33]
በመጨረሻም ቦንሆፈርና ሌሎች ናዚን የተቃወሙ ሕይወታቸውን በመሥዋዕትነት ከፍለዋል።
ከ1933-1945 ናዚዎች የፈጠሩት “የጀርመን ክርስትና” በአንድ በኩል፣ ነባሩ
ፕሮቴስታንት ክርስትና (ኮንፌሲንግ ቸርች) ደግሞ በሌላ በኩል ያደረጉት ትግል ከባድና መራር ነበር፡፡ በ1945 ጀርመን በጦርነት ስትሸነፍ ፋሺዝም
ፈጥሮት የነበረው “የጀርመን ክርስትናም” አብሮ ተሸነፈ፡፡ ኮንፌሲንግ ቸርች ደግሞ አሸናፊ ሆነ። ለኑፋቄው ንቅናቄ የሕጋዊነት ሽፋንና
ሁለገብ ድጋፍ ሲሰጥ የነበረው የናዚ ፓርቲ ሲወድቅ አጋፋሪዎቹ አፋቸው ተዘጋ፣ ተበተኑም።
“የጀርመን ክርስትና” ንቅናቄ እምነት በመንግሥታት
ተስፋ ሰጭነት፣ በዘረኝነትና በብሔርተኝነት ጉዳይ ሲታወር ምን እንደሚከተል ጥሩ ማስተማሪያ ሆኖ አልፏል። ይህን የኑፋቄ
ጠባሳ የጀርመን ክርስቲያኖች የሚዘክሩት የክህደት ሁሉ ቁንጮ አድርገው ነው። “የጀርመን ክርስትና” ንቅናቄ ክርስቲያኑን
ከድባቴ በመቀስቀስ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።
የአገራችን አሁናዊ ሁኔታ በጀርመን ከተፈጸመው አንጻር ሲቃኝ ምን ይመስላል?
አሁን በአገራችን ያለው ሁኔታ በጀርመን አገር
በናዚ ፓርቲ የተደረገውን የሚመስል ሆኖ ይታያል፡፡ አሁን በአገራችን በበተለይም ደግሞ ሁሉም የፓለቲካ ፓርቲና ነጻ አውጪ የራሱን ክርስትና እየፈጠረ ነው። የኦፒዲኦ እና የህወሀት በኦሮሚያና
በትግራይ ቤተ ክህነት አቀንቃኞች ዝንባሌ ውስጥ ልዩ ኑፋቄ ተወልዷል። ክርስትናውን ለዘረኛ ፖለቲካ መገልገያነት የማመቻቸት ግብ
ይዞ በመነሣት፣ የናዚ ጀርመን የፈጠረውን “የጀርመን ክርስትና” ዓይነት የብሔር ክርስትና (የኦሮሞ፣ የትግሬ፣ የሲዳማ ወዘተ) በሚል
ለንዑስ ፖለቲካ-ወለድ ማንነት የሚመች ኑፋቄያዊ “ክርስትና” ለመፍጠር እየተሠራ ነው፡፡ ኦርቶዶክስን ለየብሔረሰቡ ፖለቲካ ለማስማማት ጥረት
እየተደረገ ነው።
ወያኔ ትግራዋይነት ከኦርቶዶክሳዊነት የበለጠ እንዲመስል ተግቶ አስተማረ፣ ፖሊሲያዊ እርምጃዎችንም
ወሰደ። ኦሮሙማ የተባለ የብሔር ፖለቲካ ፅንሰ ሐሳብም ኦርቶዶክስን ለማጥፋት በቋንቋና በተለያዩ በሐሰት የተፈጠሩ ትርክቶችን በመናኘት
ኦርቶዶክስን ከኦሮሞነት ለመነጠል እየሠራ ነው። በዚህ ሂደት በብሔር ፖለቲካ የተጠለፉ ሰባክያንና ጳጳሳትን አጀንዳ አሸክሞ ቤተ
ክርስቲያን ውስጥ በማስገባት እንደ “የጀርመን ክርስትና” ያለ “የኦሮሚያ ክርስትና” ለመፍጠር እየታገለ ነው።
የኦሮሞ
ፖለቲከኞች ኦሮሞን ለማስተባበር፣ የትግራይ ፖለቲከኞች ትግሬን ለማስተባበር፣ ሌሎች ብሔር ተኮር ፖለቲከኞችም ብሔራቸውን እነርሱ
በፈጠሩት አዲስ መንገድ ዐይኑን ጨፍኖ እንዲከተላቸው ለማድረግ ዘመናትን የተሻገረችና ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብር ኦርቶዶክሳዊት
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በጠላትነት ፈርጀዋታል። ከዚህ የተነሣም የኦርቶዶክስ ክርስትና በደርግ፣ በኢሕአዴግ እና በብልጽግና ዘመነ
መንግሥት በየወቅቱ ከተቀነቀኑ የፖለቲካ ትርክቶች ጋር እንድትጣጣም አለዚያ ግን እንድትጠፋ ተፈርዶባታል። ደርግ “አብዮታዊ ወንጌል”፣
በኢሕዴግ/ብልፅግና የብሔር ቤተ ክህነትና ጎሳ ተኮር የሆነ ቅይጥ እምነት እንዲጠናከር ተሠርቷል።
ወያኔም
ሆነ የኦሮሞሙማ ብልፅግና ሁለቱም ቤተ ክርስቲያንን ለፖለቲካቸው ርእዮት ተገዥና አገልጋይ ለማድረግ ታግለዋል፣ እየታገሉም ነው።
ይህን መንፈሳቸውን ወደ ሌሎች ብሔረሰብ ድርጅቶች በማጋባት በሲዳማ፣ በደቡብ ብሔረሰቦችም ላይ ለመጫን እየሠሩ ብቻ ሳይሆን ይህን
የሚቃወሙ የቤተ ክርስቲያን ካህናትን ከማሳደድ እስከ መግደል ተራምደዋል።
ጀርመን
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተሸነፈች በኋላ ከጦር ወንጀል ተጠያቂነት አምልጠው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ አንዳንድ “የጀርመን ክርስትና”
አቀንቃኞችና ፋሽስቶች በወለጋና መሰል አካባቢዎች ውስጥ ተሸሽገው በአገራቸው ሞክረው የከሸፈውን ጸረ-ኦርቶዶክስነትና ጸረ-ሴማዊነት
አሳቤ ኢትዮጵያውያንን በማሠልጠን ዛሬ የምናየውን አደገኛ ፍሬ አፍርተዋል፡፡
በማርክሲስት
የተማሪ ንቅናቄ የተቀጣጠለውን ጸረ-ዘውድ ንቅናቄ ወደ ጸረ-አማራና ጸረ-ኦርቶዶክስ አሻግረውት ከ40 ዓመታት በላይ ከተራመደ በኋላ
የጀርመን ናዚን አስተምህሮ ተውሶ የኩሽ ፕሮጄክት በሚል ወደ ጸረ-ሴማዊነት አደገ።
በዚህ
መንገድ ተወልዶ ያደገው የኦሮሙማ እንቅስቃሴ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከምና ከኦሮሚያ ለማስወገድ ለኦሮሙማ የሚስማማ
ልክ እንደ “ጀርመን ክርስትና” ያለ “ኦሮማዊ ኦርቶዶክስ” ለመፍጠር እየሠራ ነው፡፡ ይህ ተልእኮ አቅም አንዲያገኝ ደግሞ የጣዖት
