ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ከሴፕቴምበር, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ልማት ለምን? በማን መቃብር ላይ?

ልማቱ በማን መቃብር ላይ፣ ለማን? ብሎ መጠየቅ ይገባል። ዝም ብለህ አታጨብጭብ!! ልማት ያስፈልገናል፣ ግን እኛን ቀብሮ አይደለም። ኦርቶዶክሳውያን፣ አማሮች እና ሌሎችም ዒላማ የተደረጉ ማኅበረሰቦች ይጠይቁ። ልማት ያስፈልገናል፣ ግን እኛን ቀብሮ አይደለም። ኦርቶዶክሳውያን፣ አማሮች እና ሌሎችም ዒላማ የተደረጉ ማኅበረሰቦች ይጠይቁ። ወገኔ ከሰው ክብርና ከህልውና መረጋገጥ ተጋድሎ የሚያዘናጋ ፕሮፓጋንዳ ሊፈጠር አይችልም። ከንቱ ልፋት ነው። ከሁሉ በፊት ክብረ-ስብእ!! ከሰው የሚበልጥልማት የለም!! ልማት ለሰው ነው እንጂ ሰው እንደ ግባት ሌላው ለሚጠቀምበት ለልማት አይደለም። ገልብጦ ማሰብ የዘረኞችና ይቅኝ ገዥዎች እንጂ የአንድ ሉዓላዊ አገር መንግሥት ፖልቲካና ፍልስፍና ሊሆን አይገባዉም ነበር። ሰማይና ምድር የተፈጠሩት፣ አምላክ ሰው ሆኖ የተሰቀለውና ዛሬ መስቀልን የምናከብረው ሁሉም ለሰው ልጆች ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጸጋና ጸጋውን የመጠበቅና የማመስገን ሕይወት ነው። ታዲያ ሰውን ከሰውነቱ ያዋረደ፣ በቋንቋ፣ በእምነትና በጎሣ ከፋፍሎ የሚያጠፋ፣ ከሰው ነፍስ ይልቅ የማይጸድቀው የፕሮፓጋንዳ ችግኝ ይበልጥብኛል ያለን፣ ጦር ሠራዊት “ልምራህ ላበልጽግህ” በሚለው ዜጋ ላይ ያዘመተ መንግሥት፣ ፈጣሪዎቹ የውስጥ እና የውጭ ወዳጆቹ ሁሉ #አብይ አህመድ #ግድብ፣ #ወደብ፣ #ኒውክለር፣ #ችግኝ፣ #መናፍሻ፣ #ሳተላይት ማምጠቅ ወዘተ ሁሉ ---- ለሚያጠፋቸው ኦርቶዶክሳውያንና አማሮች ሳይሆን --- መርጦ ልዩ ጥቅም፣ ልዩ ክልል፣ ልዩ ልማት፣ ልዩ ከተማ፣ ልዩ ተርክት፣ ልዩ --- ወዘተ የገባዋል ለሚባለውና የኦነግ የዘር ልሂቃን ለፈጠሩት “ኦሮሙማ” ለተባለ የፖልቲካ ፍጡር አይደለም ማለት ይቻላል። ቀይ ባሕር ወድብ ብቻ ሳይሆን የኢሬቻ ማክበሪያ የሌሎች መ...
ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።። 1) ሻሸመኔ ከተማ I. የተገደሉ 1. አያሌው ተረፈ ● በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ● ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ● በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ● በ ጥር 30 2015 ዓ/ም ሰማዕትነትን ተቀብሏል 2. ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ● የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ● በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ● ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ● በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም ሰማዕትነትን ተቀብለዋል። 3. ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ● የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገልጋይ የማኅበረ ቅዱሳን አባልና የበገና ደርዳሪና 4. አየለ ማንደፈሮ ● የሻሸመኔ ልደታ ማርያም አገልጋይ ወጣት ነው። ● ቤተክርስቲያንን ከመታገላችሁ በፊት እኔን ጣሉኝ ብሎ የደወል ጥሪዋን ሰምቶ በቅጥሯ ተገኘ። ● በመሳርያ የሚባርኩት የ...

ከሁሉም የህልውና አጀንዳዎች የቱ ይብስብሃል? ይብስብሻል?

