7ቱ ጥያቄዎችና ማብራሪያዎቻቸው ጥያቄ 1፦ በሕገ-መንግሥት፣ በፖለቲካ ማኒፌስቶ፣ በመደበኛ ትምህርት፣ በሚዲያና መሰል መንገዶች ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮንና ኦርቶዶክሳዊያንን ለጥቃት የሚጋልጡ መልዕክቶች በአስቸኳይ በሕግ እንዲታገዱ ። የተዛባ ታሪካዊ ግኑኝነት የሚል ቃል የተጠቀሙት ሕገ-ምንግሥቱን ያዘጋጁ የብሔር ፖለቲከኞች ናቸው። የብሔር ፖለቲከኞች የተዛባ የሚሉት በሕገ መንግሥት ያጸኑት ታሪክ አላቸው፤ ኮሚኒስቶች ለሺ ዘመናት እሥራት ውስጥ ነበረች እንድተፈታ የቀደመውን ማጥፋት አለብን ይላሉ፤ በዚህ መሠረት ትምህርቱን፣ኪነቱን፣ ሚዲያውን፣ መዋቅሩን ተቆጣጠሩት፣ “ተዛባ” የባለው “ታሪክ” ከታሪካዊት ኦርቶዶክስ ክርስትና ክርስቲያን ማኅበረሰብ፣ ቅርሥ፣ ሀብት፣ ታሪካዊ ጀግኖች፣ መጽሐፍት፣ አስተመህሮ ጋር ተጣምሮ የማስወገድ ዒላማ ተደረገ፤ ኦርቶዶክሳዊነት ሀብት ለማደለብ፣ ለዲሞክራሲ የአስተዳደር ሥርዓት፣ ለዘመናዊ አኗኗር፣ ለሥራ ስነ-ምግባር እንቅፋት የሆነ፣ የድኽነት ምክኒያት ናት፤ በቁስ የደኸየ በሰማይም ተስፋ የለውም የሚል አስተምህሮ የሚያራምዱ ብዙዎችን አሳስተው ኦርቶዶክስ-ጠል ለማድረግ ሠሩ፤ ከኮምኒስት የመደብ፣ የብሔረሰብ እና የተጨቋኝ-ጨቋኝ የፖለቲካ ትግል ፅንሰ ሀሳብ ጀምሮ እሰክ ብልጽግ ፓርቲ እስተሳብ ድረስ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊነትን ዒላማ አደረጉ፤ የአሁኑ ዘመን ፖለቲካም ኦርቶዶክሳዊና አገር በቀል እሴቶችን በጀርመኑ ሉተርና በማክስ ዌበር ትምህርት መተካት መበልጸግን እንደሚያስገኝ ይናገራሉ። ከዚያ ለውጥ ሁሉ ነባሩን ማጥፋት ወደሚል ያዘነብላሉ በውስጥና በውጭ ይህን ዝንባሌ ተከትለው ነባር ኦረቶዶክሳዊነት ላይ የተመሠረቱ ኢትዮጵያዊ እሴቶችንና ክርስቲያኖችን በማጥፋት የሚሳተፉ ሌሎች እምነቶችና...
የህልውና ትግል ሃይማኖትን አይመለከትም ለምትሉ ጥያቄ እና ሤራችሁን የማጋልጥበት መለእክት አለኝ፦ 👉 የህልውና ትግላችን ሌሎች ፍላጎቶችን አያስተናግድም ማለት ምን ማለት ነው? 👉 የሃይማኖት ነገር አይነሳ ማለት ምን ማለት ነው? 👉 ህልውናን መታደግ የማኅበረሰቡን ሥጋዊ አካል ብቻ ነው? 👉 ህልውና ሃይማኖት፣ ታሪክ፣ ርስት፣ ቅርሥ፣ ትውልዳዊ ተስፋ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር፣ ዓለም አቀፋዊ ትሥሥር፣ ቀጠናዊ ሰላም አይጨምርም? 👉የህልውና ተጋድሎ በምእራባውያን ፍልስፍናና ይሁንታ ብቻ የሚትረጎም ነው? ከእኔ ዐሳብ የትሻል የሙስሊሙና ክርስቲያኑ የሃይማኖትና የታሪክ ልሂቃን ይህን ሰውር ሤራ ማክሽፍ የጠበቅባችኋል። ============================================ በአንድን ክፍለ-ሕዝብ ላይ እየተሞከረ ያለው ድምሳሴ ከተሳካ የሚያጠፋው የማኅበረስቡን፡- 1) አባላት (ሰዎችን) እና የትውልድ ቀጣይነትን 2) ባህሉን 3) ሃይማኖቱን 4) ታሪኩን 5) የስነ-መንግሥትና የእምነት አሻራ የሆኑ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሦቹን 6) ማኅበረ-ሰበእ-ፈለቅ ዕውቀቶቹንና ጥበቦቹን 7) ቋንቋዎቹን 8) ርስቶቹንና ማኅበራዊ ትሥሮቹን ወዘት ሁሉ ነው። የህልውና ተጋድሎ የሚታደገው 8ቱንም ለማዳን ነው። ዛሬ ላይ ግን በአማራ የህልውና ጠላቶችን አጥፊ ፍልስፍናዎች የወረሱ ወይንም ባለማወቅ የጠላት ሤራ ሰለባ የሆኑ አንዳንድ የፋኖ ልሂቃንና መሪ ካልሆንን ሞተን እንገኛለን የሚሉ ሰዎች "የአማራ ህልውና በ1ኛው ተራ ቁጥር ላይ የተገለጸውን ብቻ የመለክታል--- --- የተቀረው ግን ያረጀ፣ ያፈጀ፣ የጃጀ ስለሆነ እኛ በምንበይነው ይተካልና ትግላችን ለሌሎች ፍላጎቶች ዝግ ...