አምልኮንና ባህልን አይነኬና የማይቀየሩ በማስመሰል የፖለቲካው አካል አድርጎ ይሠራል።
ኦርቶዶክሳዊነትና ኦሮማዊ ለማድረግ (Oromizing
Orthodoxy) እምነቱን ለመግለጥ በግእዝና በአማርኛ የተጻፉ መጻሕፍትን አዲሱ የኦሮሞ ትውልድ እንዳያነባቸውና እውነቱን እንዳይረዳ
የላቲን ፊደልን በፖለቲካና በእምነት ደረጃ አስገዳጅ አድርጎ ፊደል-ጠል ትውልድ በመፍጠር፣ የባህል ማዕከላትን በመመሥረት የኦርቶዶክስ
ኦሮሞ ባህሎችና ቅርሶች ፈጽመው እንዳይታዩበት ኦሮሞን ከኦርቶዶክሳዊ ባህሉና ትውፊቱ ለመለየት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው።
በናዚ
ጀርመን ጊዜ ሴማዊነትን መጥላት የትግል ማቀጣጠያ እንደነበረ ሁሉ እዚህም “ኩሽ” የሆነ እና ያልሆነ የሚል ጎራ ለመፍጠር ተሠርቷል።
በጸረ-ሴማዊነት አንፃር ጸረ-ኦርቶዶክስ ክርስትናና ጸረ-አማራ ብሔረሰብን የትግል ማቀጣጠያ አድርገዋቸዋል።
ልክ
እንደ “ጀርመን ክርስትና” ሁሉ የኦሮሞ አክራሪ ብሔርተኞች ፖለቲካም ኦርቶዶክሳዊያንን በጎሣ መስመር ከፋፍሎ ለማጥፋት እንዲመቸው
ካህናትን በዘር፣ ጸሎት ቤትን በቋንቋና በጎሣ ከፋፍሎ የማዳከም፣ የክህነት አገልግሎትን በዘር የማጽዳት ሥራ ይሠራል። ጀዋር መሐመድ ኦሮሞ በአማራ ቤተ ክርስቲያንና መስጊድ አንዳይሰግድ መክሯል። በአዳማ
በኦፌኮ ጉባኤ ኦሮሞ ከሌላ እንዳይጋባና የዘር ንጽሕና እንዲጠብቅ የናዚን የኑረምበርግ ዐዋጅ የመሰለ ሐሳብ በአንዲት የፓርቲው ጉባኤ
ተሳታፊ ተሰብኮ በቴሌቪዠን ተሰራጭቷል። በባሌ ሮቤ ሕዝብ ተሰብስቦ በአካባቢ የፖለቲካና የአክራሪ ኢስላም መሪ የባሌ ሕዝብ ከመካከሉ
ለነፍጠኛ (ለአማራ ኦርቶዶክስ፣ ለኦሮሞ ኦርቶዶክስ)፣ ለዶርዜ፣ ለጉራጌና ለሌሎች ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች የንግድና የመኖሪያ
ቤት አንዳያከራዩዋቸው፣ የተከራዩትንም አንዲያስለቅቁ በአደበባይ ሕዝብ በተሰበሰበበት ጥሪ ቀርቧል።
እንደ
“ጀርመን ክርስትና” የፋሺስት ዘረኞች በእኛ አገር ያሉትም ዘራችን የሚሉት ነገር ከእምነቱ በልጦባቸዋል። ብሔርተኝነት ከክርስቶስ
መስቀል በላይ እንዲታሰብና ቋንቋ ከኦርቶዶክሳዊነት የበለጠ ማንነት ያለው አስመስሎ መስበክና መሥራት የዚህ ሂደት ውጤትና ማሳያ
ነው፡፡ ይህ ዝንባሌ ከባህልና ከታሪክ የሚስበው ክር ቢኖረውም የውጭ ቅኝ
ገዥዎች በተለይ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ እንግሊዝና ግብጽ የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው።
የማንነት ፖለቲካን ከርትዕት የክርስትና ሃይማኖት በላይ ከፍ አድርገው ለማንበር
የሚሞክሩ እነዚህ የአገራችን የቋንቋ አምላኪ ብሔርተኞች ከክርስቶስ ትምህርት ይልቅ የእኛ ማንነትና ባህል ይበልጣል እስከ ማለት
ደርሰዋል። ለዚህ አስተሳሰባቸው እንዲስማማ ለምሳሌ የኩሽ ፐሮጄክት አራማጅ የኦሮሞ ልሒቃን መጽሐፍ ቅዱስን ቀይረው እስከ መጻፍ
ተራምደዋል። ይህን የፈጸሙት ፓስተር ዶ/ር በንቲ ኡጁሉ በጀርመን የነገረ መለኮት ትምህርት ቤት የተማሩ ናቸው፡፡ ይህን
የሚያደርጉት ከ185 ዓመታት በፊት በንጉሥ ሣሕለ ሥላሴ ከኢትዮጵያ የተባረሩት ጀርመናዊ ሰላይ የጆሃን ሉድዊግ አኒክራምፍ የጀመሩት
ለዘረኝነት የተመቸ ጀርመን ሠራሽ ሉተራዊ “ክርስትና” በኦሮሙማ ስም መልሶ ለመትከል አስፈላጊ ነው ብለው ስላመኑ ነው። የኩሽ ፕሮጄክት
ደጋፊው ፓስተርና መሪዎቹ የማንነት ፖለቲካ አራማጆች የአንድ የፖለቲካ ርእዮትን ግብ ለመሳካት በክርስትና ስም የሚራመደው ልዩ ብሔረሰብነት
የመፍጠር
ቅዠት በጀርመን ተሞክሮ የወደቀና ዓለምን
ከፍተኛ ዋጋ ያስከፈለ እንደነበር መማር አልቻሉም።
በናዚ ጀርመን የተፈጠረው “ክርስትና” ጸረ-ሴም እንደነበረው ሁሉ በብሔር ፖለቲካ የሚፈጠር የእምነት
ቡድን “ሌላ” የሚለውን ሁሉ ጠላቱ ያደርጋል። ለጊዜው “ነፍጠኛ” በሚል ኮድ ሥር አማራ የጥላቻው ዒላማ ተደርጎ ተወስዷል። ይህ
ኮድ የበለጠ አንዲደምቅና ሌሎች የቋንቋ ብሔረሰቦችን በማሰባሰብ ለሚቀጥለው የዘር ጥፋት እንዲንደረደር በግብፃዊው ጸረ-ሴሜቲክና
ጸረ-ክርስትና ፕሮፌሰር ሙሀመድ ሸምሰዲን ሜጋሎማቲስ (Muhammad
Shamsaddin Megalommatis) የሐሰት “ምርምር” እና በጀርመኖቹ አማካሪነት በዶክተር በንቲ ቴሶ ኡጁሉ ተርጓሚነት የኩሽ እና የሴም ትርክት ተጨመረለት።
በብሔር ፖለቲካ እየተፈጠረ ያለው ክርስትና ራሱን ከክርስቶሳዊ ማንነቱ እያወጣ በፖለቲካዊ፣ ቋንቋና የተለያዩ ትርክቶች በሚያመጡት
የተዛባ አስተሳሰብ “ሌሎች” ብሎ የሚፈርጃቸውን በመጥላት ዘረኝነትን ያራምዳል። ቅድመ ክርስትና የነበሩ የማኅበረሰብ ግጭቶችንና
አረማዊ የጭካኔ ጠባያትን እያወደሰ ወደ ኢክርስቲያናዊ ግብር ይንደረደራል።
