ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ኦርቶዶክሳዊነትና የፖለቲካው ትክክለኝነት ( ዘመናዊ ሥዝም ኑፋቄ ነው)

       ኦርቶዶክሳዊነትና የፖለቲካው ትክክለኝነት ( ዘመናዊ ሥዝም ኑፋቄ ነው ) ፋንታሁን ዋቄ ህዳር 2013 ኦርቶዶክሳዊነትና የሰይጣን መንግሥት ከሚለው መጽሐፍ መግቢያ ተወስዶ ተስፋፍቶ የተጻፈ ይህ ኑፋቄ ስነኳንስ ሕዝባዊውን ጳጳሳትን፥ መነኮሳትን፥ ካህናትን፥ የባህል መሪዎችን፥ ሙፍቲዎችንና ዑስታዞችን፥ ሰባኪያነ ወንጌል ሁሉ የበከለ የፍትሕ፥ የእውነት፥ የሰብአዊነትና የማኅበረሰብ አጠቃላይ አጥፊ ሆኖ ተከስቷል።  የፖለቲካ መሪዎች፥ የሲቪልና የቢሮክራሲ ባለሚያዎች፥ በአንድ የሥራ ጽ/ቤት ውስጥ ያሉ ተዋረዳዊ ግኑኝነት ያላቸው ሠራተኞች ሳይቀር የሚነጋገሩት ፖለቲካዊ ትክክለኝነትን ታሳቢ አድርገው ነው።  ሐሰትና እውነት፥ ፍትሕና ግፈኝነት፥ ሰብአዊነትና አራዊትነት፥ እኩል በዓለአገራዊነት፥ ክብረ-ሰብእ የመሳሰሉት ወሳኝ የመኖር ትርጉም መሠረታዊ እሤቶች ሁሉ ዋጋ አጥተዋል። በዚህ ጉዞ መእመናንና ዜጎችም በየበኩላቸው በተክርስቲያንን ትተው የሚያስደስቱትን ጳጳስ ቆሞስ፥ ዜገችም የአገራቸውንና የትውልድ ነገር ትተው በወቅቱ ሥልጣን ላይ ያሉትን  ለማስደሰት ፖለቲካዊ ትክክለኝነታቸውን ጠብቀው የሚናገሩ፥ የሚያደርጉና ግኑኝነት የሚፈጥሩ ናቸው። ስለ እውነት፥ ስለ ፍትሕ፥ ስለ ክብረ-ሰብእ፥ ስለ ቤተ ክርስቲያንና አገር፥ ስለ ሕዝብና መጭው ትውልድ ጥቅም የሚናገር የለም።  አብዛኛው በፖለቲካዊ ትክክለኝነት እግዚአብሔርን ሳይቀር እንደሚገባ በአምልኮታቸውና በአርአያነት ሊመሰክሩ አልቻሉም። ፖለቲካዊ ትክክለኝት ሲገለጥ፦ የየዘመኑን ፖለቲካ ( የየዘመኑ ፖለቲካ መሠረቱ በየዘመኑ የበላይነት የሚጎናጸፍ ነፅሮተ ዓለምና ፍልስፍና ነው) ለመምሰልና ለማስደሰት መናገር እ ና እግዚአብሔርን ለ...