ኢትዮጵያኖችን ከእብደት ጠርቶ የማስታረቅ ኃላፊነታችሁን ተወጡ፡-- ለጳጳሳት፣ ለካህናት፤ ለሸኾች፣ ዑስታዞች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የጎሣ መሪዎች፣ የዘረኝነት ደዊ ያልለከፋችሁ የዩኒቭረሲቲ ፕሮፌሰሮች ሁሉ፡- ተቆንጥጦ ያላደገ ልጅ ጉልበት ሲያወጣ ወልደው ያሳደጉትን ወላጆቹን አንደሚዳፈር በሐገራዊ እውቀት፣ ጥበብ፣ አስተዳደርና ፍልስፍና ሳይበለጽጉ ላለፉት 100 ዓመታት ከውጭ በተቀዳ ባዕድ ትምህርተት የደነቆረው ትውልድ ወደ ፍጹም እብደት ደርሶ እናት ሀገሩን እየተዳፈረ ይገኛል፡፡ ይህ ትውልድ እውነተኛ ሀገራዊ ሰው የመሆንና የመኖር ትርጉምን፣ እውነተኛ ታሪክን የሚማርበት እድል ተነፍጎታል፤ በተቃራኒው የታሪክ ትምህርትና ትርጓሜ የሚሰጠው ግልብ በሆነ የባዕድ ትምህርት ማያቸው በተባለሹ ከእውነት ይልቅ ለፖለቲካ ርዕዮተዓለም ታማኝ በሆኑ ካድሬዎችና የፖለቲካ ሰባኪዎች(አክቲቪስቶ) ነው፡፡ የሰው ልጅ ምንነትና ማንነት የሚበየነው በኢኮኖሚያዊ ጥቅምና በሆድ ደረጃ ብቻ ነወው፤ የሰው መንፈሳዊና ባህላዊ ክብሩ ተዘንግቶአል፤ ኢትዮጵያዊያን እንደ ምርት ግብአት፣ እንደ ኢኮኖሚ ማሽን፣ አንደ ጦር መሣሪያ በሚቆጥሩት የጎሣ ፖለቲከኞች እጅ ተይዟል፤ ወደ ራሱ ተመልሶ ከወገኒ አንዳይ ታረቅ ገዥዎችና የሚዲያ ጀግኖች አጨልመውበታል፡፡ የፍትህና የእስተዳደር ሥርዓት ትርጉም የሚያገኘው በብልጥና ጉልበተኛ ልጆች አመራር ሥር ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ሰው በጎሣና በታሪካዊ ልዩነቶች እየተፈረጀ እኛና እነርሱ በመባባል አንዱ በሌላው ላይ የጠላትነት እንቅስቃሴ በማድረግ ሰውን እንደ በግ ሲያሳርድና ሲያሳድድ፣ ሕፃናትን በቡድን ሲያስደፍር፣ ጎረቤትን በቆንጭራ ሲያስቆርጥ (ቡራዩን፣ በሻሻ፣ አወዳይን፣ ጅጅጋ፣ ቀይና ...
This is a spot where I post and share part of my daily reality. I would love to hear from others too to learn how differently we interpret daily encounters including our imaginations. ይህ ሥፍራ የየዕለት ገጠመኞቼን፣ እንዴት በዕለቱ እንተረደሁትና የማስበውን ለሌሎች ያማጋራበት ነው፡፡ የሌሎችን በመስማትና ምን ያህል ዓለማችንን በተለያየ መንገድ እንደምንመለከታት ለመማር እጓጓለሁ፡፡