የብሔር
ፖለቲካ ያ ብሔረሰብ በጋር የሚጠላውና ሊያሸንፈው የሚገባው አንድ ጠላት ብሔረሰብ ያስፈልገዋል። ስለዚህም ከዳርዊን የዝግመተ ለውጥ
የሥነ ፍጥረት አመጣጥ አስተምህሮ የሚመነጭ ማኅበራዊ ዳርዊናዊነት፣ እንዲሁም ከማርክሲዝም በፈለቀው የጨቋኝ ተጨቋኝ ፖለቲካዊ ርእዮት
መሠረት “ነፍጠኛ፣ አማራ፣ ኦርቶዶክስ” የሚባሉ ጠላቶችን ፈጠሩ። ይህ መለያየትና ጥላቻ አንዲስፋፋ ኩሽ እና ሴም የሚባል አጥር
ሠርተው ተጨቁነናል የሚሉ ሌሎች ብሔረሰቦችን በተለይ ኦርቶዶክስ ያልሆኑትን ማስተባበርና ለዚህም ትርክት ግብፃውያን ኢትዮጵያን ለማዳከም
የፃፏቸውን አያሌ በምርምር ስም ስለ ኑቢያ የተተረኩ የእነ ፕሮፌሰር መሀመድ ሸምሰዲን መጠቀም እንደ አንድ ስልት ይዘውታል። በተጨማሪ
በካናዳ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ሰዊድን፣ ኖርዌይና ጀርመን የሚኖሩ የብሔር ፖለቲካ ለመሰደድና መማር እድል የሰጣቸውን በምዕራባውያን የዘረኝነት
ማኅበራዊና ሥነ-ሰብእ ሳይንስ፣ በፖለቲካና ሥነ-ሰብእ ዶክተር ፕሮፌሰር የተሰኙ ሰዎች የሚፈበርኳቸውን ትርክቶች አገጣጥሞ ጸረ-ኦርቶዶክስ፣
ጸረ-አማራ ትውልድ ማጠናከር በሚል በግልጽ እየተሠራበት ነው።
ለምሳሌ ቄስ በላይ መኮንን “የሚኒሊክ ተፈናቃዮችና ለማኞች” ሲሉ ቄስ ሳሙኤል ብርሃኑ “አንድም
ክርስቶስን ብሎ የሞተ የለም፣ በኦሮሚያ የሚያልቀው እምዬ ምኒልክ እያለ ነው” በማለት የዘመኑን የንዑስ-ማንነት ፖለቲካ ከክርስትና
ማንነታቸው አስበልጠው ታይተዋል። የንዚህ ሰዎች ክርስትና
ከክርስቶስ ያለመሆኑን የሚያሳየው እነሱ እንደሚሉ የሚኒሊክ ክስ ቢሆን
እንኳን ግድል፣ እረድ፣ ጨርስ የሚል የክርስቶስ ትምህርት በኦርቶዶክስም የለም። ይህ የመጣው ፕሮፌሰር ከማርቲን ሉተር ይሁዳዎችን
ጨርሱ፣ ቤተ እምነታቸውን አቃጥሉ፣ ልጆቻቸውን ግድብ ብሎ ከጻፈው የሰይጣን አስተምህሮ ነው።
በላይ መኮንን ከ86 በላይ ኦርቶዶክሳዊያን የተጨፈጨፉበትን የጀዋር መሐመድ የድረሱልኝ ጥሪ ተከትለው
የሞቱትን ክርስቲያኖች ከማጽናናት ይልቅ የግጭት ምክንያት የሆነውን ሙስሊም በቋንቋ ዝምድናቸው አስበልጠው በማግስቱ አጋርነታቸውን
ለመግለጽ ቤቱ ድረስ ሄደዋል። ይህ የሚያመለክተው “እኛና እነርሱ” በሚለው ፖለቲካ ወጥመድ ውስጥ መውደቃቸውንና ክርስቶስን ጥለው ጎሳን ማምለካቸው ነው። ፩ ዮሐንስ 4:20 ላይ የእግዚአብሔር ቃል እንደተጻፈው “የሚያየውን ወንድሙን የልወደደ
ያላየውን እግዚአብሔርን እንዴት ይወዳል?” እነዚህ የኦኦፒዲኦ ጳጳሳት ሊያጠምቁ፣ ሊያቆርቡ፣ እግዚአብሔር ይፍታህ ለማለት የተሾሙ
ካህናት ድንቅ አይተው ፈርጀው ግድያን የሚደግፍ ከሳጥናኤል እንጂ ከክርስቶስ ጋር ምን አይነት ህብረት ይኖራቸዋል። የምምእመናን በጅምላ በመፍጀትና ኦርቶዶክሳውያን የሚበዙባቸው ከተሞችን አሰፋፈር ለመቀየር የተቻለውን ሁሉ ተንኮል በመፈጸም
ጥቃቱ በስፋት እየተካሄደ ነው፡፡
የክርስቶስ ትምህርት ወደ ሮሜ ሰዎች 16:17 “ወንድሞቻችን ሆይ፣ እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት የሚቃወሙትን፣ መለያየትንና ማሰናክፕያን የሚያደርጉትን እንድታውቁዋቸው ማማዳችኃለሁ፣ ከእነሱ ትለዩ፣ነርሱ ለጌታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ያይደልፕ ለሆዳቸው ይገዛሉ፣ በነገር ማታለልና በማለዛዘብ የብዙዎች የዋሃንን ልብ ያስታሉ” በማለት መከፋፈል የክርስቶስ ትምህርት ያለመሆኑን
የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ሮሜ ሰዎች ያስጠነቅቃል።
ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች ፩ ም ፲፪: ፲፪-፲፫
ደግሞ “አካል አንድ እንደ ሆነ ብዙ የአካል ክፍሎችም እንዳሉት ሁሉ ብዙዎችሳሉ አንድ አካል አንድ ሆኑ ክርስቶስ ደግሞ እንዲህ
ነውና እኛ ሁላችንም በአንድ መንፈስ አንድ አካል ለመሆንተጠምቀናል፣ አይሁድብንሆን፣ አረማውያንብንሆን፣ባርይልዎችም ብንሆን ፣ ነጻዎችምብንሆን
ሁላችንም አንድ መንፈስን ጠጥተናልና። ይላል።
በክርስቶስ የሆነ አንድንትን እንዲ ልዩነትን አይሰብክም። የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
ም ፲ “አንድሞቻችን! አንድ ቃል እንድትናገሩ፣ እንዳታዝኑ፣ ፍጹማንም እንድትሆኑ ሁላችሁንም፣- በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ስም
እማለዳችኃለሁ፣ እንዳትለያዩ አንድ ልብና አንድ አሳብ ሆናችሁ ኑሩ። ብሎ ይመክራል። ታድያ የትኛው የእየሱስ ክርስቶስ አስተምህሮ
ነው በየቋንቋችሁ፣ በየ ብሄራችሁ፣ በየ ጎሳችሁ ተከፋፈሉ የሚለው። ዛሬ የኦሮሞ፣ የትግራይ፣ የሲዳማ ክርስቲያን ተብሎ ተከፋፍሎ
