ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ሐሰተኛ ትርክትን ሳይንሳዊ የማስመሰል የዘረኞች ወንጀል

             ዘር ማጥፋትና የሐሰት ትርክት ቁርኝት፡- የሐሰት ትርክትን ሳይንሳዊ የማድረግ ፕሮጄክት እና ለእውነተኞች ምሁራን የቀረበ ጥሪ   የጽሐፉ መደምደሚያ አጽሕሮት ·        በኢትየጵያ ጠልነት፣ በኦርቶዶክስ ጠልነትና በአማራ ጠልነት የተሰለፉ ምሁራን የሚከተሉት ሃይማኖትና ፍልስፍናቸው በአብዛኛው ከኦርቶዶክስ ክርስትናና ከባር የኢትዮጵያ እሰልምና ውጭ የሆኑ ናቸው (ለምሳሌ ማርክሲሰት፣ ዉሀቡ ጽንፈኛና የጝራኝ አህመድ ናፋቂ፣ የናዚ ፍጡር “የጀርምን ክርስትና”-ቀመስ ፕሮቴስታንን፣ ከክርስትናና እስልምና ውጭ ሆኖ በባህል ስም የጠራና የሀሰት አምላክ የሚመልክ፣ ከማርክሲዝም የመደብ ፀንሰ ሀሳብ ተውሶ አዲስ የብሔረሰብና የጎሣ አሰላለፍን በመደብ ደረጃ የፖለቲካ ርእዮት አድርጎ የሚያምን፣ ማንኛዉም የአገሩን ሃይማኖትና እምነት ሳይማርና ሳያውቅ በምዕራባዊያን ወይንም በአረቦች እሴት ተመስጦት ሰመመን ውስጥ የገባ ምሁር) ። ·        የአገራችን የኢትዮጵያ የዘረኝነት ፖለቲካ ርእዮትና፣ ርእዮቱን እውነት ለማድረግ የሐሰት ትክትን ታሪካዊ የማድረግ ስልት ሁለቱም በአውሮፓ ቅኝ ገዥዎችና ባሪያ አሳዳሪዎች በተለይ በናዚ ፓርቲ የተሚከሩት በቀጥታ በመገልበጥ ነው ·        ዘረኝነት ላይ የመሠረተ ፖለቲካ ተቀባይ አግኝቶ ለሥልጣን የሚያበቃው ሐሰትን ሳይንሳዊ አስመስለው ማቅረብ የሚችሉ ምሁራን ሲገኙ እና ፐሮጄክቱን ሲያገለግሉ ብቻ ነው ·        ዘረኝነት ሕዝብን ከፋፍሎ...