የፖለቲካ ጠላት የተደረገውና የህልውና አደጋ የተጋረጠበት ኦርቶዶክሳዊነት እና የተከዳው ኢትዮጵያዊነት 24-10-2015 ዓ/ም ካምፓላ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። የቤተክርስቲያን የሕልውና አደጋ የአግርም ነው!!! ዛሬ አደጋው ከውጭ አይደለም። በእርግጥ መርዛማው የኢትዮጵያዊነትና ኦርቶዶክሳዊነት ጠላት ፖለቲካ የሀሳብ ምንጩ ከውጭ ነው፤ ይህ ፖለቲካዊ አመለካከት የተጣባው ትውልድ ማንኛውንም ነባር ባህልና እምነቶች የማጥፋት ዝንባሌውን ከራሱ ያመነጨው እስኪመስለው የተጋተው ከውጭ ነው። በቅኝ ገዥዎችና ከባዕዳን ከ700 ዓመታት አስቀድሞ የተጀመረ ሂደት ነበር፥ የዛሬ 180 ዓመታት ገደማ አስቀድሞ ሸዋ አንኮበር ቤተመንግሥት የጀርመኑ ጆሃን ሀኒክራፍ ሉድዊግ በቤተክርስቲይን እና በነባሩ የኢትዮጵያ ስነ መንግሥት ላይ እሾኽ ተከለበት፥ ያ እሾኽ ከተተከለ ከ50 ዓመታት በኃላ የዛሬ 130 ዓመታት ገደማ በጣሊያን ተኮትኩቶ አገር በቀል ተከታይ አፈራ፤ ከናዚ ሶሻሊሰት ፓርቲ መሸነፍ በኋላ ከጀርመን ያመለጡትና ወለጋ የተጠጉት “የጀርመን ክርስትና” የተሰኘ ለዘረኝነት የሚስማማ ፕሮቴስታንቲዝም ያነገቡ ሰባኪያን የዛሬ 72 ዓመት ገደማ ሥር እንዲሰድ በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤትና በቀ/ኃ/ሥ ዩኒቭረሲቲ መዋቅራዊ የትምህርት አቅም ተሰጠው፤ የዛሬ 60 ዓመታት አካባቢ የመጀመሪያው መርዛማ ፍሬ እሸቱ ታየ፥ በመንበረ ልዑል ቤተ መንግሥት ውስጥ መሪዎችን ሰውቶ የመጠፋፋት ባህልን አስተዋወቀ፥ የዛሬ 50 ዓመት ገደማ በአገራዊነትና ነባርነት ላይ የሚያምፀው ትውልድ እግዚአብሔር የለሽ የፖለቲካ ርእዮተ ዓለምን ታጥ...
This is a spot where I post and share part of my daily reality. I would love to hear from others too to learn how differently we interpret daily encounters including our imaginations. ይህ ሥፍራ የየዕለት ገጠመኞቼን፣ እንዴት በዕለቱ እንደተረደሁትና የማስበውን ለሌሎች ያማጋራበት ነው፡፡ የሌሎችን በመስማትና ምን ያህል ዓለማችንን በተለያየ መንገድ እንደምንመለከታት ለመማር እጓጓለሁ፡፡