ገነትም ሲገባ የኦሮሞ ክልል የትግሬ መንደር የልምምና ከአማራ ጋር አንጸድቅም እንውጣ ሊሉ ይሆን። ለዚህ ነው ይህ የብሄር ክርስትና
የመድሀኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን ምእመናንን ከፋፍሎ በይቅርታ ሳይሆን በጥላቻ ልብን መርዝ ለገሀነም የሚያዘጋጅ
ይፋ መንፈስ ነው።
ለዚህ ነው የክርስቶስ ልጆች አትከፋፍሉ የምንለው።
የኦሮምያ የትግሬ የአማራ መንግሥተ ሰማያት አልተፈጠረም። በክርስቶስ በአንድ ሀይማኖት በአንድ ጥምቀት አንድ አድርጎናልና። አድርጎናልና።
የጥላቻ፣ የመከፋፈል የኑፋቄ አስተምህሮ
በዚህ ሂደትም የቀደምት አበው ክርስቲያናዊ አሻራን
ለአካባቢና ለብሔር የመሰጠት ፖለቲካ፣ ቅዱሳንን ሳይቀር ለብሔር ለማከፋፈል የሚሞክሩ ፖለቲከኞች ተፈጥረዋል፡፡ የዚህ ኑፋቄ ሰለባ
የሆኑ መምህራንና ካህናት አቡነ ጴጥሮስ የዓለም ስሙ አንደዚህ ስለሆነ ኦሮሞ ነው እያሉ ቅዱሳንን በመንደራቸው ሊደለድሉ ሞክረዋል፡፡
አንዱ የፕሮቴስታንት ፓስተር ቅዱስ ያሬድ ኦሮሞ ነው በማለት ፖለቲካው ባሸከመው የአእምሮው ሚዛን ልክ ቅዱሱን ማኅሌታይ የሰፈሩ
ዘማሪ ለማድረግ ሞክሯል፡፡ ሌላኛው የፖለቲካ ሎሌ ደግሞ ማሸብሸብ የአማራ ነው ሲል ሰብኳል። ጀርመኖች ያደሩበት አንደኛው ፓስተር
ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ መጥፋት አለበት ብሎ ኩሽ እያለ ቀይሯል። አንዳንድ የዘር ፖለቲካ አገልጋይ ካህናትና መምህራን
በያሬዳዊ ዜማ መቀደስ አያስፈልገንም በማለት ቅዳሴውን ፖለቲካውን በሚያስደስት መንገድ ለማካሄድ ተዳፍረዋል። የመድኀኔ ዐለምን ስም፣
የታቦታቱን ስያሜ ሁሉ ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ በመቀየር ፖለቲካው የገነባው የማንነት ግድግዳ ለማጠናከር የሚሠሩ “ቁሶችና ጳጳሳት” ታይተዋል።
እነ አቶ ጁሐር መሐመድ ከአማራ ቤተ መቅደስ ውጡና የራሳችሁን የጸሎት ቤት ፍጠሩ
በማለት ለእያንዳንዱ የማንነት ፖለቲካ የራሱ እግዚአብሔርና የአምልኮ ቦታ፣ ሥርዓትና አስተምህሮ እንዲፈጥር ተናግረዋል። ከእውነተኛው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምህሮ ያፈነገጠ አዲስ በፖለቲከኞች ልኬት የሚሠራ የአምልኮ ሥርዓት
ለኦሮሞ ኦርቶዶክስ ማበጀቱን በፕሮጄክት ደረጃ ተያይዘውታል።
የብሔር
ፖለቲከኞች የብሔራቸውን አንድነት ለማጠናከር የኦርቶዶክስ ዶግማንና ቀኖናን እስካልተመቻቸው ድረስ ለመደለዝ መድፈራቸው፣ ከጀርመኖች
ጋር በመተባበር መጽሐፍ ቅዱስን መቀያየራቸው፣ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን በቋንቋ ማንነት እየለዩ ማሳደድና መግደላቸው
የዚህ በጀርመን አገር በፋሺስቶች ተሞክሮ የነበረው ዘመቻ ግልባጭ ነው። የኦርቶዶክሳውያንን ኢኮኖሚና አሰፋፈር ለመቀየር ግድያ፣
ንብረት ማውደም፣ ማፈናቀልና የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ካህናት ሳይቀሩ መሳተፋቸው፤ ንቅንቄው ወደ ከፍተኛ ናዚ-መሰል ዘረኝነት የተጠጋ
መሆኑን ይመሰክራል። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በፖለቲካ ጣልቃ ገብነትና በፖለቲካው በሚደገፉ መናፍቃን እና በኦርቶዶክሳዊያን መካከል
እየተካሔደ ያለው ትግል ከፍተኛ ነው። የዚህ ትግል ውጤት የኢትዮጵያን የወደፊት ህልውና ይበይናል።
የዩክሬይን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን
የዩክሬይን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በ1686
ዓ.ም. ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር ተዋሕዳ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ
ክርስቲያን መንበር ሥር እንድትተዳደር ኦርቶዶክሳዊ ቀኖናን በጠበቀ ሁኔታ ተደርጋለች፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በመላው የምስራቅ
ኦርቶዶክስ ዘንድ የዩክሬይን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የሚያውቋት የሞስኮ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አካል እንደሆነች
ነው፡፡
ይህ በሆነበት ሁኔታ ላይ በ2018 ላይ የቁስጥንጥንያው ፓትርያርክ በርተሎሜዎስ የምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትን
ሳያማክሩና ጉባኤ ሳይጠሩ፣ በተለያዩ ጂዖ-ፖለቲካዊና ጂዖ-ስትራቴጂያዊ ግፊቶችና ፍላጎቶች የተነሣ በራሳቸው ግላዊ ውሳኔ ብቻ የዩክሬይን
ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ከሩሲያ መንበር ነጥለው ራሷን የቻለች ናት (Autocephalous) ብለው ዐወጁ፡፡ የዩክሬይን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የሰጧት ደግሞ ቀደም
ብለው በውግዘት ለተለዩ ሁለት አንጃዎች ነበር፤ እነርሱም፡-
1) “የዩክሬይን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የኪየቭ ፓትርያርኬት” የተባለና ከሩሲያ
መንበር ኢቀኖናዊ በሆነ መንገድ ራሱን የገነጠለ፣ ቀድሞ ከክህነቱ ተሽሮና ተወግዞ በነበረ የቀድሞው የኪየቭ ሜጥሮጶሊስ በነበረው
በመነኩሴው ፊላሬት ዴኒሴንኮ የሚመራ ቡድን፤ እና
2) “የዩከሬይን ራሱን የቻለ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን” የሚባል፣ መቃሪ ማሌቲች
በተባለ ቀደም ሲል ከሩሲያ ቤተ ክርስቲያን ተወግዞ በተለየና ክህነቱ በተቀማ ግለሰብ የሚመራ ቡድን ናቸው፡፡ ይህን ግለሰብ ኢቀኖናዊ
በሆነ መንገድ የውሸት “ጳጳስ” አድርጎ የሾመው ደግሞ ቪክቶር-ቪታሊ-ቼካሊን የተባለ መጀመሪያ የፕሮቴስታንት ፓስተር የነበረ፣ ኋላ
ኦርቶዶክስ ሆኛለሁ ያለ፣ ከዚያም ጳጳስ ነኝ ያለ፣ በመጨረሻም በከባድ ነውር ተፈርዶበት ከአገልግሎት እንዲወርድ የተደረገና
በአውስትራሊያ አገር በሕግ ጤነኛ አይደለም ተብሎ የተፈረደበት ግለሰብ ነው፡፡[34]
ይህ መቃሪ ማሌቲች የተባለው ሰው ምንም ዐይነት ቀኖናዊ ክህነት ያልተቀበለ
ቢሆንም ራሱን “የኪየቭ እና የመላዋ ዩክሬይን ሜጥሮጶሊስ ነኝ” ይላል፡፡ ይህ ሰው በ1920ዎቹ የሩሲያን ቤተ ክርስቲያን እናድሳለን በሚል በሶቪየቶች የተፈጠረውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ
ያራምዱ ከነበሩ ሰዎች ግንኙነት የነበረውና ተልእኳቸውን በ1980ዎቹ ለማንቀሳቀስ ይሞክር የነበረ ሰው ነው፡፡ ክህነት ተቀብያለሁ የሚለው
ከእነዚህ የተሐድሶ አራማጆች ነው፡፡
የቁስጥንጥንያው ፓትርያርክ በርተሎሜዎስ በተለያዩ ምክንያቶች የዩክሬይንን ቤተ
ክርስቲያን ከሩሲያ ገንጥለው ለእነዚህ በሃይማኖትም በቀኖናም ብዙ ችግር ላለባቸው ግለሰቦች ሰጥቻለሁ ብለዋል፡፡ ድርጊታው ፍጹም
ኢቀኖናዊና ኢኦርቶዶክሳዊ ነው፡፡ የተወገዙ፣ ከክህነታቸው የተሻሩና ራሳቸውን በራሳቸው የሾሙ ግለሰቦችን በደብዳቤያቸው ብቻ ይህ
ሁሉ ነገር ይወገድ ይመስል በተወገዘው በፊላሬት ዴኒሴንኮ ተሹሜያለሁ የሚለውን ኤጲፋኒ ዱሜንኮ የተባለውን ግለሰብ የመላዋ
ዩክሬይን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አድርጌያለሁ አሉ፡፡ በዩክሬይን ያሉት አብዛኞቹን ኦርቶዶክሳውያን ያሉበት ቀኖናዊው
የኪየቭና የመላዋ ዩክሬይን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሜጥሮጶሊስ የሆነውን ዖኑፍሪን ግን ከመንበሩ እንዲወርድና እንዲሳደድ ለማድረግ
ሞክረዋል፡፡
ይህን የቁስጥንጥንያውን ፓትርያርክ ግለሰባዊ ውሳኔ አብዛኞቹ የምስራቅ ኦርቶዶክስ
አብያተ ክርስቲያናት አልተቀበሉትም፡፡ ዐላማው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ከእናቷ ከሩሲያ በመነጠል ለማዳከምና በዩክሬይን
እየሆነ ላለው ጂዖ-ፖለቲካዊ ተልእኮ መጠቀሚያ ለማድረግ የታሰበ መሆኑ ግልጽ ነውና፡፡ ናዚዎች በጀርመን እንዳደረጉት ሁሉ
አሁንም “ሌላኛው ዐለም” በዩክሬይን ኦርቶዶክስ ላይ ለራሱ ዐላማ አገልጋይ የሆነች “ቤተ ክርስቲያን” ለመፍጠር በመሥራት ላይ
ነው፡፡
አሁን ዩክሬይን በዚህ አሳዛኝ ሁኔታ ላይ ናት፡፡ አብዛኛው ኦርቶዶክሳዊ
ክርስቲያን በሥሯ ያለው ቀኖናዊው በሞስኮ ፓትርያርኬት ሥር ያለው ነው፡፡ ሆኖም “በዘመዳችን” ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት
የሚዘወረውና ፕሬዚደንቱ አይሁዳዊ የሆነው የዩክሬይን መንግሥት ቀኖናዊውን የዬክሬይን ሲኖዶስና ቤተ ክርስቲያን ኢቀኖናዊ
በሆነውና በተወገዙ ግለሰቦች በሚመራው አዲስ ሲኖዶስ ሥር ካልሆናችሁ በማለት ገዳማትንና አብያተ ክርስቲያናትን በመውረርና ብዙ
ግፎችን በመፈጸም፣ ምእመናንና ካህናት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይሄዱ ጫና በመፍጠር፣ . . . ብዙ ፈተና እያደረሱባቸው
ነው፡፡ ዛሬ የምዕራቡ ዐለም ይህን አጋጣሚ መጠቀምና በመጨረሻም ኦርቶዶክሳውያን አማኞችን በማስፈራራና በማጥፋት
ኦርቶዶክሳዊነትን ከዩክሬይን ለማጥፋት በርብርብ ላይ ነው፡፡
ሊዮኒድ ሬሽትኒኮቭ፣ የሩሲያ ስትራቴጂክ ምርምር ተቋም ዳይሬክተር ይህን
በተመለከተ እንዲህ ብሏል፡-
“በኦርቶዶክሳዊው ዐለም ውስጥ ግጭቶችን ማነሳሳትና ማበረታታት እስካሁን ድረስ የአሜሪካ
