ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ከ2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እየገደሉ የምሥራች

 የድንቁርናና ሕሊና-ቢነስት ያነገሣቸው  የጎሣ ልሂቃን "የምሥራች" ትርጉም አምባገነን፥ ቁማርተኛና የወሮበሎች መንግሥት የሚመራውን ሕዝብ መከራ "የምሥራች" እያለ ያለማምደዋል።  የሕወሃት/ኢሕአዴግና ብልጽግና በዚህ ሞትና መከራን ድልና እድገት አድርገው በማቅረደብ አንድ አይነት ናቸው። ስዩም መስፍንና አሊ አብዶ  የሕወሃትና የሻዕብያ የዘረፋ ሀበት ክፍፍል ግጭት በባድሜ እንደ ምክንያት ትርጉም-የለሽ   ከ120 ሺህ ሕዝብ በላይ ወገን አስፈጅተው፥ ይግባኝ በሌለው የአልጀርስ ስምምነት "የምሥራች፥ እንኳን ደስ ያላችሁ" ብለው ሕዝቡን አስጨፍረዉታል። የፈረደበትን ዐመሓራና ኦርቶዶክስ ክርስትናን በማጠፋት አጀንዳ ላይ ቢስማሙም  ነገር ግን በተለመደው የሀብት፥ የብሔር ግዛት በሰስፋት፥ ዲሞግራፊ በመቀየር፥ አሰስ አገር የመፍጠር እና የበላይነት ለማስፈን ባደረጉት ግጭት ሕወሃትና ብልጽግና በየበኩላቸው ወደ ጦርነት የመሩትን ወገን ድል አግኝተናል፥ የባሰ አደጋ እንዳይመጣ አድርገናል ብለው "የምሥራች" ብለዋል። ብልገግና የአባይ ግድብ ከደ ጋየወረደው የክረምት ጎርፍ ስለ ሞላ የምሥራች በሚ ልሕበቡን በተለይ አሰስ አበባ ውስጥ አስጨፈሩ ፥ ግን የኢትዮጵያን ባንዲራ ያውለበለቡ ወጣቶችን የኦሮሙማው ፖሊስ ሠራዊት ቀጠቀጠው፤ አብይ አህመድ የአዲስ አበባ፥ የደብረ ዘይት፥ የናዝሬትና ሌሎች ከተሞች ነዋሪችን የሕዝብ አሠፋፈር ለመቀየር ኦርቶዶክስ ክርስቶያቸኖችን፥ ጉራጌዎች፥ ኮንሶዎች፥ ወላይታና ጋሞዎች ወዘተ ዒላማ ያደረገ ማፈናቀል እያካሄደ "ከተሞቻችን እያማሩ ነውና የምሥራች"  ብሏል።    የአማራን ሕዝብ በምድርና በረር ኃይል ሕዓናትን፥ ካህናትን፥ ገዳማውያንን፥ ገበሬዎችን በመጨፍጨፍ ላይ የሚገኘው የአብ...

የአብይ አህምድ አሊ በመተግበር ላይ የሚገኙ ዘር የማጥፋት ስልቶች

 የአብይ አህምድ አሊ  በመተግበር ላይ የሚገኙ ዘር የማጥፋት ስልቶች  የአብይ አህመድ አሊ የአእምሮ ወላጆችና ተልዕኮው አብይ አህምድ አሊ ከጣሊያን ፋሽት፥ ከግራኝ አህመድ ላኪዎች ጽንፈኞች እና  ዓለምን በባርነት ለመግዛት ከሚሠሩ ኃያላን አገራት አስተምህሮ እና ከቅድመ ክርስትና አሕዛባዊ የአረሜነነት ጠባይ ተቀይጦ  በተፈጠረ አስተምህሮ የተወለዱ  ደርግ፥ ማርክሲስት ንቅናቄዎች፥ የጎሣ ነጻ አውጭዎች፥ በተለይ ሕወሃትና ኦነነግ  ተዳቅሎ የተወለደውን የአነግ-ኦርኦሙማ የብልጽግና ፓርቲ ሠሪና መሪ ነው። ይህ ሰው የአእምሮ ወላጆቹን ዕሳቤዎች አዳቅሎ የቆየ ዓለማቸውን ከግብ ለማድረስ ሥልጣን ላይ እንዲቀመጥ የተደረገ ሰው መሆኑን በቆይታው በተግባር አረጋግጧል።  በፖለቲካ አስተዳደጉ ከሤራ፥ ቁማርና ዘረኝነት፥ ሌብነትና ሐሰተኝነት ውጭ ምንም አይነት ከሰብአዊነት፥ ከፍቅር፥ ከእውነት፥ ከአገራዊነትና የማኅበረሰብ ሰላምና ተዋህዶ ጋር የሚያስተዋውቅ  ፖለቲካ፥ ትምህርት፥ አስተዳደርና አሠራር ለማየት እድል አላገኘም።  ያደገው በሕወሃትና በኦነግ የጥላቸና የሐሰት ትርክት የመርዝ ጡጦ ነው። ጥመቱን፥ ክህደቱን፥ አላዋቂነቱንና ለማንኛዉም አነይት የባዕዳን አጀንዳ ተሸካሚነት የተዘጋጀ መሆኑን የተረዱ የውጭ አካላት ተሯሩጠው ሕወሃትን ተክቶ የተጀመረውን፦ በአፍ መፍቻ ቋንቋው አማራ የሆነ (ሕወሃትና ኦነግ በጻፉት የብሔርና ብሔረሰብእ ተርጓሜ መሠረት አማራ የተባለ ሁሉ)  ማንኛውንም ሰው እና  ሁለተኛ   በሃይማኖት ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የሆነ ማንኛውንም ማኅበረሰብእ    ከኢትዮጵያ ምድር አስተሳሰቡንና ታሪኩን፥ ከተቻለ በአካል የማጥፋት ፕሮጄክት አስፈጻሚ አድርገ...

