ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ማን ገደላቸው? ለምን? ለሚለው ጥያቄ ፬ መላምቶች እናስቀምጥ:- ፩) አማራን እና ኦርቶዶክስን ከኢትዮጵያ ለማጽዳት የሚንቀሳቀሰው የብልጽግና ወንጌል መንግሥት ሠራዊት ሉሆን ይችላል ፣ ፪) "ከሃይማኖት የጸዳ" ትግል እናካሄዳለን የሚሉ አምላክ-የለሽ አንዳንድ ሤረኛ የታጋዮቻችን አመራር ደረጃ ላይ ተቀምጠው ኢአማኒ ወይንም መናፍቅ፣ ወይንም ሃይማኖትን መጥቀስ ትግል የሚጎዳ ነው ብለው የሚያምኑ፣ ወይንም ምእራባውያን ጽንፈኛ ይሉናል ብለው አስበው ድጋፍ ለማግኘት የተላላኪነት ሚናንየወሰዱ አመራሮች አጋጣሚውን በመጠቀም መምህራንና ተማሪዎችን የሚያጸዱ፣ ፫) ምናልባት የተገደሉት መምህር እጅግ ዐዋቂ መሆናቸው እና እውነትን፣ ርቱዕነትን ለሕዝቡ ስለሚያስተምሩ፣ ጎጠኛ የዘር ብሔር አምልኮን በማቆም ራሳቸውን ብቸኛ ዐዋቂና የወደፊት አብን ተክቶ አማርኛ ተናጋሪ አዲስ አብይ ንጉሥ ለመሆን ሲንቀሳቀስ መምህሩን እንደ እንቅፋት የሚመለከቱ ከአሉ፣ ፬) ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን ለማዳከም ከዘመነ ሱሲኒዮስ እና አልፉንሶ ማንዴዝ እና ይፕዛሬዎቹ የደብረ ኤልፓስ መናፍቃን ቅባት፣ ፕሮቴስታንት፣ ዉሃቢያ እስላም፣ ኢአማኒ ከፋፋይ ፖለቲከኞች የፋኖን አመራር ጠልፈው የተዋሕዶ መምህራንን በስንት እያስጠፉ ሊሆን ይችላሉ። ከእነዚህ መላ ምቶች ውጭም ሉታሰብ ስለሚችል ጨምሩበትና ለህልውና ትግል የወጣው አምላክ ያላቸው ታጋዮች በሚጠላቸው አስመሳይ መሪዎች ሥር ተሰልፈው ደማቸውን ከንቱ እንዳያደርጉ አንቁአቸው። እስቲ ከመንጋነት ተላቅቀን በሚጠቅምና ወደ መፍትሄ በሚያመላክት ዓላም እንወያይ። ============= ይህ በሽታ ወደ አንዳንድ ናርሲሲስት የፋኖ ጎጠኛ መሪዎች እና ጭፍን የማኅበራዊ ሚዲያ እንጀራ ጋጋሪዎች የተጋባ ይመስላል። አይ ሽሜ? እንዲህ የጥቀር ናዚ ፖሊሲያች...