ተግባር ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በዚህ ሂደት የዩክሬይን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ከሩሲያ አርቶዶክስ እንድትነጠልና ራሷን የቻለች
እንድትሆን አድርገዋል፡፡ . . . ኦርቶዶክሳዊነትን ከዩክሬይን ጨርሶ ለማጥፋት ሙከራ እየተደረገ ነው፡፡ ይህ ኦርቶዶክሳዊነትን
ከዩክሬይን የማጽዳት ፕሮጄክት የተጠነሰሰው በምዕራቡ ዐለም ነው፣ በካቶሊክ አገሮች ነው፣ አሁን ደግሞ እየተተገበረ ነው፡፡”[35]
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭም እንዲህ ብሏል፡-
“ክርስቲያኖች እየተሳደዱ ያሉት በመካከለኛው ምስራቅ ብቻ ሳይሆን በዩክሬይንም
ነው፣ በ2014 የተደረገውን የመንግሥት ግልበጣ ተከትሎ ብሔርተኛና ጽንፈኛ የሆኑ ኃይሎች የሃይማኖት ግጭት እንዲኖር በመቀስቀስ
ላይ ናቸው፡፡ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያኖች እና ገዳማት እየፈረሱ ነው፣ ካህናትና ምእመናን ዛቻና ማዋረድ እየተፈጸመባቸው
ነው፡፡ በዩክሬይን ደቡብ ምስራቅ 10
ቤተ ክርስቲያኖች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፣ 77
ደግሞ ፈርሰዋል፡፡ 3
ኦርቶዶክሳውያን ካህናት ተገድለዋል፣ ሌሎች ብዙዎች ደግ ከጽንፈኞች ዛቻ የተነሣ ወደ ሩሲያ ተሰደዋል፡፡”[36]
፫. ማጠቃለያ
በአገራችን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጸረ-ኦርቶዶክስ ዘመቻ ረጂም ገመድ ያለውና
የዐለም አቀፋዊ ጂዖ-ፖለቲክስና ጂዖ-ስትራቴጂ ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ግንኙነት ያለው ነው፡፡ ከአገሪቱ ታሪካዊ ማንነት
ጋርም የተቆራኘ ነው፡፡ ስለሆነም ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠውን የመዳን ጸጋ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ትሰብክ ዘንድ በደሙ በመሠረታት
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቋንቋን ወይም የብሔር ማንነትን ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ጉዳይ የቤተ ክርስቲያንን
ባሕርይና አስተምህሮ እንዲዘውርና እንዲመራ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች ፍጻሜያቸው ለቤተ ክርስቲያንም ለአገርም መልካም
አይሆንም፡፡ በጀርመን የናዚ ፋሺስቶች የፈጠሩት “የጀርመን ክርስትና” ያስገኘው ውጤት ከ60
ሚሊዮን በላይ ሕዝብ እንዲያልቅ ማድረግ ነበር፡፡
በዩክሬይንና መሰል ኦርቶዶክስ አገሮች በተለያየ መንገድ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ
የሚደረጉ ጣልቃ ገብነቶችም ዓላማቸው ሰዎች ወንጌልን እንዲማሩና መልካም አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ አይደለም፡፡ ዓላማው ሌላ
ነው፡፡ በአገራችን እየሆነ ያለውም ዓላማው ወገኖቻችን በቋንቋቸው እንዲገለገሉ በሚል ማር የተለወሰ ውስጡ ግን አደገኛ የሆነ
ለቤተ ክርስቲያናችንም ለአገራችንም የማይበጅ አደገኛ ዘመቻ ነው፡፡
ስለሆነም በጀርመን እነ ሂትለር የፈጠሩትን “የጀርመን ክርስትና” የተባለ
ጀርመናዊነትን ከክርስትና ያስበለጠ፣ ጸረ ሴማዊነትን የታጠቀ አካሄድ እነ ቦንሆፈርና መሰሎቹ እስከ መታሰርና መሞት ደርሰው
በጽኑ እንደ ተቃወሙት እኛም በጽኑ ልንቃወመው ያስፈልጋል፡፡ በቋንቋና በሆነ ብሔር ማንነትና የበላይነት ላይ የሚመሠረት
ክርስትና ከክርስቶስ ያይደለ እንደ “የጀርመን ክርስትና” ያለ ለፋሺስቶች የዘር ማጥፋት አጀንዳ መሳሪያ ይሆን ዘንድ የሚፈጠር የፖለቲካ
መሳሪያ ነውና፡፡ ኦርቶዶክሳዊነትን ከኢትዮጵያ በልዩ ልዩ ስልቶች ለማዳከምና ለማጥፋት የሚደረገው የሰይጣንን እቅድ የዐለም አቀፋዊ ዘመቻ አካል ነው፡፡ በዚህ ሂደት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ
የሚሳተፉ ሁሉ በታሪክም በእግዚአብሔር ዘንድም ወንጀለኞችም ተጠያቂዎችም ናቸው፡፡ በይቅርታ በፍቅር እና በወንድማማችነት ህብረት ህብረት እንጂ
በጥላቻ፣ በበቀል፣በግል ስልጣን ምኞት የሚመሰረት ቤተ እምነት የጽድቅ በር አይሆንም። ዛሬ በብሄር የተከፈተው መንገድ ነገ
ስልጣንናንጥቅም በሚፈልጉ በወለጋ፣ በባሌ፣ የሸዋ፣ የአድዋ የሽሬ፣ የአክሱምን ጳጳሶች እራሳቸውን እየሾሙ ብቅ እንደ ይሉ ምን
ማረጋገጫ አለ። የዚህ መጨረሻው ሁሉም በየሰፈሩ አዳራሽ እየተከራየ ነብይና የእግዚአብሔር ሰው እያለ እንደሚነግደው ኦርቶዶክስስ
ምን ማረጋገጫ አለ።ዛሬ በክርስቶስ አስተምህሮ ሳይሆን በኦፒዲ እና በህወሓት ጠመንጃ እንዲሆን እየተሞከረ ያለው ጵጵስና ነገስ