ለፋኖ ብሔርተኝነት የሚሰብኩ ልሂቃን የዐመሓራነት፥ የኦርቶዶክሳዊነት፥ የኢትዮጵያዊነት ጠላቶች ናቸው

 ለፋኖ ብሔርተኝነት የሚሰብኩ ልሂቃን የዐመሓራነት፥ የኦርቶዶክሳዊነት፥ የኢትዮጵያዊነት ጠላቶች ናቸው! አንዴት? እነሆ የእኔ የግሌ መከራከሪያ ብሔርተኞች ከፈጠሩት ግጭት፥ ከዘሩት ጥላቻ፥ ከከፉት የመጠፋፋት በር የተወሰነ ጊዜ ለማረፍና ራሳቸውን ማደላደል ሲፈልጉ የሚቀርቧቸው ደካማ  የማስታረቂያ  ንንግግሮች አሉአቸው፦ ተዋልደናል የመከራ ጊዜን አብረን አሳልፈናል እጣ ፈንታችን አንድ ነው  በመቻቻል እንደ ሌሎቹ አገራት መበልጸግ እንችላለን ያለፈ ቁስልና የታሪክ ቁርሾን መልሶ መቀስቀስ አያስፈልግም አጥፍተናል ብለው የታሪክ በደልን የሻሩ አገራት አሉ እንድ ቤተ እምነት ውስጥ እናመልካለን ወዘተ  ይላሉ። እንዚህ አነጋገሮች ሁሉ ውስጥ የመለያየት፥ የበቀል፥ የልዩነት፥ እነርሱና እኛ የሚል ድምጸት፥ የታሪክ ካሣን ባልነበሩበት ዘመን አሁን ካለው ትውልድ የመፈለግ፥ ጥላቻ፥ አለመተማመን በግልጽ ይታያል።  በሌላ አነጋገር  ብንዋለድም እኔ የተለየሁ ፍጡር ነኝ ብቻ ሳይሆን እኔና አንተ ጠላቶች ነን የሚል መልእክት ያዘለከሚል ነው።  በዚህ ንግግር ውስጥ ክብረ-ሰብእ፥ እውነት፥ ፍትሕ፥ የትውልድ የመዋሐድ ተስፋ የለም። ሁሉም ተጠባብቀን በጥንቃቄ መኖር ወይንም መጠፋፋት ከደጃችን አለ የሚል በትክክል የሰው ልጅን ክብር፥ የአገርን ምሥጢር፥ የእውነተኝነትና የሕይወት መሠረት፥ የፍትሕና የርትዕና የሰብአዊነት መገለጫ ፈጽሞ የዘነጋ መሠረተ-ፍልስፍናው ጸረ-ሰላም፥ ጸረ-ሰብእ እና ጸረ-ሀገራዊ አንድነት የሆን አስተምህሮ ነው። ለምሳሌ እነ አቶ ወልደአብ ወልደማርያም ውልደታቸው ትግራይ ቢሆንም በጣልያን ቅኝ ግዛት ግዜ ጣልያንንም ሆነ አንግሊዝን ሲቃወሙ አልታዩም።  እነ አክሊሉ ሀብተወልድ ከጣልያንና ከጣልያን ደጋፊዎች የካ...