ብርሃን ሲለግም ጨለማ ይነግሣል፦ አልቦነት፣ ፖልቲካዊና መንፈሳዊ ውድቀት (ለሲኖዶስ የተጻፈ ነበር፣ ዛሬ ለፋኖ የውስጥ ችግር መንሻ የሆነ የአስተሳሰብ መዛባትን መንስዔም ጠቋሚ ነው ብዬ ለጠፍኩት)

ብርሃን ሲለግም ጨለማ ይነግሣል! የሲኖዶስ አባላት መሠዘም(being secularized) ለፖለቲካ ሲታዘዙ ሰይጣን ከእሥሩ ይፈታል! ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ/ም  © ፋንታሁን ዋቄ የዘሬውን ዓለም ያጨለመው አልቦነት (Nihilism) ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቅድሰት ቤተክርስቲየዓን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ገብቷል! አገራችን ኢትዮጵያ  ተማርን በሚሉ ጥቂት አእምሮአቸው በተቀሰፉ የፖለቲካ ልሂቃን ምክኒያት እጃችን ላይ ከሟሟች ቆይታለች።  ዘሬ ደግሞ ሲኖዶሱ ከጎሠኛና ዘረኛ መንግሥት ትዕዛዝ ተቀብሎ በሐዋሪያት አምሳል ሳይሆን በብሔር ፖለቲካ የፌደራል ምክር ቤት አርአያነት  የቤተክርስቲያን መሪዎና እረኞች ጳጳሳትን ለመሾም ተወስኗል።  ውሳኔውን የሚያከፋው፦ ✝️ የመንግሥት ትዕዛዝ መሆኑ፥  ✝ ጥቆማውን ተቀብለው መርጠው ለሲኖዶስ እንዲያቀርቡ ከተመለመሉት መካከል  በክፋታቸውና በኢቀኖናዊነታቸው የሚታወቁ ሰዎች መኖራቸው፥  ✝️ እነዚህ ሰዎች የቅዱስ ሲኖዶስን ውግዘት ባለመቀበል መልሰው የሚኣወግዙና በሐዋሪያት የክህነት ሥልጣን አንደማያምኑ በተግባራቸው የገለጡ ሰዎች መሆናቸው ነው።  ✝️ ተጨማሪውና አስቃቂው የሆደት ተፋልሶ የቆሞሳት ምርጫ ሕግና የማጽደቅ ሂደት  ከተጻፈ ሕግ ያፈነገጠና ከምእመናን የተደበቀና በፖለቲከኞች የሚመራ መሆኑ፤  ✝️ በዚያ ላይ ሰኔ 30ቀን 2015  የተመረጡት ታውቀው፥ ምእመኑ አስተያየት ሳይሰጥ፥ ገደማት ሳያውቁ፥ የሰ/ት/ቤትና ሌሎች ማኅበራት ስለ ቅድስናቸው ምስክርነት ሳይሰጡ በሳምነት ሐምሌ 9 ቀን  ለሲመት እንዲቀርቡ መታቀዱ፤ ይህ የሚያሳየን አልቦአዊነት ባጨለማት ዓለም በርሃን መሆን የሚገባትን ቤተክርስቲያን የሴኩላር ዲሞክራሲና የዘረኞ...

የዐመሓራነት የህወሃትና የኦነግ አይነት “ብሔርተኝነት” እይደለም! ዐመሓራነት ሰብአዊነትና ፍትሕ፥ እኩልነትና እውነት ነው!!

የዐመሓራነት  የህወሃትና የኦነግ አይነት “ብሔርተኝነት” እይደለም! ዐመሓራነት ሰብአዊነትና ፍትሕ፥ እኩልነትና እውነት ነው!! ተጻፈ ከፋንታሁን ዋቄ መስከረም ፫ ቀን ፳፻፲፯   ●  ዓለም ዐቀፍ ዝና የነበረው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት በወራዳ ድንክ አእምሮዎች፥ አገርና ሕዝብን ከሆድና ከሕጻን ቅዠታቸው አሳንሰው በገዛ ወገኑ ላይ አዘመቱት። እንደዚህ አድርገው አዋረዱት።  ላም እሣት ወደለች አንዳትልሰው እሣት ሆነባት፥ እንዳት ተወዉ ልጅ ሆነባት እንዲሉ  የዐመሓራ ሕዝብ ራሱን ከታወጀበት የ50 ዓመታት የዘር ማጥፋት ሁለገብ ጥቃት በኋላ  በሕወሃትና ኦነግ ሕገ አራዊት መሠረት የተወለደው ብልጽግና በይፋ በተመሠረተው የኦነግ-ኦሮሙማ የብልጽግና አመራር ቀጥተኛ ፍጅት ተካሄደበት፤ ማፈናቀል፥ እያደኑ መግደል፥ ማደኸየት፥ በበሽታ ማስጠቃት፥ ከትምህርትና ከፖለቲካ ተሳትፎ ማራቅ ወዘተ እየተፈጸመበት ታገሰ፤ በመጨረሻም ለመታገስ የማይመች በጦእ ሠራዊት ቀጥታ ፍጅት ተከፈተበት።  ፍጅቱን የሚፈጽመው በአብይ አህመድ የጠቅላይ ጦር አዛዥነት የሚመራው ይከበር የነበረው የአገር መከላከያ ጦር ሠራዊት ነው።  እናም ለዐመሓራ የቀረበለት አማራጭ ራሱን መከላከል፥ እያለቀሰ በራሱነ ወገን ላይ መተኮስና እያዘነ መማረክ ነው።   ●  እነርሱ የቆሎ ተማሪ ከጎጆ እየጎተቱ ሲረሽኑ፥ መነኩሴና ሕጻን ሲደፍሩ፥ ሰብል ሶያቃጥሉና ከተማ ሲያፈርሱ ሰውነቱን ዛሬም አስከብሮ የኖረው በዓለ ሕሊና ዐመሓራ (ባንዳ፥ ዘረኛ፥ ስስታምና ሸቃጭ አማራን አይመለከትም)  ግን የማረከውን በጠላትነት ያሰለፉበትን "ጠላት" ወገኑን እየደባበሰ እና እያጽናና፥ ጫማ ሳያስወልቀው፥ ግፍ ሳይፈጽምበት   ወንደሜ "ጥላችን ከሥርዓት ...