የቱ አጀንዳ ይብስብሃል? ኢትዮጵያውያን ሁሉ በተለይ ኦርቶዶሳውያን አጀንዳ በዛብን። ፺፱ በ፻ ፈታኝ አጀንዳዎች የተሰጡን ከውጭ ነው። ነገር ግን ፩ በ፻ው የውስጡ ለውጭው ፺፱ኙ ጉዳት የማድረስ አቅም ምንጭ ናቸው። አጀንዳዎቹ በአብዝኃኛው ይቆዩ የማይባሉ ተጣማሪ፣ ተደጋጋፊና ተናባቢዎች ሆነው የህልውና አደጋ የጋረጡ ናቸው። እናም ካልፈታማቸው ያጠፉናል። እያጠፉንም ነው። ከብዛታቸው የተነሳ ምላሽ ለመስጠት (፩) በአንገብጋቢነት፣ (፪) በስልታዊነት፣ (፫) በወሳኝ ቁልፍነት፣ (፬) በአስቸኳይነታቸው ፣ እና (፭) የጥምር አጥፉዎቻችንን ትብብር በማዛባት ባለው ፋይዳ እየመዘንን ቅድመተከተል ማስያዝ ቢሞከር ከ፶ በ፻ው በላይ በ፩ኛ ደረጃ ሊቀመጡ የሚችሉ ይሆኑና ግራ ያጋቡናል። ጥቂቱን ልጥቀስና እናንተ ቅደምተከትል አውጡለት:- ፩) ከፋፋይ የዘር ፖለቲካን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከህግነት፣ ከትምህርትና ከትውልድ አእምሮ መፋቅ፤ ፪) የጎሣ ክልልና አስተዳደር ማፍረስና በዜጎችገንቢ መስተጋብርና ሁለንተናዊ ሰላምና እድገት አመቺነት ብማደራጀት፤ ፫) በባውዳን ፈጣሪነትና ምሁርነትን የተቀቡና የተላላኩነት ሚናቸው ባረከሰው ሰብእናቸው የሐሰት ትርክት በማምረት ማኅበረሰባችንን የመረዙ ሰነዶች፣ በሰነዶቹና ትርክቶቹ አንጻር የተፈጠሩ አደረጃጀቶችና የአስተሳሰብ አሰላለፎችን ማፍረስ፤ ፬) ኦርቶዶክስ ክርስትናን በአሉታዊነት በመሳል የቆመውን ስሕተት በሁሉም ዘርፍ፣ በውስጥም በውጭም ያለውን ሰልፍ ማሸነፍ፤ ፭) በስሑት ርእዮት ሞተርነት፣ በሐሰተኛ ትርክት አቀጣጣይነት፣ በጎሣ ነጻ እውጭ ነን ባዮች፣ በጽንፈኛ ዉሀብያዎች፥ እና የናዚ የየጀርመን ክርስትና ዘር አጥፊ ፕሮቴስታንቶች ቀጥተኛ ፈጻሚነት፣ በብልጽግና ወንጌል የሃይማኖት መንግሥት አመራርና አስተባባሪነት በ...

ታሪክ እና ትርክት የፖለቲካ ቁማር በኢትዮጵያ ክፍል 1

የዉሀብያ ዑስታዞች ማጭበርበር ማብቃት አለበት

#ማጭ*በር*በር አይበቃም?  እሁንም ታሪክ መገልበጥና፣ ጥፋትን ለማስቀጠል  መዋሸትና ደም ማፍሰስ አይሰለቻችሁም? ህክምና ሰብአዊነት የሚባል ነገር በቃ አዲሱ እምነታችሁ ውስጥ ለጠብታም የለም? ከጎሣ ፖለቲካ ቁማርተኝነትና ደም አፍሳሽነት ጋር አጋርነታችሁን የጸናው የአዲሱ እምነታችሁ አስትምሬና የቁራኑ አተረጓጎም ሆኖ ነው በክፋትና በሐሰት  ቦታ ሁሉ የምትገኙት? ================== ሶሪያ፣ ሊቢያ፣ ኢራቅ፣ ኩርድ፣ ናይጀሪያ፣ ሶማሊያ፣ የመን፣ ፓኪስታን፣ ግብጽ ደ*ም የሚያፈ*ስስ ማነው? ሳውዲ አረቢያ ክርስትና እንዳይኖር ያደረገው የማነው አስተምህሬው? ሊቢያ ያ*ረ*ደን የማነው አስተምህሮው? እዚህም እንዲቀጥል ነው ሩጫው? አረ #ተዉ!! ይህ #አካሄድ #አይበጀንም? ========= #ወገኖቼ ነባሩ ሙስሉምና ክርስትያን ተባብረን ከዘር ፖለቲካ አገር እፍራሽ ጋር ቄመው ጥፋት የጠሩብንን አዳዲስ ውጭ-ገብ ተላላኪዎችን ራሳችንን ለመታደግለመታደግ እንተባበር። ====== =========== "የኢትዮጵያ ነባር እስላም ሰላማዊ ነው" ስንል በተቃቃራኒው  "የኢትዮጵያ የሚባል የለም፣ እስልምና አንድ ዓለም አቀፋዊ ነው" ይሉሃል። እናማ ሊቢያ ያ*ረ*ደን፣ ዶዶላ የጨፈጨፈን፣ ሻሸመኔ አላሁ አክበር እያለ ከብልጽግና ሠራሽ የሳዊሮስ የጨረቃ ጳጳሳት ጋር እየገደለን ቤተ መቅደሳችን የገባው አንድ ናቸው ማለታችሁ አይደለምን? እርሱው አይደል ባሌ የሚያሳድደን? ከኦነግ-ኦሮሙማ አጋር ሆኖ አሁን #ግራኝ እህመድን ለመቀደስ #አጼዎቹን የምታረክሱ ዉሀቢዎቹ ናቸው ብለን ስንጠረጥር "አዎ እኛ ነን" ብላችሁ በድፍረት ብቅ ማለታችሁ አይደለም? ይህን #ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ አትፈቅዱም፣ ቅንጭብ ትርክ...