መርዛማ ብሔርተኝነት ወደ ውስጥ የተዘራው ከውጭ ነው_አረሙን ማረም የሁላችን ኃላፊነት ነው

  መርዛማ ብሔርተኝነት ወደ ውስጥ የተዘራው ከውጭ ነው፥ አረሙን መንቀል አእምሮ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉ ኃላፊነት ነው 24-1-2017 ጠላትስ ጠላት ነው ከእኛ መካከል ፍቅርን፥ ሰላምንና አንድነተን የሚፈለግ እንዴት ጠፋ?   በአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች ኢትዮጵያን ከውሃ አካል ለመለየት፥ ለመከፋፈል፥ ለማጥፋትና መላውን የጥቁር ዘር ባርያ ለማድረግ የተከተሉት የተባበረ ሤራ፤ በሰይፍ ዓለምን ለማስለም የተነሱት መሐመድና የመሀመድ ተከታዮች ሊቢያን፥ ግብጽን፥ ሱዳንን፥ ሰሜት አፈሪካን፥ የኦርቶዶክስ አገር አልጄርያን (ካርቴጅን) ደምስሰው ወደ ኢትዮጵያ ሲዞሩ ያደረጉት የባህር ጠረፎችን በሁሉም አቅጣጫ መውረር ነበር።  ይህ የዘመናት ጥቃት አሁን የምንገኝበትን ሁኔታ ፈጥሯል። የጠላት ሤራ በተግባር የአገራችንን ቅርጽና የሕዝብን አስታሰብና እምነት አዛብቷል፥ ስነ-መንግሥቷን ግራ አጋብቷል።     ከዚህ ሁሉ በላይ ዘመናዊ ትምህርት አመሠራረታችን ጥበብና ዕደ ጥበብን ሳይሆን መጣላትን፥ ያለንን መጥላትን፥ ባዕድ መናፈቀን አሸከመን። የሚገርመው በዚያ ጥቃት የተፈጠረውን መለያየጥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር የተሰጠን መለኮታዊ ብያኔ አስመስለው የተነሱ የዘመኑ ልሂቃን ቀሳፊነት ነው። የኤርትራ ነጻነት ብለው ሲነሱ አባባላቸው ባርነታችንን፥ የኢትዮጵያ አጥፊዎች የጀመሩትን ፐሮጄክት ከግብ እናደርሳለን ብለው መነሳታቸው ነው። ከ3000 ዘመናት ታሪካቸው ይልቅ የ60 ዓመታት የጣሊያን ባርነታቸውን ያደንቃሉ።   ሕሃትና ኦነግም አንደዚሁ ጣሊያንና የናኒ ፋሽቶች አስተሳሰብን፥ የማርክስን የመደብ ጭቆና አስተምህሮ ብቸኛ ማሰቢያ በማድረግ ይህ አገር አጥፍትን አንኖራለን ብለው ይነሳሉ።  ጀዋር መሐምድ "ይህ...

የስግብግብነትና የጭካኔ ጥግ ለማየት የዳረዊን ልጆችን ሤራና አሠራር ለልጆቻችን በመግለጥ ክርስትናቸውን እንዲጠብቁ እንርዳቸው

Fantahun Wakie    ·  Shared with Public የስግብግብነትና የጭካኔ ጥግ ለማየት የዳረዊን ልጆችን ሤራና ዓለምን ማመስ ማስተዋል ያስፈልጋል። አገር በቀል ዝንጀሮ ነን ባዮችም ለዚህ ነው ሰውብ በጎሣ ተካፍለው የሚያፋጁት። ክፋታቸውን ከምእራብ ተውሰው አገር በቀል ያደረጉት ሕወሃትና ኦነግ/ብልጽግና እግዚአብሔርን ስነኳ ለጎሣ የሚቀም አይነት ብዝኃ-አማላክት ለመፍጠር ሲሉ መጅልስና ሲነዶስን በሐሰት ይፈጥራሉ። ይህ ለምን ሆነ? የእኔ መልስ የማኅቀፈ-ዕሳቤ መዛባትና ከሰብአዊንተ ውጭ መሆን ነው! ------------------------------------ ለማንኛዉም በምሳሌ እንነጋገር፦ በነፍስም በሥጋም እንዳንሞት ማሥቀፈ0ዕሳቤያችንን ከወረራ እንጠብቅ! ሐምሌ ፲፪ ቀን ፳፻፲፮ ዓ/ም አንዳንድ የማኅቀፈ-ዕሳቤ ልዩነቶች ርቀት እንደ ጨለማና ብርሃን ያህል ነው። ነባርና በአብዛኛው ለሺዎች ዘመናት ኢትዮጵያውያንን የመራው የጋራ ማኅቀፈ ዕሳቤ የሚተረጎመው፦ (፩) ሰብአዊ-ክብር፥ (፪) ፍትሐዊነት፥ (፫) ባለርስትነት፦ ዜጎች ሁሉ በእኩል የአገር ባለቤትነትና የግል ርስት በተዋህዶ፥ (፬) ፈሪሐ እግዚአብሔር፦ ሁሉን ስለ እግዚአብሔር፥ ስለ ዘላለማዊ ሕይወት ማሰብ፥ መናገርና ማድረግ (፭) ሕግ፥ ፍትህና አስተዳደርን ከሕገ-እግዚአብሔር ጋር የተናበበ መሆኑን ማረጋገጥ ናቸው። የኢትዮጵያዊነት ጠላቶች ማኅቀፈ-ዕሳቤ ኢትዮጵያን የሚጠሉና ባለፉት 700 ዓመታት፥ በተለይ ከ100 እና ከ50 ዓመታት ወዲህ ብሶ የመጣውን ጥቃት የከፈቱብን አካላት ዋና ማኅቀፈ-ዕሳቤ፡ (፩) ኢሰብአዊ (ሰውን በምርት ግብአትነት የሚመለከት የዳርዊን ዝንጀሮ)፥ (፪) ፍትሕ (በአሸናፊዎች የሚተረጎም ቋሚ ትርጉም የሌለው ዕሳቤ ነው) (፫) ባለ ርእት ጥቂት ዜጎች ፥ ርስት አልባ...