የበዛ ራስ ወዳድነትና (የናርሲሲት ባሕርይ) የመሪነት ፈተናዎች በኢትዮጵያ     1) የኢትዮጵያ ሕዝብ የመስዋዕትነት የስነ-ለቦና፣ የነጽሮተ ዓለም (ስለ ራሳቸው፣ ስለ ሀገር፣ ስለ ዓለም፣ ስለ ትውልድ፣ ስለ አመራር)  ጤንነታቸው  ለብዙኋን ዜጎች በሚጎዳ ሰዎች እየተነጠቀ ከመከራ ወደ መከራ ተሻግሯል 2)  መሪዎች በተፈጥሮ፣ በሀገር-ፈለቅ ትምህርት፣  በማኅበረሰብ ነባር ባህል፣ በተቀደስ ትውፊት የተገኙ ማያዎችን፣ እሤቶችን እና መዋቅራትን ዋጋ በማሳጣት የእነዚህ ሀብታት ጠላት በሆኑ የባእዳን ፍላጎትና አስተሳሰብ በመመራት ሀገራችንና ትውልዱን ክፍተኛ ግራ መጋባትና የህልውና አደጋ ላይ ጥሎታ 3)  አሁንም ሀገራችን ከጥልቅ ወደ በለጠ መቀመቅ ወይንም ወደ ትንሳኤ የመሻገር መስቀለኛ ጎዳና ላይ ቆማለች። ሁለቱም መንገድ የሚወሰነው በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታዎች ይኖራሉ። ነገር ግን ወሳኙ አዎንታዊ  ተጋድሎአቸውን በሚመሩት ሰዎች ጤንነት ይወሰናል። መሪዎች፦ ከቤተሰብ እስከ ሀገርና ዓለም ዐቀፍ የሕዝብን መስዋእትነት ለመልካም ወይንም ለጥፋት ያደርጉታል፦ ከደርግ እስከ ዛሬ ሕዝብ ይሞታል፣ ጠቂቶች ግን በደሙ ይነግዳሉ በፖለቲካ፦ በሀገራችን ከቅርቡ ብንነሳ መንግሥቱ ንዋይ፣ መንግሥቱ ኃ/ማሪያም፣ የኢሐፓ መሪዎች፣ የሕወሃት መሪዎች፣ የኦነግ መሪዎች፣ የኢሕዴግ መሪዎች፣ የብልጽግና መሪዎች፣ የፋኖ መሪዎች፣   ወዘተ ጤንነት እና ውጤቱን ከታሪክ እውቀታችንና ምርምሮች በመነሳት አሁን እየተካሄዱ ያሉ የልዩ ልዩ አካላት ተጋድሎ አዎንታዊ ውጤት እንዲያስገኝልን  የመሪዎቻችንን ጤንነት እየገመገምን ወደፊታችንን ማስተካከል እንድንችል ይህን ዝግጅት በተከታታይ ለማቅረብ ወድጄአለሁ። መግቢያ ይ...