እነዚህ ሲቀየሩ በየ ግዜው መፈንቅለ ጵጵስና እንደሚያስከትል መረዳት እንዴት አቃተን። ይህ ደግሞ ለሁለት ሺ ዘመን የቆመችውን
ቤተ ክርስቲያን አፍርሶ እንደ ጀርመኖቹ ክርስትና ከፓለቲከኞች
ጋር የሚገንና የሚከስም ክርስትና የጽድቅ መንገድ አይሆንም። ስለዚህ ሁሉም ይሄንን የሰይጣን እቅድ ማውገዝና እራሱን ማግለል
አለበት።
ታሪክ የሚያሳየው የጀርመን ክርስቲያን መሪ
ሆኖ (Bishop of the German Christian) ጳጳስ ተብሎ የተሾመው ሉድዊግ ሙለር (Ludwig Muller) ጀርመን በፈረንጆቹ በ1945 ሲሸነፍ ሉድዊግ ሙለርም እራሱን አጠፋ። የመጨረሻው
ሀጥያቱ የራሱን ነፍስ ማጥፋት ነውና ከአለቃው ሂትለር ጋር አንድ ቤት በፍርድ የሚገናኙ ይመስላል። ከመያዝና ከመሞት ያመለጡት የዚህ ክርስትና አይንተ ሰባኪዎች በመላው ዓለም ሲበታተኑ የተወሰኑት ኢትዮጵያ፥
ወለጋ-ግምቢ ተሸሽገው መሳዮቻቸውን አሁን በኦነግነት የተገለጹትን ልጆች አፈሩ።
ለዚህ ነው በክርስቶስ ደም እንጂ በሽመልስ
አብዲሳ ወይንም በደብረጽዮን ጡንቻ የሚቆም የክርስቶስ ቤተመቅደስ አይኖርምና ወደ ህሊናችሁ ተመለሱ፣ ንስሀ ግቡ የምንለው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ግራኝ መሀመድ በእሳት ለብልቦ ያጠፋት መስሎት ነበር። ይሁንና ከቃጠሎው ውስጥ ለምለም
በድጋሜ ብቅ አለች። ጣልያንም እንዲሁ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ክርስቲያንን በመርዝ ጋዝ በቦንብ፣ እነ ደብረ ሊባኖስን ደግሞ
ዘርፎ አቃጥሎ ምናንያንን ጭኖ ወስዶ ደብረ ብርሀን አባ ሳሙኤል ወስዶ ረሽኖ ዲያቆናቱን ዲናኔ ሱማልያ ወስዶ አስሮ የካቶሊክ
ጳጳስ ሾሞ ከአራቱ ጳጳሳት ውስጥ ሁለቱን አቡኑ ጴጥሮስን ፒያሳ ላይ አቡነ ሚካኤልን ደግሞ ጎሬ ላይ ረሽኖ አስፈራርቶ
ኢትዮጵያን ካቶሊክ ለማድረግ ሞክሮ አልተሳካለትም። ሙሱሎኒ እና ውሽማው በሚላን አደባባይ ተረሽነው እግራቸው ወደላይ ታስሮ
በሚሌን አደባባይ ታዩ።
የኢትዮጵያ ኮሚኒስቶች ሀይማኖት ለአብዮት
ጠንቅ ነው የሚል ሚስጥራዊ ባለ አስራ ሁለት ውሳኔ ወስነው። የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት ለጭቁኑ ህዝብ መገልገያ እንዲሆኑ ወደ
ቤተ መዘክርእንዲቀየሩ፣ ወጣት ቆንጆ ካድሬዎች በየ ገዳሙ እየገቡ መናኞችን እንዲያሳስቱ፣ የቤተ ክርስቲያን መገልገያ ከገበያ
እንዲጠፋ፣ የቤተ ክርስቲያን መጽሀፍት ተሰብስበው እንዲጠፏ ብሎ እቅድ አውጥቶ ብዙ ደክሞ ነበር። ይሁንና ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር
ኮሚኒስቶቹ ተጫረሱ እቅዳቸውም ከሸፈ። ኦርቶዶክስ ሰብረነዋል ብለው የታበዩት የዋልድባን ገዳም ወደ ስኳር እርሻ እንቀይረዋለብ
ብለው መናኞችን በሰንሰለት አስረው ያመጡትም መቅሰፍት በሚመስል በግንባራቸው ጥይት ገብቶ አየን።
አሁንም ክርስቶስን ሳይሆን ክላሽንኮቭን
መከታ አድርገው ሰው የሚገሉ ቤተ ክርስቲያንን የሚያቃጥሉ፣ ሙዳይ የሚገለብጡ ፈጣሪ በቸርነቱ ለንሰሀ ግዜ ቢሰጣቸውም እንደሌለ
እንደማይፈርድ ያሰቡ ይመስላልና ተዉ ንስሀ ግቡ ከእርኩሰት መንገድ ታቀቡ እንላለን።
ጉዲት፣ የግራኝ ጅሀድ፣ ሞሶሊኒ ፋሺዝም፣ የነ
ሀይሌ ፊዳና ሰናይ ልክ ኮሚኒዝም፣ ዩነ አባይ ጸሀዬ ማሌሊት ያላጠፋትን በአለት ለይ የተገናባች እምነት የሽመልስ አብዲሳ
የብልጽግና መጽሀፍ ቅዱስ ያጠፋታል ማለት ታሪክን ያለማወቅ ነው።
መዝሙራችንም
አህዛብ ዝክራችንን ሊየጠፋ
ሊገሉን ብዙ ዘመን ቢለፋ
አሽንናፊዎች ሁሉ በልጠን
አልሞትንም ዛሬም በህይወት አለን
ስለዚህ አትድከሙ፥ አንድ ሆነን በመነሳት፥
በግልም ነፃ አውጭና መፍትሔ ሰጭ ሳንጠብቅ መርዘኛውን የአገርና የሃይማኖት ጠላት የሆነ ፖለቲካና ሥርዓቱን በሁሉም ዘርፍ ተዋግቶ
ማሸነፍ የሚያስፈልገው።
የተኛህ ንቃ!!
[1] በእንተ ተሠግዎተ ቃል፣ ቁ. 46
[2] Otto Brokelschen, What do German Christians Want?: 118 Questions and Answers. Translated in Solberg, A
Church Undone, 418.
[3] A.J.P. Taylor, The Course of German History, (London: Hamish Hamilton, 1945), 1.
[4] Quoted in Ibid, 21.
[5] Joachim Hossenfelder, The Original Guidelines of the German Christian Faith Movement, 1932.
Translated
and cited in Solberg, A
Church Undone,
43-52.
[6] The Handbook of the German Christians, 1933. Translated in Solberg, A Church Undone, 172.
[7] Bergen, Twisted Cross, 24.
[8] Solberg, A Church Undone, 177.
[9] Ibid.
[10] Henrich Detel to Hossenfelder, 16 Sept. 1935, Bresalu, BA Potsdam, DC-I, 1933-35. Cited and translated
in Bergen, Twisted Cross, 333.
[11] Organization for German Christianity, Jesus and the Jews, 1936. Translated
in Solberg, A Church
Undone, 435.
[12] Bergen, Twisted Cross, 156.
[13] Joseph Goebbels, Michael (Verlag Fraz Eher, 1934), 82. (English: Michael: A
Novel, Trans. Joachim Neugroschel (New York: Amok Press, 1987).
[14] Bergen, Twisted Cross, 143.
[15] Bergen, “Anti-Semitism in Germany,”334.
[16]
Brokelschen, What do German Christians Want?,418.
[17] Bergen, Anti-Semitism in Germany,” 333
[18] On the Jews and Their
Lies - Wikipedia. https://en.wikipedia.org/wiki/On_the_Jews_and_Their_Lies.
[20] (1) ANTISEMITIC WRITINGS FACE
REPUDIATION - The Washington Post.
https://www.washingtonpost.com/archive/politics/1993/10/17/antisemitic-writings-face-repudiation/c6c6367c-1737-42fe-87b9-62168e8830ed/.
(2)
Early Modern Hate speech—Martin Luther`s Anti‐Semitism ... - JSTOR.
https://www.jstor.org/stable/26605814.
(3)
On Luther and his lies about the Jews | The Christian Century.
https://www.christiancentury.org/article/critical-essay/on-luther-and-lies.
(4)
Martin Luther and antisemitism - Wikipedia.
https://en.wikipedia.org/wiki/Martin_Luther_and_antisemitism.
(5) goodreads.com.
https://www.goodreads.com/book/show/23836588-on-the-jews-and-their-lies.
[21] Metaxas, Bonhoeffer, 166.
[22] Metaxas, Bonhoeffer, 180.
[23] Bergen, “Chaplaincy and the Christian Movement,” 526
[24] አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዘደንት በጄኔራል ታደሰ ብሩ 100ኛ
ዓመት መታሰቢያ በዓል ላይ ያደረጉት ንግግር
[25] Kyle Jantzen, Faith and Fatherland: Parish Politics in Hitler's Germany,(Fortress Press, 2008), 4-5.
[26] ibid
[27] “Revision of Scripture is urged on Germans”, The New York Times, November 14, 1933.
[28] Bergen, Twisted Cross, 17.
[29] Erickson, Theologians under Hitler, 48.። Ulrich Duchrow, “The Confessing Church, and the Ecumenical Movement,” The Ecumenical Review 33,
no. 3 (April 2010): 267.
[30] The Aryan Paragraph in the Churches and Responses. See Solberg,
A Church Undone, 57.
[31] Ibid, 308.
[32] Erickson, Theologians Under Hitler, 48.
[33] Dietrich Bonhoeffer, The Cost of Discipleship, (New York: Touchstone, 1995), 141.
[34]
The Ecclesial Crisi in Ukraine, and Its Solution
According to the Sacred Canons, Nikiforos, Metropolitan of Kykkos and Tylliria,
Cyprus, 2021.
[35] Interfax-Religion፣
Moscow, January 15, 2016)፣ interview with
the Radonezh radio
[36] Interfax-Religion, 3/3/2015
አስተያየቶች